አትሌት ፈይሳ ለሊሳ ሪዮ ላይ ታሪክ ሲሰራ።
ዛሬ ነሐሴ 15፣2008 ዓም ኢትዮጵያ ጭንቀት ላይ ነበረች።የህወሓት አጋዚ ወታደሮች ከጎንደር እስከ ባሌ፣ከባህርዳር እስከ አርሲ በመቶ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን ሕይወት በሕዝብ ገንዘብ በተገዛ ጥይት ሕዝቡን ሲፈጁት ከርመዋል። በሁለተኛው የዓለም ጦርንነት ወቅት አይሁዶችን ጀርመኞች እንደሚያጉሩት በትግራውነታቸው የምመፃደቁት ህወሓቶች በሺህ የሚቆጠሩ የአማራ እና ኦሮሞ ወጣቶችን በኢየቦታው አጉረዋል።ይህ ሁኔታ ያሳሰባቸው ኢትዮጵያን አክትቪስቶች በአዲስ አበባ በገዢው ህወሓት ላይ ሰልፍ እንደሚደረግ ገለፁ።ከቅዳሜ ምሽት ጀምሮ ግን የህወሓት ወታደሮች የአዲስ አበባ ወጣት በተኛበት እየያዙ ወደ እስር ቤት ወሰዱት።እናቶች እያለቀሱ ልጆቻቸውን እያዳፉ ወደ እስር ቤት ወሰዷቸው።ምሽት ላይ እና እሁድ ጧት ለቤተ ክርስቲያን ቅዳሴ የሚሄዱ ካህናት ሳይቀሩ ሲፈተሹ አረፈዱ።የአዲስ አበባ ዋና ዋና መንገዶች እና መንደሮች ሁሉ በአጋዚ ወታደሮች ተትለቀለቁ።መስቀል አደባባይ በከባድ የጦር ካሚዮኖች አጠረው።የተጠራው ሰላማዊ ሰልፍ እንጂ ጦርንት አይደለም በሚል ኢትዮጵያውያን ህወሓት ካለ ጦርነት ሰላም የሚባል ቃል እንደማታውቅ ደግመው አረጋገጡ።
ይህ ሁሉ በሆነበት ወቅት ነበር።በብራዚሏ ከተማ ሪዮ ዲጀነሮ የሚደረገው የ2016 እኤአቆጣጠር ኦሎምፒክ ላይ በማራቶን የሚወዳደረው አትሌት ፈይሳ ለሊሳ 42 ኪሎ ሜትሩን ማራቶን 2ኛ ሆኖ በመጨረስ የብር ሜዳልያ ማሸነፉን ባረጋገጠበት ቅፅበት የኢትዮጵያንን በዘረኛው እና አምባገነኑ ህወሓት መረገጥ በቀጥታ ቴሌቭዥን ከ3 ቢልዮን በላይ ሕዝብ የሚመልከተው ስርጭት ላይ ለዓለም አጋለጠ። ህወሓት ከጎሳው ውጭ ለሆኑ ኢትዮጵያውያን ላይ የሚፈፅመውን ግፍ ለመላው ዓለም ነገረው።አዲስ አበባ ላይ ታንክ ደግነው በቴሌቭዥን ህዝቡ ተስማምተነዋል እያሉ ሲሳለቁ ለነበሩ አረመኔዎች በሳሎናቸው ሶፋ ፊት ለፊት ባለው ቲቪ ፊት ለዓለም አጋለጣቸው።በልጆቻቸው፣ቤተሰባቸው ፊት አረመኔነታቸውን ነገራቸው። ቃል አቀባዩ አቶ ጌታቸው ''አሁን የምሳ ሰዓት ደረሰ''እያሉ በአዲስ አበባ ወጣት ላይ እንዳልተሳለቁ ምሳ በልተው እራት ሳይደግሙ በዓለም ፊት ከጀርመኑ ናዚ የማያንሱ መሆናቸውን ነገራቸው።
አትሌት ፈይሳ ከኦሎምፒክ ሜዳ በኃላ በጋዜጣዊ መግለጫው መድረክ ላይም በደላችንን አሰምቷል።
በኦሎምፒክ አደባባይ ዘረኛ መንግስት ማጋለጥ ትልቅ መልዕክት ያለው ብቻ ሳይሆን ቀጣይ መዘዝ ለወያኔ ይዞ ይመጣል። ጋዜጠኛ ካሳሁን ይልማ የእዚህ አይነቱ ተግባር ከእዚህ በፊት በኦሎምፒክ አደባባይ መደረጉን እና ውጤቱን በፌስ ቡክ ገፁ ላይ የጠቀሰውን እንደሚከተለው አስቀምጠዋለሁ።
''አሜሪካዊያን አትሌቶች ጆን ካርሎስ እና ቶሚ ስሚዝ በ1968ቱ የሜክሲኮ ኦሊምፒክ በ200 ሜትር ሩጫ ውድድር የወረቅ የብር እና የነሐስ ሜዳሊያ ካሸነፉ በኋላ ባገኙት ድል መፈንጠዝ ሳይሆን በቆዳ ቀለም ልዩነት ብቻ በጥቁር ሕዝብ ላይ የሚፈጸመውን ጭቆና እና ዘረኝነት በመቃወም ጥቁር ጓንት አጥልቀው እጃቸውን ወደላይ ከፍ በማድረግ የጥቁር ኃይል ምልክትን አሳይተዋል። የለበሱት ጃኬት ላይ የሰብአዊ መብት ባጅ ለጥፈዋል። ጫማቸውን አውልቀው ጓንት ባለደረጉት እጃቸው ይዘዋል።
ከዚያ በኋላ በኦሊምፒክ ኮሚቴ እና በተለያዩ አካላት ከፍተኛ የትችት ውርጅብኝ ወርዶባቸዋል። ከናዚ ሰላምታ ጋር አመሳስለው እንዲሸማቀቁ የሞከሩ ሁሉ ነበሩ። ከአሜሪካ ቡድን እንዲገለሉ ቅጣት ተጥሎባቸዋል።ሆኖም ሁለቱ እንቁ አትሌቶች በዓላማቸው ጸንተው ተምሳሌት ሆነው ዛሬ ድረስ ይወሳሉ። በሳንሆዜ ዩኒቨርሲቲ የድል ሰላምታ ተብሎ ሐውልት ቆሞላቸዋል።የነርሱ ለእውነት መቆም ከሺህ ሰላማዊ ሰልፍ በላይ ለጥቁሮች መብት የሚያስፈልገውን መልዕክት ለዓለም አስተላልፏል። ከጎናቸው የቆመው ለህሊናው ያደረውና የወቅቱን የጥቁሮች ጭቆና የተገነዘበው ነጩ አውስትራሊያዊ ፒተር ኖርማን የብር ሜዳሊያውን ሲያጠልቅ የሁለቱ አትሌቶችን ዓላማ በመጋራት የሰብአዊ መብት ምልክት የሆነውን ባጅ ደረቱ ላይ አኑሮ አጋርነቱን አሳይቷል።
ነጭ ቢሆንም የነጮችን ዐይን ያወጣ በደል፣ ጭቆና፣ ዘረኝነት፣ አድልዎ...ተረድቷል።ትግሬ በመሆናቸው የሌላው መረገጥ መሰደድ መገደል የሚያስደስታቸው ህወሓትን የሚደግፉ ሰዎች ስለ ሌሊሳ ምን ይሉ ይሆን?"እዚህ ሀገር አይገባትም፣ ተመልሶ ከመጣ ደግሞ ይገባታል፣ ይኼ ኦነግ...ከልቢ..." ምን እያሰባችሁ ነው?እኛስ ለሌሊሳ የክብር ሐውልት በልባችን ተክለናል። ነፃነት በምታገኘው ኢትዮጵያም ለትውልድ ትምህርት የሚሆን ሐውልት ይቆምለታል።'' የጋዜጠኛ ካሳሁን ፅሁፍ መጨረሻ።
ነጭ ቢሆንም የነጮችን ዐይን ያወጣ በደል፣ ጭቆና፣ ዘረኝነት፣ አድልዎ...ተረድቷል።ትግሬ በመሆናቸው የሌላው መረገጥ መሰደድ መገደል የሚያስደስታቸው ህወሓትን የሚደግፉ ሰዎች ስለ ሌሊሳ ምን ይሉ ይሆን?"እዚህ ሀገር አይገባትም፣ ተመልሶ ከመጣ ደግሞ ይገባታል፣ ይኼ ኦነግ...ከልቢ..." ምን እያሰባችሁ ነው?እኛስ ለሌሊሳ የክብር ሐውልት በልባችን ተክለናል። ነፃነት በምታገኘው ኢትዮጵያም ለትውልድ ትምህርት የሚሆን ሐውልት ይቆምለታል።'' የጋዜጠኛ ካሳሁን ፅሁፍ መጨረሻ።
ወያኔ ዘረኛ መሆኑን ከአይሮፕላን አብራሪ ካፕቴን ገብረመድህን እስከ የአልጋ ላይ ቁራኛ ሀብታሙ አያሌው የመሰከሩት ነው።ፈይሳን የአዕምሮ በሽተኛ ነው እንዳትሉ ጤናው በዓለም አቀፍ ደረጃ ተመርምሯል።እረስታችሁ እንዳትሉ ብዬ ነው። ዛሬ ታሪካዊ ቀን ነው።ሪዮ ኦሎምፒክ ታሪክ ተሰራ! ሌሊሳ ስለ ሁሉ ተሰለፈ! ታሪክ የምለው ዝም ብዬ ለማዳነቅ አይደለም።ለልጅ ልጆቻችን ስለ ኦሎምፒክ እና ኢትዮጵያ ትምህርት ቤት ሲማሩ የፈይሳ ተጋድሎ ይወሳል።ሲቀጥል ኢትዮጵያ ወያኔ በሚባል ዘረኛ ቡድን ምን ያህል ተጨቁና እንደኖረች ይማራሉ።ታሪክ ማለት ይህ ነው።የቅርብ ጊዜው ታሪክ ግን የምናየው ነው።
ጉዳያችን GUDAYACHN
www.gudayachn.com
No comments:
Post a Comment