ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Friday, May 31, 2013

በአባይ ግድብ 'ጅኦ-ፖለቲካል' ጉዳይ ተቃዋሚዎች ያላቸው ሃሳብ እና መፍትሄ ሳይሰማ ህዝቡ በመላ ምት ላይ በተመሰረተ አስተሳሰብ ሀገሪቱ ወደ አልተፈለገ መንገድ እንዳትሄድ- የውጭ ፖሊሲያችንን የሚቀይሰው ማነው?((አጭር ማስታወሻ ከአልጀዚራ ቪድዮ ዘገባ ጋር)

ዛሬም የቅኝ ግዛት ውል መጥቀስ ምን ያህል ኃላ ቀርነት ነው? ግብፆች ዛሬም በ 1959 እአኤ  የተፈረመውን ግብፅን እና ሱዳንን የሚጠቅመውን ውል ይጠቅሳሉ።ኢትዮጵያ ግን ከቀዳማዊ አፄ ሃይለስላሴ ዘመን እስካሁን ድረስ ውሉን ተቀብላ አታውቅም። የአባይ ጉዳይ አሁን ላለንበት በተለይ የመካከለኛው ምስራቅ ሃገራት ግብፅን ጨምሮ ከቅኝ ግዛት ተላቀው ነፃ ሀገር መሆን ከጀመሩበት ጊዜ እና የነዳጅ ዘይት ግኝት ማለትም ከ 1950 ዎቹ ወዲህ ለነበረን የሰሜንም ሆነ የሱማሌ ጦርነት ኢትዮጵያ በአቅም እንዳትደረጅ እና የአባይን ውሃ አጠቃቀም ጉዳይ እንዳታነሳ የተሸረቡ ተንኮሎች አካላት ነበሩ ማለት ይቻላል።
በኤርትራ ''ጀብሃን'' ለመርዳት ቀጥሎም ''ሻብያን'' ለማገዝ አንዳንድ የመካከለኛ ምስራቅ ሀገራትን፣ግብፅ እና ሱዳንን ያማለላቸው አንዱ እና ዋነኛው ምክንያት የተዳከመች ኢትዮጵያን ለማየት ካላቸው ሕልም እና ከእዚሁም በአባይ ላይ እና በቀይባሕር ላይ ያላቸውን የበላይነት የማሳያ አንዱ እና ብቸኛ መንገድ አድርገው ስለሚያስቡ ነበር። በእዚህ ጉዳይ ብዙዎች ብዙ ብለዋል።እኔ የማክልበት የለም።

ሆኖም ግን የውጭው ተፅኖ መንስኤዎችን ብንዘረዝርም ትልቁ ጉዳይ ግን እኛ የውስጥ ጉዳይ አያያዛችን እና የመንግስታቶቻችን ብልህ የሆነ የህዝብ አስተዳደር ዘይቤ ማጣት ብሎም የውጭ ግንኙነቱን ባማከለ መንገድ አለመሆን አንዱ መጤን የሚገባው የነበረ እና አሁንም ያለ የችግሮቻችን ምንጭ ነው።በሌላ አንፃር  በየጊዜው የሚነሳውን ትውልድ ፍላጎት እየተመለክቱ መንግሥታቱ  እራሳቸውን ማስተካከል አለመቻል ከአባይ ጋርም ሆነ ካለንበት 'ጂኦ-ፖለቲካል' አቀማመጥ አንፃር የሚነሱትን ችግሮች በፍጥነት ከህዝብ ጋር ሆነው ለመፍታት ሲሳናቸው እንመለከታለን።

የተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶችም በሃገርውስጥ ባሉ የመንግስት አሰራሮች ላይ ብቻ ሳይሆን በአለምአቀፍ ጉዳዮች በተለይ ኢትዮጵያን በቀጥታ የሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ የሚይዙትን አቋም በየጊዜው ግልፅ ማድረግ ያለባቸው ይመስለኛል።ይህ ካልሆነ ሕዝብ በፅናት የሚቆምበትን መስመር ሳይመለከት እና ግልፅ የሆነ መንገድ አጥቶ የመዋለል አዝማምያ ለብሔራዊ አንድነትም ሆነ ለሉአላዊነታችን አድገኛ አዝማምያ ይፈጥራል። 

በአንድበኩል ህዝቡ መንግስት  የውጭ ኃይላትን በተመለከተ የሚሰጣቸውን  ማብራርያዎች አለማመን በሌላ በኩል ተቃዋሚዎች ስለጉዳዮች ያላቸው ሃሳብ እና መፍትሄ ሳይሰማ  ህዝቡ በመላ ምት ላይ በተመሰረተ አስተሳሰብ ሀገሪቱ ወደ አልተፈለገ መንገድ እንዳትሄድ ሁሉም ወገኖች ሊያስቡት የሚገባ አንኳር ጉዳይ ነው።

በመጨረሻም የአባይን ግድብ በተመለከተ ብዙ ጥያቄዎች ሊኖሩ ይቻላሉ። እኔም አለኝ።ጥያቄዬ ግን በግድቡ ጥቅምና ጉዳት አልያም መዋጮ ወዘተ በሚሉ ዙርያ አይደለም።ባለፈው በግንቦት 20 እለት መንግስት ውሃውን 'የማስቀየር ሥራ' ሰራሁ ብሎ በቀጥታ ለሕዝቡ ባስተላለፈው መልእክት ዙርያ ነው። አንድ ፕሮጀክት ያውም ከሀገር ውስጥ አልፎ የአካባቢ ሃገራትን ብሎም ስሩ እስከ መካከለኛው ምስራቅ ድረስ የሚዘልቅ ጉዳይ የያዘን ጉዳይ- 'የአባይን ግድብ' ለምን በአደባባይ ውሃውን መንገድ የማስቀየስ ሥራ ሰራሁ ተብሎ ያውም በቀጥታ በኢቲቪ ማስተላለፍ  አስፈለገ? ለምን የበለጠ ለግብፅ እና ሱዳን አስጊ አለመሆኑ ላይ የማሳመን ሥራ አልተደከመም?

እርግጥ ነው የማሳመን ስራው ተሰርቷል የሚል ሃሳብ ሊነሳ ይችላል። ነገር ግን የግብፃውያንን ስሜት ከሞራልም አንፃር ስሜታዊ እንዲሆኑ የታሰብ ካልሆነ በስተቀር የውሃውን መንገድ ማስቀየስ ሥራ በግንቦት 20 እለት ያንን ያክል መለፈፍ አስፈላጊ አይመስለኝም።የግድቡ መኖር በእራሱ ውሃውን መንገድ እንደሚያስቀይረው የታወቀ እስከሆነ ድረስ። ኢህአዲግ ለምን ግንቦት 20 ቀን ይህንን አደረገው?  የውጭ ፖሊሲያችንን እየቀረፀ ያለው ማነው? ኢህአዲግ የሚሰራውን እያወቀ ነው? ጥያቄዬ ነው።የግድቡ ሥራ የበለጠ የዲፕሎማሲ ሥራ በሚጠይቅበት ጊዜ የእዚህ አይነት ግብፅን ለማስደንበር እና ብሔራዊ 'ጀግንነትን' ለማስፈን የታሰበ እስኪመስል ድረስ በግንቦት 20 ቀን ''ውሃውን መንገድ አስቀየስኩት''  ማለት ለግብፅ ሕዝብ  የግብፅን መንግስት ''ጉሮሮህ ታነቀ ብለህ ንገረው'' ይመስላል። አሁንም እጠይቃለሁ የውጭ ፖሊሲያችንን የሚቀይሰው ማነው? 

አልጀዚራ ''inside story'' ፕሮግራም ግንቦት  22፣2005 ዓም (may 30,2013) በአባይ ግድብ ጉዳይ ላይ ከአዲስ አበባ አቶ በረከት ስምዖንን ፣ከለንደን ክሊር ፓስካ በአካባቢ ጥበቃ እና የምግብ ዋስትና  ኤክስፐርት እና ከካይሮ ላማ አልሃታል የአባይ ውሃ ኢንስቲቱት መስራች አባል ውይይት አዘጋጅቶ ነበር።



Inside Story- Death on the Nile

Thursday, May 30, 2013

ሰበር ዜና-የግብፁ ፕሬዝዳንት ሙሐመድ ሞርስ ዛሬ ከመከላከያ ሚኒስትራቸው አብደል ፋታህ አልስሲን ጋር ስብሰባ ተቀምጠው ነበር ፣ኤርትራ በአባይ ግድብ ጉዳይ ከግብፅ ጋር መሰለፏ ይፋ ሆኗል

ሰበር ዜና 
''አህራም ኦን ላይን'' የተሰኘው የግብፅ የድህረ-ገፅ የአንግሊዝኛ ጋዜጣ ዛሬ ሐሙስ ግንቦት 22፣2005 (may 30,2013) ከካይሮ እንደዘገበው የግብፁ ፕሬዝዳንት ሙሐመድ ሞርስ ዛሬ ከመከላከያ ሚኒስትራቸው አብደል ፋታህ አልስሲን፣የሃገር ውስጥ ሚኒስትራቸውን ሙሐመድ እብራሂምን እና የደህንነት ሚንስትር ራፋት ሸሃታን ይዘው ኢትዮጵያ እየገነባች ባለችው የታላቁ የህዳሴ ግድብ ላይ ስብሰባ አድርገዋል።
እንደ ፕሬዝዳንቱ ቃል አቀባይ ኢሃብ ፋህሚ  ገለፃ ውይይቱ የተደገው ግድቡ በግብፅ ላይ የሚያመጣውን አይነተኛ ተፅዕኖ ላይ መሆኑን ጠቁመው በመቀጠል ''በጉዳዩ ላይ ፕሬዝዳንቱ ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋር በጋራ አጠቃቀም ዙርያ ላይ አሁንም ንግግር  እየተደረገ ነው'' ብለዋል።
በመጨረሻም እንደ ጋዜጣው ዘገባ  ፕሬዝዳንቱ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትራቸው ሙሐመድ ከማል ኦመር ጋር እና ከ ውሃ ሀብት ሚኒስትሩ ሞሐመድ በሃ ኤልድን ጋር መመካከራቸውን እና ''በግብፅ የውሃ አቅርቦት ላይ ማንም እንዲያስፈራራን አንፈቅድም'' የሚል መግለጫ ከፕሬዝዳንቱ ቤተመንግስት መሰጠቱን አጥቷል።


ከ''አህራም ኦን ላይን'' ዘገባ  ውጭ ተጨማሪ
 

ኤርትራ ናዋን ለይታለች 

 ባለፈው ወር የአባይን ጉዳይ አስመልክቶ የሱዳኑ ''ሱዳን ትሪቡን'' እንደዘገበው። ኤርትራ ሱዳን እና ግብፅ በቅኝ ግዛት ዘመን ኢትዮጵያን አግልለው ለብቻቸው የአባይን አጠቃቀም በተመለከተ የተፈራረሙትን ውል እንደምትደግፍ መግለጧን ዘግቧል። ለእዚህም ተግባሯ የግብፁ መሪ ሙሐመድ ሞርስ አቶ ኢሳያስን ማሞገሳቸውን እና በቅርቡ ሊያገኛቸው እንደሚሻ መግለጣቸውን ጋዜጣው አትቷል።

ግብፅ የኤርትራን ጦርነት ለማስጀመር ከዛሬ 35 አመት በፊት ለአቶ ኢሳያስ ካይሮ ላይ የነዳጅ ማደያ በመስጠት የሻብያን የመጀመርያ መነሻ ካፒታል ከሰጡት ውስጥ የምትቆጠር መሆኗንየሚገልጡ አሉ።
በ 1990 በኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ወቅት የግብፅ አማካሪ ጀነራሎች አስመራ መታየታቸውን ጠቅሶ አንድ በአዲስ አበባ የሚታተም የግል ጋዜጣ እውነትነቱን እንዲያረጋግጡ ለጠየቃቸው  በአዲስ አበባ የግብፅ  አምባሳደር በሰጡት መልስ ''ጡረታ ከወጡ በኃላ ጀነራሎቻችን ምን እየሰሩ እንደሆነ የማረጋገጥ ግዴታ የለብንም'' ማለታቸው እና ጉዳዩን በተዘዋዋሪ ማረጋገጣቸው ይታወሳል። 

ዛሬ የወጣው የግብፁ ''አህራም ኦን ላይን'' እና ባለፈው ወር በሱዳን የታተመው ''ሱዳን ትሪቡን'' የእንግሊዝኛ ዘገባን ከእዚህ በታች  በተያያዘው የ ''ጉዳያችን ጡመራ'' ላይ ያንብቡ።

1/ ''አህራም ኦን ላይን'

ahramonline

http://english.ahram.org.eg/News/72768.aspx 

Thursday, 30 May 2013
Egypt's Morsi, top officials mull response to Ethiopia dam move
Egyptian officialdom awaits outcome of tripartite commission's report on Ethiopian dam project – expected on Sunday – before deciding on appropriate response
Ahram Online , Thursday 30 May 2013
Share/Bookmark
Views: 283
Morsi
President Morsi and the officials during the meeting (Photo: Presidency Official Facebook Page)
President Mohamed Morsi on Thursday met with Defence Minister Abdel-Fatah El-Sisi, Interior Minister Mohamed Ibrahim and General Intelligence head Rafaat Shehata to discuss recent developments in Sinai and Egypt's position regarding Ethiopian plans to build a series of dams on the Nile.
According to presidential spokesman Ehab Fahmy, meeting attendees discussed the options available to Egypt to deal with Ethiopia's 'Renaissance Dam' project and the project's potential impact on Egypt and its share of Nile water.
Fahmy also stated that talks were ongoing with Ethiopian officials in an effort to reach an agreement to the "mutual benefit" of both countries.
President Morsi, Fahmy said, had also discussed the issue with Foreign Minister Mohamed Kamel Omar and Water Resources Minister Mohamed Bahaa El-Din.
At a press conference held earlier on Thursday at the Presidential Palace in Cairo, Fahmy said that the presidency would "not allow anyone to threaten Egypt's supply of Nile water."
Egypt supports development projects in Africa "as long as they don't affect Egypt's national security," the presidential spokesman stressed. He went on to note that President Morsi was keen to cooperate with "all African states" on water-sharing issues.
At a press conference convened following the meeting with the president, Bahaa El-Din declared that the Egypt had ruled out a military response in the event that Ethiopia insisted on going ahead with its dam project.
The minister added that a report on the dam project by an international tripartite commission – consisting of representatives from Egypt, Sudan and Ethiopia – would be issued on Sunday.
If the report concluded that the Ethiopian dam project would adversely affect Egypt, Bahaa El-Din said that Egypt would prepare "a number of scenarios."  

2/ ''ሱዳን ትሪቡን''


SUDAN TRIBUNE 

FRIDAY 19 APRIL 2013
http://www.sudantribune.com/spip.php?article46276

Eritrea supports Egypt’s position over Nile water dispute

separation
increase
decrease
separation
separation
  • facebook
  • myspace
  • twitter
  • buzzyahoo

By Tesfa-Alem Tekle
April 18, 2013 (ADDIS ABABA) – The Eritrean government said this week that it supports Egypt’s stance over a colonial-era treaty that granted Egypt a right to utilise the lions share of Nile river’s water resources.
The Red Sea nation expressed its support in a message sent from the Eritrean president and delivered to Egypt’s president by Eritrean Foreign Minister Osman Saleh and Presidential Adviser for Political Affairs, Yemane Gebreab.
The Egyptian president, Mohamed Morsi, has highly welcomed Eritrea’s position towards Egypt’s "historic rights" over the sharing of the water of the Nile River.
Morsi said that he looks forward to meeting his Eritrean counterpart.
Although Ethiopia is the source of 85% of the Nile’s water, downriver countries, Egypt and Sudan, use 51 billion and 18 billion square meters a year respectively, around 90% of the Nile’s resources.
In April 2010, Ethiopia, Rwanda, Uganda, Kenya and Tanzania signed a new agreement in Entebbe, Uganda, to overturn a colonial-era treaty seeking a more reasonable and equitable utilisation of the river.
The deal was approved after Burundi later signed the agreement and joined the group in March 2011.
Newly-independent South Sudan has not yet signed the Cooperative Framework Agreement but it has also rejected the 1959 Nile water agreements between Sudan and Egypt.
Downstream countries of Egypt and Sudan have, however, dismissed the deal, saying the agreement is insignificant because it did not include all Nile basin countries.
Egypt has in the past warned against construction of further dams along the Blue or White Nile’s.
One year after the Cooperative Framework Agreement was signed; Ethiopia launched the construction of a massive $4.8 billion dam on the Blue Nile River raising protests from Sudan and Egypt that the dam - Africa’s biggest - would reduce the flow of the water to their territories.
Currently a tripartite committee, which is composed of six experts drawn from Ethiopia, Egypt and Sudan, and four more international experts are assessing the impacts of the project.
The team is expected to announce the final findings and conclusions in May 2013.
(ST)

Wednesday, May 29, 2013

የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ በ''ቢቢሲ'' ''ሃርድቶክ'' ፕሮግራም ከአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ቀጥታ ስርጭት (ቪድዮ)

  የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ በ''ቢቢሲ''  ''ሃርድቶክ'' ፕሮግራም ከአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ  ቀጥታ ስርጭት (ቪድዮ) 

የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ ባለፈው ሳምንት ግንቦት 18፣2005 ዓም ለአፍሪካ ህብረት 50ኛ የወርቅ 
እዮቤልዩ በዓል ላይ ለመገኘት አዲስ አበባ ተገኝተው ነበር።ታዋቂዋ እና  ድምፀ መረዋዋ የ''ቢቢሲ'' ጋዜጠኛ ዘና በዳዊ ታዲያ ከአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ዝነኛውን ''ሃርድቶክ'' ፕሮግራም በመምራት በቀጥታ ለመላው አለም እንዲተላለፍ አድርጋለች። ዘና በዳዊ በአያቷ ኢትዮጵያዊት ስትሆን ሱዳን ውስጥ ስታድግ ስለኢትዮጵያ ብዙ ታሪክ እንደተማረች መናገሯ  ሰሞኑን ከአዲስ አበባ ተዘግቧል።

ቪድዮውን ይመልከቱት።


Tuesday, May 28, 2013

ለብዙ ኢትዮጵያውያን ግንቦት 20 ካለፈው ይልቅ መጪውን የሚፈሩበት ጊዜ ነው

ግንቦት 20፣1983 ዓም ታላቁ ቤተመንግስት በር 
ዛሬ ግንቦት 20 ነው።ግንቦት 20 የኢትዮጵያ የፖለቲካ መዘውር የተዘወረበት ለመሆኑ አሌ አይባልም። ዕለቱ እንደ አቶ ሃይለማርያም የመጀመርያ በጠቅላይ ሚኒስትርነት ማዕረግ እንዳደረጉት ንግግር '' ኢትዮጵያ ልትበታተን ስትል የዳነችበት ቀን'' ነው ለብዙ ኢትዮጵያውያን ግን ግንቦት 20 ካለፈው ይልቅ መጪውን የሚፈሩበት ጊዜ ነው።ይህንን ሁለተኛውን ሃሳብ እኔም እጋራዋለሁ። ካለፈው ይልቅ መጪው ይቀርበናል።ያለፈውማ አለፈ።መጪው ግን ቢዘገይም ቢፈጥንም አይቀርም።እና ግንቦት 20 ካለፈው ይልቅ ለመጪዋ ኢትዮጵያ እንዴት አስጊ ያደርገዋል። ይህንን ለማብራራት ግንቦት 20 እንደ ሀገር ለኢትዮጵያ ይዞት የመጣውን በጥቂቱም መጥቀስ ይፈልጋል።ስለተሰራው የመንገድ እርዝመት፣ህንፃ፣ወዘተ ማተት ይቻላል።እርግጥ ነው መንገድ ተስርቷል።ህንፃ ተገንብቷል።ከተሞች ሰፍተዋል።ይህ ሁሉ  ግን መጪውን አስፈሪ ጊዜ ለሀገር ከመተው አልገታውም።

መጪውን አስፈሪ የሚያደርገው የግንቦት 20 ውጤቶች ምን ምን ናቸው? 

እንድሜ ለግንቦት 20 ብዬ ብጀምርስ-

  • እድሜ ለግንቦት 20 ዛሬ ኢትዮጵያ በአለም ታይቶ በማይታወቅ መልክ በቁጥር ተከልላ ክልሎች ስለ ድንበሮቻቸው ሲደራደሩ አንዳንዴም ሲጋጩ ለማየት በቅተናል።ምሳሌ የአፋር እና ትግራይ፣የሱማሌ እና ኦሮሞ፣የአማራ እና አፋር ወዘተ መጥቀስ ይቻላል።
  • እድሜ ለግንቦት 20 አንድሰው ከአንዱ የሃገሪቱ ክልል ተነስቶ እንበል ደቡብ ወይንም ጅጅጋ  ገብቶ መሬት ገዝቶ ልረስ ወይንም ልነግድ  ቢል እርሱ ከመምጣቱ በፊት ከ 60 እና 70 አመት በፊት የሰፈሩቱ ከጉርዳፈርዳ፣ጋምቤላ፣ጅጅጋ እና አሶሳ ካለምንም ካሳ ሲባረሩ ያያል እና መጪው እያስፈራው አይሞክረውም።
  • እድሜ ለግንቦት 20 ወላጆች ልጆቻቸውን በፈለጉት ቋንቋ ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ለማድረግ በታሪካዊ አጋጣሚ የሚኖሩበት ክልል ቋንቋ ውጭ እንዳይስተምሩ ታግደዋል።ለምሳሌ ኦሮምኛ ተናጋሪ ልጁ በአማርኛ እንዲማር ቢፈልግ ግን በኦሮምያ ክልል ቢኖር አማርኛ ወደምነገርበት ክልል መሄድ ብቸኛ አማራጩ ነው።በምዕራቡ አለም የሚኖር አንድ ኢትዮጵያዊ ግን ልጁን በሀገሩ ቋንቋ እንዲያስተምር ባህሉን እንዲጠብቅ ድጋፍ ይደረግለታል።
  • እድሜ ለግንቦት 20 ኢትዮጵያ ወደብ አልባ ሆና የባህር ኃይሏን በትና  30 እና 40 ኪሎሜትር እርቀት የባህሩ ማዕበል ሲማታ እየተሰማ ከ85ሚልዮን በላይ ሕዝብ ወደብ አጥቶ የጅቡቲን እና የሱዳንን ወደቦች በከፍተኛ ገንዘብ እንዲከፍል ተወስኖበታል፣
  • እድሜ ለግንቦት 20  ጦርነት ቆመ በተባለበት ጊዜ በአዲስ አበባ ብቻ ከ 100ሺህ በላይ ''ጎዳና ቤቴ'' ያሉ ሕፃናት መንገድ ላይ ፈሰው ኃላፊነት የሚወስድ መንግስት አጥተው ለማየት የበቃነው በግንቦት 20 ፍሬ ነው። (በቀድሞው መንግስት የተመሰረተው የሕፃናት አንባ እንዴት በአሁኑ መንግስት እንደፈረሰ ይህንን ሊንክ ከፍተው ቪድዮውን ይመልከቱ (http://gudayachn.blogspot.no/2013/05/main-play-list-on-home-page-playlist.html)፣
  • እድሜ ለግንቦት 20 ከሃያ ሁለት አመት በፊት ''የጫት ቤት'' ብሎ በር ላይ መለጠፍ የምያሳፍርባት አዲስ አበባ ዛሬ ጫት በየዘርፉ ''የበለጩ ፣የባህርዳር፣ የወልሶ ጫት ቤት'' ብቻ ተብሎ ሳይሆን የሚለጠፈው ''ጫት እናስቅማለን፣ እንፈርሻለን'' ተብሎ የተፃፈባቸው ባብዛኛው ትምህርት ቤቶች የሚገኙበትን ቦታ ፈልገው የሚከፈቱ የጫት ቤቶች በዝተው ለመታየት በቅተዋል። ምን ይህ ብቻ ዩንቨርስቲዎቻችን በየዶርሙ ጫት ሸጉጠው ሲገቡ- ሲ ቃምባቸው ደጉ መንግስታችን በዝምታ አልፎ ትውልዱን ጫት ቃሚ አድርጎታል። 
  • አድሜ ለ ግንቦት 20 ምሳ ሰዓት ላይ ከቢሮ ወጥተው ጫት ቅመው የሚመለሱ የባንክ ሰራተኞች፣መሀንዲሶች ወዘተ አፍርቷል ግንቦት 20።ከደንበል ህንፃ ጀርባ የሚገኙ የመቃምያ ቦታዎችን ብንመለከት በምሳ ሰዓት ደንበል ህንፃ የሚሰሩ ምሁራን ዩንቨርስቲ ሳሉ በተፈቀደላቸው የመቃም መሰረት ሥራ ከያዙ በኃላም ለመላቀቅ ትቸግረው ይታያል።እረ  እንዲያውም በሥራ ሰዓት ሾለክ ብለው የሚቅሙ ሰራተኞች መኖራቸውን የእዚህ ፅሁፍ ፀሐፊ እማኝ ነው። እድሜ ለግንቦት 20።
  • እድሜ ለግንቦት 20 ወላጅ አልባ ሕፃናት ጎዳና እንዳይወጡ በሕዝቡ የሚደገፍ እንደ ሕፃናት አምባ መስርቶ ከማሳደግ ይልቅ ለአንድ ሕፃን እስከ 25000 ዶላር መንግስት እየተቀበለ በጉዲፈቻ ስም ለአሜሪካ እና አውሮፓ የተቸበቸቡት እና ብዙዎች በህሊና ስቃይ እና የማንንነት ጥያቄ እንዲሰቃዩ የተደረጉት በግንቦት 20 ፍሬ ነው (ሰኔ 25/2012 እአአቆጣጠር  በቢቢሲ ድህረ ገፅ ላይ በወጣ አንድ ዘገባ መሰረት ኢትዮጵያ በአመት 5ሺህ በላይ ሕፃናት በማደጎነት ወደ አሜሪካ  ብቻ እንደሚሄዱ  እና አሜሪካ ከዓለም ላይ በማደጎነት ከምትወስደው ሕፃናት ኢትዮጵያውያን ሕፃናት ከ አምስቱ አንዱ እንደሆኑይገልፃል።(http://www.bbc.co.uk/news/world-africa-18506474)
  • እድሜ ለግንቦት 20 ሴት እህቶቻችን ተስፋ ቆርጠው ለአረብ ሀገር ባርነት  በአስርሺዎች የተጋዙት በሄዱበት ሀገርም ስበልደሉ የሚሰማቸው አጥተው አሳር ፍዳቸውን የሚያዩት ከግንቦት 20 ፍሬ ወዲህ ነው።
  • እድሜ ለግንቦት 20 ''የኤርትራ ጥያቄን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መፍታት የሚቻለው የ ሻብያን ሃሳብ በመቀበል ነው'' ብለው ስያግባቡን የነበሩት  አቶ መለስ- ጦርነቱ አበቃ ከተባለ ከ ሰባት አመታት በኋላ ለዳግም እልቂት ''ድንበር'' በሚል ሰበብ ዳግም የኢኮኖሚ ፀባቸውን ወደ ወታደራዊ ግጭት ቀይረው በአስር ሺዎች የረገፉት በ ግንቦት ሃያ ውጤት ነው፣
  • እድሜ ለግንቦት 20 ስደት ቀድሞ የነበረ ቢሆንም በከፍተኛ ተስፋ መቁረጥ በባህር፣በእግር ወዘተ ወጣቱ ከሀገር የሚወጣው ከግንቦት 20 ፍሬ ወዲህ ነው (ወደየመን በጀልባ ተሳፍረው ከገቡት ስደተኞች ከ 70%በላይ ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ኮሚሽን በዘንድሮው ዘገባው መጥቀሱን ልብ በሉ) ፣
  • እድሜ ለግንቦት 20 ወጣቶች ተምረው በእውቀታቸው ሀገርንም መጥቀም ሲገባቸው፣የስራ ዕድል የሚያገኙበት ወይንም  ስነልቦናቸውን የሚጠብቅ ግን ለፈጠራ የሚያዘጋጅ የስራ መስክ ከመፍጠር ይልቅ በምረቃቸው ጊዜ (የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ  2004ዓም ምረቃ ላይ አቶ ጁነዲን ለተማሪዎቹ እንደተናገሩት)ከዩንቨርስቲ ሲወጡ  የኮብል ስቶን ሥራን መስራት እንደሚገባ የተነገራቸው በግንቦት 20 ውጤት ነው። 
  • እድሜ ለግንቦት 20 በሚድያውስ ቢሆን (ጎረቤት ኬንያን ለማነፃፀርያ እንጠቀም) ኬንያ የህዝብ ብዛቷ 30 ሚልዮን ሲሆን እኛ 85 ሚልዮን መሆኑን እናስታውስ እና ኬንያ በይዘታቸውም ሆነ በአቀራረባቸው የመንግስት እጅ ያልተጫናቸው 8 የቴሌቭዥን ጣቢያ፣ 38 ራድዮ ጣብያዎች፣ ከእሩብ ሚልዮን በላይ አንባቢ ያላቸው በየቀኑ የሚታተሙ 4 ጋዜጦች (http://www.pressreference.com/Gu-Ku/Kenya.html#b) ሲኖሩ ሃሳብን የመግለፅ መብት እና በሀገሪቱ የፖለቲካ ጉዳይ ላይ የመወያየት ነፃነት ከእኛ ጋር ሊወዳደር የማይችል መሆኑን ስናስብ እና ጋዜጠኞች መንግስትን ወቀሱ ተብለው በአሸባሪነት ዘብጥያ መውረዳቸውን ስናስብ እድሜ ለግንቦት 20 እንላለን።
  • እድሜ ለ ግንቦት 20 ጋና ነፃነቷን ስታገኝ የገነባነው ስታድዮም ዛሬ ጋና ከነፃነት አልፋ እስከ መቶ ሺሕዝብ የሚይዝ ስታድዮም ስትገነባ እኛ አሁንም አንድ ለእናቱ በሆነ ስታድዮም መገኘታችን የግንቦት 20 ውጤት ነው።እርግጥ ነው በዛሬው የግንቦት 20 በዓል የስፖርት አካዳሚ ምረቃ በአል እየተከበረ ነው። ስታድዮምስ ?
  • እድሜ ለግንቦት 20 ቀድሞ ጉቦ የሚለው ቃል ሲነሳ ስለ 20 እና 30 ብር ጉቦ እናስብ ነበር። ዛሬ ጉቦ፣ሙስና እና ዝርፍያ ማለት አድገው ተመንድገው  ዝርፍያ ማለት የብሔራዊ ባንክን የወርቅ ክምችት በወርቅ መሰል ነገር መቀየር ሲሆን ጉቦ ማለት ደግሞ የሀገር መሬት እና ውሃን  ለሕንድ እና ለአረብ በርካሽ መቸብቸብ ፣ በባለስልጣናት ቤት እንደባንክ ቤት በኢይሮ ብሉ በዶላር ቢሉ በፈለጉት የገንዘብ አይነት ከቤት ማስቀመጥ ማለት ነው (በቅርቡ የግምሩክ ባለስልጣናት ቤት  ተገኘ የተባለውን ብር ያስታውሱ)።

ይህንን ሁሉ ስናስብ ነው እንግዲህ ግንቦት 20 ካለፈው ይልቅ መጪውን የሚያስፈራ የሚያደርግብኝ።ከሁሉ የከፋው ግን መንግስት ስለሰራሁት መንገድ እና ድልድይ ስታመሰግኑኝ መስማት ብቻ ነው የምፈልገው ከማለቱም በላይ መሰረታዊ ስህተቶችን ''የጨለምተኞች አመለካከት'፣ የአመለካከት ችግር'' እያለ ማጣጣሉን መቀጠሉ ነው አሳዛኙ።

አበቃሁ 
ጌታቸው 
ኦስሎ 

Sunday, May 26, 2013

አጥንት የሚሰብር ድርጊት (ቪድዮ)

የሕፃናት አምባ እንዴት ተዘጋ? ጉዳያችን ጡመራ በሚያዝያ ወር 2005 ዓም

(http://gudayachn.blogspot.no/2013/04/blog-post_8.html)ወላጅ አልባ ሕፃናትን በተመለከተ ቀረበ ፅሁፍ ''የሕፃናት አምባ'' በቀድሞ መንግስት እንደተመሰረተበአሁኑ መንግስት ደግሞ መዘጋቱን እና በአሁኑም ጊዜ ሕፃናትን በጉድፈቻነት ወደውጭ ከመላክ ይልቅ በአንድ ላይ የማሳደግ በጎ ስራ መስራት የመቻሉን እውነታ ቸል መባሉን የሚያሳስብ   ነበር።
ሆኖም ግን ፅሁፉ   እንዴት በአሁኑ መንግስት እንደተዘጋ በቂ መረጃ አልያዘም ነበር።የኢሳት ቴሌቭዥን ''ምን አለሽ መቲ?'' ፕሮግራም ላይ የአምባው ሕፃናት እንዴት እንደተባረሩ የሚያሳይ ቃለ መጠይቅ ቀርቧል።ጉዳዩ እጅግ አሳዛኝና አጥንት የሚሰብር ድርጊት ነውአሁንም ስላለፈው ጉዳይ በማዘን መቆጨቱ ምንም ላይፈይድ ይችላል።ይልቁንስ አሁንም በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ አባት እናት የሌላቸው ሕፃናትን እንዴት እንድረስ?መንግስትም ኃላፊነቱን እንዴት ይወጣ? የሚለው ላይ ማተኮር ከዜጎች የሚጠበቅ ግዴታ ነው። 


ኢሳት ''ምን አለሽ መቲ?'' ፕሮግራም

Friday, May 24, 2013

የቀዳማዊ አፄ ሃይለስላሴ ታሪካዊ ንግግር በ አፍሪካ አንድነት ድርጅት (የሁኑ አፍሪካ ህብረት) የመሪዎች ስብሰባ።


የቀዳማዊ አፄ ሃይለስላሴ ታሪካዊ ንግግር በ አፍሪካ አንድነት ድርጅት (የሁኑ አፍሪካ  ህብረት) የመሪዎች ስብሰባ።












Tuesday, May 21, 2013

ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት የ ‹‹ሰማያዊ›› ፓርቲ ሊቀመንበር ከላይፍ መጽሄት ጋር ያደረጉት ቃለ መጠይቅ (ግንቦት 13/2005 ዓም (ግንቦት 21/2013ዓም)

ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት ‹‹ሰማያዊ›› ፓርቲ ሊቀመንበር ናቸው፡፡ ፓርቲው ከተመሰረተ ጥቂት እድሜ ያስቆጠረ ቢሆንም በአሁኑ ወቅት በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች የሚነሳ ለመሆን በቅቷል፡፡ የላይፍ መጽሄት አዘጋጅ የሆነው ዳዊት ሰለሞን ግንፍሌ አካባቢ በሚገኘው የፓርቲው / ቤት በመገኘት አነጋግሯቸዋል፡

 ላይፍ - ለፖለቲካ ስራ ሙሉ ጊዜን መስጠት በኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ አስቸጋሪ አይሆንም?

ኢንጅነር ይልቃል - መኖር ስላለብኝ ጥቂት ስራ እሰራለሁ፣ የሚበዛውን ጊዜዬን ግን የማሳልፈው ለፓርቲው ስራ ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ ነገሮች ለምርጫ አስቸጋሪ ሲሆኑ የምትወስደው ውሳኔ አንዱን በማጠፍ ለአንደኛው ብቻ ራስህን መስጠት ይሆናል፡፡

ላይፍ - የሚመሩት ፓርቲ ሰማያዊ የፖለቲካ ፍልስፍናው በምን ላይ የተመሰረተ ነው?

ኢንጅነር - ጥያቄው ሰፋ ያለ ነው፡፡ በዋናነት ግን የፖለቲካ ፍልስፍናችን በግለሰብ መብት ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ ሴንተር ራይት ሞደሬት ሊበራሊዝምን የፖለቲካ አመለካከት እናራምዳን ብለን ነው የምናምነው፣ የግለሰብ መብት ከተከበረ የሁሉም መብት ይከበራል እንላለን፣ መብት ከግለሰብ ይጀምራል፡፡ ለምሳሌ ይልቃል ወንድ ነው ስለዚህ ጾታ አለው፣ ይልቃል ቋንቋ፣ ትምህርትና ሞያ ያሉት በመሆኑ ሌላ የተለየ ነገር አያስፈልግም፡፡ የእኔ መብት ከተከበረ የምናገረውም ቋንቋ ይከበራል ማለት ነው፡፡ ቡድንና ግለሰብ እኩል ይታያሉ የሚለው አመለካከት ምክንያታዊ አይደለም፡፡ ከቡድን በፊት ግለሰብ ይቀድማል፡፡ እናም የግለሰቡ መብት ሲከበር የቡድኑ ይከበራል ብለን እናምናለን፡፡ የፖለቲካ ድርጅት በየጊዜው ራሱን እያረመ የሚሄድ እንጂ በቅድመ ድንጋጌ ላይ ተመስርቶ ፖለቲካ ሊሰራ አይችልም፡፡ ለምሳሌ የጎሳ ድርጅት እንጂ የጎሳ ፓርቲ መሆን አይቻልም፡፡ እዚህ አገር ጉዳዩ በጣም ስስ በመሆኑ አንነካውም እንጂ አንድ ሰው የኦሮሞ ድርጅት ነኝ ብሎ ከተነሳ ከኦሮሞ ወዴት መሄድ ይችላል? ምክንያቱም ከመነሻው የተወሰነ ነው፡፡ በጎሳ መደራጀት አሁን እየተፈጠሩ ያሉ ነገሮች መነሻ ነው ብለን እናምናለን፡፡ በቡድን መብቶች መከበር እናምናለን፡፡ ነገር ግን የሁሉ ነገር ማጠንጠኛ በኢትዮጵያችን ውስጥ ጎሳ መሆን ይገባዋል የሚል አመለካከት የለንም፡፡

ላይፍ ገዢው ፓርቲ ዜጎችን ከመደራጀት ውጪ የማያውቅ የማይመስልበት ሁኔታዎች እየተፈጠሩ ነው፡፡ የፌደራል ስርዓቱም ክልላዊነት፣ ቡድናዊነትና መንደርተኝነት እንዲፈጠር ምክንያት ሆኗል በማለት የፖቲካ ምሁራን ይተቻሉ፡፡ እናንተ ደግሞ የሁሉ ነገር መነሻ ግለሰብ ነው እያላችሁ ነው፡፡ እነዚህ ጫፎች እንዴት ይታረቃሉ?

ኢንጅነር - ፖለቲካ ለጊዜው በሚፈጠር ንፋስ የሚነሳ መሆን የለበትም፡፡ ሩቅ አሻግረህ በማየትም አሰላለፍህን መቅረጽ ይኖርብሃል፡፡ ጎሰኝነት እዚህ አገር ውስጥ ከሰፋ አንተ ኢትዮጵያዊ ነኝ ብለህ ብትሄድ ተቃውሞ ሊያጋጥምህ ይችላል፡፡ ይህ በመሆኑ ግን በቃ በማለት ነገሩን ተቀብለህ እንድትሄድ ሊያደርግህ አይገባም፡፡ የጎሰኝነት አመለካከት የመጣው ከቅኝ ገዢዎች ጋር ተያይዞ ነው፡፡ ቅኝ ገዢዎች ተገዢዎቹን ከፋፍለው ለመግዛት ያመቻቸው ዘንድ ተጠቅመውበታል፡፡ እንግሊዞች በዚህ መንገድ ብዙ ርቀት መጓዝ ችለዋል፡፡ ነገር ግን አሁን ይህ አመለካከት ስልጣንና አቅም ያገኘ በመሆኑ አገር እያተራመሰ ይገኛል፡፡ ምንም እንኳን የእኔ እበልጥ የእኔ እበልጥ ፉክክር ነግሶ አገራችንን ሊያጠፋብን የተቃረበ ቢሆንም የግለሰብ መብት መከበር ቅድሚያ ሊሰጠው ይገባል በማለት እየታገልን እንገኛለን፡፡ ኢትዮጵያዊያን ታላቅ ነበርን፣ ኢንተርኔት ውስጥ ገብተህ ስለ ኢትዮጵያ ለማወቅ ብትፈልግ ከአለማችን ጥንታዊ ህዝብ አንዷ ስለመሆኗ ትገነዘባለህ፡፡ ይህ የጎሳ አመለካከት ግን አሁን የተፈጠረና የቅርብ ጊዜ ታሪክ ነው፡፡ህዝቡ ወደቀደመው ታላቅነቱ መመለስ ይኖርበታል፡፡

ላይፍ የነበረንን ብሔራዊና የአንድነት መንፈስ ያላላና ወደ ቡድናዊነት እንድናዘነብል ያደረገን ነገር በአንተ ዕይታ ምንድን ነው?

ኢንጅነር - አንዳንድ ሰው ደርግን ብሔራዊ ስሜት የነበረው በማለት ሲያቀርበው እገረማለሁ፡፡ ደርግ አለም የወዛድሮች ትሆናለች የሚል አመለካከት ነበረው፡፡ ኢትዮጵያዊነት በአለም አቀፋዊ ወዛደራዊነት ጥላ ስር ገብቶ ነበር፡፡ ኢህአዴግ የደርግን አለም አቀፋዊ ወዛደራዊነት በብሔር ብሔረሰቦች ለወጠው፡፡ ስለዚህ ኢህአዴግ ይህንን አመለካከቱን ለማስረጽ በብዙ ነገሮች ላይ ዘምቷል፡፡ እኔ ዩኒቨርስቲ የገባሁት ኢህአዴግ ስልጣን በያዘበት ወቅት ነበር፡፡ በትምህርት ቤት ይሰጥ የነበረን የታሪክ ትምህርት አፋለሰ፣ ትልቅ ክብር ይሰጣቸው የነበሩ መመህራንን ከዩኒቨርስቲዎች እንዲባረሩ አደረገ፣ ከዚያ በመቀጠልም በኢትዮጵያ ውስጥ ትልቅ ትርጉም የነበረውን ሽምግልና አጠፋ፡፡ ሕዝቡ ሃይማኖተኛ በመሆኑ ለሃይማኖቱ ላቅ ያለ ግምት ይሰጣል፣ ኢህአዴግ በዚህ ዙሪያ ያሉ ሰዎችን በመያዝ የሃይማኖት ቤቶችን በካድሬዎች እንዲሞሉ አደረገ፡፡ የአገሪቱ አንኳር ነገሮችን በመያዝ ሚዲያውን በመቆጣጠር ለህዝቡ ውሸት መመገብ ጀመረ፡፡ እንግዲህ በዚህ ውስጥ ያለፈ አንድ 20 አመት ወጣት ታሪክ፣ ሃይማኖት፣ ሽምግልና እና ትምህርት ከሌለው እንዴት ማንነቱን ማግኘት ይችላል? በእነዚህ ነገሮች ላይ በአቋም ደረጃ ተዘምቷል፡፡ የአገሪቱ ምሰሶ የነበሩ ነገሮች አሁን በቦታቸው አይገኙም፡፡ በአንድነት ውስጥ የነበረን ህዝብ በጎሳው እንዲሰባሰብ በማድረግ በህዝቡ መካከል አለመተማመን እንዲሰፍን ተደርጓል፡፡ የፖለቲካው ዋነኛ ኃይል ደግሞ ከጥቅም ጋር እንዲተሳሰር በመደረጉ አንድ ሰው ለምን ኢህአዴግ እንደሆነ ብትጠይቀው ምላሽ አይሰጥህም፡፡ ምክንያቱም ወደዚያ የሚሄደው የስራ ዕድል፣ የትምህርትና ሌሎች ጥቅሞችን እንደሚያገኝ የሚሰበክ በመሆኑ ነው፡፡ ብሔራዊ ስሜት የምንለውን ነገር ይህ መንግስት ያሳሳው በአጋጣሚ ሳይሆን ሆን ብሎ አስልቶ ነው የሚል እምነት አለኝ፡፡

ላይፍ - ነገር ግን ኢህአዴግ የመንግስትነቱን ሚና መጫወት ከጀመረ ወዲህ ማንነታችን ተከበረ፣ በራሳችን ቋንቋ መናገር ጀመርን የሚሉ ቡድኖች ተፈጥረዋል፡፡ ኢህአዴግም የደርግን የአንድነት ፍልስፍና በመተቸት በልዩነታችን ውስጥ አንድነታችን እንዲወጣ አድርጊያለሁ ይላል፡፡

ኢንጅነር - እኔ ምን እንደተገኘ አይገባኝም፡፡ በቋንቋ መናገር የሚባለውም ነገር አዲስ አይደለም፡፡ ለምሳሌ ደቡብ ኢትዮጵያ ብትሄድ ህዝቡ በአማርኛ ሲናገር ታገኘዋለህ፡፡ አማርኛን ድሮ ይናገር ከነበረው ህዝብ አሁን የሚበልጠው ይናገረው እንዲሆን እንጂ አያንስም፡፡ መጻህፍት ከድሮ ይልቅ አሁን በአማርኛ በብዛት ይጻፋሉ፡፡ ድሮ ብዙ መጽሔት አልነበረም፡፡ አሁን ግን በዛ ያሉ መጽሄቶችን በአማርኛ ማግኘት ይቻላል፡፡ የተወሰኑ የየጎሳዎቹ ልሂቃን የራሳቸውን ጥቅም በማግኘታቸው ብቻ ካልሆነ በስተቀር አዲስ ነገር ተፈጥሯል የሚል ግምት የለኝም፡፡ ኦሮምኛ እኮ በኢህአዴግ ዘመን አልተፈጠረም፡፡ ድሮም ይነገር ነበር፡፡ ነገር ግን ቋንቋውን ለማስፋፋት የላቲን ፊደል ከመጠቀም የግእዝ ፊደልን ብንጠቀም ይሻል ነበር፡፡ ኢህአዴግ ሆን ብሎ ቅኝ ገዢዎች እንዳደረጉት ህዝቡን ለመግዛት እነዚህን ነገሮች ተጠቅሞባቸዋል፡፡ ኢህአዴግን በመጠጋት በአንድ ሌሊት ሚልየነር የሆኑ ሰዎች አሉ፡፡ ግን ደሀው ኢትዮጵያዊ ኦሮምኛ፣ አማርኛ ወይም ሲዳምኛ ይናገር የእርሱ ችግር አይደለም፡፡ ከስንዝር መሬቱ ጋር ተጣብቆ ከመኖር ውጪ ጠብ ያለለት ነገር የለም፡፡ ድሮም ገጠር ውስጥ ኦሮምኛ ይናገር ነበር አሁንም ይናገራል፡፡ ድሮም የከለከለው የለም፣ አሁንም ምንም አላገኘም፡፡ ተራ ፕሮፓጋንዳ እንጂ መሬት የያዘ ምንም ነገር የለም፡፡

ላይፍ - ክልሎች የራሳቸውን አስተዳደር መርጠው ህግ በማውጣት እንዲተዳደሩ ስለመደረጋቸው ይነገራል፡፡ ማዕከላዊ የነበረው የመንግስት አወቃቀር ፌደራላዊ በመሆን ስልጣኑን ለክልሎች መስጠቱን ሰማያዊ ፓርቲ የሚመለከተው እንዴት ነው?

ኢንጅነር - የፌደራል ስርዓት በራሱ መጥፎ አይደለም፡፡ እኛ ኢትዮጵያዊያን ለፌደራል አስተዳደር አዲስ አይደለንም፡፡ በየክልሉ ከድሮ ጀምሮ አስተዳዳሪዎች ነበሩ፡፡ 90 ሚልዮን ህዝብ በላይ የሚገኝባትን አገር በአሀዳዊ አስተዳደር ለመምራት መሞከር ትልቅ ችግር ነው፡፡ ክልሎች የራሳቸውን አስተዳደር በመመስረት ስልጣን ከማዕከላዊው መንግስት መጋራታቸው ጥሩ ነገር ነው፡፡ ችግሩ ግን ህዝቡን በጎሳ ከረጢት ውስጥ በመክተት በመከራውና በደስታው ወቅት አንድ የነበረውን ህዝብ ማለያየት ነው፡፡ ዘውዴ ነሲቡ የሚባሉ ሸዋ ውስጥ 130 አመት ኖረው ያረፉ ሰው ሲናገሩ ‹‹እርሱ የሲዳማ፣ የጎጃምና የወለጋ ሰው ነው›› ይሉ ነበር፡፡ ያኔ ሰውን በጎሳው ሳይሆን በሚኖርበት አካባቢ ባለው ተቀባይነት በመነሳት ይጠራ እንደነበር መረዳት እንችላለን፡፡ እኛም ብንሆን የፌደራል ስርአቱን በመቀበል የየክልሉ ሰዎች ክልላቸውን ያስተዳድሩ መባሉን እንደግፋለን፡፡ ድሮም እኮ የሸዋ፣ የትግሬ፣ የኦሮሞ ንጉስ የሚባሉ ነበሩ፡፡ እነዚህ የየክልሉ ንጉሶች የነበሩ ቢሆንም ለንጉሰ ነገስቱ ይገብሩ ነበር እንጂ እንገነጠላለን አይሉም፡፡ ቴክኖሎጂው ባልነበረበት ዘመን የነበሩ ነገስታት ከምንም በላይ ለአገራዊ አንድነት ቅድሚያ ሲሰጡ አሁን ላይ የሚገኙ የፖለቲካ ሳይንስ ፕሮፌሰር ነን የሚሉ ግን ኦሮሞን እንገነጥላለን ይላሉ፡፡ የኢህአዴግ ፌደራሊዝም የይስሙላ ነው፡፡ ፓርቲው ሶሻሊስት በመሆኑ መሰረቱ ማዕከላዊነት ነው፡፡ ጥቂት የበላይ አመራሮች ሁሉን ነገር የሚወስኑበት ፓርቲ ነው፡፡ ለክልሎች ሰጠሁ ያለውን ስልጣን ጣልቃ በመግባት ብዙ ጊዜ ሲያፍን ተመልክተነዋል፡፡ እንደውም ከኢህአዴግ ዘመን ይልቅ በድሮ ጊዜ የየክልሉ ገዢዎች የተሻለ ስልጣን ነበራቸው፡፡ የራሳቸውን ጦር በማደራጀት ያስተዳድሩ ነበር፡፡ አገራዊ በሆነ አጀንዳ ላይ ግን በህብረት ከሌሎች ጋር ይሰሩ ነበር፡፡ የኢህአዴግ የድርጅት ባህሪና ፌደራሊዝም አብረው መሄድ የሚችሉ ነገሮች አይደሉም፡፡ ይህ የአስመሳይነትና የአታላይነት የፖለቲካ ባህል ነው፡፡ በአጭሩ በእኛ አመለካከት የፌደራል ስርአት ጂኦግራፊውን፣ በውስጡ የሚኖሩ ህዝቦች በስነ ልቦና የተገናኙ መሆናቸውን፣ ቋንቋቸውን፣ ለአስተዳደር ምቹ መሆኑን የመዘነ መሆን ይገባዋል፡፡ በአንድ አገር ውስጥ ክፍላተ ሀገራት እንዲኖሩ በማድረግ ስልጣኑ የክፍላተ ሀገራቱ እንዲሆን እንታገላለን፡፡

ላይፍ - ኢህአዴግ እኔ ባልኖር አገሪቱ ትበታተናለች በማለት ሁልጊዜም ሲናገር ይደመጣል፡፡ የመበታተን ስጋት ተጋርጦባት ለነበረች አገር የመሰረትነው የፌደራል አወቃቀር ፍቱን መድሀኒት ሆኗል ማለቱን እንዴት ይመለከቱታል?

ኢንጅነር - እኛ የምንከተለው የአስተሳሰብ መስመር ከኢህአዴግ የተለየ ነው፡፡ ከጋራ ጉዳይ ይልቅ ልዩነትን በማጉላት አገርን እጠብቃለሁ ማለት አታላይነት ብቻ ነው፡፡ አሁን ባለው እውነታ የብሔረሰብ አስተዳደር አለን በማለት ብትጠይቀኝ ምላሼ የለም ነው፡፡ አገሪቱን እየመሩ የሚገኙት ጥቂት ቡድኖች ናቸው፡፡ ባንኩን፣ መከላከያውንና ሌሎቹን ቁልፍ ቦታዎች እየመሩ የሚገኙት ከአንድ አካባቢ የመጡ ሰዎች ናቸው፡፡ የብሄር ጭቆና ከየትኛውም ጊዜ በከፋ ሁኔታ ውስጥ ያለው በዚህ አገዛዝ ነው፡፡ ብዛት ያላቸው ነጻ አውጪ ድርጅቶች የተፈጠሩት እኮ በዚህ ወቅት ነው፡፡ የብሄር ጥያቄ ከተመለሰ እነ ኦብነግን የመሳሰሉ ድርጅቶች እንዴት ሊፈጠሩ ቻሉ፡፡ መከላከያው ውስጥ ምን ያህል የብሄር ብሔረሰብ ተወካዮች በአመራር ቦታው ላይ ይገኛሉ? ፖለቲካን ትንተና ብቻ ማድረግ የለብንም፡፡ መሬት ላይ ያለውን እውነታም ልንመለከትበት ይገባል፡፡

ላይፍ - የአንድ ቡድን የበላይነት ወይም ከአንድ ክልል የወጡ ሰዎች የስልጣን መደላደሉን በመያዝ የወጡበት ክልል ወይም ብሄር ስልጣን መያዝ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል?

ኢንጅነር - የቡድኑን ተጠያቂነት ያሳያል፡፡ ከዚህ በላይም ለማደናገሪያነት ይውላል፡፡ ለምሳሌ ህወሃት ይህን ነገር ተጠቅሞበታል፡፡ አንደኛ ስልጣን የያዙት የእኛ ልጆች ናቸው፡፡ ተዋግተዋል፣ ደምተዋል መስዋዕትነት በመክፈላቸው ስልጣኑን መያዝ አለባቸው የሚል ስነ ልቦና እንዲፈጠር ሆኗል፡፡ የትግራይ ሰዎች ከዚህ በመነሳት ነገሮችን በዝምታ ማየቱ በስሙ እንዲነገድበት ሆኗል፡፡ ነገር ግን ጥቂቶች ይህንን ተገን በማድረግ እየተጠቀሙ ነው፡፡ ህወሃቶች ለትግራይ ህዝብ እኛ ከሌለን ሌላው ያጠፋሃል በማለት ከቀሪው የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር እንዲቃረን እያደረጉት ነው፡፡ የትግራይ ህዝብ ተጠቅሟል ለማለትም አመራር ላይ ያለው ቡድን በተወሰነ ደረጃ የሚያደርገው ነገር አለ፡፡ ማደናገሪያ ቢኖረውም በዚያ አካባቢ ያለው ሰው ፊት ለፊት ወጥቶ መናገር አለበት፡፡ ሌላው ሰው በእነርሱ ቅር እንዲሰኝ እያደረገ የሚገኘው ነገርም ለዘብተኝነታቸው ይመስለኛል፡፡ አሁን አሁን ግን ይህ ነገር እየተቀረፈ ነው፡፡ በመቀሌ ዩኒቨርሲቲና በአረና ፓርቲ ውስጥ ያሉ አንዳንድ ወጣቶች ብቅ እያሉ ነው፡፡

ላይፍ - በቅርቡ በጉራፈርዳና ቤኒሻንጉል አካባቢ ወደተከሰቱ መፈናቀሎች እንምጣ፡፡ ዜጎች የአንድ ክልል ተወላጆች በመሆናቸው ብቻ እንዲፈናቀሉ ተደርገዋል፡፡ ይህ ነገር በእርስዎ እይታ በምን መንስኤነት የተፈጠረ ነው?

ኢንጅነር - ከጥቂት ቀናት በፊት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ለፓርላማው ቀርበው ሲናገሩ እንደሰማሁት ችግሩ የተፈጠረው በአቅም ማነስና በብቃት ችግር አይደለም፡፡ ወይም እዚያ አካባቢ ያሉ ኃላፊዎች በሙስና ከመጨማለቃቸው የተነሳ የተፈጠረ ነው ማለታቸውንም አልቀበልም፡፡ ነገሩ የተፈጠረው በፖሊሲ ደረጃ በደንብ ተጠንቶ ነው፡፡ አንደኛ ይህ ነገር አሁን የተፈጠረ አይደለም፣ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በአንድ ወቅት ፓርላማ ቀርበው ‹‹ ደቡብ ውስጥ ለመኖር በመጀመሪያ የደቡብን አስተዳደር መጠየቅ ይገባል›› ብለው ነበር፡፡ ስለዚህ ከክልላችን ውጡ የሚለው ነገር ፖሊሲው ከተቀረጸበት እውነታ በመነሳት የተፈጠረ ነው፡፡

ላይፍ - ፖሊሲውን ወይም ንድፉን ያወጣው ማን ነው ?

ኢንጅነር - ህወሃት ነዋ፡፡ አንተ ለመጽሔትህ በደንብ እንድናገርልህ ፈልገህ ካልሆነ በስተቀር ይህ የሚታወቅ ነው፡፡ የተጨቆነ ብሄረሰብ እንዳለ ካመንክ እኮ ጨቋኝ የምትለው አካል የግዴታ ይኖራል፡፡ ከዚህ አንጻር ድርጅቱ አማራን በጨቋኝነት በመፈረጅ የአማራን አከርካሪ እሰብራለሁ በማለት ተነስቷል፡፡ 1997 ምርጫ ወቅት ኢህአዴግ በዋናነት በከተሞች አካባባቢ ከፍተኛ ሽንፈት ሲያስተናግድ መለስ አሁንም የአማራና የቀድሞ መንግስት ናፋቂዎች እንዳልጠፉ ተረድቻለሁ በማለት መናገራቸው አይዘነጋም፡፡ እነዚህ ንግግሮች እየዋሉ እያደሩ እንዲህ አይነት ችግሮች እንዲፈጠሩ ምክንያት ሆነዋል፡፡ በአንድ ቋንቋ ተናጋሪ ላይ ያነጣጠረ ማፈናቀል መከሰቱ ትልቅ ትኩረት ማግኘት ይኖርበታል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የዘር ማጥፋት ወንጀል እየተፈፀመ ነው የሚለውን ክስ ለማስቀረት ሲሉ ችግሩ የተፈጠረው በጥቂት ሃላፊነት በማይሰማቸው ሰዎች ነው በማለት ነገሩን ለማድበስበስ ሞክረዋል፡፡ ነገር ግን ኢህአዴግን ጠንቅቆ የሚያውቅ ሰው አንድ ተራ ባለ ስልጣን ከመሬት ተነስቶ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን እንዲፈናቀሉ ያደርጋል በማለት ለመናገር ይቸገራል፡፡ ሌላው አስገራሚ ነገር በአሁኑ ሰአት አማራ ብቻ ሳይሆን ኦሮሞም ተፈናቅሏል ለማለት ኦሮሞ ነን የሚሉ ሰዎች ከቤኒሻንጉል እንደተፈናቀሉ ሲናገሩ እያደመጥን ነው፡፡ እነዚህ ሰዎች እስካሁን ድረስ የት ነበሩ ? ኢህአዴግ የመሬት ባለቤቶች ብሄር ብሄረሰቦችና ብሄሮች ናቸው ብሏል፡፡ በኢህአዴግ አመለካከት መሰረት እኔ የመሬት ባለቤት መሆን አልችልም፡፡በኢህአዴግ አስተሳሰብ ሁላችንም በህግ እኩል አይደለንም፡፡ ያለ ብሄርህ በመሄድ መሬት የምትዘው አንተ ማን ነህ? የሚለው አስተሳሰብ የመነጨው ስርኣቱ ከሚከተለው ፖሊሲ ነው፡፡

ላይፍ - አንዳንዶች አቶ ኃይለማርያም በፓርላማው በመቅረብ ችግሩን በማመን በተወሰነ ደረጃም ቢሆን ኃላፊነቱን የሚወስድ አካል እንደሚኖር መጠቆማቸውን እንደ በጎ ጅምር በመውሰድ መለስ ቢሆኑ ኖሮ ተፈናቃዮቹን መሬት ወራሪዎችና ተስፋፊዎች በማለት ይነቅፏቸው ነበር ይላሉ፡፡ በዚህ አስተያየት ይስማማሉ፡፡

ኢንጅነር - አንዳንድ ሰው እንግዲህ ያለበትን ሁኔታ መቀየር ያስፈልገው ይሆናል፡፡ መለስም እኮ በተወሰነ ደረጃ አቋማቸውን እንደቀያየሩ የመጡበት መንገድ ማሳያ ሆኖ መቅረብ ይችላል፡፡ እንደውም እንደ መለስ ተገለባባጭ አይነት ሰው ተመልክቼ አላውቅም፡፡ ሲመጡ ሊበራል ዴሞክራሲ፣ ነጭ ካፒታሊዝም ነው የምናራምደው አሉ፡፡ መጀመሪያ ማሌለት ነበሩ፡፡ ከዛ 1997 ላይ ታማኝ ጠንካራ ተቃዋሚ ብናገኝ ግማሽ መንገድ ድረስ ተጉዝን እንቀበላለን አሉ፡፡ ነገር ግን የሆነው ከሆነ በኋላ ልማታዊ መንግስት ነን፣ መስመሩም ዴሞክራሲ ነው አሉን፡፡ አሁንም ቢሆን በህይወት ቢኖሩ ኖሮ የማይጠበቅ ነገር ሊናገሩ ይችላሉ፡፡ አውቃለሁ መለስ መሸነፍ የማይፈልጉ እልኸኛ ሰው ናቸው፡፡ ቢሆንም ግን አለም አቀፍ ጫናው የማያምኑበትን እንኳን እንዲናገሩ ሊያደርጋቸው እንደሚችል አምናለሁ፡፡ መለስ ወጥ አቋም የነበራቸው የመርህ ሰው አይደሉም፡፡ ዛሬ ያነበቡትን መጽሀፍ በመያዝ የሚከራከሩ ነገ ደግሞ የትናንቱን በመተው የሚቀየሩ በጓደኞቻቸው ዘንድም ተለዋዋጭ ተደርገው የሚወሰዱ ነበሩ፡፡ በእርግጥ የአቶ መለስ አይነት የትግል መሰረትና መነሳሳት አቶ ኃይለማርያም ሊኖራቸው አይችልም፡፡ ምክንያቱም የመጡት ከትምህርት አካባቢ ነው ፡፡ ስለዚህ አማራውን ጨቋኝ በማድረግ በመሳል የመከትከት አላማ ሊኖራቸው አይችልም፡፡ ከዚህ በመነሳት ነባራዊውን ሁኔታ ከግምት በማስገባት የተወለጠ ነገር ተናግረዋል፡፡ መለስም አቅም ሲያጡና የሚገቡበት ሲጠፋቸው እንዲህ ሊናገሩ ይችሉ ነበር፡፡ አሁንም ቢሆን ግን ከንግግር ያለፈ ነገር አለመደረጉ መሰመር ይገባዋል፡፡ ተፈናቅለው ለነበሩ ሰዎች ምን ተደረገ ? ንብረታቸውን በትነውና የልጆቻቸውን ትምህርት አቋርጠው ለሶስት ወራት ያህል ሲንከራተቱ መንግስት ምን ይሰራ ነበር ? የአሁኑ ንግግር ከጫና የመጣ እንጂ አምነውበት የተናገሩት አይደለም፡፡ ኃይለማርያም ምናልባት የአፈጻጸም ችግር በማለት በግልጽ ተናግረው ይሆናል፡፡ መለስ በዚህ ቦታ ቢሆኑ ኖሮ ነገሩን በብልጣብልጥነት ለማለፍ ይሞክሩት እንደነበር ይሰማኛል፡፡

ላይፍ - ሁኔታውን ለማጣራት ወደ ቤንሻንጉል ክልል የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ማምራታችሁንና ለተወሰኑ ሰዓታትም መታሰራችሁን ሰምተናል፡፡ እስኪ በአጠቃላይ ስለተፈጠረው ነገር ይንገሩን?

ኢንጅነር - እውነት ለመናገር ስራ ስትሰራና ስትንቀሳቀስ ለአምስት ሰዓታት ያህል ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ እንድትቆይ መደረግህ ያን ያህል የሚወራለት አይሆንም፡፡ ይህ ግን የሚያሳየው ዜጎች በነጻነት ከቦታ ቦታ ተዘዋውረው መረጃ ማግኘት እንደማይችሉ ነው፡፡ በተጨማሪ ደግሞ በእኛ ላይ እንዲህ አይነት ነገር ያደረጉ ሰዎች እዛ በሚኖሩ ሰዎች ላይ ምን ሊያደርጉ እንደሚችሉ እንድናስብ ያደርገናል፡፡ ከዜጎች ጋር በመገናኘታችን ብቻ ይህንን እርምጃ ከወሰዱ መሬታችንን ወስዳችኋል በሚሏቸው ሰዎች ላይማ ምን ሊያደርጉ እንደሚችሉ ማሰብ በራሱ ይከብዳል፡፡ ተፈናቃዮቹ በአፋጣኝ ይዞታቸውን እንዲለቁ በመደረጋቸው ዘጠኝ ብር የምትሸጥ ላም በአንድ ሺህ አምስት መቶ ሸጠዋል፡፡ ተንቀሳቅሰን የተመለከትነው ሶስት ቀበሌዎችን ነው፡፡በአንድ ቀበሌ 58 ሰው በህገ ወጥ መንገድ ስለገባችሁ እንድትለቁ የሚል ወረቀት በይፋ ነው የተለጠፈባቸው፡፡

ላይፍ - የትና ማን ነው የለጠፈው ? ወረቀቱስ ማህተም ነበረው ?

ኢንጅነር - ማህተሙ የቀበሌ ገበሬ ማህበር ነው፡፡ ወረቀቱ ሌላው ቀርቶ ያላችሁን ንብረት ሸጣችሁ እንድትለቁ በማለት ያዛል፡፡ እቃቸውን እንኳን ይዘው የመውጣት መብት አልነበራቸውም፡፡

ላይፍ - ንብረታቸውን እንዲህ በወረደ ዋጋ የገዛው የአካባቢው ማህበረሰብ ነው ?

ኢንጅነር - የሚገዛ በማጣታቸው እኮ ነው ከመጣል ብለው የሸጡት፡፡ ዘጠኝ ሺህ ብር የሚያወጣ ላም በአንድ ሺህ ብር ስለተሸጠ ሸጠው ወጡ በማለት መናገር አይቻልም፡፡ እኔ ጥለው በትነው ወጡ ነው የምለው፡፡ እንዲመለሱ ከተደረገ በኋላ የአማራ ክልል ኃላፊዎች መጡ ተባለ፡፡ ነገር ግን ምንም ያደረጉላቸው ነገር የለም፡፡ ሰዎቹ እኮ ዝርፊያና ድብደባ ጭምር ተፈጽሞባቸዋል፡፡

ላይፍ - ድብደባውን የፈፀሙት ይታወቃሉ ?

ኢንጅነር - ፖሊሶችና የአካባቢው ታጣቂዎች ናቸው፡፡ እኔ ካናገርኳቸው ተፈናቃዮች መካከል 60 ሺህ ብር የተወሰደበትና 60 መሃለቅ የአንገት ወርቅ የተነጠቀች እናት ይገኙበታል፡፡ በሰደፍ የተደበደቡ ሰዎች ቁስላቸው ገና ባለመድረቁ ድብደባው ያደረሰባቸውን ጉዳት መመልከት ይቻላል፡፡

ላይፍ - ያለ ፍላጎታቸው እንዲፈናቀሉ የተደረጉት የአማራ ብሄር ተወላጆች በድጋሚ ያለ ፍላጎታቸው ተገድደው ወደ ቤንሻንጉል እንዲመለሱ ስለመደረጋቸው አንዳንድ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ እርስዎ በዚህ ዙሪያ የተመለከቱት ምንድን ነው ?

ኢንጅነር እነርሱ ምንም አይነት ስልጣን እዚህ ውስጥ የላቸውም፡፡ በኃይል እንዲወጡ እንደተደረጉ ሁሉ በኃይል እንዲመለሱ ተደርገዋል፡፡ ሲሄዱም ሆነ ሲወጡ የእነርሱ ፈቃድ አልተጠየቀም፡፡

ላይፍ - ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደተናገሩት ይህንን ድርጊት የፈፀሙ ኃላፊዎችን በማንሳት ብቻ መፈናቀሉ እንዲቆም ማድረግ ይቻላል ብለው ያምናሉ ?

ኢንጅነር - አይቆምም፡፡ አንድ ሰው በኢሳት ተጠይቆ እኮ ‹‹ ምንግዜም ችግር ሲመጣባቸው በእኛ ላይ መለጠፋቸው የተለመደ ካልሆነ በስተቀር ክልሉ ሳያውቀው የተሰራ ምንም ነገር የለም›› ብሏል፡፡ ነገሩ በፖሊሲ ደረጃ ተይዞበት የተሰራ ስለመሆኑ ምንም መከራከርያ አያስፈልግም፡፡

ላይፍ - የአማራው ውክልና አለኝ የሚለው ብአዴን በጉዳዩ ዙሪያ ዝምታን መምረጡን እንዴት ተመለከቱት ?

ኢንጅነር - ቅድም እኮ ብዬሃለሁ፡፡ እዚህ አገር የፌደራል አስተዳደርም ሆነ ስልጣን ያላቸው ፓርቲዎች የሉም፡፡ አገሩን የሚመራው የተወሰነ የፖለቲካ ቡድን ነው፡፡ ጣልያን በወረራው ወቅት የተወሰኑ የጎሳ መሪዎችን በመሾም ቅኝ ግዛቱ ሊያደርግን ሞክሮ ነበር፡፡ ሌላው አማራ የሚባል ጎሳ(ብሄር) መኖሩን አማሮች የምትላቸው ሳይቀሩ አያምኑም፡፡ ለምሳሌ እኔ ጎጃም ነው የተወለድኩት፣ ከጓደኞቼ ጋር ስንጨዋወት እስላም አማራ እንላለን እንጂ አማራ ጎሳ ስለመሆኑ አናውቅም፡፡ እኔ አማራ የሚባል ጎሳ ስለመኖሩ የሰማሁት ዩኒቨርስቲ ከገባሁ በኋላ ነው፡፡ አማርኛ ተናጋሪው በብሔረሰብ የሚያምን አይደለም፡፡ እንደው ከአንዳንድ አክራሪዎች ጋር እንዳታጣለኝ እንጂ አማራ የሚባል ጎሳ(ብሄር) ስለመኖሩ የሚያሳይ ማስረጃ የለም፡፡ ልክ ትግሬ፣ ኦሮሞ፣ ጉራጌ ከዚህ ወጣ እዚህ ገባ እንደሚባለው አይነት ማስረጃ የለም፡፡ አማራ የሚለውን ቃል የሚጠቀሙበት እስላም ክርስቲያን ለማለት ነው፡፡ ይህ የህብረተሰብ ክፍል ከበሮ ተመትቶ አገር ተወረረች ሲባል ብሎ ተነስቶ ጦርነት ይገጥማል፡፡ባህሉ፣ ሃይማኖቱና አመለካከቱ ሁሉ በኢትዮጵያዊነት የታጠረ ነው፡፡ ይህንን የሚያደርገው የተለየ ጥቅም በማግኘቱ አይደለም፡፡ ከኩርማ መሬት ውጪ በየትኛውም ስርዓት ተጠቃሚ አልሆነም፡፡

ላይፍ - ምናልባት ግን መፈናቀሉ በዋናነት አማራው ላይ ያነጣጠረው አማራውን የሚወክል ድርጅት ባለመኖሩ ይሆን ?

ኢንጅነር - እኔ እንዲህ አይነት ድርጅት መኖር አለበት ብዬ አላምንም፡፡ የእነዚህ ሰዎች አስተሳሰብ ኢትዮጵያዊነት ነው፡፡ በጎሳው ለማያምን ሰው የሆነ የጎሳ ድርጅት ማቋቋም ተገቢ ነው ብዬ አላስብም፡፡ አማራው በጎሳ እንዲታጠር ከተደረገም ኢትዮጵያ አለቀላት ብዬ ነው የማምነው፡፡

ላይፍ - በቅርቡ የቀድሞው የህወሃት አንጋፋ ታጋይ አቶ ስብሃት ነጋ ኢህአዴግ የአፍሪካ ምርጡ ፓርቲ ነው በማለት መናገራቸው ተሰምቷል፡፡ በእርስዎ ደረጃ ኢህአዴግ ግን የት ያስቀምጡታል ?

ኢንጅነር - በመጀመሪያ ደረጃ ኢህአዴግ የሆነ የፖለቲካ መስመር የሚከተል ድርጀት አይደለም፡፡ ከህወሃት አንስቶ ዝብርቅርቅ ያለ መስመር የሚከተል አንድ አይድኦሎጂ የሌለው ነው፡፡ ቀደም ብዬ ለመጠቆም እንደሞከርኩት ብሄራዊ ስሜት፣ ታሪክን፣ ባህልንና ማንነትን ያዋረደ ነው፡፡ ጉልበት በእጁ በማስገባቱም ሁሉንም አዳክሞ እየገዛ ነው፡፡ አዎን ከዚህ አንጻር ከሆነ ስብሃት እንዳሉት የአፍሪካ ምርጡ ፓርቲ ነው፡፡

የመጀመርያዋ የኢትዮጵያ ሴት ፕሬዝዳንት የነበሩት ክብርት አምባሳደር ሣህለወርቅ ዘውዴን በክብር አለመሸኘት የኢትዮጵያን ክብር ብቻ ሳይሆን ለሴት ልጅ ያለንን የክብር ልኬት የሚያሳይ ነው።

የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሣህለወቅ ዘውዴ ጉዳዩ የዲሞክራሲ ባሕላችን ያኋልዮሽ ጉዞ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። የኢትዮጵያ ታዳጊ ሴትና ወንድ ልጆች የምናስተምራቸው ምንድን ነው? የመጀመርያዋ ሴት ፕሬዝዳንት ሲሰናበቱ እንዴት...