ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Friday, May 17, 2013

የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን የሙዚቃ አቀራረብ ትውልዱን እንዳይተዋወቅ እያደረገ ነው።


በ1990ዎቹ አጋማሽ ላይ ይመስለኛል።አዲስ አበባ የሚገኘው የፈረንሳይ የባህል ማዕከል በየአመቱ የአዝማሪ ቀን ብሎ የሚያዘጋጀው መርሃግብር እንደነበረው አስታውሳለሁ።በእዚህ ዝግጅት ላይ በኢትዮጵያ የሙዚቃ እድገት ላይም ሆነ ታሪክ ላይ ልዩ ልዩ ቅንብር ይቀርብበታል። አንድ ጊዜ ታድያ አንድ ፈረንሳዊ የኢትዮጵያን ሙዚቃ  ለረጅም ጊዜ ማናቱን ከተናገረ በኃላ  እንዲህ ማለቱን አስታውሳለሁ -
''የኢትዮጵያ አዝማሪ የህዝቡን ልዩነቱን እያኮሰሰ  አንድነቱን አጉልቶ የሚያሳይ የጅማት ክር ነው '' ማለቱንእውነት ነው ኪነት በትንታውውም ሆነ በዘመናውቷ ኢትዮጵያ ላይ ያለው ቦታ የሚናቅ አይደለም።ዛሬ ምን እየተደረገ ነው? 

የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን እና '' የኅብረት ትርዒት '' የተሰኘ  ፕሮግራሙ 

ላለፉት ሰላሳ አመታት ገደማ   የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን የሙዚቃ ፕሮግራም የሚቀርብበት '' የኅብረት ትርዒት '' የተሰኛ ፕሮግራም አለው። ይህ ፕሮግራም ካልተሳሳትኩ አሁንም የቀጠለ ይመስለኛል። የኅብረት ትርዒት ዝግጅቶች ላይ ያሉት ልዩነቶች ምን ያህል ህዝብን አንድ የማድረግ እና የመለያየት ልዩነት እንዳላቸው ልብ ብላችሁ ካልሆነ  ልንገራችሁ። ነገሩ እንዲህ ነው።
በመጀመርያ ደረጃ ኢትዮጵያ ያላት አንድ ለናቱ ቲቪ ከሰላሳ አመታት በላይ መዝለቁን እና አሁን የጣብያ ቁጥር አንድ፣ ሁለት ቢባልም የተለየ ዝግጅት እንደማይቀርብ አንዘንጋ። 
ይህ ምን ማለት ነው? ስንል አሁን ያለነውን ትውልድም ሆነ የታዳጊ ሕፃናቱን ስነልቦና ወደድንም ጠላንም በየሳሎኑ ገብቶ እየተስተናገደ ነው ማለት ነው።የዜና ዘገባውን ህዝቡ በሚገባ አይከታተልም ብንልም  የኅብረት ትርዒትን ዝግጅት ግን በዘመናችን እንመንለከት ነበር።የዛሬው ታዳጊም እንዲሁ ያደርጋል። የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን  ''የኅብረት ትርዒት ፕሮግራም'' እንዴት ሕዝብ ያቀራርብ ነበር? ዛሬ ደግሞ እንዴት  ያራርቃል?
ቀድሞ  የኅብረት ትርዒት ፕሮግራሙቹ መሃከል በሚቀርበው በያንዳንዱ ዝግጅት ላይ በተቻለው መጠን የተለያዩ ብሔረሰብ ዘፈኖችን ያሳየን ነበር። የኪሮስ አለማየሁን እና የፀሃየ ዮሐንስን ትግርኛ፣ የእነ አሊቢራ ኦሮምኛ ወዘተ ትውልዱ ያወቀው የሀገሩን ብሔረሰቦች እያከበረ ያደገው አንዱ አስተማሪ የነበረው ለጆሮ የሚመቹ የኪነት ውጤቶች በአማርኛ ብቻ ሳይሆን በልዩ ልዩ የሀገሪቱ ብሔረሰቦች እንዴት እንደሚከይኑ እየተመለከተ እያደነቀ ስላደገም ጭምር ነው። 

በዘመነ ኢህአዲግ ቴሌቭዥን ጣብያው መርሃግብሮቹን ከአማርኛ ሌላ ተጨማሪ ቋንቋዎችን መክፈቱ ተገቢ ቢሆንም በሙዚቃ ፕሮግራሙ ግን ትውልዱን የማይተዋወቅ አድርጎታል። የአማርኛውን የኅብረት ትርዒትን ዝግጅት በሙሉ በአማርኛ ዘፈን የተሞላ እና ዘመናውም ሆነ ባህላዊ የሆኑ ለምሳሌ የኦሮምኛ፣የትግርኛ፣ወላይትኛ ዘፈኖች ዝር እንዳይሉ ታግደዋል። በትግርኛ  የኅብረት ትርዒትን ዝግጅ ላይም  አንድም  የአማርኛም ሆነ የኦሮምኛ ዘፈን ማቅረብ ብርቅ ብቻ ሳይሆን ፈፅሞ የማይሞከር ሆኗል።በኦሮምኛው መርሃግብር ላይም የትግርኛም ሆነ የአማርኛ ዘፈኖች የሉም።እዚህ ላይ ነው እንግዲህ  የአማርኛውን ፕሮግራም የሚመለከት ስለ ትግርኛ ወይም ኦሮምኛ ዘፈኖች እንዳያውቅ፣የትግርኛ ተመልካቹም እንዲሁ  የኦሮምኛም ሆነ የአማርኛ ዘፈን እንዳይመለከት ሲደረግ የኦሮምኛውም ሆነ የአፋር ፕሮግራሞች ሁሉ ተመሳሳይ ዕጣ ደርሶባቸዋል።
የእዚህ ሁሉ የተንኮል ሥራ ውጤት የሚታየው ደግሞ  በዘመነ ኢህአዲግ  የተወለደ ትውልድ ኢትዮጵያትን የመምራት ዕድል የገጠመው ጊዜ የሌላውን ባህል እንዴት ያከብራል? እንዴት የኦሮምኛ ወይንም የትግርኛ ተናጋሪ ወገኑን ያከብራል? 
የብሔር ብሔረሰቦች እኩልነት በፉከራ እና ከ ሌኒን መፅሀፎች በመጥቀስ አይከበረም። ጥቃቅን በሚመስሉ ግን ትልቅ ፋይዳ ባላቸው እንደ ኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ህብረት ትርዒት መርሃግብሮች በሚሰሩት የዕለት ተዕለት ሥራ መሆኑን መዘንጋት አይገባም። በነገራችን ላይ ይህ ድርጊት በሀገሪቱ ብሔራዊ ራድዮም ላይ የሚታይ ነው። በዘመነ ደርግ የተለያዩ የሀገራችንን ቋንቋዎች ሙዚቃዎች መስማት የተለመደ ነበር።ለብሄር ብሔረሰቦች ቆምያለሁ እስከ ክልል ድረስ ከልያለሁ የለው መንግስት ግን የሌላውን ወገናችንን ዜማ አንዳንሰማ አግዶናል። እዚህ ላይ ይህ በትውልድ ላይ የሚሰራ ወንጀል የሚፈፀመው በአጋጣሚ ሳይሆን ታስቦበት እና ታቅዶ በመመርያ መሆኑ ነው ትልቁ አደጋ።


WACH HISTORY OF ETHIOPIAN MUSIC (The documentary film was recorded before22 years)
No comments:

ወቅታዊ የዓለም ሁኔታ እንድንነታረክ ዕድል የሚሰጥ አይደለም።ብንነቃ መልካም ነው።

========== ጉዳያችን ወቅታዊ ========== የዓለም ታሪክ እንደሚያስተምረን ዓለም በወሳኝ የእጥፋት(turning point) ታሪኮች ውስጥ አልፋለች። እነኝህ የእጥፋት ጊዜዎች የዋዛና የፈዛዛ ጊዜ አይደሉም።መላው ዓለ...