ጉዳያችን - በጉዳያችን ሚድያ፣ኮምኒኬሽን እና ምክር አገልግሎት የሚዘጋጅ ሲሆን ከ2003 ዓም ጀምሮ በድረ-ገፅ ላይ የነበረ በአሁኑ ጊዜ ከአንድ ሚልዮን በላይ ጎብኚዎች ያሉት ገፅ ነው። Gudayachn is prepared by Gudayachn Multimedia, Communication and Consultant Organization. It has been online since 2011. Currently, Gudayachn is being visited by over One-million readers from all over the world.
ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages
Saturday, October 30, 2021
ኢትዮጵያን እንደሶርያ ሊበትናት ከተነሳው የትግራይ ወራሪ ለማዳን በሚልዮን የሚቆጠር ኢትዮጵያውያዊ አሁንም መነሳት አለበት።ሰሜን ወሎ ዋግህምራ ዞን የሰቆጣ እና አበርጌላ ዙርያ በኢትዮጵያ ኃይሎች እጅ ገብቷል።አሁን 8 ጉዳዮች ትኩረት ይፈልጋሉ።
Friday, October 29, 2021
የፍትህ ሚኒስቴር በሰሜን እና ደቡብ ጎንደር እና በአፋር ክልል በህወሃት የሚመራው የትግራይ ወራሪ ቡድን በንጹሃን ላይ የፈጸመው ወንጀል ዛሬ ያቀረበው ሪፖርት
⮚ እናት እና ልጅን በአንድ ላይ ደፍረዋቸዋል፤
⮚ ከተፈጥሮ ተቃራኒ የወሲብ ጥቃቶች ፈጽመዋል፣
⮚ ልጆችን በእናቶቻቸው ፊት ደፍረዋል፤
⮚ አንዲትን ሴት ከደፈሩ በኋላ በጠመንጃ አፈሙዝ ብልቷን በመውጋት የፌስቱላ ተጠቂ እንድትሆን አድርገዋታል፤
⮚ የ8 ወር እመጫትን ጨቅላ ልጇን በፈላ ዉሃ ዉስጥ እንጨምራለን በማለት እናትዋን አስፈራርተው ደፍረዋታል፤
⮚ አንዲት የሰባት ወር ነፍሰ ጡር ሴትን ለሶስት አስገድዶ ደፍረዋታል፤
..........................
አዲስ አበባ ጥቅምት 19/2014 ዓ.ም (አደባባይ ሚድያ)
..........................
የምርመራ ቡድኑ ቀድሞ በተሰጠው እቅድ እና ዝርዝር የአፈጻጸም መመሪያ መሰረት ያከናወነው ምርመራ ትኩረቱን ያደረገው ከሰኔ ወር 2013 ዓ.ም. ጀምሮ መንግስት የተናጠል ተኩስ አቁም ካወጀ በኋላ የህወሃት አሸባሪ ቡድን በአፋር እና በአማራ ክልል አዋሳኝ ቦታዎች ላይ መጠነ ሰፊ ወረራ በማካሄድ የአለም አቀፍ ሕግ ድንጋጌዎች እና የአለም አቀፍ የሰብዓዊነት ሕግጋትን በመጣስ በሰላማዊ ሕዝብ ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ሲፈጽም ከቆየባቸው አካባቢዎች መካከል በደቡብ ጎንደር ዞን የላይ ጋይንት ወረዳ፣ የንፋስ መውጪያ ከተማ አስተዳደር፣ የጉና በጌምድር ወረዳ፣ የፋርጣ ወረዳ፣ እስቴ ወረዳ /በከፊል/፣ ደብረታቦር ከተማ አስተዳደር /በከፊል/ ፤ በሰሜን ጎንደር ዞን ደግሞ በዳባት፤ደባርቅ እና ዛሪማ ንዑስ ወረዳዎች እንዲሁም በአፋር ክልል ጋሊኮማ ቀበሌ በሚገኝ የተፈናቃዮች መጠለያ ጣቢያ እና በፈንቲረሱ ዞን ሥር በሚገኙ እዋ፣ አውራ እና ጉሊና ወረዳዎች ላይ ባልታጠቁ እና ሰላማዊ ህዝብ ላይ የተፈጸሙ ወንጀሎችን ብቻ በመሆኑ ምርመራው በመንግስት በኩል ሕግ ለማስከበር ተሳታፊ የሆኑ ተዋጊ ወታደሮችን እና አጋዥ አካላት ለአብነትም ምርኮኞች ላይ የተፈጸሙ ወንጀሎችን አያካትትም፡፡
ወንጀሉ በአሸባሪው ድርጅት መሪነት ከሐምሌ 2013 ዓ.ም ጀምሮ አካባቢዎቹ በፌዴራል እና በክልል የጸጥታ አካላት ቁጥጥር ስር ተመልሰው እስከ ገቡበት ጊዜ ድረስ ባሉት ጊዜያት የተፈጸሙ ሲሆን ምርመራው ከተጀመረበት ከመስከረም 05 ቀን 2014 ዓ.ም. ጀምሮ እስከአሁን ድረስ የደረሰበትን የመጀመሪያ ደረጃ ግኝቶችን ለህዝብ ለማሳወቅ ስለሆነ በምርመራው ቀጣይነት የሚገኙ አዳዲስ ውጤቶች በቀጣይ በሚቀርቡ ሪፖርቶች የሚገለጽ ይሆናል፡፡
በዚህ መሰረት በደቡብ ጎንደር ዞን የተሰማራው የምርመራ ቡድን በጠቅላላው ከ790 በላይ ምስክሮችን የምስክርነት ቃል ፣ በሰሜን ጎንደር ዞን የተሰማራው የምርመራ ቡድን ደግሞ 285 የምስክሮች ቃል እንዲሁም በአፋር ክልል የተሰማራው ቡድን 148 ምስክሮች ቃል ተቀብሏል፡፡ ሶስቱም ቡድኖች ከተጠቀሰው የተጎጂዎችና ቀጥታ ምስክሮች የምስክርነት ቃል በተጨማሪ ከምስክርነት ቃል ውጭ ወንጀሎቹን ሊያስረዱ የሚችሉ የሰነድ ማስረጃዎችን፣ ገላጭ ማስረጃዎችን ፣ኤግዚቢቶችን እንዲሁም የቴክኒክ ማስረጃዎችን ለማሰባሰብ ችለዋል፡፡
በውጤት ደረጃም አሸባሪው ቡድን በሰሜን ጎንደር ዞን ለጊዜው በዝርዝር ማስረጃ የተለዩ የ96 ሰዎች ሞት፣ 53 የአካል ጉዳት፣ 29 አስገድዶ መደፈር፣ 11 ኢ-ሰብዓዊ አያያዝ፣ 6 እገታ እንዲሁም የመንግስት፣ የግል እና የሀይማኖት የተለያዩ ተቋማት ንብረቶች ላይ መጠነ ሰፊ ዘረፋና ውደመት መፈጸሙ ተረጋግጧል፡፡ በደቡብ ጎንደር ዞን ባሉ አምስት ወረዳዎች ደግሞ በድምሩ የ129 ሰዎች ሞት፣ የ54 ሰዎች የአካል ጉዳት፣ በንፋስ መውጫ ከተማ ብቻ የ73 ሴቶች የአስገድዶ መድፈር ወንጀል እንዲሁም በርካታ ግለሰቦች ንብረት ላይ ውድመት ደርሷል፡፡ በሌላ በኩል በአፋር ክልል ነሃሴ 29 ቀን 2013 ዓ.ም. በጋሊኮማ ቀበሌ መጠለያ ጣቢያ ላይ በተፈጸመ ጥቃት የ240 ሰዎች ሞት፣ 42 ሰዎች የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን በቀሪዎቹ ሶስት ወረዳዎች ደግሞ የ17 ሰዎች ሞት እና ለ17 ሰዎች የአካል ጉዳት እንዲሁም 7 ሴቶች የአስገድዶ መድፈር ወንጀሎች እንደተፈጸመባቸው ተረጋግጧል፡፡
በሁለቱም ክልሎች ከሰላማዊ ዜጎች ንብረት በተጨማሪ በመንግስት እና በግል ተቋማት ላይ ማለትም ት/ቤቶች፣ ጤና ኬላዎች፣ የህብረት ስራ ማህበራት እንዲሁም በአብያተ ክርስቲያናት፣ በመስጊዶች እና መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች ላይ የዘረፋ እና ውድመት ድርጊቶች በስፋት መፈጸማቸው ተረጋግጧል፡፡
ድርጊቱ ሲፈጸምም የግለሰብ ቤቶችን እንደ ምሽግ መጠቀም፣ ታሪካዊ እና ሀይማኖታዊ ቦታዎችን እንዲሁም እንደ ዩኤስኤይድ፣ አክሸን ኤይድ እና በመንገድ ስራ ላይ የተሰማራ የቻይና መንገድ ተቋራጭ ድርጅትን ንብረቶችን ኢላማ ያደረገ ጭምር ነበር፡፡ እነዚህን ንብረቶች ለመዝረፍም የባለሙያ እገዛ የሚያስፈልጋቸውን በመለየት በተጠና እና ጥንቃቄ በተሞላበት መልኩ በሜካኒክ ፈትቶ እስከመውሰድ የደረሰ የዘረፋ ድርጊቶች ተስተውለዋል፡፡
ወንጀል አድራጊዎቹ ተቆጣጥረውት በነበርዋቸው ቦታዎች ድርጊቱን ሲፈጽሙ ከተናገሩት፣ ቤቶች ላይ በቀለም በተጻፉ ጽሁፎቻቸው እንዲሁም በወቅቱ የወንጀል ድርጊቱን ሲፈጽሙ ሲናገሩ ከነበሩት በመነሳት ለማረጋገጥ እንደሚቻለው አሸባሪው ድርጅት ይህንን መጠነ ሰፊ ጥቃት የፈጸመበት ዋንኛ አላማ ብሄር ተኮር ከሆነ ጥላቻ የመነጨ እና በአሸባሪው ድርጅት የበላይ አመራሮች ውሳኔ እና ትእዛዝ በብሄር የተመሰረተ የበቀል እርምጃ ለመውሰድ፣ የተወሰነ ብሄርን እንደማህበረሰብ በኢኮኖሚ እና በሞራል የተጎዳ እንዲሆን ለማድረግ ከድርጊት በተጨማሪ ጸያፍ የሆኑ ስድቦችን በመጠቀም እና በመፈረጅ፣ የፌደራል መንግስት ተረጋግቶ ሀገር እንዳይመራ ለማድረግ፣ ህወሃት ከሌለ ሀገር አትመራም በማለት የተዳከመ የፌደራል መንግስት እንዲኖር ለማድረግ፤ ማህበረሰብ ባህሉ እሴቱ እና መሰረታዊ ስሪቱ እንዲጠፋ የማድረግ አላማ አድርጎ የተነሳ መሆኑን በምርመራው ሂደት የታዩ እውነታዎች ያስረዳሉ፡፡
በአጠቃላይ ከላይ በተገለጸው አግባብ አሸባሪው ቡድን ወንጀሉን ለመፈጸም ከተነሳበት ምክንያት እና ከምርመራው ግኝት ለማሳያነት የሚቀርቡ ዋና ዋና አሰቃቂ ኢሰብአዊ ድርጊቶች እንደሚከተለው ቀርበዋል፡-
የአስገድዶ መድፈር ወንጀልን በተመለከተ፤-
⮚ አንድን ሴት እስከ አስራ አምስት በመሆን እየተፈራረቁ መድፈር፤
⮚ እናት እና ልጅን በአንድ ላይ መድፈር፤
⮚ ከተፈጥሮ ተቃራኒ የወሲብ ጥቃቶችን መፈፀም፣
⮚ ልጆችን በእናቶቻቸው ፊት መድፈር፤
⮚ አንዲትን ሴት ከደፈሩ በኋላ በጠመንጃ አፈሙዝ ብልቷን በመውጋት የፌስቱላ ተጠቂ እንድትሆን ማድረግ፤
⮚ የ8 ወር እመጫትን ጨቅላ ልጇን በፈላ ዉሃ ዉስጥ እንጨምራለን በማለት እናትዋን በማስፈራራት መድፈር፤
⮚ አንዲት የሰባት ወር ነፍሰ ጡር ሴትን ለሶስት አስገድዶ መድፈር፤
⮚ የመደፈር ወንጀል የደረሰባቸው ሴቶች ለአባላዘር እና ለአእምሮ ጤና መታወክ በሽታዎች ተጋላጭ ማድረግ፤
⮚ የተለየ የስነ ልቦና ጫና ለማድረስ በሚል የማህበረሰቡ ሀይማኖታዊ እና ባህላዊ እሴቶች የሆኑትን የካህናት ሚስቶችን እና ቆራቢ መነኮሳትን ለይቶ አስገድዶ መድፈር፤
⮚ በአፋር ክልል ሴቶችን ለረዥም ጊዜ አግቶ በማቆየት የአስገድዶ መድፈር ወንጀል በተደጋጋሚ በመፈጸም እና የህክምና እርዳታም ሳያገኙ አቆይተው መልቀቀ ናቸው።
የተለየ ጨካኝነትን እና ነውረኝነትን የሚያሳዩ የግድያ እና ተያያዥ ወንጀል ድርጊቶች
⮚ ከ30 ቀን ጨቅላ ህጻን እስከ 70 ዓመት ሽማግሌ ድረስ ተጠቂ የሆኑባቸው ግድያዎች መፈጸማቸው፤
⮚ የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ 6 ሰዎችን በጅምላ መግደል፤
⮚ በአብያተ ክርስቲያናት እና በመስጊዶች ውስጥ የነበሩ የሃይማኖት አገልጋዮችን መግደል፤
⮚ በዳባት ወረዳ ጭና ቀበሌ ሟች ጥላሁን ንጉሴ የተባሉ የ68 ዓመት አዛውንትን ጭንቅላቱን በጥይት በመምታት ገድለው ለአምስት ቀናት በቤት ውስጥ ሳይቀበር ሚስቱን ከአስክሬኑ ጋር በዚያው ቤት በማቆየት ለገዳዮች ምግብ እንድታዘጋጅ ማስገደድ፤
⮚ ደባርቅ ወረዳ አብርሃም ቀበሌ ሟች ዘለቀ አስመራ የተባለ አባትን ከህጻን ልጁ ፊት አንገቱን በማረድ ሶስት ልጆቹ እግሩን እና እጁን እዲይዙ በማድረግ ከአንገቱ እስከ ሆዱ በልጆቹ ፊት በሳንጃ አካሉን መሰንጠቅ፤
⮚ የማህበረሰቡ መኖሪያ ቤቶችን የሞቱ የሽብር ቡድኑ አባላትን ለመቅበሪያነት እና ለመጸዳጃ ቤት ለምግብ ማብሰያነት መጠቀም፣ እንዲሁም ቤቶችን በማፍረስ ፤
⮚ ሰዎችን በማገት አሰቃቂ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን መፈጸም [በዚህም ብዙ ሰዎች እስከ አሁን የደረሱበት አልታወቀም]፤
⮚ በአፋር ክልል የስድስት ወር ህጻን የእናቱን ጡት እንደያዘ በከባድ መሳሪያ ከእነ እናቱ ተመትቶ ተገድሏል፡
⮚ በአፋር ክልል ሙሉ የስደተኛ ጣቢያ ላይ የተጠለሉ ስደተኞች በተኙበት ከሌሊቱ 9 ሰዓት ላይ የጅምላ ከባድ ተኩስ በመክፈት በተኙበት እንዲያልቁ አድርገዋል፤
በንብረት ላይ የተፈጸሙ ወንጀሎች
⮚ በመንግስት የጤና ተቋማትን መዝረፍ እና ሙሉ በሙሉ በማውድም ከአካባቢው ማህበረሰብ ባለፈ በወንጀሉ የአስገድዶ መድፈር እና የአካል ጉዳት የደረሰባቸውን ተጎጂዎች የህክምና አገልግሎት እንዳያገኙ ማድረግ፤
⮚ ማህበራዊ አገልገሎት የሚሰጡ ባንኮችን፣የቴሌኮም መሰረተ ልማቶች ላይ፣ የመብራት ኃይል አውታሮች ላይ ዘረፋ እና ጉዳት ማድረስ፤
⮚ አሸባሪው ቡድን በወረራቸው አካባቢዎች የግለሰብ ንብረት የሆኑ እንስሶችን በጥይት መግደል በተለይም ለእርሻ አገልግሎት የሚውሉ በሬዎችን እና የጋማ ከብቶችን፣ ለወተት የሚውሉ ላሞችን መግደል እና በራሳቸውም ለሽያጭ እና ለምግብነት የሚውሉ ዶሮዎችን መዝረፍ እና መግደል በአጠቃላይ ማህበረሰቡን ማደህየትን ዓላማ አድርጎ የተፈጸመ ሲሆን፤ ከዚህ ጋር በተያያዘም ከማህበረሰቡ እሴት እና ሞራል ፍጹም ተቃራኒ በሆነ መንገድ እርጉዝ ላምን ገድሎ ሽሏን በማውጣት ጠብሶ መብላት፤ ያልደረሱ እና ያልበሰሉ አትክልት እና ጥራጥሬን መመገብ፤ በተቆጣጠሩባቸዉ አካባቢዎች የቤት እንስሳትን እና ከብቶችን መግደል፣ በአጠቃላይ የገበሬው ህልውና መሰረት በሆኑት ነገሮች ላይ ፋት በመፈጸም፤
⮚ የገበሬውን አዝመራ አጭዶ መውሰድ አልያም የአትክልት ምርቶችን መንቀል እንዲሁም ለመሰብሰብ ያልደረሰውን ሰብል ማቃጠል እና ምርት እንዳይሰበሰብ በተሸከርካሪ እና በከባድ መሳሪያዎች መዳመጥ፤
⮚ ከጦርነት ቦታዎች በብዙ ኪሎሜትሮች በሚርቁ አካባቢዎች ላይ የከባድ መሳሪያ /የመድፍ/ ጥቃት መፈጸም፤
አለም አቀፍ የተራድኦ ድርጅቶችን በተመለከተ
⮚ ለሰብዓዊ እርዳታ የሚውሉ መኪኖችን እና ምግቦችን ለጦርነት አላማ ማዋል፤
⮚ ንብረቶቻቸውን መዝረፍ፤ ለአብነት ያህል በደቡብ ጎንደር ዞን ጋይንት ወረዳ ንብረትነቱ ዩኤስኤድ/ ኤፍ ኤች ኢትዮጵያ/ የዋጋ ግምቱ 19 539 918.68 ብር የሚያወጡ ለድንገተኛ አደጋ ተጎጂዎች የሚውል 482.9569 ሜትሪክ ቶን የምግብ እህል፣ የመጋዘን እቃዎች ሞተር ሳይክ፣ መኪኖች እና ሌሎች ንብረቶች ተዘርዋል፤
የእምነት ተቋማትና አምልኮ ስፍራዎችን በተመለከተ
አብያተ ክርስቲያናትና መስጊዶችን ለወታደራዊ ዓላማ ከመጠቀም በተጨማሪ ማቃጠልና ማውደም ለአብነትም በደቡብ ጎንደር ዞን ውስጥ የሚገኙ 22 አብያተ ክርስቲያናትና 1 መስጊድ በከባድ መሳሪያ በመምታት ማውደም፤ ንብረቶቹንም መዝረፍ
ከሀይማኖታዊ እሴት ያፈነገጠና ነውነኝነትን በሚያሳይ ሁኔታ ለቁርባን የተዘጋጀን እህል በመዝረፍና በመጠቀም ሀይማኖታዊ ተግባርን የማራከስ ድርጊት መፈፀም
በአጠቃላይ ምርመራው በሂደት ላይ ያለ ከመሆኑ አንጻር እስከ አሁን በተደረሰበት ብቻ በሽብር ድርጅቱ እና በአባላቱ በሁለቱም ክልሎች በተፈጸሙት የወንጀል ድርጊቶች 482 ሞት፣ 165 የአካል ጉዳት እና 109 የአስገድዶ መድፈር ኢሰብዓዊ ድርጊቶች የተፈጸሙ ሲሆን ንብረትን በተመለከተ በመቶ ሚሊዮኖች የሚገመት ንብረት ውድመት እና እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ላለው ሰላማዊ ዜጋ ከቤት ንብረቱ መፈናቀል ምክንያት ሆኗል፡፡ ለአብነትም በአፋር ክልል 112,158 ዜጎች ፣ በሰሜን ጎንደር 135,310 ዜጎች እንዲሁም በደቡብ ጎንደር ከ 47000 በላይ ዜጎች ተፈናቅለዋል፡፡
በሌላ በኩል ምርመራው ያልተጠናቀቀ እንደመሆኑ በቀጣይ በተጠቀሱት ቦታዎች የተሰማራው የምርመራ ቡድን የጀመረውን ስራ በማጠናቀቅ ወንጀል ፈፃሚዎችን ለሕግ ለማቅረብ እንዲቻል ስራዎችን አጠናክረን የምንቀጥል ሲሆን ምርመራው ወዳልደረሰባቸው ቦታዎች ጭምር ሌሎች ቡድኖችን በማዋቀር ሰፊ የምርመራ ስራ ማካሄድ እና በየደረጃው ለህዝብ ማሳወቅ የሚሰራበት መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡
የአሸባሪው ቡድን በአማራና አፋር ክልሎች የፈጸመው ወንጀል ሪፖርት
ሰበር ዜና - ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አሕመድ በመሩት የሁሉም ክልሎች ፕሬዝዳንቶች እና የፀጥታ ኃይሎች በተሳተፉበት ዛሬ በባሕርዳር ተሰብስበው በሽብርተኛው ህወሓት ላይ ውሳኔ አሳልፏል።በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጥሪ አስተላልፏል።የመልዕክቱን ሙሉ ቃል ቪድዮ ይመልከቱ።
Wednesday, October 27, 2021
የኢትዮጵያ ሕዝብ ጦርነት የጀመረው አሁን ነው። በህወሓት የሚመራው የትግራይ ወራሪ ቡድን ጀሌውም ሆነ የመሃል ሀገር ደጋፊው ከሞያሌ እስከ መቀሌ ይነቀላል።
- ከፅሁፉ ስር የህወሓት እና የሸኔ ምስጢራዊ የስልክ ንግግር የያዘ ዶክመንተሪ ፊልም ያገኛሉ።
Tuesday, October 26, 2021
ጆሮ ያለው ይስማ! ሽብርተኛው፣ ከህወሓት ቡድንነት ወደ የትግራይ ወራሪነት መቀየሩን የኢትዮጵያ ሕዝብ አሁን አምኗል።በመሃል ሀገርም ሆነ በውጪ የሚኖረው የትግራይ ማኅበረስብ ይህንን ወራሪ ከመቃወም መዘግየቱ ዋጋ የሚያስከፍለው ሰዓት የደረሰ ይመስላል።
Monday, October 25, 2021
Full speech of Ethiopian PM Abiy Ahmed (PhD) at Sudanese transitional government peace agreement in 2019 (video)
Tuesday, October 19, 2021
መንግስት የሰብዓዊ ቀውሱን ለማስቆም እና ሀገርን ለማዳን ወሳኝ ወደ ሆነው ወደየማይፈለገው ነገር ግን አማራጭ ወደ የሌለው እርምጃ የግድ መግባት ሊኖርበት ይችላል።
Monday, October 18, 2021
ኢትዮጵያን ሊያፈርሷት እያደሟት ነው።አሁን ታሪክ የመስርያ ጊዜ ነው።በውጭም በውስጥም ያለው ሕዝብ እና መንግስት ትኩረት ሊሰጧቸው የሚገቡ ሰባቱ ቁልፍ ተግባራት።
In the last Five days, terrorist TPLF killed Hundreds and looted thousands of civilians in Amhara Region in Ethiopia.International Humanitarian Organizations and Media are quite.
=============
Gudayachn
=============
It is becoming more clear that the International Media loyal to the west is quiet, when Terrorist TPLF killed innocent civilians in Amhara and Afar Regions in Ethiopia. On the other hand, during the Ethiopian National Defence Force law enforcement process, almost all channels of the International media talk about Human Right issues and start to criticize the Ethiopian Government.
Starting from the end of June 2021, terrorist TPLF killed, raped and looted thousands of Amhara and Afar civilians. These savage acts of TPLF are recorded and witnessed by the local people and even with aid workers. For the last Five days, terrorist TPLF randomly killed civilians for only being from the Amhara ethnic. The total death toll is increasing.However reports from Maychew, Weldia and North Wello administrative regions say the TPLF massacre on Amhara ethnics is on innocent civilians who do not have any involvement on the ongoing law enforcement.
One sided, the so-called International Humanitarian Organizations and International media are very selective in their reports regarding Ethiopia’s current case. Even though, since the end of June 2021, there have been multiple accusations of atrocities, killing and looting innocent civilians in Amhara and Afar Regions in Ethiopia, most of them were ignored by the Humanitarian and International media which seems intentional.
More recently in the last Five days, the terrorist TPLF militias bombarded civilian residents in Wuchale city and killed a number of civilians that the local people are not yet finished counting the dead body.At the result of terrorist TPLF atrocities,only in the last three months, Tens of thousands of people have fled out from North Wello and increased Internal Displaced People (IDP) by another Ten thousands in addition to the previous one.
In General, Ethiopians and Africans as a whole are watching carefully the way how the west under the title of International Community is sided with the terrorist TPLF with its atrocities. There is no question and any doubt that Ethiopia will overcome the current internal and external influences. However,when times comes those who stand on the side of the terrorist TPLF will be ashamed with their own ignorance to the death of Ethiopian civilian people.
Saturday, October 16, 2021
ሰበር ዜና - ህወሓት በሰሜን ወሎ የመጨረሻ ውግያ ብሎ የላከው ጀሌ ክፉኛ ተመቷል።የመጨረሻ ውግያ የሚሉ ቃላት ሰሞኑን መጠቀም የፈለገባቸው ሦስት ምክንያቶች ታውቀዋል።
================
ጉዳያችን/Gudayachn
===============
ህወሓት የመጨረሻ ውግያ የሚሉ ቃላት ሰሞኑን መጠቀም የፈለገባቸው ሦስት ምክንያቶች
Friday, October 15, 2021
የምዕራቡ ዓለም በተለይ አሜሪካ ለዩጎዝላቭያ መፍረስ ምን አድርጋ እንደነበር የሚያሳይ ጥናታዊ ፊልም ከህወሓት ደጋፊ እስከ የፅንፍ የኦሮሞ ብሔርተኝነት አራማጆች፣ከአማራ አክራሪ ብሔርተኝነት እስከ ኢትዮጵያዊነት ይቅደም የምንል ሁሉ በትዕግስት እንመልከተው።
- ኢትዮጵያ ውስጣዊ የፖለቲካ ግጭቶቿ ታሪካዊ ዳራ እና ስነልቦናው ከዩጎዝላቭያ ጋር አይመሳሰልም።ይህ ማለት ግን ለኢትዮጵያ ካልሰራን አደጋ የለብንም ማለት አይደለም::
- ዩጎዝላቭያ የነበረው ሕዝብ የመከፋፈል አካሄድ፣ የአሜሪካ እና የምዕራቡ የጣልቃ ገብነት መጠን እና ደረጃዎች በትክክል አሁን እያደረጉት ካለው ጋር ይመሳሰላል።
- በኢትዮጵያ በብ/ጄ አሳምነው ዙርያ የተነሳው የባህርዳሩ አስዛኝ የአመራሮች ሞት፣የአርቲስት ሃጫሉ መገደል፣በሰሜን ዕዝ ላይ በህወሓት የተወሰደው ማጥቃት ሦስቱ ኢትዮጵያውያንን እርስ በርስ አጋጭቶ ለማፍረስ የመጡ መቅሰፍቶች ነበሩ።እነርሱን አልፈናል።ለቀጣይ ተመሳሳይ አደጋዎች ቢፈጠሩ ወደ ብሔር ስሜት እንዳይሄድ እያንዳንዱ ምሁር፣ጋዜጠኛ፣የማኅበራዊ ሚድያ ተጠቃሚ ሳይቀር ኃላፊነቱ ምን ያህል ከባድ እንደሆነ ያሳያል።
- የትም ሆንክ የትም፣ህወሓትን ደገፍክ፣ኦነግ፣ኢትዮጵያዊነትን አስቀደምክ አላስቀደምቅ በምትሰራው ሥራ ሕዝብ የሚከፋፍል እና ኢትዮጵያን ለባዕዳን ከሚያስማማ ድርጅት እንደ ህወሓት እና ኦነግ ሸኔ ጋር ከቆምክ ሕዝብህን፣እራስህን እና ልጆችን ወደባርነት እየመራህ መሆኑን እወቀው።
Tuesday, October 12, 2021
The US Government must respect the parliamentary decision of the land with over 3000 years of statehood history,Ethiopian Parliament decision.
==============
Gudayachn Alert
=============
Ethiopia and United State diplomatic relations started in 1903. It has over a century of diplomatic relations which is unique among African countries. Because following the Berlin conference, which is also known as the scramble of Africa signed in 1885, all African countries except Ethiopia were under colony. However, this Shiny and historical diplomatic relation is about to be spoiled due to the failed Foreign Policy of the current Biden administration.
After the end of the cold war, at the end of the 1980s, the Tigray Liberation Front (TPLF) got a chance to control the Political power of Ethiopia. It continues to rule the whole Ethiopia for almost 30 years. During that period, ten of thousands of Ethiopians were sent to prison and other thousands were killed without any justice. The resource of the country was controlled by the minority elites of ethnic Tigran loyal to the TPLF. Even though the majority of Ethiopians got down and poorer, the few elites from ethnic Tigray region got richer.
However, thanks to the 2018 popular movement against the TPLF ethnocentric rule, Ethiopians could control the political power and started the new reform. The reform has continued and on the last June,2021, the first and more accepted National election took place and the Prosperity party led by the 2019 Nobel Peace Prize winner, Abiy Ahmed (PhD) win the majority seats in the parlament.
In all the past 30 years, when Ethiopians suffered under the brutal rule of TPLF, the United States Government was the main supporter for the regime in all logistic, financial and even media coverage. When the reform started in 2018, Ethiopians were in a forgiving mood to any foreign power assisting the TPLF regime, as was expected the same support could be provided for the newly emerged Ethiopian Government. However, the current Biden administration failed Foreign Policy stands against both Ethiopia and the United States National interest.
Ethiopians at home and around the world are not feeling comfort with the Biden administration's Foreign Policy towards Ethiopia. The core reason for this discomfort is that the United States Government's disrespect the Ethiopian Parliament decision on categorizing TPLF as the terrorist group.
The Biden administration's attempt to dictate the Ethiopian highest legislative body, just by disregarding the sovereignty of Ethiopia, may cost a lot for the Ethio -US diplomatic relationship. The United States Government is clearly showing its support for the terrorist group TPLF. This was reflected in different ways including -
The United States did not officially condemn the TPLF attacks on Ethiopian National Defence Force on November 2,2020.
The Biden administration did not appreciate properly for the Ethiopian Government's unilateral action of ceasefire.
The Biden administration attempted to interfere with a very internal issue of Ethiopia including where to be assigned the regional army like the Amhara Region's local army.
The Biden administration did not condemn properly the TPLF genocide on Amhara and Afar regions in Ethiopia.
After all these terrorist acts of the TPLF and Ethiopian Parliament decision on categorizing TPLF as the terrorist organization, Secretary Antoni Blinken tweeted today, October 13,2021, as he met with African Union High Representative Obasanjo, IGAD Chair, Sudan's PM Hamdok and the Ethiopian core Group of the European Union, France and Germany. In this particular tweet, the objective of all these talks was to bring TPLF as a legal body and empower it to negotiate with the legally elected Ethiopian Government.
In General, it is quite clear that the US Government is violating the sovereignty of the Ethiopian Government. Ethiopia was a member of the League of Nations and the founder of the United Nations. All nations have equal rights and their relationship is based on mutual benefits. Therefore, since Ethiopia is not interfering in the internal issue of the US domestic politics, the US Government must also respect the 3000 years history of the statehood country's parliament. That is the Ethiopian Parliament's decision on TPLF.
Monday, October 11, 2021
እንደሚገረፍ ያወቀ ልጅ አባቱ ገና ቀበቶውን ሲነካካ እሪ! ይላል።
Friday, October 8, 2021
Breaking News - CNN can face charges and stand in front of International court for its fake news on Star Alliance member, Ethiopian Airlines.
Gudayachn / ጉዳያችን
- CNN fake News may cost over 100 thousand Americans.
- The recent CNN allegation against Ethiopian Airlines has seriously annoyed many Africans.
Cable News Network (CNN) fake news on the Star Alliance member airline, Ethiopian Airlines may result in a court charge from Ethiopian Airlines. The news released by CNN says ''Ethiopian Airlines used to transport arms for the military''. Ethiopian Airlines press release responding to CNN says '' Ethiopian Airlines strongly refutes the recent allegation by CNN''.
Ethiopian Airlines is a leading airline in Africa and member of the Star Alliance. Star Alliance is a global airline network which was established by five airlines, Air Canada, Lufthansa, Scandinavian Airlines, THAI and United on May 14, 1997. It has grown to 27 member airlines to become the first truly global airline alliance to offer worldwide service. Among these 27 member airlines Ethiopian is one of them.
Ethiopian Airlines was founded on December 30,1945, by Emperor Haile Selassie. The Airline provides basic pilot and aviation maintenance training to trainees from African countries including Rwanda, Tanzania, Chad, Djibouti, Madagascar, Sudan. And its training service is also extended to Europe and the Middle East countries. The number of countries using its pilot and aviation maintenance training is increasing from time to time. In the near future, Ethiopian Airline will upgrade its training center to Aviation University.
Currently, Ethiopian Airlines is one of the huge global companies which provides job opportunities for over 100 thousand Americans. The Airline purchasing power from American and other parts of the world is over a billion dollars. All these purchases give an opportunity to thousands of workers globally, particularly in the USA over 100 thousand Americans are benefited. Therefore, it is clear that the recent CNN's fake news may affect 100 thousands Americans also.
The recent CNN allegation against Ethiopian Airlines has seriously annoyed many Africans. A Ugandan living in Norway said to Gudayachn that this is not less than opening a clear war against African icon, Ethiopian Airlines. Now the 'talk of the town' in Addis and other African cities is the importance of Ethiopian Airlines needing to open charges against CNN for its fake news. The latest press release from Ethiopian Airlines seems ''a yellow sign'' to CNN to give the last chance to ask for an official apology. If not, Ethiopian may be obliged to open charges against CNN. Many are saying this can be a good lesson to CNN to respect both international Media ethics and business law.
================///==================
Wednesday, October 6, 2021
ክቡር ጠ/ ሚ/ር ዓቢይ አሕመድ አዲሱን ካቢኔ አስተዋወቁ።3 ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ተካተዋል። የመከላከያ ሚኒስትር ከትግራይ ተሹመዋል።የተሿሚዎች ስም ዝርዝር ሊንኩን ከፍተው ያገኛሉ። PM Abiy Ahmed introduced the new cabinet members.He included 3 opposition political party leaders. Defence Minister is appointed from Tigray.(See the list of the new appointed ministers).
2 አብርሃም በላይ (ዶ/ር) - የመከላከያ ሚንስትር
3.አህመድ ሽዴ - የገንዘብ ሚኒስትር
4.ሙፈሪሃት ካሚል- የከተማ ልማት ሚኒስትር
5.ኡመር ሁሴን ኦባ -
የግብርና ሚኒስትር
6.ኢንጂነር አይሻ መሐመድ - የመስኖ እና ቆላማ ልማት ሚኒስትር
7.ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ ገለታ- የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር
8.ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ- የትምህርት ሚኒስትር
9.ዳገማዊት ሞገስ - የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር
10.ገብረመስቀል ጫላ - የንግድና የክልል ውህደት ሚኒስትር
11.አቶ መላኩ አለበል - ኢንዱስትሪ ሚኒስትር
12.ብናልፍ አንዱዓለም - የሰላም ሚኒስትር
13.ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ፒኤችዲ) - የፍትህ ሚኒስትር
14.ዶ / ር ሊያ ታደሰ - የጤና ጥበቃ ሚኒስትር
15.በለጠ ሞላ - ፈጠራ እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር
16.አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ - የቱሪዝም ሚኒስትር
17.አያሌው ሐይቅ - የገቢዎች ሚኒስትር
18.ጫልቱ ሳኒ ኢብራሂም - የከተማ እና የመሠረተ ልማት ሚኒስትር
19.ኢንጂነር ታከለ ኡማ በንቲ - የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስትር በመሆን
20.ከጀላ መርዳሳ ቱሉ - የባህል እና ስፖርት ሚኒስትር
21.እርጎጌ ተስፋዬ (ዶ / ር) - የሴቶችና የማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር
22.ፍፁም አሰፋ (ዶ / ር) - የዕቅድና ልማት ሚኒስትር
Facts from today's new cabinet ministers proposed by the PM Abiy Ahmed and ratified by Ethiopian Parliament
Three big opposition party leaders are included1.Demeke Mekonnen Hassen – Deputy
Prime Minister and foreign affairs minister
2.
3.Ahmed Shide – Finance Minister
4.Muferihat Kamil- Urban
Development Minister
5.Oumer Hussen Oba – Minister of Agriculture
6.Engineer Aisha Mohammed –
Irrigation and Lowland Development Minister
7.Engineer Habtamu Itefa Geleta- Water and Energy Minister
8.Professor Birhanu Nega- Education Minister
9.Dagemawit Moges – Transport and
Logistics Minister
10.Gebremeskel Chala – Trade and
Regional Integration Minister
11.Melaku Alebel – Industry
Minister
12.Binalf Andualem – Peace
Minister
13.Gedion Timothewos (Ph.D.) –
Justice Minister
14.Dr. Lia Tadesse – Health
Minister
15.Belete Mola – Innovation and
Technology Minister
16.Ambassador Nasise Chali – Tourism Minister
17.Lake Ayalew – Revenue Minister
18.Chaltu Sani Ibrahim – Urban
and Infrastructure Minister
19.Engineer Takelle Uma Benti –
Mines and Petroleum Minister
20.Kejela Merdasa Tulu – Culture
and Sports Minister
21.Ergoge Tesfaye (Ph.D.) – Women
and Social Affairs Minister
22.Fitsum Asefa (Ph.D.) – Plan
and Development Minister
===================/////===============
Beynouna Village - Ethiopia (Video) ባለፈው ሳምንት የተመረቀው መተሃራ እምብርት ላይ የተገነባው አስደናቄው የበይኑና ሪዞርት መንደር (ቪድዮ)
Beynouna Village - Ethiopia (Video) ባለፈው ሳምንት የተመረቀው መተሐራ እምብርት ላይ የተገነባው አስደናቄው የበይኑና ሪዞርት መንደር (ቪድዮ)
-
የቅዱስ ላልይበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ጉዳያችን/ Gudayachn ሰኔ 2/2011 ዓም (ሰኔ 8/2019 ዓም) ግንቦት 29/2011 ዓም ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል በለቀቀው ዜና እንዲህ ይነበባል: - ...
-
Foto source:- Royal Norwegian Embassy in Addis Ababa, Ethiopia http://www.norway.org.et/News_and_events/press_releases/New-Norwegia...
-
በ ካርታ ጫወጣ ጎበዝ አደለሁም። ግን ጆከር የተባለች ካርታ መኖሯን አውቃለሁ።ጆከር ካርታ በ ሁሉም ቦታ ስለምትገባ በ ካርታ ጫወታ ጆከር የደረሰው ሰው የማሸነፍ እድል ስላለው ፊቱ በ ፈገግታ ይሞላል። የ አትዮጵ...