ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Tuesday, August 30, 2016

በኢትዮጵያ ከገጠር እስከ ከተማ በከፍተኛ ደረጃ በድብቅ እየተደመጠ እና እየተሰራጨ ያለ ወኔ ቀስቃሽ ሙዚቃ

ጉዳያችን GUDAYACHN www.gudayachn.com

በኢትዮጵያ አሁን ያሉት አማራጮች (በቀጣይ የሚሆኑት) ሁለት ነገሮች ብቻ ናቸው።ምርጫው በእያንዳንዳችን ውጤት ይወሰናል። (የጉዳያችን ማስታወሻ)


ሀ/ ነባራዊ ሁኔታው 

1/ የኢትዮጵያ ሕዝብ ወያኔ በቃኝ ብሏል። 
2/ ወያኔ ለእውነተኛ የፖለቲካ መፍትሄ ዝግጁ አይደለም።
3/ ወያኔ ፋሽሽት መንግስት መሆኑን በሚያፈሰው የንፁሃን ደም አስመስክሯል።
4/ የወያኔ ደጋፊዎች  ወያኔ በሕዝቡ ላይ መዝመቱን ሲሰሙ ´´እሰይ ይበለው!´´ ሲሉ እየተሰሙ  ነው።በእዚህም የበለጠ የህዝብ ልብ አድምተዋል።እነኝህ ነባራዊ ሁኔታዎች ናቸው።
5/ አቶ ኃይለ ማርያም ድምፁን ያሰማው ሕዝብ እንዲገደል ፈርምያለሁ ብለው በይፋ ተናግረዋል።

ለ/ ሁለቱ ብቸኛ አማራጮች 

አማራጭ አንድ 

ወያኔ በሕዝቡ ላይ የጀመረውን ዘመቻ አጠናክሮ ቀጥሏል።ትናንት ነሐሴ 23/2008 ዓም ጀምሮ ተጨማሪ ከባድ መሣርያዎች እየገቡ ነው።ስለሆነም ወያኔ ይህንን አመፅ ከጨፈለቀ በሰልፍ ላይ የታዩትወጣት፣ሽማግሌ  ሁሉ የሱዳን እና የአረብ አገር ስደተኛ ይሆናሉ።በበረሃ ያልቃሉ።የቀሩት እስር ቤት ገብተው ይማቅቃሉ።የአንድ ጎጥ ፖለቲካ በባሰ ፋሽሽታዊ መልኩ ይቀጥላል።ትግሉ ግን አይቆምም።የጎጥ በደል የደረሰበት ሕዝብ ደግሞ በማንኛውም መልኩ በደሉ የመንግስት ብቻ ሳይሆን የአንድ አካባቢ ሕዝብ መሆኑን አምኖ ባገኘበት ቦታ ሁሉ ጥቃቱን ይፈፅማል።በእየቦታው በማናቸውም ጊዜ እና ሰዓት ለምሳሌ በስፖርት ውድድር፣ሆቴል፣ ሆስፒታል ሁሉ ሕዝብ አመፁን በመግደል ሊያሳይ ይችላል።

አማራጭ ሁለት  

አማራጭ ሁለት በስሩ ሶስት ክፍሎች ይዟል።ይሄውም ወያኔ በሕዝቡ ላይ የጀመረውን ወታደራዊ ዘመቻ ሲቀጥል የሚከተሉት ሶስት ሁኔታዎች ውስጥ አንዱ ሊከሰት  ይችላል። ወደድንም ጠላንም እነኝህ ሁኔታዎች በአጭር (በጥቂት ቀናት እስከ ጥቅምት)  ወይንም በመካከለኛ ጊዜ (እስከ የካቲት፣2009 ዓም ) ይፈጠራሉ ብሎ ማሰብ ይቻላላ።

እነርሱም -

1ኛ/ በጦር ሰራዊቱ ውስጥ ትግሪኛ ተናጋሪ ያልሆነው እራሱን ከእነ መሳርያው ይለያል።በአንዱ የአገራችን ክፍል ተቆርጦ ባለበት ይታኮሳል።አንዳንድ ቦታዎች ላይ የጎበዝ አለቃውን  ከበታች መኮንኖች መርጦ እረዘም ላለ ጊዜ ይዋጋል።ምናልባትም ሕዝብ እየተቀላቀለው የሚሄድ ያልታወቀ አለቃ ሊነሳ ይችላል። ይህ በአፍሪካ የተለመደ ነው።

2ኛ/ በሰሞኑ ሰልፍ የተሳተፈው ወጣት ተመልሶ እቤቱ ቢገባ ወያኔ እንደሚያደርገው እንደሚታፈስ ስለሚያውቅ ያለውን መሳርያ ይዞ ወደ ገጠሩ ክፍል ይገባል። ለእለት የሚሆነውን ከወያኔ ካምዮኞች ላይ እየዘረፈ አንዳንዴም ወደ ከተማ የተቀናበረ ዘመቻ እያደረገ ወያኔን መቆምያ መቀመጫ ያሳጣል። ይህ ሁኔታ በተደራጀ መልኩ ማለትም በፖለቲካ ኃይሎች አደረጃጀት ከታገዘ አጠቃላይ ለውጥ በኢትዮጵያ ያመጣል።የሰው ሕይወት እና የንብረት አደጋ ማጥፋቱ አይቀርም።በአዲስ አበባም በማናቸውም ሰዓት በህወሓት ባለስልጣናት ላይ ጥቃት ሊፈፅም ይችላል። 

3ኛ/ ሁኔታዎች ከእጃቸው መውጣቱን የተረዱት ወያኔዎች በግብፅ እንደተደረገው ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት (በጀነራል ፃድቃን ሃሳብ መሰረት) አንድ ቀን ማለዳ የተወሰኑ የህወሓት ባለስልጣናት መታሰራቸውን ይነግሩን እና የፖለቲካ ኃይሎች ለውይይት ይምጡ ሊሉ ይችላሉ።ይህ ለህወሓት ሁለት ጥቅም አለው።አንዱ  የዘረፉትን ንብረት እንደማይወሰድባቸው ዋስትና ከመጪው ወታደራቸው ያገኛሉ።ሁለተኛ በተዘዋዋሪ የተቃውሞውን ጎማ ሽክርክሪት ያበርዱበት እና ከአንድ እና ሁለት ዓመት በኃላ መልሰው የህወሓት አስተዳደርን ቀለም ቀብተው አግባብተው ይመልሱታል።

መፍትሄው 

ፀረ ወያኔ ትግሉ መቆም የለበትም።ከላይ የጠቀስኩት ሁሉ ከመምጣቱ በፊት የትግራይ ኤሊት ህወሓት የሚሄድበት መንገድ ትክክል አለመሆኑን በግልፅ  ተረድቶ የትግሉ አካል መሆን ብቸኛ አማራጩ ነው።ኤሊቱ ወደ እዚህ ትግል በግልፅ መግባቱ ለጊዜው የሚያሳጣው ነገር ያለ ይመስለዋል። ሆኖም ከተወሰነ ጊዜ በኃላ የሚያጣው የከፋ እና ለብዙ አመታት ቁስል ጥሎ የሚሄድ ነው እና አያዋጣም።ይህንን የትግራይ ኤሊት አያደርገውም ምቾት ቀጠና (comfort zone) ስለሆነ መንቀሳቀስ አይፈልግም የሚሉ ብዙዎች አሉ።ነገሩ አያሳምንም ማለት አይቻልም።

ከእዚህ በተለየ ግን የኢትዮጵያ ሕዝብ በሰላማዊ መንገድ ምርጫ ተሳተፈ ውጤቱ ድምፁ ተነጠቀ።ሰላማዊ ሰልፍ ፍቀዱልኝ አለ።ምላሹ ዱላ ሆነ።በኃይል ተነስቶ እጁን እያጣመረ  በቃኝ አለ።በምላሹ በጥይት ተገደለ።አሁን ደግሞ በታንክ እየዘመቱበት ነው።ስለሆነም ከእዚህ በኃላ የሽምቅ ውግያ በየትኛውም ቦታ ቢደረግ ተጠያቂው ህወሓት እና አይዞህ ባዮቹ ብቻ ናቸው።እንደ እኔ አስተያየት ከላይ ከጠቀስኩት ውጭ ታምር ይፈጠራል ብዬ አላስብም። እርግጥ ነው ከላይ የተፃፉት ስፃፉ እንጂ ሆነው ስናያቸው ታምር መሆናቸው አይቀርም።መሆናቸው ግን አይቀርም።


ጉዳያችን GUDAYACHN 

 www.gudayachn.com

Sunday, August 28, 2016

ህወሓት ምንም አዲስ መልዕክት የሌለው መግለጫ ዛሬ ሰጠ።ለመግለጫው አጭር መልስ የሚሆነው ´´ከዝንብ ማር አይጠበቅም´´ የሚል ነው EPRDF press release is the same as ´´square one´´ expression of its failed policy for the last 25 years


የአማርኛ ፅሁፍ ከስር ይመልከቱ።
EPRDF press release of August 28,2016 is the same as ´´square one´´ expression of its failed policy for the last 25 years. It is  full of empty words. There is no single word of ´´excuse´´ for over 1000 Ethiopians killed in last seven months by the regime. The press release is expected to invite more people to protest  TPLF. Because it did´t even reason out the real situation of the country plus the possible solutions suppose to be proposed by this particular press release. In addition to that the press release, at the last statement conclusion, warns peaceful protestors and appreciate the regime´s security personnels. Such a kind of approaches of TPLF is very common for Ethiopians in the last 25 years. In short it is possible to say that this is another confirmation as dictators will make fast their last days by following poor minded advisers. The same is happening in TPLF. For your easy information about the press release, please read the below Amharic version of Gudayachn´s view and full press release of TPLF video at the end of article.

የኢትዮጵያ ሕዝብ እያገባደድነው ባለው የ2008 ዓም ለነፃነት የሚያደርገውን ትግል በአዲስ መልክ ያቀጣጠለበት ዓመት ነው።በእዚህ ዓመት ብቻ እስካሁን ትክክለኛ ቁጥሩ ባይታወቅም በኦሮምያ እና አማራ ክልሎች ብቻ በሰላማዊ ሰልፍ መብታቸውን በመጠየቃቸው ብቻ ከ1000 በላይ ኢትዮጵያውያን በጥይት አረር ተገድለዋል። በአስር ሺዎች ወደ እስር ቤት ተግዘዋል።ሌሎች አስር ሺዎች ካሉበት ቀዬ ወደ ሌላ ቦታ ተሰደዋል።

ሕዝባዊ አመፁ እያየለ መጥቶ ይህ ፅሁፍ በምፃፍበት በእዚህ ቅፅበት በጎንደር እና ጎጃም ሕዝብ የህወሓት መዋቅር የሆኑ የአስተዳደር እርከኖችን አፍርሶ እራሱን በእራሱ ጊዝያዊ የአስተዳደር መዋቅር እየዘረጋ እና መሪውን እየመረጠ መሆኑ እየተዘገበ ነው።በእዚህ ሁኔታ እያለ ነው እንግዲህ የኢህአዴግ ማዕከላዊ ኮሚቴ ከስብሰባ በኃላ ደረሰበት የተባለውን ውሳኔ ዛሬ ነሐሴ 22፣2008 ዓም በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን የተነበበው።

መግለጫው በእራሱ የኢህአዴግ ነው ወይ? የሚለው መሰረታዊ ጥያቄ ነው።ምክንያቱም የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች ብአዴን እና ኦህዴድ ቀድሞም በህወሓት መዋቅር የመታዘዛቸው ጉዳይ እንዳለ ሆኖ በእዚህ ዓመት ይብሱን በሕዝባዊ አመፁ ሳብያ ሕልውናቸው ማክተሙን በግልፅ የታየበት ነው።ስለሆነም የኢህአዴግ ማዕከላዊ ኮሚቴ ሲባል ህወሓት እና ህወሓት ብቻውን ያሰበውን መግለጫ በሚል ስም እንዳወጣው መረዳት ተገቢ ነው።

በተሰጠው መግለጫ ላይ በመጀመርያ ክፍል ላይ ´´ውዳሴ ህወሓት´´ የተሞሉ ቃላት ብቻ ሲገኙበት።በሚልዮን የሚበሉት እና የሚጠጡት ባጡባት አገር ውስጥ ይልቁንም ረሃብ እንደ አዲስ አበባ ያሉ ታላላቅ ከተሞች ውስጥ ተማሪዎች የምግብ ድጋፍ ካልተደረገላቸው ትምህርታቸውን መቀጠል እንደማይችሉ እነዩኒሴፍ የመሳሰሉ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች በገለፁበት ሁኔታ ሁሉ የኢህአዴግ መግለጫ ኢትዮጵያ እንዳደገች ለመስበክ መሞከሩ አሁንም በአስራአንደኛው ሰዓት ላይ ቆመውም ህወሓቶች ለለውጥ ሳይሆን ለበለጠ ግድያ መነሳታቸውን አመላካች ነው።

የመግለጫው ዋና እና ቁልፍ ምክንያት የኢትዮጵያን ሕዝብ አዘናግቶ የበለጠ ጦር ሕዝባዊ አመፁ ወደተነሳባቸው ቦታዎች አዝምቶ ለመጨፍለቅ እና የምዕራባውያንን ውትወታ በሆነች ለውጥ በምትመስል መግለጫ ይሄው እየሰራን ነው ለማለት የታሰበ ነው።ለእዚህም ነው የህወሓት የማኅበራዊ ሚድያ አፈቀላጤዎች  መግለጫውን በተመለከተ በእንግሊዝኛ ለመፃፍ የሚደክሙት።ሌላው አስቂኝ የመግለጫው ሂደት አሁን ኢህአዴግ የሚያደርገው ለውጥ ከአስራ አምስት ዓመት በፊት የተጀመረው አካል ነው ሲል መደመጡ ነው።ይህ ´´ ሃያ አምስት ዓመት በጥይት ስገድሉን ኖረው አሁን ደግሞ በሳቅ ገደሉን ´´የምትለዋን አባባል ያስታውሳል። ስህተት ተሰርቷል ለውጥ ያስፈልጋል ብሎ በድፍረት የለውጥ አስፈላጊነትን አፍን ሞልቶ ለመናገርም ያፈረ ስርዓት ዛሬ በህዝባዊ አመፅ ለለውጥ ተገደድኩ ይሉኛል በሚል ጭንቀት ለውጡን ከአስራ አምስት ዓመት በፊት ባቀጣጠልነው መሰረት ነው ብሎ መግለጫ ማውጣት ለምንም አይነት እርምጃ አለመዘጋጀታቹን የበለጠ ግልፅ ያደርገዋል። 

ህወሓት በእዚህ መግለጫ ላይ ለችግሩ መነሻ ብሎ ያቀረባቸው ነጥቦች በእራሳቸው ደካማ እና መሰረታዊ የህወሓት የፖሊሲ ውድቀት እና ስልጣንን በብቸኝነት የመቀራመት አባዜ ያገለለ ነው።በዛሬው መግለጫ ህወሓት የአገራችን ችግር ብሎ ያቀረባቸው ችግሮች ያሉ ችግሮች ቢሆኑም ዋናው እና መሰረታዊው ችግር ከላይ እንደተጠቀሰው የህወሓት የፖሊሲ ውድቀት፣ጎጠኛ እና አድሏዊ ስርዓት መስፈን እና ስልጣንን በብቸኝነት የመቀራመት አባዜ የሚሉት ዋነኛ ናቸው።ለእነኝህ መፍትሄዎቹ ደግሞ በዋናነት ህወሓት ስልጣኑን በፍጥነት እንዲለቅ ማድረግ እና ሕዝባዊ እና የሽግግር መንግስት መመስረት ነው።ከእዚህ ያነሰ መፍትሄ ቁስል የበለጠ እንዲመረቅዝ እና ኢትዮጵያን ወደ ባሰ ማጥ ውስጥ የመክተት ግልፅ ፍላጎትን ብቻ ያመለክታል።ህወሓት በዛሬው መግለጫው ግን ችግሮች ብሎ ጉዳዩን በጥገናዊ ለውጥ ለማለፍ የሞከረበት መንገድ ችግሮቹን  የህዝብ መብዛት፣የሕዝብ ፍላጎት መጨመር፣ስልጣንን የሀብት ማከማቻ የማድረግ ሂደት በኢህአዴግ ውስጥ በመስረፁ ወዘተ ናቸው በሚሉ ቃላት ለማድበስበስ ሞክሯል።

ባጠቃላይ መግለጫውን በሶስት ክፍሎች ልንከፍለው እንችላለን።የመጀመርያው ክፍል ህወሓት እራሱን ያሞገሰበት እና ኢትዮጵያውያን ´´ምግብ በልታችሁ ያደራችሁት እኔ ስልጣን ከያዝኩ በኃላ ነው´´ ቀረሽ ሐተታ ሲሆን ሁለተኛው ችግሩን ከህወሓት የስልጣን ጥማት እና አገሪቱን በተሳሳተ የጎጥ ፖለቲካ  መከፋፈል የመጣ መሆኑን ሸሽጎ የችግሩን መነሻ በገሃድ ካሉ ግን ብቸኛ ችግሮች ካልሆኑት የስልጣን መባለግ፣የህዝብ ብዛት መብዛት እና የህዝብ አዳዲስ ፍላጎቶች በሚሉ ቃላት ሊያድበሰብስ የሞከረበት ነው።በመግለጫው የመጨረሻ ክፍል ላይ ደግሞ ሕዝባዊ አመፁን የጥፋት ኃይሎች መሆኑን ሊሰብክ ይሞክርና ከጎኑ ቆመው ሕዝብ የገደሉትን ሲያሞግስ እና አይዟችሁ በርቱ ሲል ታገኙታላችሁ። መግለጫው ባጭሩ ይሄው ነው።ለመግለጫው አጭር መልስ የሚሆነው ´´ከዝንብ ማር አይጠበቅም´´ የሚል ነው።ህወሓት ማር ሊያመነጭ አይችልም።ማር የንብ ሥራ እንጂ የዝንብ ሊሆን እንደማይችል ሁሉ።

ሙሉ መግለጫውን ለመመልከት  ይህንን ይጫኑ።

ጉዳያችን GUDAYACHN 

 www.gudayachn.com

Friday, August 26, 2016

ጥልቅ ሐዘን / Our deep condolences==============
OUR DEEP CONDOLENCES FOR ALL ETHIOPIANS KILLED IN -OROMIA,AMHARA,GAMBLE,BENISHANGUL,KONSO,AFAR,ASOSA, HARER AND OTHER PLACES BY TPLF SOLDIERS.

በኢትዮጵያ፣በኦሮምያ፣አማራ፣ጋምቤላ፣አፋር፣አሶሳ፣ኮንሶ፣ቤንሻንጉል ሐረር እና ሌሎች ቦታዎች በህወሓት ወታደሮች ለተገደሉት እና አሁንም እየተገደሉት ላሉት ኢትዮጵያውያን ሁሉ ሃዘናችን የጠለቀ ነው።
=========================
ጉዳያችን GUDAYACHN www.gudayachn.com

Wednesday, August 24, 2016

US must stop all relation ships with TPLF and stand on the side of Ethiopian people


Finite Selam town protesters removing pro-TPLF posters.

Gudayachn (www.gudayachn.com)

Amhara regional state big towns Fnote Selam, Gondar and Bahirdar protests against TPLF regime is continuing.(According to ESAT this morning breaking news).

Fnote selam people is currently demonstrating. TPLF security forces shooting is hearing every where.On the other hand, Bahirdar home siting strike is continuing for another fourth days. Gonder start also the same strike today . Last week, it was recalled that Gonder's three days strike was completed successfully. Today's Gonder protest is another and fresh one. The same is happening in Oromia region. For last seven months most rural and urban areas of Harer, Bale, Shoa, Welega region residents are in continuous protest against TPLF. 

The response from TPLF both in Amhara and Oromia regions is savage act. According to International human rights organisations and independent Ethiopian sources up to this week over 1,100 Ethiopians are killed with live bullet of TPLF security personnel. The situation is not hided from all over the world. Even last Sunday Rio Olympic´s typical title was not sport. It was about non-humanitarian act of TPLF on its own people. Athlete Feyisa Lelisa, after he finalised his 42 kms. marathon computition at the second level, he show his hands up and tell to an international community, Ethiopian protest against ethnocentric and dictatorial rule of TPLF. (See 'Maybe They Will Kill Me': Ethiopian Runner Feyisa Lilesa Stages Protest Against Government)

Having said this, the bad news is that TPLF ethnocentric and dictatorial regime didn't show any sign to respond the peoples' tangible demand of democracy and regime change. Moreover EPRDF central committee press release this week appreciates it's own so called past success.

On the other hand, many Ethiopians and humanright activists abroad are feeling bad on ignorant respond of USA and international community. These days people are calling USA, "Mr.concern state'. This is because US ignorance for daily killing Ethiopians by TPLF live bullet is sense less. That means  the sole American Embassy in Addis press release regarding the popular rise and government forces respond was expressed by  full of soft phrase, "USA is concerned".

Many believes that USA is loosing its long-aged base in Ethiopia. US was repeatedly expressing Its relations with dictatorial and ethnocentric government of TPLF is strategic and based on anti-Terrorism common goal. The case of Somalia was raised repeatedly by US high officials as typical example. But here US missed the big reality that Terrorism fighter is the mass Ethiopian people not dictator and isolated ´state´ of TPLF. Ethiopians need now regime change. No more no less. Infact not only regime change, they need also to be supported to establish responsible government both regionally and internationally. This is the key point to fight terrorism. TPLF is now isolated and counting its minutes to loose all power. This is the fact on the ground in Ethiopia. USA shouldn't make her top century foreign policy fail regarding Ethiopian political situation. It must stop all relation ship with TPLF as soon as possible  and stand on the side of nearly one-hundred million Ethiopians.


ጉዳያችን GUDAYACHN
 www.gudayachn.com

Tuesday, August 23, 2016

ለኢትዮጵያ ድምፃውያን በሙሉ! አፋጣኝ መልዕክት


በአዲስ አበባ የኢትዮ-ፍራንስ አልያንስ በኢትዮጵያ ሙዚቃ ዙርያ በተለይ ባህላዊው ላይ ያተኮሩ ጥናታዊ ፅሁፎች እና ታዋቂ ድምፃውያንን እየጋበዘ ሽልማት ይሰጥ እንደነበር አስታውሳለሁ።በአንድ ወቅት ለምሳሌ ጋሽ መሐሙድ አህመድ የአንድ ዓመት እንግዳ ነበር።ከጥቂት አመታት በፊትም አሁን ዓመተ ምሕረቱን ባላስታውሰውም፣ በእዚሁ ዝግጅት ላይ አንዲት ፈረንሳዊት የኢትዮጵያ አዝማሪን በተመለከተ አንድ ፅሁፍ ማቅረቧን አስታውሳለሁ።በእዚህ ፅሁፍ ላይ ከጥንት ጀምሮ አዝማሪ በሕበረተሰቡ መልካም ግንኙነት ላይ ያለውን ሚና በዝርዝር ካቀረበች በኃላ አዝማሪን ስትገልፀው እንዲህ አለች።
      ´´ አዝማሪ በኢትዮጵያ በፖለቲካም ሆነ በተለያዩ ምክንያቶች የልዩነት ስፋቶች ሲመጡ ይህንን የልዩነት ክፍተት የሚሞሉት አዝማሪዎች ነበሩ´´ብላለች። አባባሉን በደንብ አስፍተን ብናየው ከብዙ አቅጣጫ በደንብ መፈተሽ ይቻላል።

ይህች ማስታወሻ ግን የኢትዮጵያ ድምፃውያን 
- የኢትዮጵያን ሕዝብ አንድነት፣
- የቀደመ እና አሁን መጉላት ያለባቸው የሕዝብ ፍቅር፣
- ኢትዮጵያዊነት፣ 
- በጎጥ መከፋፈል ያለውን አደጋ ወዘተ ላይ ያተኮሩ አዲሱን ትውልድ ሊያስተምሩ የሚችሉ የኪነት ስራዎች መስራት እንደሚጠበቅባቸው አበክሮ ለማሳሰብ ነው።ወጣቱ ትውልድ ሊሰማቸው እና ጎጠኝነትን እንዲጠላ ሕብረት፣ፍቅር እና በነፃነት መኖር  የነገ የኢትዮጵያን ሕይወት ብሩህ የሚያደርግ መሆኑን ሁሉ ማሳየት አሁንም ከከያንያኑ ይጠበቃል።በአገር ቤት ያሉ ከያንያን በተለይ አንጋፋዎቹም እንደገና ማይክ የምታነሱበት እና ስለ ኢትዮጵያ ሕዝብ አንድነት የምታስተምሩበት ጊዜ ነው።ባለፈ ዘመን ጥሩነት እያሰቡ ከንፈር መምጠጥ አንዳች አይፈይድም።

ይህ ትውልድ በማህበራዊ ድረገፆች አንዴ ኦሮሞነትን ብቻ ሌላ ጊዜ አማራነት ብቻ፣በተደራጀ መንግስታዊ መልክ ደግሞ ትግራይነትን ብቻ በጆሮው ላይ እየጮሁበት ኢትዮጵያዊነት ሳይጎላ እየቀረ የታሪክም ሆነ የትውልድ ተጠያቂ እንዳትሆኑ አስቡበት።እኔ እንደማስበው ከላይ በተጠቀሱት ሃሳቦች ዙርያ አዳዲስ ነጠላ ስራዎችን ለማውጣት ስሜቱ፣ቁጭቱ እና ከጉዳዩ አጣዳፊነት አንፃር ሲታይ በቀናት ውስጥ ሰርታችሁ ማድረስ ያለባችሁ ይመሰልኛል።

በመጨረሻም አንዲት የቴዎድሮስ ካሳሁንን (ቴዲ አፍሮ)  የዜማ ስንኝ ብቻ በመምዘዝ ምን ያህል በሕዝብ ዘንድ ኃይለኛ እና አዎንታዊ ስሜት እንደፈጠረ በናሙናነት ላንሳ። 

´´ ተስማምቶ የሚኖረው እስላም ክርስቲያኑ፣
    ተዘነጋሽ እንዴ ኢትዮጵያ መሆኑ ´´

ይህ ስንኝ ቴዲ አፍሮ ከዘፈነው በኃላ አዲሱ ትውልድ ላይ እስልምና እና ክርስትና  ኢትዮጵያ ውስጥ ያላቸው ግንኙነት ከሌላው ዓለም የተለየ መሆኑን በማስተማር ደረጃ የእራሱን በጎ አሻራ ጥሎ አልፏል።ይህ ማለት ቀድሞ አይታወቅም ለማለት ሳይሆን የኪነት ሰዎች በጎ ግንኙነታችንንም አጉልተው እና አስፍተው ሲያሳዩ ሕዝብ በበጎ ግንኙነቱ ይበረታታል።በሌላ በኩል ሕዝቡን ሊለያዩ የሚፈልጉ በጎጥ ሲከፋፍሉት እና ከያንያን ይህንኑ ወቅሰው ስራቸውን ሲያቀርቡ አጥፊም እጁን ይሰበስባል። ስለሆነም የኪነት ሰዎች ከእናንተ ብዙ ይጠበቃል።ኢትዮጵያ መከራ ላይ ሆና አንዳች ሳትሰሩ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከእዚህ ፈተና የወጣ ጊዜ የድል አጥብያ አርበኛ ብትሆኑ ሕዝብ አይቀበላችሁም። ጉዳያችን GUDAYACHN www.gudayachn.com

Sunday, August 21, 2016

ሪዮ ኦሎምፒክ ታሪክ ተሰራ! አንዱ ፈይሳ ሌሊሳ ስለ ሁሉ ተሰለፈ!

አትሌት ፈይሳ ለሊሳ ሪዮ ላይ ታሪክ ሲሰራ።

ዛሬ ነሐሴ 15፣2008 ዓም ኢትዮጵያ ጭንቀት ላይ ነበረች።የህወሓት አጋዚ ወታደሮች ከጎንደር እስከ ባሌ፣ከባህርዳር እስከ አርሲ በመቶ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን ሕይወት በሕዝብ ገንዘብ በተገዛ ጥይት ሕዝቡን ሲፈጁት ከርመዋል። በሁለተኛው የዓለም ጦርንነት ወቅት አይሁዶችን ጀርመኞች እንደሚያጉሩት በትግራውነታቸው የምመፃደቁት ህወሓቶች በሺህ የሚቆጠሩ የአማራ እና ኦሮሞ ወጣቶችን በኢየቦታው አጉረዋል።ይህ ሁኔታ ያሳሰባቸው ኢትዮጵያን አክትቪስቶች በአዲስ አበባ በገዢው ህወሓት ላይ ሰልፍ እንደሚደረግ ገለፁ።ከቅዳሜ ምሽት ጀምሮ ግን የህወሓት ወታደሮች የአዲስ አበባ ወጣት በተኛበት እየያዙ ወደ እስር ቤት ወሰዱት።እናቶች እያለቀሱ ልጆቻቸውን እያዳፉ ወደ እስር ቤት ወሰዷቸው።ምሽት ላይ  እና እሁድ ጧት ለቤተ ክርስቲያን ቅዳሴ የሚሄዱ ካህናት ሳይቀሩ ሲፈተሹ አረፈዱ።የአዲስ አበባ ዋና ዋና መንገዶች እና መንደሮች ሁሉ በአጋዚ ወታደሮች ተትለቀለቁ።መስቀል አደባባይ በከባድ የጦር ካሚዮኖች አጠረው።የተጠራው ሰላማዊ ሰልፍ እንጂ ጦርንት አይደለም በሚል ኢትዮጵያውያን ህወሓት ካለ ጦርነት ሰላም የሚባል ቃል እንደማታውቅ ደግመው አረጋገጡ። 

ይህ ሁሉ በሆነበት ወቅት ነበር።በብራዚሏ ከተማ ሪዮ ዲጀነሮ የሚደረገው የ2016 እኤአቆጣጠር ኦሎምፒክ ላይ በማራቶን የሚወዳደረው አትሌት ፈይሳ ለሊሳ 42 ኪሎ ሜትሩን ማራቶን 2ኛ ሆኖ በመጨረስ የብር ሜዳልያ ማሸነፉን ባረጋገጠበት ቅፅበት የኢትዮጵያንን በዘረኛው እና አምባገነኑ ህወሓት መረገጥ በቀጥታ ቴሌቭዥን ከ3 ቢልዮን በላይ ሕዝብ የሚመልከተው ስርጭት ላይ ለዓለም አጋለጠ። ህወሓት ከጎሳው ውጭ ለሆኑ ኢትዮጵያውያን ላይ የሚፈፅመውን ግፍ ለመላው ዓለም ነገረው።አዲስ አበባ ላይ ታንክ ደግነው በቴሌቭዥን ህዝቡ ተስማምተነዋል እያሉ ሲሳለቁ ለነበሩ አረመኔዎች በሳሎናቸው ሶፋ ፊት ለፊት ባለው ቲቪ ፊት ለዓለም አጋለጣቸው።በልጆቻቸው፣ቤተሰባቸው ፊት አረመኔነታቸውን ነገራቸው። ቃል አቀባዩ አቶ ጌታቸው ''አሁን የምሳ ሰዓት ደረሰ''እያሉ በአዲስ አበባ ወጣት ላይ እንዳልተሳለቁ ምሳ በልተው እራት ሳይደግሙ በዓለም ፊት ከጀርመኑ ናዚ የማያንሱ መሆናቸውን ነገራቸው።

አትሌት ፈይሳ ከኦሎምፒክ ሜዳ በኃላ በጋዜጣዊ መግለጫው መድረክ ላይም በደላችንን አሰምቷል።

በኦሎምፒክ አደባባይ ዘረኛ መንግስት ማጋለጥ ትልቅ መልዕክት ያለው ብቻ ሳይሆን ቀጣይ መዘዝ ለወያኔ ይዞ ይመጣል። ጋዜጠኛ ካሳሁን ይልማ የእዚህ አይነቱ ተግባር ከእዚህ በፊት በኦሎምፒክ አደባባይ መደረጉን እና ውጤቱን በፌስ ቡክ ገፁ ላይ የጠቀሰውን እንደሚከተለው አስቀምጠዋለሁ።
''አሜሪካዊያን አትሌቶች ጆን ካርሎስ እና ቶሚ ስሚዝ በ1968ቱ የሜክሲኮ ኦሊምፒክ በ200 ሜትር ሩጫ ውድድር የወረቅ የብር እና የነሐስ ሜዳሊያ ካሸነፉ በኋላ ባገኙት ድል መፈንጠዝ ሳይሆን በቆዳ ቀለም ልዩነት ብቻ በጥቁር ሕዝብ ላይ የሚፈጸመውን ጭቆና እና ዘረኝነት በመቃወም ጥቁር ጓንት አጥልቀው እጃቸውን ወደላይ ከፍ በማድረግ የጥቁር ኃይል ምልክትን አሳይተዋል። የለበሱት ጃኬት ላይ የሰብአዊ መብት ባጅ ለጥፈዋል። ጫማቸውን አውልቀው ጓንት ባለደረጉት እጃቸው ይዘዋል።

ከዚያ በኋላ በኦሊምፒክ ኮሚቴ እና በተለያዩ አካላት ከፍተኛ የትችት ውርጅብኝ ወርዶባቸዋል። ከናዚ ሰላምታ ጋር አመሳስለው እንዲሸማቀቁ የሞከሩ ሁሉ ነበሩ። ከአሜሪካ ቡድን እንዲገለሉ ቅጣት ተጥሎባቸዋል።ሆኖም ሁለቱ እንቁ አትሌቶች በዓላማቸው ጸንተው ተምሳሌት ሆነው ዛሬ ድረስ ይወሳሉ። በሳንሆዜ ዩኒቨርሲቲ የድል ሰላምታ ተብሎ ሐውልት ቆሞላቸዋል።የነርሱ ለእውነት መቆም ከሺህ ሰላማዊ ሰልፍ በላይ ለጥቁሮች መብት የሚያስፈልገውን መልዕክት ለዓለም አስተላልፏል። ከጎናቸው የቆመው ለህሊናው ያደረውና የወቅቱን የጥቁሮች ጭቆና የተገነዘበው ነጩ አውስትራሊያዊ ፒተር ኖርማን የብር ሜዳሊያውን ሲያጠልቅ የሁለቱ አትሌቶችን ዓላማ በመጋራት የሰብአዊ መብት ምልክት የሆነውን ባጅ ደረቱ ላይ አኑሮ አጋርነቱን አሳይቷል። 
ነጭ ቢሆንም የነጮችን ዐይን ያወጣ በደል፣ ጭቆና፣ ዘረኝነት፣ አድልዎ...ተረድቷል።ትግሬ በመሆናቸው የሌላው መረገጥ መሰደድ መገደል የሚያስደስታቸው ህወሓትን የሚደግፉ ሰዎች ስለ ሌሊሳ ምን ይሉ ይሆን?"እዚህ ሀገር አይገባትም፣ ተመልሶ ከመጣ ደግሞ ይገባታል፣ ይኼ ኦነግ...ከልቢ..." ምን እያሰባችሁ ነው?እኛስ ለሌሊሳ የክብር ሐውልት በልባችን ተክለናል። ነፃነት በምታገኘው ኢትዮጵያም ለትውልድ ትምህርት የሚሆን ሐውልት ይቆምለታል።'' የጋዜጠኛ ካሳሁን ፅሁፍ መጨረሻ።

ወያኔ ዘረኛ መሆኑን ከአይሮፕላን አብራሪ ካፕቴን ገብረመድህን እስከ የአልጋ ላይ ቁራኛ ሀብታሙ አያሌው የመሰከሩት ነው።ፈይሳን የአዕምሮ በሽተኛ ነው እንዳትሉ ጤናው በዓለም አቀፍ ደረጃ ተመርምሯል።እረስታችሁ እንዳትሉ ብዬ ነው። ዛሬ ታሪካዊ ቀን ነው።ሪዮ ኦሎምፒክ ታሪክ ተሰራ! ሌሊሳ ስለ ሁሉ ተሰለፈ! ታሪክ የምለው ዝም ብዬ ለማዳነቅ አይደለም።ለልጅ ልጆቻችን ስለ ኦሎምፒክ እና ኢትዮጵያ ትምህርት ቤት ሲማሩ የፈይሳ ተጋድሎ ይወሳል።ሲቀጥል ኢትዮጵያ ወያኔ በሚባል ዘረኛ ቡድን ምን ያህል ተጨቁና እንደኖረች ይማራሉ።ታሪክ ማለት ይህ ነው።የቅርብ ጊዜው ታሪክ ግን የምናየው ነው።

ጉዳያችን GUDAYACHN
 www.gudayachn.com

Thursday, August 18, 2016

አዲስ አበባ ፍልስፍና ነች። ለፍልስፍናዋ ትዋደቃለች።


በሃያ አንደኛው ክ/ዘመን ውስጥ ሆና በ4ኛው ክ/ዘመን አስተሳሰብ ውስጥ ባሉ መሪዎች የምትመራው አዲስ አበባ፣ከተመሰረተች 130 ዓመታት ለመድፈን ቀናት የቀሯት  አዲስ አበባ በኢትዮጵያ የቀደመውም ሆነ የወቅቱ ፖለቲካ ትኩሳት ውስጥ እራሷን የቻለች ፍልስፍና ነች።ከሁሉም የአገሪቱ ክፍል በአንድነት ተሰብስቦ የሚኖርባት አዲስ አበባ ባለፉት 25 ዓመታት ውስጥ የህወሓት የመከራ ዶፍ ከወረደባቸው የአገራችን ክፍሎች ውስጥ አዲስ አበባ በቀዳሚ ከሚጠቀሱት ውስጥ ነች።አዲስ አበባ ከጋዜጠኛ እስከ ከፍተኛ ምሁር፣ከቀን ሰራተኛ እስከ ለምኖ አዳሪ፣ከትላልቅ ለፍተው ጥረው ሀብት ካፈሩ ቱጃሮች እስከ ጉልት ቸርቻሪ ድረስ በህወሓት እስር፣ግድያ እና እንግልት ያየች ከተማ ነች አዲስ አበባ። 

ያስለቀሷት አዲስ አበባ
አዲስ አበባ ከሳቀች ቆይታለች።ምናልባት እኔ በዕድሜዬ አዲስ አበባ ሳቀች የምለው እንደ ከተማ (ሕዝብ ሳቀ አገር ሳቀ ነውና) የሳቀችው የምስራቅ እና ደቡብ አፍሪካ እግር ኩአስ ጫወታ ኢትዮጵያ ያሸነፈች ጊዜ ነው ብዬ አስባለሁ።ይህም በደርግ ዘመን መሆኑ ነው።ከእዛ ወዲህ አዲስ አበባ ከሳቀችው ይልቅ ብዙ ጊዜ አልቅሳለች።የአዲስ አበባ እናቶች መንገድ ለመንገድ በልጆቻቸው ስቃይ ለብቻቸው የምያወሩባት ከተማ ሆናለች በህወሓት ዘመን።የአዲስ አበባ ለቅሶ የጀመረው በጧቱ ገና ህወሓት አዲስ አበባን ሲቆጣጠር ነበር። ከተማዋ የመጡት የአልባንያ ሶሻሊስቶች መሆናቸውን ከማንኛውም የአገሪቱ ክፍል ነዋሪ ቀድማ ያወቀች ነበረች።በመሆኑም ግንቦት 20፣1983 ዓም ህወሓት ያረጁ ሶቭየት ሰራሽ ታንኮቹን በአዲስ አበባ መንገዶች ላይ እያቅጨለጨለ ሲገባ የአዲስ አበባ ሕዝብ ሆ! ብሎ አልተቀበለም።በሃዘን ከቤቱ ተቀምጦ አሳለፈው እንጂ። የአዲስ አበባ ለቅሶ ህወሓት አዲስ አበባ በገባ በሳምንቱ በለቅሶ ቤት ፍንዳታ ለዓለም ከፍ ብሎ ተሰማ። ምን ይሄ ብቻ የሸጎሌ ፋብሪካ ቃጠሎም ሌላው ሃዘን ነበር። ቀጥሎ አዲስ አበባ ከገጠማት ሃዘን ውስጥ ሌላው በ1997 ዓም ከነበረው ምርጫ ተከትሎ ከ200 በላይ ልጆቿን በህወሓት አጋዚ የጥይት አረር ያጣችው አዲስ አበባ ትልቅ ሃዘን ላይ ወድቃ ነበር።እናቶች ልጆቻቸው እንደወጡ ቀሩ፣ጧት ያዩት ልጅ ምሽት ላይ በጨካኞቹ የህወሓት አጋዚዎች አስከሬን ሆኖ መጣ።አቶ መለስ በለቅሶ ባዘነው ሕዝብ ላይ በቴሌቭዥን መስኮት ብቅ ብለው ደነፉበት።የሰዓት እላፊ አወጁበት።

አዲስ አበባ ፍልስፍና ነች 

በኢትዮጵያ የወቅቱ የፖለቲካ የአስተሳሰብ ዘውጎች ውስጥ የአዲስ አበባ እራሱን የያዘ አንድ እና ልዩ ምናልባትም የብዙውን የኢትዮጵያዊ ሕልም እና ምኞት የያዘ ነው።ይህ ሕልም ኢትዮጵያ መሆን ይገባታል ብሎ የአዲስ አበባ ሕዝብ የሚያልመው የእራሱ ፍልስፍና አለው።ይህ የአዲስ አበባ  ፍልስፍና ሰውን በኢትዮጵያዊነቱ የሚለካ ብቸኛ መስፈርት ነው።ፍልስፍናው  በህወሓት የተረጨው የጎሳ መርዝ ሊበጣጥሰው ያልቻለው የአዲስ አበባ ፍልስፍና ይሄው የህወሓት ወጣት ልጆችንም ውጦ ያስቀረ እና የማረከ ከመሆን አልፎ ወጣቶቹ በወላጆቻቸው ኃላ ቀርነት በአዲስ አበባ ብሔር አልባ ፍልስፍና መስታወትነት እንዲመለከቱ አደረገ። የቆዩት ህዋታውያን ከጎጥ ፖለቲካ ያፈነገጡ የመሰላቸውን አባሎቻቸውን ''የአዲስ አበባ ውሃ እየቀመሱ'' የምትል አሽሙር ይወረውራሉ። 

አዲስ አበባ አንድ ሰው በአማራነት ወይም በጉራጌ አልያም በሱማሌነት የተለየ ክብር ላግኝ ብሎ የተለየ መንገድ ቢያሳይ በአዲስ አበባ ፍልስፍና ይስተካከላል።ሕዝብ በእራሱ የሚያገልበት የማህበራዊ  ቅጣት አለው።ከመስመር ወጥቶ በጎሳው ሊኩራራ የሚፈልግ ያለው አማራጭ በቶሎ በአዲስ አበባ የጋራ አገራዊ ኢትዮጵያዊ መስመር መግባት ነው።አዲስ አበባ ጎረቤት ተከራይቶ ሲገባ የት ተወለደ? ከየት መጣ ሳይሆን የሚባለው ጥሩ ሰው ይመስላል፣አይመስልም ነው ጥያቄው።አዲስ አበባ ላይ እንደ ሰው ሆኖ መኖር እንጂ ወላጆቹ ባላስመረጡት ቦታ የት ተወለደ አይደለም ጥያቄው። ለእዚህ ነው የአዲስ አበባ ሕዝብ 25 ዓመት ሙሉ የህወሓት የጎጥ ፖለቲካ ያንገሸገሸው።  የአዲስ አበባ ፍልስፍና በእየጊዜው የሚነሳው ጊዝያዊ የጎሳ ስሜቶች አይደሉም።ዘለቂታው እና ዘመን አሻጋሪ ለሆነው ኢትዮጵያዊነት ትዋደቃለች።ኢትዮጵያዊነት ለአዲስ አበባ የኦሮሞው ሞት ሞቴ ነው ማለት ነው።ኢትዮጵያዊነት ማለት ለአዲስ አበባ አማራ በኖረበት አገር ባለስልጣን ተብዬ ሲሰደብ እኔ ልሰደብ ብሎ መነሳት ነው።ኢትዮጵያዊነት ለአዲስ አበባ የሱማሌው፣ጋምቤላው፣ሲዳማው፣አፋሩ ሁሉ ሳይከፋው በገዛ አገሩ በነፃነት የመኖሩ ፋይዳ ነው። አዲስ አበባ ፍልስፍናዋ ዘመን የተሻገረ፣ተሞክሮ ነጥሮ የወጣ ያጎፈረ አብዮተኛ ነኝ ባይ ሁሉ እንደፈለገ በክላሽ የማይቀይረው ጠንካራ ፍልስፍና ነው።

አዲስ አበባ ህወሓት በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ለፈፀመው ወንጀል መቀጣት አለበት የምትለው ይህንን መሰረታዊ የአገር ፍልስፍና ከኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ እና ክብር ጋር በዓለም አደባባይ ስላዋረደ ነው።አዲስ አበባዎች ፍልስፍናቸውን ይዘው ለኢትዮጵያ በአደባባይ ወጥተው የሚዘምሩበት ቀን ደርሷል።በሕብረታቸው እና በፍቅራቸው ታሪክ የሚሰሩበት ጊዜ ደርሷል።ለዓመታት ያለቀሰች አዲስ አበባ ከመራራ ትግል በኃላ በአደባባዮቿ የጎጥ ፖለቲካን ከትቢያ ላይ ጥላ የምትዘምርበት ቀን እሩቅ አይደለም።ጉዳያችን GUDAYACHN 
 www.gudayachn.com

Monday, August 15, 2016

ከሰባቱ የህወሓት መስራቾች አንዱን ጨምሮ 16 የትግራይ ተወላጆች መግለጫ አወጡ።''ህወሓት ስልጣኑን ይልቀቅ የሽግግር መንግስት ይመስረት'' ብለዋል።TPLF is at the beginning of the end.
Including the founder of TPLF, former first commander of its army and Ethiomedia editor plus other 13 Tigray province born Ethiopian issued statement. The statement demanded an immediate removal of TPLF from power and establishment of transitional Government in Ethiopia. See the Amharic version of the statement here below.

የመጀመርያው ህወሓትን ከመሰረቱት ውስጥ ዶ/ር አረጋዊ በርሄን እና የመጀመርያው የህወሓት ኮማንደር አቶ ተስፋዬ አፅብሃ   ጨምሮ አስራ ስድስት የትግራይ ተወላጆች ህወሓት ስልጣን እንዲለቅ እና የሽግግር መንግስት እንዲመሰረት በይፋ ጠይቀዋል።ሌሎች የክልሉ ተወላጆችም እንዲቀላቀሏቸው ጠይቀዋል።መግለጫውን ዘሐበሻ በድረ-ገፁ ላይ ያሰፈረውን ከእዚህ በታች ይመልከቱ።


ከትግራይ ተወላጆች የተሰጠ መግለጫ 8 ነሓሴ 2008
በአጠቃላይ ለ25 ዓመታት ሙሉ ህዝባችንን አፍኖ ሲገዛ የቆየና፣ ለ40 ዓመታት ሰላማዊ ዜጎችን እየረሸኑ አገራችንን እየዘረፉ የቆዩ ባለስልጣኖች ያሉበት ህወሓት/አህአዴግ በተለይ በዚህ ዓመት በኦሮሞና በአማራ ህዝባችን ላይ ጦርነት ከፍቷል። የአገዛዙን የግድያ ወንጀሎች እናወግዛለን፤ የህዝቡን ተቃውሞ እንደግፋለን።
ስለዚህ በአገራችን ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እንዲገነባ፣ የህዝባችን አንድነት እንዲጠናከርና የአገራችን ሉኣላዊነት እንዲከበር᎓-
1. ህወሓት/ኢህአዴግ ከስልጣን መወገድ አለበት
2. በኢትዮጵያውያን የፖለቲካ ድርጅቶች፣ ሲቪክ ማህበሮችና ብቃት ባላቸው ግለሰቦች የሽግግር
መንግስት መቋቋም አለበት።
ከዚህ በላይ የተጠቀሱትን ዓላማዎች ለማሳካት የሚከተለውን ጥሪ እያቀረብን ፣ እኛም ከህዝባችን ጐን ተሰልፈን ለትግሉ መሳካት የአቅማችንን እንደምናበረክት ቃል እንገባለን።
1. ሁሉም የኢትዮጵያ ህዝብ ተባብሮና ፋታ ሳይሰጥ አፋኙን አገዛዝ እንዲያስወግድ፣
2. በሰላማዊ ህዝብ ውስጥ የእርስ በርስ ደም መፋሰስ እንዳይከሰት ጥንቃቄ እንዲደረግ፣
3. ሰራዊቱና ሌሎች የመንግስት ታጣቂዎች በህዝባቸው ላይ እንዳይተኩሱ፣
4. ሁሉም የፖለቲካ እስረኞች ካለ ምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ ትግሉ እንዲጠናከር፣
5. የትግራይ ህዝብ በራሱ ላይ ብዙ ግፍ የሚፈፅመውንና በስሙ ሌሎች ኢትዮጵያውያንን
የሚጨፈጭፈውን ህወሓት አውግዞ ከኢትዮጵያውያን ወገኖቹ ጎን እንዲሰለፍ
በተጨማሪ ነፃነት ባላቸው አገሮች ውስጥ እየኖሩ የግፍ ስርዓቱን ዕድሜ ለማራዘም የሚሞክሩት ግለ ሰቦች፣ በተለይም የህወሓት ደጋፊዎች አደብ ካልገዙ የኢትዮጵያ ህዝብ አንደሚፋራዳቸው እንዲያውቁ፣ ማሳሰብ እንፈልጋለን።
የስም ዝርዝር᎓
1. ህይወት ተሰማ
2. ሕሉፍ በርሀ
3. ስልጣን ኣለነ
4. በየነ ገብራይ
5. ተስፋዬ መሓሪ
6. ተስፋይ ኣፅብሃ
7. ታደሰ በርሀ
8. ነጋሲ በየነ
9. ናትናኤል ኣስመላሽ
10. ዶክተር ኣረጋዊ በርሀ
11. ኣብራሃ በላይ
12. ኪዳነማርያም ፀጋይ
13. ካሕሳይ በርሀ
14. ዘልኣለም ንርአ
15. ደስታ ኣየነው
16. ዶክተር ግደይ ኣሰፋ
በዚህ መግለጫ ይዘት ሊስማሙ ከሚችሉ ሰዎች ጋር በሙሉ ስላልተነጋገርን በዚህ የሚስማሙ ስሞቻቸውን ወደሚከተለው ኣድራሻ ከላኩልን መግለጫውን በድጋሚ እናወጣዋለን᎓:
ethiocivic@gmail.comጉዳያችን GUDAYACHN www.gudayachn.com

Friday, August 12, 2016

ሰበር ዜና - አርበኞች ግንቦት 7 እና ኦሮሞ ዲሞክራቲክ ግንባር ጥምረት ፈጠሩ። Breaking News Ethiopia - Patriotic Ginbot 7 for Unity and Democracy (PG7) and the Oromo Democratic Front (ODF) formed an alliance.የአርበኞች ግንቦት 7 እና በአቶ ሌንጮ የሚመራው የኦሮሞ ዲሞክራቲክ ግንባር ጥምረት መመስረታቸውን የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቭዥን በሰበር የእንግሊዝኛ ዘገባው ዛሬ ገልጧል።ስምምነቱን በአርበኞች ግንቦት7 በኩል ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ሲፈርሙ በኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባር በኩል አቶ ሌንጮ ለታ ፈርመዋል።
እንደ ኢሳት የእንግሊዝኛ  ዘገባ  ጥምረቱ  ሶስት መርሆዎችን ይዟል። ከብዙ በጥቂቱ ከመርሆዎቹ ውስጥ የሚከተሉት ይገኙበታል-
1/ ኢትዮጵያ የበርካታ ብሔረሰቦች እና ሃይማኖቶች አገር መሆኗን፣ መንግስት የሁሉንም የማንነት መብት በእኩልነት እና መከባበር ላይ በመመስረት ማንፀባረቅ  እንዳለበት እና ሁለቱ ድርጅቶችእኩልነት እና የህዝብ አንድነት፣ማህበራዊ ፍትህ፣እኩልነት፣ዜግነት፣ኢኮኖሚያዊ ብልፅግና እና የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ያረጋገጠ እውነተኛ ዲሞክራሲያዊ ፈድራሊዝም ግንባታ ላይ ለመስራት፣
2/ ሁሉም አይነት የፖለቲካ ኃይሎች በነፃ የህዝብ ፈቃድ ላይ የተመሰረተ እንዲሆን፣አምባገነናዊ ስርዓት እንዲያከተም ለማድረግ፣ነፃ ምርጫ ለማስፈን እና ዲሞክራሲያዊ የስልጣን ሽግግር እንዲሰፍን ለማድረግ እና 
3/ ነፃነት፣ፍትህ፣እኩልነት እና ዲሞክራሲ በኢትዮጵያ ለማስፈን።የመቻቻል፣የውይይት እና ልዩነትን ግልፅ እና ክፍት በሆነ ውይይት መፍታት። የሚሉት በሶስቱ የጥምረቱ መርሆዎች ውስጥ የተጠቀሱ ናቸው።ዝርዝር ስምምነቱን ይዘት ለመመልከት ከእዚህ በታች በእንግሊዝኛ የተፃፈውን ዘገባ ይመልከቱ።
ከእዚህ በታች ያለው ፅሁፍ የተወሰደው ከኢሳት የእንግሊዝኛ ድረ-ገፅ ነው።
Patriotic Ginbot 7 for Unity and Democracy (PG7) and the Oromo Democratic Front (ODF) announced that they have formed an alliance. The Memorandum of Understanding was signed by Prof. Berhanu Nega and Leenco Lataa representing their respective organizations.
Following is the full text of the MoU.
Memorandum of Understanding (MoU) Oromo Democratic Front (ODF) and Patriotic Ginbot 7 (PG7)
August 11, 2016
After several candid discussions and careful considerations of the current political, social, economic and humanitarian situations in Ethiopia, and all the damages caused by successive regimes and the TPLF/EPRDF regime in particular on the welfare and national interests of the peoples of Ethiopia and the security and sovereignty of our country, the ODF and PG7 have made important observations and conclusions. The longer the current regime is allowed to stay in power, the harsher will be the pain, suffering and humiliation endured by the peoples of Ethiopia. Therefore, both parties are fully convinced that a transition from the current TPLF regime towards a new and genuinely federal and democratic state is of utmost urgency.
Both organizations take note of the fact that millions of people in Oromia for the last nine months, and now in the Amhara regions, as well as in the south, coming out and protesting in massive show of defiance, just a few months after the regime claimed a 100 percent victory in the sham elections it conducted in May 2015, and the manner of its reaction to the legitimate popular protests, demonstrate beyond doubt that the regime has lost any semblance of legitimacy. We believe that the mass killings, brutality, and inhuman treatment perpetrated by the TPLF regime against the peaceful protesters are enough indications that the Woyyane clique is determined to control all spheres of life in Ethiopia by sheer use of force and cling to power at all costs. The regime’s unwillingness to function in a multi-party political environment, provided for in its own tailor made constitution, and unabated repression and brutal killings in all parts of Ethiopia, harassment and persecution of the legal opposition, civil society and journalists, as well as gross abuse of power, looting of public and state resources demonstrate that the regime has closed all political space and avenues for reform. Therefore, ODF and PG7 firmly believe that the people have no other choice to end this tyranny and humiliation, but to engage in a concerted and coordinated mass democratic movement, popular uprisings, and rebellion to bring an end to repression, economic exploitation, national humiliation, tyranny, and dictatorship.
ODF and PG7 are mindful of the long standing call of the Ethiopian peoples for unity of all opposition political organizations and their strong desire to see that the different political and civic organizations coordinate their efforts and resources to bring an end to the illegitimate and tyrannical regime. Towards this end, the two organizations pledge to work jointly to bring all credible opposition political groups together into a broad democratic coalition.
Therefore, believing that a coalition of the Ethiopian democratic and liberation forces is the only alternative to get rid of the dictatorial regime and to create a truly united and genuinely democratic federation in Ethiopia, where justice, peace, equality, freedom, and economic prosperity prevail, ODF and PG7 have agreed on this day, August 11, 2016, to form an alliance on the basis of the following three cardinal principles. 
  1. Ethiopia being a multinational, multilingual and multi religious country, the state should respect and equitably reflect all its identities. The two organizations shall strive to build a truly democratic federal state, which promotes and guarantees the equality and unity of its peoples on the basis of social justice, equality, citizenship, economic prosperity, and protects and safeguards the sovereignty of the country.
  1. Bring an end to tyranny, dictatorship, and exclusive monopoly of political and economic power in Ethiopia, and lay the foundation for a democratic system where political power at all levels of government is subject to the free will of the people. All member organizations of the alliance and future coalition shall agree that genuinely free and fair elections are the only path to power. The primary objective of the alliance shall be bringing an end to tyranny and paving the way and laying the ground work for a democratic transition of power.
  1. The paramount purpose of the alliance is to achieve the prevalence of freedom, justice, equality and democracy in Ethiopia, and the empowerment of the people. Hence alliance and future coalition members shall not use minor policy differences to hinder these noble goals. Once they are empowered, the people shall be the ones who decide on alternative political, economic and social policies. The alliance and coalition members shall promote a culture of tolerance and dialogue and resolution of differences through frank and open discussions.
Both organizations, ODF and PG7, have agreed to form a joint working group, composed of representatives from each organization, to undertake all duties of coordinating different tasks as assigned by the agreements between the leaderships of the two organizations. 
Justice and Freedom for all!

Signed:

Leenco Lataa, President   , Oromo Democratic Front (ODF)

Birhanu Nega, Chairman, Patriotic Ginbot 7 (PG7)ጉዳያችን GUDAYACHN 
 www.gudayachn.com

Wednesday, August 10, 2016

የነፃነት ትግሉ ዓለም አቀፍ ትኩረት ስቧል።ትግሉን እስከ ነፃነት በመግፋት ዕድሉን እንጠቀምበት።ኢትዮጵያ የሃያ አንደኛ ክፍለ ዘመን አዲስ ትውልዷ በፀረ ወያኔ የትግል መንፈስ በአዲስ መልክ ነፃነት ወይንም ሞት! ብሎ ተነስቷል።የህወሓት ወያኔ ቡድን በጎጥ ተጠራርቶ ኢትዮጵያን ዳግም በባርነት ቀንበር ለመተብተብ በንፁሃን ኢትዮጵያውያን ገላ ላይ አዲስ ሳንጃ ወድሯል።በሺህ የሚቆጠሩትን ደም በከንቱ አፍስሷል።ብዙዎችን አካለ ስንኩላን አድርጎ የቤተሰብ ሸክም ሆነዋል።ሌሎች ሚልዮኖችን ከሀገር አሰድዷል፣በገዛ አገራቸው የበይ ተመልካች ሆነዋል።
በአንፃሩ ግን ህወሓት ለአድር ባይ እና ለመንደሩ ሰዎች ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ሻንጣ ተሸካሚ እስከ ከፍተኛ የንግድ ሥራ ድረስ በአንድ ጎጥ ሰዎች አስይዞ ኢትዮጵያን የቅምጥል ህወሐታውያን እና የበይ ተመልካች ዜጎች በሚል ከፋፍሏታል።

ከወራት በፊት በኦሮምኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያን የተነሳው ሕዝባዊ አመፅ እና ባለፉት ሳምንታት በጎንደር እና ጎጃም የተነሱት ፀረ ወያኔ ንቅናቄዎች የመላው ዓለምን ትኩረት ስቧል።ይህ ለነፃነት ትግሉ ትልቅ አስተዋፅኦ አለው።ላለፉት ሃያ አምስት ዓመታት በኢትዮጵያ የትኛውም ክፍል የተደረጉ ፀረ ወያኔ እንቅስቃሴዎች ከአለፈው 1997 ዓም ወዲህ የአሁኑን ያህል የዓለምን ትኩረት ስቦ አያውቅም።በኢትዮጵያ የሥርዓት ለውጥ እንደሚመጣ እና ሁኔታዎች እንዳሉ ሊቀጥሉ እንደማይችሉ ዓለም አቀፍ ሚድያዎች ብቻ ሳይሆን ከወያኔ ጋር የጥቅም ሽርክና ያላቸው መንግሥታትም ተረድተውታል። ይህ ማለት ግን የወያኔ ስርዓት አብቅቶለታል ማለት አይደለም።እያንዳንዱ ግለሰብ የእኔ አስተዋፅኦ ምንድነው? ብሎ መጠየቅ እና ለተግባራዊ ሥራ መነሳት አለበት። በምንም አይነት ሁኔታ ግን ወያኔ በመግደል ብዛት እድሜውን ለጥቂት ጊዜ እየተንገታገተ ያቆይ ይሆናል እንጂ በስልጣን እርከን የመቆየቱ ሁኔታ ግን አብቅቶለታል።

ዓለም ስለኢትዮጵያውያን የነፃነት ትግል ምን አሉ?

           ''የኢትዮጵያ መንግስት በመቶ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን እየገደለ የምዕራቡ ዓለም ለምንድነው እርዳታ የሚሰጠው?'' ዋሽንግተን ፖስት ጁላይ 9/2016 
''Ethiopia’s regime has killed hundreds. Why is the West still giving it aid?'' Washington post July 9,2016.
/////////////////////////////
''ሰኞ እለት ተቃዋሚ መሪዎች እና አምነስቲ ኢንተርናሽናል እንዳሳወቁት በሳምንቱ መጨረሻ በመላ አገሪቱ በተደረገ ተቃውሞ  የኢትዮጵያ የፀጥታ ኃይሎች አያሌ ሰዎችን ገደሉ።በመንግስት በኩል መደነባበሩ እየጨመረ ነው።'' 
''Ethiopian security forces shot dead several dozen people in weekend protests across the country as frustration with the government grows, an opposition leader and Amnesty International said Monday'' New York times, August 9,016.

//////////////////////////////////////////////////////

''ኦባማ ከጎበኙአት አንድ ዓመት የሆናት ኢትዮጵያ በተቃውሞ እየተናጠች ነው'' ዋሽንግተን ፖስት፣ኦገስት 9፣2016
''A year after Obama’s visit, Ethiopia is in turmoil'' Washington Post, Augest 9,2016
///////////////////////////
''የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብት ኮሚሽን በኦሮምያ እና አማራ መንግስት ለተጠቀመውን ከመጠን ያለፈ ኃይል በገለልተኛ አካል መመርመር አለበት''  ሮይተርስ ኦገስት 10፣2016 
''U.N. High Commissioner for Human Rights, said that allegations of excessive use of force across the Oromiya and Amhara regions must be investigated''
//////////////////////////////////////////////////

የአውሮፓ ህብረት  ኦገስት 10/2016 ጉዳት ለደረሰባቸው ሁሉ ማዘኑን ገልጦ ባፋጣኝ ሰላም የሚመጣበት መንገድ እንዲፈለግ ይጠይቃል።
//////////////////////////////////////////////////
የአሜሪካ ኢምባሲ ሰኞ ኦገስት 8/2016 ባወጣው መግለጫ በአመፁ ለደረሰው ጉዳት ማዘኑን ገልፆ ጉዳዩ እንዳሳሰበው ይገልጣል። 
/////////////////////////////////////////////////

ከእዚህ በተጨማሪ ቢቢሲ በተደጋጋሚ፣አልጀዝራ፣ አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ፣ ሮይተርስ ተቃውሞውን አስመልክቶ ህወሓት ከፍተኛ ቀውስ ውስጥ እንደገባ ኢትዮጵያም በብዙ ውጥረት ውስጥ እንዳለች ፅፈዋል።
////////////////////////////////////////////////

በሌላ በኩል የእንግሊዝ መንግስት ዶ/ር አርከበ ዕቁባይን ጨምሮ ሌሎች ባለስልጣናትን አስጠርቶ እንግሊዝ የኢትዮጵያ ሁኔታ በእዚሁ ከቀጠለ አዲስ አበባ የሚገኝ ኤምባሲዋን እንደምትዘጋ መግለጧን ኢሳት በነሐሴ 3/2008 ዓም  ዜናው ገልጧል። 

ባጠቃላይ ከላይ የተጠቀሱት ለናሙናነት የቀረቡት ዘገባዎች በሙሉ በሶስት ቀናት ውስጥ ብቻ የወጡ ዘገባዎች ናቸው።ይህ የሚያሳየው የኢትዮጵያ ሕዝብ ለዲሞክራሲ፣ፍትህ እና ነፃነት የሚያደርገው ትግል ከፍተኛ ደረጃ መድረሱን ብቻ ሳይሆን ዓለም አቀፍ ሕጋዊ እውቅና እያገኘ መምጣቱን ነው። ይህ ለትግሉ ትልቅ ዕድል ነው። የፖለቲካ ድርጅቶችም ሆኑ በአገር ቤት እና በውጭ የሚኖር እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ትግሉን በሁሉም አቅጣጫ ማስፋፋት እና ወደ ግብ የማድረስ ኃላፊነት አለበት።


ጉዳያችን GUDAYACHN 
 www.gudayachn.com

ዝም ያለ ከተስማማ እኩል ይቆጠራል።በሀገር ውስጥ እና በውጭ የሚኖረውን የትግራይን ሕዝብ ይመለከታል (የጉዳያችን ማስታወሻ)ህወሓት ከመነሻው ጀምሮ ግድያ የጀመረው በትግራይ ሕዝብ ላይ ነበር።የትግራይ ሽማግሌዎች ''የፊውዳል እና የነፍጠኛ አምላኪ'' እየተባሉ በህውሃት ግልፅ እና ስውር የግድያ መንገድ ተፈጅተዋል።የህወሓትን እንቅስቃሴ በቀዳሚነት የተቃወመ የትግራይ ሕዝብ ነበር።የአክሱም እና ተንቤን ሕዝብ ህወሓትን ደግፎ ቆሞ አያውቅም ነበር።ህወሓት በማኔፌስቶው ላይ '' የትግራይ ሕዝብ ትግል ፀረ-አማራ፣ ፀረ-እምፔራሊዝም እና ፀረ ንዑስ ከበርቴ'' መሆኑን ከገለፀ በኃላ አላማውም ''የትግራይ ሪፑብሊክ መመስረት ነው'' ይላል። ይህንን አባባል በመጀመርያ ላይ የተቃወሙት እና ለሰማዕትነት የደረሱት የትግራይ ወጣቶች እና አረጋውያን ነበሩ።ይህ ሁኔታ እስከ 1983 ዓም ሲቀጥል የአክሱም እና ተንቤን ሕዝብ በተለይ በኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ጉዳይ ህወሓትን በእየቦታው ሲሞግቱ የነበሩ አሁንም የትግራይ አዛውንት ነበሩ።በ1990 ዓም የተቀሰቀሰው የኢትዮ-ኤርትራ ግጭት ላይ የኢትዮጵያ ሕዝብ ለሰንደቅ አላማው እና ለኢትዮጵያዊነቱ ያሳየው ፅናት (ህወሓት ኢትዮጵያውያንን በአደባባይ ሲዋሹ ቢታዩም) ለትግራይ ሕዝብ ሰንደቅ አላማ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ዳግም ያረጋገጠ ታሪካዊ አጋጣሚ ነው።  

በ1968 የወጣው የህወሓት ማኔፈስቶ -

ኢትዮጵያውያን የህወሓት የጎጥ ፖለቲካ አይን ያወጣ ቢሆንም ሁሉን ችለው ኢትዮጵያዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ብቻ ሲያተኩር ቆይቷል።አቶ መለስ ሕይወት ሲያልፍ የአዲስ አበባ ሕዝብ ትግራይ ተወለዱ ኤርትራ ሳይል ከአየር መንገድ አስከሬን አጅቦ የወጣው ሕዝብ በኢትዮጵያ ላይ የተፈፀመውን ድርጅታዊ ወንጀልን ማንም እረስቶት አይደለም።በመላው ኢትዮጵያ ለቀናት የዘለቀ ሃዘን ሲታወጅ የኢትዮጵያ ሕዝብ በጨዋነት ቀናቱን በዝምታ አሳልፏል።
ይህ ሁሉ የሚያሳየን የኢትዮጵያ ሕዝብ ከሚገባው በላይ ጨዋ ሕዝብ መሆኑን ነው።ህወሓት ከጎንደር እና ዓለም ከተማ የመብራት ትራንስፎርመር በምሽት ሊሰርቅ እጅ ከፍንጅ የያዘው ሕዝብ የዘር አድልዎ እንደተደረገበት እያየ በአርምሞ አሳልፏል።በያዝነው ዓመትም በአርማጮ እና ወልቃይት ሕዝብ ላይ ህወሓት ከአድዋ እና ሽሬ እናቶችን በመኪና አመላልሶ ጠብመንዣ እያስያዘ በአማራው ሕዝብ ላይ ሁለት ጊዜ በሰልፍ ሲዝቱ የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን በዜና እወጃው ሲያሳይ የትግራይ ሕዝብ ይቃወማል ተብሎ ይጠበቅ ነበር።

ባለፈው ሳምንት መጨረሻም ጎንደር እና ጎጃም ላይ በህወሓት ሰራዊት ግልፅ የሆነ ወረራ ተፈፅሟል።እስከ አሁን ድረስ እንደ ሁማን ራይት ዘገባ ከአንድ መቶ በላይ ሕዝብ ተገድሏል።በሆስፒታል የሚገኙ በከባድ ሁኔታ የቆሰሉ ደግሞ ከ500 በላይ እንደሆኑ እና ከእነኝህ ከቆሰሉት ውስጥ አሁንም የሞቱት አስከሬን እየወጣ መሆኑ ይታወቃል።አሁንም ከትግራይ ሕዝብ በህወሓት ላይ የተሰማ ተቃውሞ የለም።


ይህ ብቻ አይደለም ዛሬ ሮብ ነሐሴ 4/2008 ዓም ከባህር ዳር እና ጎንደር የሚወጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ከመቀሌ በአንቶኖቭ አይሮፕላን የመጡ የአጋዚ ወታደሮች ወደ ጎንደር እና ባህርዳር ገብተዋል።ይህም ግልፅ የሆነ የጅምላ ፍጅት ህወሓት ልትፈፅም መሆኑን አመላካች ነው።ይህንንም የሚቃወም የትግራይ ሕዝብ ሰልፍ አልታየም።

ስለሆነም የትግራይ ተወላጅ እስካሁን እየሆነ ላለው ሁሉ ግልፅ ተቃውሞ በህወሓት ላይ ሲያሳይ አይታይም።ይልቁንም በማህበራዊ ድረ-ገፆች ላይ  የትግራይ ተወላጅ መሆናቸውን የሚናገሩት ''ትግራይ ኦንላይን'' እና ''አይጋፎረም'' በገፃቸው ላይ የሚፅፉት አማራውን እና ኦሮሞውን የሚያጣጥሉ እና ንቀት የሚያሳዩ ፅሁፎችን ነው።እነኝህ ድረ-ገፆች አላስፈላጊ ፅሁፎችን ሲለጠፉ አሁንም ከትግራይ በኩል ተቃውሞ የሚያሳይ አንድም የጎላ ድምፅ አልተሰማም።

ባጠቃላይ የትግራይ ሕዝብ ህወሓት ለሚሰራው ግፍ እና አገራዊ ወንጀል ሁሉ ዝም ማለት የለበትም።በእራሱ በትግራይ ህወሓትን የሚቃወም ሕዝብ ለማየት የኢትዮጵያ ሕዝብ እየናፈቀ ነው። አሁን ባለንበት ሰዓት የኢትዮጵያ ሰራዊት ውስጥም ግልፅ የሆነ መለያየት እየታየ ነው።ሰራዊቱ ውስጥ የትግርኛ ተናጋሪ እና ሌላ አካባቢ የመጡ በጥይት እርስ በርስ እንደተጋደሉ ተሰምቷል።ሰራዊቱ ከቀናት ምናልባትም ከሰዓታት በኃላ ሰራዊቱ አፈሙዙን በአቶ አባይ ወልዱ ቅልብ ሰራዊት ላይ እንደሚያዞር ምንም  ጥርጥር የለውም።የትግራይ ሕዝብ ግን የወገኖቹ መጨፍጨፍ እንዳልሰማ ዝም ሊል አይገባም። ይህ ሁኔታ ሁላችንም  አላስፈላጊ ወደ ሆነ መሰረታዊ የአስተሳሰብ ለውጥ ውስጥ እንዳያስገባን እና በግለሰቦች የተፈፀመብን የዘር አድልዎ ወደ ከፋ ድምዳሜ እንዳያደርሰን ያሰጋናል። ነገን አርቆ ማሰብ ለእራስ ነው።የትግራይ ሕዝብ ከእዚህ ሁሉ ውጥንቅጥ ውስጥ ሊወጣ የሚችልበት ቀላሉ መንገድ ህወሓትን መቃወም እና ፋሽሽታዊ አስተሳሰብ ከተፀናወታቸው አባይ ወልዱን እና ግብረ አበሮቻቸውን በቁጥጥር ስር በማዋል እና መሰረታዊ አገራዊ ፖለቲካዊ፣ምጣኔ ሃብታዊ ለውጦች ላይ እና እኩል ተጠቃሚነት ላይ ሲስማማ ብቻ ነው።ከእዚህ ውጭ ግን ''ዝም ያለ ከተስማማ እኩል ይቆጠራል'' እንዲሉ በድርጊቱ ከመስማማት እንዳያስቆጥር ከፍተኛ ስጋት አለ።እጅ አጣጥፎ ሁኔታውን እንደ ሲኒማ ከመመልከት ህወሓትን አደብ አስገዝቶ ለዘላለም ከምንኖርበት ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር አንድ መሆን ብቸኛው አማራጭ ነው።


ጉዳያችን GUDAYACHN
 www.gudayachn.com 

ወይ ባልዘፈንሽ፤ ከዘፈንሽ ባላሳፈርሽ (የፓትርያርኩ መግለጫ) በዲ/ን ኢንጅነር ዓባይነህ ካሴ


በዲ/ን ኢንጅነር ዓባይነህ ካሴ 
ትናንት ነሐሴ ፫ ቀን ፳፻፰ በፓትርያርክ አቡነ ማትያስ የተሰጠው መግለጫ ከወቅታዊነቱ ይልቅ ወገንተኛነቱ ያየለበት እንደኾነ በገሃድ ይነበባል፡፡ ብዙ ጊዜ አሳፍረውናል አሁንም ያው መንገድ እንደተስማማቸው ያሳያል፡፡ ከአንድ ፓትርያርክ የሚጠበቀው ሰብእና እንደዚህ ባለ አስጨናቂ ጊዜ ከማንም ያልወገነ ማዕከላዊ ሀሳብ ይዞ ግልግል ውስጥ መግባት ነው፡፡ በዚህ መለኪያ ፓትርያርክ ማትያስ የሰጡት መግለጫ ሲመዘን ብዙ የሚነሳ የሚጣል ጉድ አለበት፡፡ ይህንን መለኪያ መከተል ካልቻሉ (በልባቸው ምን እያሰቡ ዝም ሊሉ እንደሚችሉ ብናወቅም) ዝም እንዳሉ ቢቀሩ ይሻለን ነበር፡፡
በአበው ብኂል ወይ ባልዘፈንሽ፣ ከዘፈንሽ ባላሳፈርሽ ይባላል፡፡ የማይችል ሰው ስለማይችል አርፎ መቀመጥ ይገባዋል፡፡ እችላለሁ ካለ ደግሞ ጉዳዩ በሚጠብቀው ደረጃ በቅቶ መገኘት አለበት፡፡ ከሁለቱም ያጣ ኾኖ እችላለሁም ብሎ ዕድሉንም አግኝቶ ባገኘው ዕድል ሳይጠቀም ከቀረ ሮቤላዊነት ይኾናል፡፡ (መቼም ሮቤል በተባለ ወጣት “ዋናተኛ” ሪዮ ኦሎምፒክስ ላይ የብዙ ጀግኖች አትሌቶቻችንን ወርቃማ ታሪክ የሚፃረር አሳፋሪ እና አዋራጅ ድርጊት መፈጸሙን ከቀደመው አብረቅራቂ የኦሎምፒክ ገድላችን በፍጹም ተቃርኖ ያስመዘገብነውን አሳፋሪ ኩነት የማያውቅ የለምና) ለእኔ ሁለቱም አንድ ናቸው፡፡
ለሁለቱም ታሪክ በር ከፍታ መድረክ አመቻችታ ተቀበለቻቸው፡፡ አንችልም ብለው ከመድረኩ መራቅ ሲገባቸው በማይችሉበት መድረክ እንደሚችሉ ኾነው ብቅ አሉ፡፡ ያ መድረክ እጅግ በጣም ቢያንስ ከተዋናዮቹ የሚጠብቀው ሚኒማ አለ፡፡ ከሚኒማው በጥቂቱ መውረድም ብዙ አያሳማም፡፡ አፈጻጸሙ ፍየል ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ ከኾነ ግን አዋራጅ ይኾናል፡፡ ከጀርባ ያለው ባንዲራ ነውና፡፡ ውድቀቱ በእነርሱ ብቻ አይቆምም ሀገርንም ያሳፍራል፡፡
የፓትርያርኩ መግለጫ ከወገብ በላይ ታቦት ከወገብ በታች ጣዖት የኾነ ግራ የገባው ኾኖ ይነበባል፡፡ ጸልዩ አስተምሩ የሚሉት እንደታቦት የሚታዩ ናቸውና፡፡ መግለጫ ሰጡ ሲባል መደንገጤ አልቀረም ደግሞ ምን ብለው አዲስ የቤት ሥራ ይሰጡን ይኾን በማለት ከልቤ ተጨንቄ ነበር፡፡ የኾነው እና ያስጨነቀኝ ተገጣጠሙ እናም አሳመመኝ፡፡
በተለይ በተራ ቁጥር ሁለት እና ሦስት ላይ የተቀመጡት ሀሳቦች ምን ማለት እንደፈለጉ ያሳብቅባቸዋል፡፡ 
2. በየአካባቢው የሚገኙ አዛውንቶችና ሽማግሌዎች፣ ምሁራንና አባወራዎች እንዲሁም እማወራዎች ልጆቻቸውንና የአካባቢው ወጣቶችን በመምከርና በማስተማር የሰው ሕይወትን ከጥፋት፣ የሀገር ሀብትን ከውድመት እንዲታደጉ ቤተ ክርስቲያናችን ጥሪዋን ታስተላልፋለች፤
በዚህ ሀሳብ ውስጥ ገላጋይነት ፈጽሞ ስፍራውን እንደለቀቀ ይታያል፡፡ የሚመከረው አንዱ ወገን ብቻ እንደኾነ ያሳያል፡፡ በእርሳቸው ሀሳብ ሌላ የሚመከር አካል የለም፡፡ ወጣቱ አጥፊ መኾኑን ጠቅሰው ምክር እንደሚያስፈልገውም ጠቁመዋል፡፡ በእርግጥ ቦታቸው ይህ ነበርን? አይደለም፡፡ በመካከል ኾነው ቢያንስ ቢያንስ አንተም ተው አንተም ተው በማለት ቃለ ተግሣጹን ለሁሉም በማዳረስ እኔ ልሸምግል ማለት በተገባቸው ነበር፡፡ ጨርሶ ወደ አንዱ አዘንብሎ ከቀሩ የተነሡበት ዓላማ ወይ አልተሳካም ወይ ከጅምሩ ዓላማቸው ሌላ ነበር፡፡

3. ሁሉም ወገኖች አለን የሚሉትን ጥያቄ በሰላማዊ መንገድ ለሚመለከተው አካል በማቅረብ፣በውይይትና በምክክር እንዲሁም በሰላማዊና ሕጋዊ መንገድ በመጓዝ ችግሩን ለመፍታት በሚደረገው ጥረት የበኩላቸውን ያደርጉ ዘንድ ቤተ ክርስቲያናችን ታሳስባለች፡፡
በዚህ መግለጫ ውስጥ “ጥያቄ አለን የሚሉት ወገኖች . . . በሰላማዊና ሕጋዊ መንገድ በመጓዝ ችግሩን ለመፍታት በሚደረገው ጥረት የበኩላቸውን ያደርጉ ዘንድ ቤተ ክርስቲያናችን ታሳስባለች” ይላሉ፡፡ “ችግሩን ለመፍታት በሚደረገው ጥረት” የሚለውን ስንመለከተው የተጀመረ ጥረት መኖሩን ያሳያል፡፡ የተጀመረ ጥረት ለመኖሩ ምን ያኽል እርግጠኛ ሊኾኑ ናቸው? ካለስ የቱ? አልነገሩንም፡፡ መንግሥት ጉዳዩ ከውጭ ኃይሎች ጋር የተዳመረ መኾኑን ገልጦ እየተናገረ ነው፡፡ ከየትኞቹ የውጭ ኃይሎች ጋር በዚህም በመንግሥት በኩል ምን የተጀመረ ነገር አለ? ካለ ተስፋ ሰጪ ነውና ቢጠቁሙ ሠናይ በኾነ፡፡ አለበለዚያ አለ ብሎ መናገሩ ግምት ውስጥ ይጥላል፡፡

ሌላው በዚሁ መግለጫ ውስጥ “በሰላማዊና ሕጋዊ መንገድ” የምትለው አባባል ወጣቱን በሕጋዊ እና ሰላማዊ መንገድ አልሄድህም ተብላ የምትተረጎም ናት፡፡ ወጣቱ በተባለው መንገድ ሄደ ሲባል ሌላውስ አካል? ነው ወይስ በዘወርዋራው መንግሥት ሕጋዊ ሲኾን ወጣቱ ሕገ ወጥ ነው መባሉ ነው? እንደዚህ ከኾነ ደግሞ አንዱን አጽድቆ ሌላውን መኮነን ስለኾነ ከገላጋይነት ይልቅ ወገንተኝነት አለበት፡፡
ራሱ መግለጫው “በሀገር ውስጥ አለመግባባት ሲፈጠር አንዱን ካንዱ ሳትለይና ሌላውን ሳታገል ሁሉንም በእኩልነትና በልጅነት መንፈስ በማየት ስትመክር፣ ስታስተምርና ስታስማማ የነበረች፣ አሁንም ያለች፣ ለወደፊትም የምትኖር የቁርጥ ቀን እናት ቤተ ክርስቲያን ናት፡፡” በማለት የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ሚና ደግሞም መለኪያ ሚዛን አስቀምጦ የተነሣ ነው፡፡ ይኸው መሥፈርት ወይም መዳልው ወይም ሚዛን ወይም መለኪያ በሁለቱ ሀሳቦች ውስጥ አለመገኘቱ ግራ ያጋባ፡፡ አንዱን ካንዱ ሳትለይና ሳታገልል ከተባለ እና አሁንም ያንን ታደርጋለች በሚል ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ከሰበከ በኋላ ይህ ሀሳብ ወዴት እንደመነነ ሳይታወቅ አንዱ ወገን ላይ ብቻ ማትኮር ተገቢነት የለውም፡፡ ለዚህም ነው ወይ ባልዘፈንሽ ከዘፈንሽ ባላሳፈርሽ የተባለው፡፡


ምንጭ= ዲ/ን ኢንጅነር ዓባይነህ ካሴ ፌስ ቡክ ገፅ (https://www.facebook.com/abayneh.kassie.5/posts/1003781496407994) 

ጉዳያችን GUDAYACHN www.gudayachn.com

Monday, August 8, 2016

''ሸዋ ባላመጠ ባመቱ ይውጣል'' ጀግናው የመርሐቤቴ፣መንዝ፣ምንጃር፣እና ይፋት ሕዝብ ለነፃነትህ ተነስ!

መርሃቤቴ ዋና ከተማ ዓለም ከተማ 

''ሸዋ ባላመጠ ባመቱ ይውጣል'' የምትል አባባል አለች።የሸዋ ሰው አንድን ነገር ለእረጅም ጊዜ በሚገባ ከመረመረ በኃላ ለተግባር ይነሳል ማለት ነው።ሃያ አምስት ዓመታት ለማላመጥ ከበቂ በላይ ነው። 

ህወሓት የዋልጌ ግለሰቦች ስብስብ ነው።ህወሓት ኢትዮጵያን ለባዕዳን የሸጡ ወንጀለኞች አባላት ያሉበት ነው።ህወሓት ከናዚዎች የተቀዳ የዘር ፖለቲካ ይዞ የሚንቀሳቀስ የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የአፍሪካ ነቀርሳ ነው። በህወሓት ውስጥ የተሰባሰቡ ግለሰቦች እና በጎጥ ገመድ ተተብትበው የሚያሽቃብጡ ሁሉ ቂም አርግዘው ቂም የሚተፉ ያለንበትን ዘመን የማይመጥኑ እጅግ ያረጀ አስተሳሰብ ይዘው የምንገታገቱ የከንቱዎች ስብስብ ነው። ህወሓት ከመነሻው አላማው ኢትዮጵያን መከፋፈል መሆኑን ያልተረዱ በደርግ ላይ ጥላቻ ያደረባቸው የኢትዮጵያን ልጆች ደም እግሩን እያጨቀየ በደማቸው ላይ  በእግሩ ተረማምዶ አራት ኪሎ ቤተ መንግስት የገባ እና በኃላ ሰማዕታቱን የከዳ የከሃዲዎች ጥርቅም ነው። ይህ ቡድን ከስልጣን መውረድ አለበት።በትዕቢት የተወጠሩ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የሚደነፉ አድር ባዮቻቸውም ካለ ችሎታቸው ከተንጠላጠሉበት በሕዝብ አጥንት የተገነባ ስልጣናቸው በሕዝብ ኃይል መውረድ አለባቸው። 

ጀግናው የኦሮሞ፣የጎንደር፣ጎጃም እና አዲስ አበባ ሕዝብ ባሳለፍነው ሳምንት ወያኔ በቃ! ብሏል።ካለፈ ያልተማረው  ህወሓት ባዶ እጃቸውን በተሰለፉ ኢትዮጵያውያን ላይ ከመትረጌስ እስከ ከባድ መሳርያ ድረስ በመተኮስ ባለፉት ሰባ ሁለት ሰዓታት ብቻ ከስልሳ በላይ ንፁሃንን ገድሏል።ወያኔ እና አድር ባዮቹ ይህ ሁሉ እልቂት በምፈፀምበት ሰዓት የትግራይ ምክትል ፕሬዝዳንት በተገኙበት ዋሽንግተን ላይ  ውስኪ እየተራጩ ሲጨፍሩ ተመልክተናል።ይህ ብቻ አይደለም የኢትዮጵያ ሕዝብ ያነሳውን ወያኔ ስልጣኑን ይልቀቅ የሚለውን ፍፁም ሕጋዊ ጥያቄ እንደ ትልቅ ድፍረት ቆጥረውት በንፁሃን ላይ የሚፈፀመውን ግድያ ፍትሃዊ አስመስለው ሲናገሩ መስማት የነፃነት ትግሉ ማንን ቀድሞ ማስተማር እንዳለበት ሁኔታውን ግልፅ ያደርገዋል።

የሰሜን ሸዋ ሕዝብ እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ በወያኔ ያልተፈፀመበት የግፍ አይነት የለም።ከመርሃቤቴ ዋና ከተማ የዓለም ከተማ እስከ ደብረ ብርሃን ከተሞች እና የገጠር መንደሮች ሁሉ ህወሓት የፈፀመው ግፍ  ምን ጊዜም የሚረሳ አይደለም። በሰሜን ሸዋ ካራ ምችግ በ1982 እና 83 ዓም በዓለም ከተማ የ1997 ዓም ምርጫ ተከትሎ በወጣቶች ላይ ግድያ ተፈፅሟል።በተለይ በዓለም ከተማ በጠራራ ፀሐይ በሕወሃቱ ሹም ሕዝብ በአደባባይ እንዲሰበሰብ አድርጎ በአደባባይ በግል ሽጉጡ የተገደሉት የሁለቱ ወጣቶች ደም አሁንም በዓለም ከተማ የፍትህ ያለህ እያለ ነው። የሰሜን ሸዋ ሕዝብ ከአጎራባቹ የኦሮሞ ማኅበረሰብ ጋር በፍቅር ለአመታት ይኖረ ሆኖ ሳለ ወያኔ ለማጣላት ያልሸረበው ተንኮል አልነበረም። ሆኖም ግን ሊሳካለት አልቻለም።አሁን ወቅቱ ያለፈውን እያነሳን የምንቆዝምበት ወቅት አይደለም።ከኢትዮጵያ ሕዝብ  ጋር ወያኔን በቃ! የምንልበት  ወሳኝ ጊዜ ነው። ሃያ አምስት ዓመት ማላመጥ ይበቃል! ''ሸዋ ባላመጠ ባመቱ ይውጣል'' ጀግናው የመርሐቤቴ፣መንዝ፣ምንጃር፣ዋግኅምራ እና ይፋት ለነፃነትህ ተነስ!

''ልቤ ነው ፍትህ የሻተው
ና! ቶሎ ዳኘው ዳኘው።
ስጠው ፍርዱን ስጠው፣
ችሎቱ ያንተው ነው።''


ጉዳያችን GUDAYACHN www.gudayachn.com

Thursday, August 4, 2016

የጎንደር የበሰለ ፖለቲካዊ እና ወታደራዊ እንቅስቃሴ ህወሃትን ''ከካሮት እና ዱላ'' አንዱን እንዲመርጥ አስገድዶታል ። (የጉዳያችን ማስታወሻ)


አንድ ወቅት አንድ የፖለቲካ ተንታኝ (ስማቸው ይቆየን) ህወሃትን በተመለከተ  ለምንድነው ይህንን ያህል ሕዝብ እየገደለ፣እያሰረ እና እያሰደደ ስልጣን ላይ ለመቆየት የቻለው? ሲሉ ከጠየቁ በኃላ መልሱን ሲመልሱ እንዲህ ማለታቸውን አስታውሳለሁ። 
'' ህወሓት የገጠሙት ተቃዋሚዎች በሙሉ የህወሃትን ተንኮል የሚመጥኑ አይደሉም። ፕሮፌሰር አስራትን ተመልከት።ፕሮፌሰሩ እድሜያቸውን ሙሉ በሽተኛ ሲያድኑ የኖሩ ሰው ናቸው።እንዴት ብለው 17 ዓመት ሙሉ ሰው ሲገድል ከነበረ ህወሓትን የሚመጥን የትግል ስልት እንዴት ይቀይሱ? ሌሎች ተቃዋሚዎችን ተመልከቱ።ግማሾቹ ዳኞች፣የሕግ ሰዎች፣የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች ናቸው።እነኝህ ሰዎች ደግሞ ሕግ እና ስርዓት ጠብቀው እንጂ እንደ ህወሓት ሕግን አፈር ድሜ እያስጋጡ አይታገሉም።ስለሆነም ህወሓት የሚመጥነው ተቃዋሚ ያስፈልገዋል።'' ነበር ያሉት።

አሁን ላይ ሆነን ስንመለከት፣የምሁሩን ሃሳብ ማቃለል አይቻልም።ህወሓት ከቅንጅት በፊት ስርዓቱን የተቃወሙ የኢትዮጵያ መምህራን ማህበርን፣ ነፃውን ሚድያ፣የ1997 ዓም ምርጫ እንቅስቃሴ እና ከእዚያ በኃላ የታሰሩት የፖለቲካ ፓርቲዎች መሪዎች ተቃውሞ ሁሉ ህወሃትን የሚመጥነው ተቃዋሚ አለማግኘቱን አመላካች ድርጊቶች ሆነው አልፈዋል።ድሮስ ሕግን የሚያውቅ በሕግ ትሞግተዋለህ።እንደ ህወሓት ላላ የሰራውን ሕግ በመደፍጠጥ ለሚታወቅ ስርዓት አብዝቶ ስለ ሕግ በማውራት ህወሓት ኢትዮጵያን በጎሳ ፖለቲካው እንዳይረግጣት ለማድረግ አልተቻለም።በአዲስ አበባ በ1997 ዓም ከ200 በላይ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ሲገደሉ፣ጋምቤላ  ላይ ኢትዮጵያውያን መሬታቸውን ሲነጠቁ፣ከ500 በላይ የኦሮምኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያን ለምን ተሰለፋችሁ በሚል ብቻ ከገደለ በኃላ ፣በመቶዎች የሚቆጠሩ የሲዳማ ሕዝብ ሲገደል ሁሉ የነፃነት ትግሉ፣የህወሃትን ትዕቢት የተሞላበት ንቀት የሚመጥን ትግል ያለህ እያለ  ነበር።

ካሮት እና ዱላ 

አቶ መለስ ህወሓት አስጨንቆ የሚታገላት እንደሚያስፈልጋት በምፀት መናገራቸው ይታወሳል። የሰላማዊ ትግልን ያናናቁት አቶ መለስ የትጥቅ ትግል የሚፈልግ ካለ ''መንገዱን ጨርቅ ያድርግለት'' የሚል መልክት አስተላልፈው ነበር።መልክቱ ''እኛ በመጣንበት መንገድ ኑ!'' መሆኑ ነው።ከሰሞኑ በጎንደር የተነሳው ተቃውሞ በህወሓት የአገዛዝ ዘመን ፈፅሞ ያልታየ እና በዓይነቱም ልዩ ነው።የወልቃይት ጠገዴ አማራነት የያዘው የአቤቱታ ኮሚቴ ጥያቄውን በአግባቡ እስከ ፈድሬሽን ምክርቤት እና የተለያዩ የመንግስት አካላት በግንባር  ላቀረበው ጥያቄ ከህወሓት የተገኘው ምላሽ በትዕቢት ''ወልቃይት ትግራይ ነው'' የሚል ''ምን ታመጣላችሁ'' ምላሽ ነበር።

የጎንደር ሕዝባዊ እንቅስቃሴ በአይነቱ ልዩ ነው።ልዩ ያደረገው የህዝቡ ሕብረት ብቻ አይደለም።ደረጃውን የጠበቀ የፖለቲካ አቀራረብ የያዘ መሆኑም ብቻ አይደለም።መላው ኢትዮጵያውያንን ቁስል እና ህመም የዳሰሰ ብቻ ስለሆነም ብቻ አይደለም።እንቅስቃሴው አላማውን የሚያሳካው ካሮት እና ዱላ ለህውሃት በማቅረብም ጭምር ነው።ህወሓት በኃይል ለመጠቀም ሲሞክር ይህ ሕዝባዊ እንቅስቃሴ ዱላ ያቀርባል።ህወሓት ሰላማዊ ለመሆን ሲሞክር ደግሞ ካሮት ያቀርባል።በእዚህም መሰረት ህወሓት ሐምሌ 5 ቀን ኮ/ል ደመቀን ለመያዝ ጦር ሲሰብቅ እንቅስቃሴው ጦር ሰብቆ መጣ።በሐምሌ 24/ 2008 ዓም ከግማሽ ሚልዮን ሕዝብ በላይ በተሳተፈበት ሰልፍ ላይ ህወሓት ሰልፉ አለመፈቀዱን በራድዮ ፋና እና ኢቲቪ ሲያስነገር ዋለ።የጎንደሩ እንቅስቃሴ ግን ካሮት እና ዱላ ይዞ ሰልፉን አካሄደ።በካሮት ሰላማዊ መልኩን አቅርቡ።በዱላው ከኃላ የሚጠብቅ ታጣቂ በማሰለፍ ህወሃትን አስገድዶ ሰልፍ ለማድረግ የቻለ እና በአይነቱ ልዩ ነበር።እንቅስቃሴው በእዚህ አላበቃም ከእሁዱ ሰልፍ በኃላ ሐምሌ 26/2016 ዓም እንቅስቃሴው ለህውሃት ግልፅ ደብዳቤ ፅፏል።የጎንደር እንቅስ ቃሴ ካሮት እና ዱላ አቀራረብ ህወሓትን ከማንቀጥቀጥ አልፎ የስልጣን መሰረቱን አናግቶታል።''በአህያ ቆዳ የተሰራ ቤት፣ፍርስርስ ይላል ጅብ የመጣ እለት'' እንዲሉ በጎጥ ላይ የተመሰረተ የህውሃት ፖለቲካ በቻለው መጠን ሕዝብ በሕዝብ ላይ ለማስነሳት ቢሞክርም ባለመቻሉ የሚይዘው የሚጨብጠው ጠፍቶታል።ህወሓት አሁን የሚመጥነው የትግል ምርጫ ቀርቦለታል።ከካሮት እና ዱላ መምረጥ የህወሓት ምርጫ ነው።
ጉዳያችን GUDAYACHN 
 www.gudayachn.com

ለፕሮፌሰር መራር፣ልደቱ፣ጀዋርና ኢንጅነር ይልቃል ዘፈን ይህችን ዜማ እንምረጥላቸው።

በቅድምያ ስለ አራቱም የመግቢያ ማስታወሻና ወቅታዊ ሁኔታቸው። አራቱም ከመስከረም በኋላ መንግስት የለም ብለው ኢትዮጵያን ለእርስ በርስ ጦርነት ሊነክሯት ሞክረዋል።ዝርዝሩን፣ከእነማን ጋር መክረው እንደነበር፣ለኢትዮጵያ ደግሰው...