ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Tuesday, August 30, 2016

በኢትዮጵያ አሁን ያሉት አማራጮች (በቀጣይ የሚሆኑት) ሁለት ነገሮች ብቻ ናቸው።ምርጫው በእያንዳንዳችን ውጤት ይወሰናል። (የጉዳያችን ማስታወሻ)


ሀ/ ነባራዊ ሁኔታው 

1/ የኢትዮጵያ ሕዝብ ወያኔ በቃኝ ብሏል። 
2/ ወያኔ ለእውነተኛ የፖለቲካ መፍትሄ ዝግጁ አይደለም።
3/ ወያኔ ፋሽሽት መንግስት መሆኑን በሚያፈሰው የንፁሃን ደም አስመስክሯል።
4/ የወያኔ ደጋፊዎች  ወያኔ በሕዝቡ ላይ መዝመቱን ሲሰሙ ´´እሰይ ይበለው!´´ ሲሉ እየተሰሙ  ነው።በእዚህም የበለጠ የህዝብ ልብ አድምተዋል።እነኝህ ነባራዊ ሁኔታዎች ናቸው።
5/ አቶ ኃይለ ማርያም ድምፁን ያሰማው ሕዝብ እንዲገደል ፈርምያለሁ ብለው በይፋ ተናግረዋል።

ለ/ ሁለቱ ብቸኛ አማራጮች 

አማራጭ አንድ 

ወያኔ በሕዝቡ ላይ የጀመረውን ዘመቻ አጠናክሮ ቀጥሏል።ትናንት ነሐሴ 23/2008 ዓም ጀምሮ ተጨማሪ ከባድ መሣርያዎች እየገቡ ነው።ስለሆነም ወያኔ ይህንን አመፅ ከጨፈለቀ በሰልፍ ላይ የታዩትወጣት፣ሽማግሌ  ሁሉ የሱዳን እና የአረብ አገር ስደተኛ ይሆናሉ።በበረሃ ያልቃሉ።የቀሩት እስር ቤት ገብተው ይማቅቃሉ።የአንድ ጎጥ ፖለቲካ በባሰ ፋሽሽታዊ መልኩ ይቀጥላል።ትግሉ ግን አይቆምም።የጎጥ በደል የደረሰበት ሕዝብ ደግሞ በማንኛውም መልኩ በደሉ የመንግስት ብቻ ሳይሆን የአንድ አካባቢ ሕዝብ መሆኑን አምኖ ባገኘበት ቦታ ሁሉ ጥቃቱን ይፈፅማል።በእየቦታው በማናቸውም ጊዜ እና ሰዓት ለምሳሌ በስፖርት ውድድር፣ሆቴል፣ ሆስፒታል ሁሉ ሕዝብ አመፁን በመግደል ሊያሳይ ይችላል።

አማራጭ ሁለት  

አማራጭ ሁለት በስሩ ሶስት ክፍሎች ይዟል።ይሄውም ወያኔ በሕዝቡ ላይ የጀመረውን ወታደራዊ ዘመቻ ሲቀጥል የሚከተሉት ሶስት ሁኔታዎች ውስጥ አንዱ ሊከሰት  ይችላል። ወደድንም ጠላንም እነኝህ ሁኔታዎች በአጭር (በጥቂት ቀናት እስከ ጥቅምት)  ወይንም በመካከለኛ ጊዜ (እስከ የካቲት፣2009 ዓም ) ይፈጠራሉ ብሎ ማሰብ ይቻላላ።

እነርሱም -

1ኛ/ በጦር ሰራዊቱ ውስጥ ትግሪኛ ተናጋሪ ያልሆነው እራሱን ከእነ መሳርያው ይለያል።በአንዱ የአገራችን ክፍል ተቆርጦ ባለበት ይታኮሳል።አንዳንድ ቦታዎች ላይ የጎበዝ አለቃውን  ከበታች መኮንኖች መርጦ እረዘም ላለ ጊዜ ይዋጋል።ምናልባትም ሕዝብ እየተቀላቀለው የሚሄድ ያልታወቀ አለቃ ሊነሳ ይችላል። ይህ በአፍሪካ የተለመደ ነው።

2ኛ/ በሰሞኑ ሰልፍ የተሳተፈው ወጣት ተመልሶ እቤቱ ቢገባ ወያኔ እንደሚያደርገው እንደሚታፈስ ስለሚያውቅ ያለውን መሳርያ ይዞ ወደ ገጠሩ ክፍል ይገባል። ለእለት የሚሆነውን ከወያኔ ካምዮኞች ላይ እየዘረፈ አንዳንዴም ወደ ከተማ የተቀናበረ ዘመቻ እያደረገ ወያኔን መቆምያ መቀመጫ ያሳጣል። ይህ ሁኔታ በተደራጀ መልኩ ማለትም በፖለቲካ ኃይሎች አደረጃጀት ከታገዘ አጠቃላይ ለውጥ በኢትዮጵያ ያመጣል።የሰው ሕይወት እና የንብረት አደጋ ማጥፋቱ አይቀርም።በአዲስ አበባም በማናቸውም ሰዓት በህወሓት ባለስልጣናት ላይ ጥቃት ሊፈፅም ይችላል። 

3ኛ/ ሁኔታዎች ከእጃቸው መውጣቱን የተረዱት ወያኔዎች በግብፅ እንደተደረገው ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት (በጀነራል ፃድቃን ሃሳብ መሰረት) አንድ ቀን ማለዳ የተወሰኑ የህወሓት ባለስልጣናት መታሰራቸውን ይነግሩን እና የፖለቲካ ኃይሎች ለውይይት ይምጡ ሊሉ ይችላሉ።ይህ ለህወሓት ሁለት ጥቅም አለው።አንዱ  የዘረፉትን ንብረት እንደማይወሰድባቸው ዋስትና ከመጪው ወታደራቸው ያገኛሉ።ሁለተኛ በተዘዋዋሪ የተቃውሞውን ጎማ ሽክርክሪት ያበርዱበት እና ከአንድ እና ሁለት ዓመት በኃላ መልሰው የህወሓት አስተዳደርን ቀለም ቀብተው አግባብተው ይመልሱታል።

መፍትሄው 

ፀረ ወያኔ ትግሉ መቆም የለበትም።ከላይ የጠቀስኩት ሁሉ ከመምጣቱ በፊት የትግራይ ኤሊት ህወሓት የሚሄድበት መንገድ ትክክል አለመሆኑን በግልፅ  ተረድቶ የትግሉ አካል መሆን ብቸኛ አማራጩ ነው።ኤሊቱ ወደ እዚህ ትግል በግልፅ መግባቱ ለጊዜው የሚያሳጣው ነገር ያለ ይመስለዋል። ሆኖም ከተወሰነ ጊዜ በኃላ የሚያጣው የከፋ እና ለብዙ አመታት ቁስል ጥሎ የሚሄድ ነው እና አያዋጣም።ይህንን የትግራይ ኤሊት አያደርገውም ምቾት ቀጠና (comfort zone) ስለሆነ መንቀሳቀስ አይፈልግም የሚሉ ብዙዎች አሉ።ነገሩ አያሳምንም ማለት አይቻልም።

ከእዚህ በተለየ ግን የኢትዮጵያ ሕዝብ በሰላማዊ መንገድ ምርጫ ተሳተፈ ውጤቱ ድምፁ ተነጠቀ።ሰላማዊ ሰልፍ ፍቀዱልኝ አለ።ምላሹ ዱላ ሆነ።በኃይል ተነስቶ እጁን እያጣመረ  በቃኝ አለ።በምላሹ በጥይት ተገደለ።አሁን ደግሞ በታንክ እየዘመቱበት ነው።ስለሆነም ከእዚህ በኃላ የሽምቅ ውግያ በየትኛውም ቦታ ቢደረግ ተጠያቂው ህወሓት እና አይዞህ ባዮቹ ብቻ ናቸው።እንደ እኔ አስተያየት ከላይ ከጠቀስኩት ውጭ ታምር ይፈጠራል ብዬ አላስብም። እርግጥ ነው ከላይ የተፃፉት ስፃፉ እንጂ ሆነው ስናያቸው ታምር መሆናቸው አይቀርም።መሆናቸው ግን አይቀርም።


ጉዳያችን GUDAYACHN 

 www.gudayachn.com

No comments:

ወቅታዊ የዓለም ሁኔታ እንድንነታረክ ዕድል የሚሰጥ አይደለም።ብንነቃ መልካም ነው።

========== ጉዳያችን ወቅታዊ ========== የዓለም ታሪክ እንደሚያስተምረን ዓለም በወሳኝ የእጥፋት(turning point) ታሪኮች ውስጥ አልፋለች። እነኝህ የእጥፋት ጊዜዎች የዋዛና የፈዛዛ ጊዜ አይደሉም።መላው ዓለ...