ሚያዚያ 30፣1997ዓም ዕሁድ አዲስ አበባ ምናልባትም በኢትዮጵያ ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ የ ዲሞክራስያዊ ለውጥ የሚጠይቅ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ተደርጎ ነበር። በሚልዮን የሚቆጠር ሕዝብ በሰላም ወጥቶ በሰላም የገባበት- ሁሉም ነገር ካለ አንዳች እረብሻ የተጠናቀቀበት ታሪካዊ ሰልፍ ነበር።ይህ ሰልፍ ከተደረገ እነሆ ስምንት አመታትን አሳለፈ።
- የዲሞክራሲ መብታችን ወደፊት እንጂ ወደኃላ መንሸራተት አይገባውም።
- አዲሱ ትውልድም ለመጪው ትውልድ ፍርሃትን እና አምባገነንነትን ማውረስ የለበትም።
- የሕገ መንግስቱ አንቀፅ 30 ማንኛውም ሰው በሰላማዊ መንገድ ሰላማዊ ሰልፍም የማድረግ መብት እንዳለው ይገልፃል።
- ይህ ግን በተለያየ መንገድ ተሸራርፎ ሕጉ ስለመፃፉም ለመርሳት የሚዳዳቸው አለቆች በዝተውብናል።
- ዜጎች ሃሳባቸውን በነፃ የመግለፅ መብታቸው ይከበር!
- የሕገ መንግስቱ አንቀፅ 30 ይከበር!
ሚያዝያ 30፣1997 ዓም የነበረው ሰላማዊ ሰልፍ (ቪድዮ)
No comments:
Post a Comment