ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Monday, August 8, 2016

''ሸዋ ባላመጠ ባመቱ ይውጣል'' ጀግናው የመርሐቤቴ፣መንዝ፣ምንጃር፣እና ይፋት ሕዝብ ለነፃነትህ ተነስ!

መርሃቤቴ ዋና ከተማ ዓለም ከተማ 

''ሸዋ ባላመጠ ባመቱ ይውጣል'' የምትል አባባል አለች።የሸዋ ሰው አንድን ነገር ለእረጅም ጊዜ በሚገባ ከመረመረ በኃላ ለተግባር ይነሳል ማለት ነው።ሃያ አምስት ዓመታት ለማላመጥ ከበቂ በላይ ነው። 

ህወሓት የዋልጌ ግለሰቦች ስብስብ ነው።ህወሓት ኢትዮጵያን ለባዕዳን የሸጡ ወንጀለኞች አባላት ያሉበት ነው።ህወሓት ከናዚዎች የተቀዳ የዘር ፖለቲካ ይዞ የሚንቀሳቀስ የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የአፍሪካ ነቀርሳ ነው። በህወሓት ውስጥ የተሰባሰቡ ግለሰቦች እና በጎጥ ገመድ ተተብትበው የሚያሽቃብጡ ሁሉ ቂም አርግዘው ቂም የሚተፉ ያለንበትን ዘመን የማይመጥኑ እጅግ ያረጀ አስተሳሰብ ይዘው የምንገታገቱ የከንቱዎች ስብስብ ነው። ህወሓት ከመነሻው አላማው ኢትዮጵያን መከፋፈል መሆኑን ያልተረዱ በደርግ ላይ ጥላቻ ያደረባቸው የኢትዮጵያን ልጆች ደም እግሩን እያጨቀየ በደማቸው ላይ  በእግሩ ተረማምዶ አራት ኪሎ ቤተ መንግስት የገባ እና በኃላ ሰማዕታቱን የከዳ የከሃዲዎች ጥርቅም ነው። ይህ ቡድን ከስልጣን መውረድ አለበት።በትዕቢት የተወጠሩ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የሚደነፉ አድር ባዮቻቸውም ካለ ችሎታቸው ከተንጠላጠሉበት በሕዝብ አጥንት የተገነባ ስልጣናቸው በሕዝብ ኃይል መውረድ አለባቸው። 

ጀግናው የኦሮሞ፣የጎንደር፣ጎጃም እና አዲስ አበባ ሕዝብ ባሳለፍነው ሳምንት ወያኔ በቃ! ብሏል።ካለፈ ያልተማረው  ህወሓት ባዶ እጃቸውን በተሰለፉ ኢትዮጵያውያን ላይ ከመትረጌስ እስከ ከባድ መሳርያ ድረስ በመተኮስ ባለፉት ሰባ ሁለት ሰዓታት ብቻ ከስልሳ በላይ ንፁሃንን ገድሏል።ወያኔ እና አድር ባዮቹ ይህ ሁሉ እልቂት በምፈፀምበት ሰዓት የትግራይ ምክትል ፕሬዝዳንት በተገኙበት ዋሽንግተን ላይ  ውስኪ እየተራጩ ሲጨፍሩ ተመልክተናል።ይህ ብቻ አይደለም የኢትዮጵያ ሕዝብ ያነሳውን ወያኔ ስልጣኑን ይልቀቅ የሚለውን ፍፁም ሕጋዊ ጥያቄ እንደ ትልቅ ድፍረት ቆጥረውት በንፁሃን ላይ የሚፈፀመውን ግድያ ፍትሃዊ አስመስለው ሲናገሩ መስማት የነፃነት ትግሉ ማንን ቀድሞ ማስተማር እንዳለበት ሁኔታውን ግልፅ ያደርገዋል።

የሰሜን ሸዋ ሕዝብ እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ በወያኔ ያልተፈፀመበት የግፍ አይነት የለም።ከመርሃቤቴ ዋና ከተማ የዓለም ከተማ እስከ ደብረ ብርሃን ከተሞች እና የገጠር መንደሮች ሁሉ ህወሓት የፈፀመው ግፍ  ምን ጊዜም የሚረሳ አይደለም። በሰሜን ሸዋ ካራ ምችግ በ1982 እና 83 ዓም በዓለም ከተማ የ1997 ዓም ምርጫ ተከትሎ በወጣቶች ላይ ግድያ ተፈፅሟል።በተለይ በዓለም ከተማ በጠራራ ፀሐይ በሕወሃቱ ሹም ሕዝብ በአደባባይ እንዲሰበሰብ አድርጎ በአደባባይ በግል ሽጉጡ የተገደሉት የሁለቱ ወጣቶች ደም አሁንም በዓለም ከተማ የፍትህ ያለህ እያለ ነው። የሰሜን ሸዋ ሕዝብ ከአጎራባቹ የኦሮሞ ማኅበረሰብ ጋር በፍቅር ለአመታት ይኖረ ሆኖ ሳለ ወያኔ ለማጣላት ያልሸረበው ተንኮል አልነበረም። ሆኖም ግን ሊሳካለት አልቻለም።አሁን ወቅቱ ያለፈውን እያነሳን የምንቆዝምበት ወቅት አይደለም።ከኢትዮጵያ ሕዝብ  ጋር ወያኔን በቃ! የምንልበት  ወሳኝ ጊዜ ነው። ሃያ አምስት ዓመት ማላመጥ ይበቃል! ''ሸዋ ባላመጠ ባመቱ ይውጣል'' ጀግናው የመርሐቤቴ፣መንዝ፣ምንጃር፣ዋግኅምራ እና ይፋት ለነፃነትህ ተነስ!

''ልቤ ነው ፍትህ የሻተው
ና! ቶሎ ዳኘው ዳኘው።
ስጠው ፍርዱን ስጠው፣
ችሎቱ ያንተው ነው።''


ጉዳያችን GUDAYACHN www.gudayachn.com

No comments:

ወቅታዊ የዓለም ሁኔታ እንድንነታረክ ዕድል የሚሰጥ አይደለም።ብንነቃ መልካም ነው።

========== ጉዳያችን ወቅታዊ ========== የዓለም ታሪክ እንደሚያስተምረን ዓለም በወሳኝ የእጥፋት(turning point) ታሪኮች ውስጥ አልፋለች። እነኝህ የእጥፋት ጊዜዎች የዋዛና የፈዛዛ ጊዜ አይደሉም።መላው ዓለ...