ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Wednesday, June 26, 2013

ሰበር ዜና - ሼህ ሁሴን ዳሄር አዌይስ ዛሬ ሰኔ 19/2005ዓም ተያዙ።Sheikh hassan dahir aweys captured

ሼህ ሁሴን ዳሄር አዌይስ (photo  FILE | NATION MEDIA GROUP)


ሼህ ሁሴን ዳሄር አዌይስ ቀንደኛ የሱማልያ ''አልሸባብ'' አመራር እና ''የእስላማዊ ፍርድቤቶች ህብረት'' መስራች ዛሬ ሰኔ 19/2005ዓም ተያዙ።

አዌይስ ''ኦጋዴንን ከኢትዮጵያ እገነጥላለሁ ''የሚለው እና በአዲስ አበባ፣በድሬዳዋ እና በጅጅጋ ለደረሱ ጥቃቶች ተጠያቂ የሆነውን ''አል-ኢታድ አል-ኢስላምያ'' በ 1990 ዎቹ ሲመራ የነበረ ግለሰብ መሆኑ ይታወቃል። 

በማከላዊ ሱማልያ የራስ ገዝ ግዛት በሆነችው በ ሂማን ግዛት እንደተያዙ የተነገርላቸው አዌይስ በ2011 ዓም በአሜሪካ መንግስት በቀንደኛ አሸባሪነት ዝርዝር ውስጥ የገቡ ናቸው።ግለሰቡ አሜሪካ እንደምትለው በታንዛንያ እና በኬንያ የአሜሪካ ኢምባሲ ለደረሰው ጥቃት ተጠያቂ የተደረገው ''አልቃይዳ'' ጋር ንክኪ እንዳላቸው በሰፊው ስትገልፅ የነበረ መሆኑ ይታወቃል።

በሐምሌ ወር 2006 ዓም እኤአቆጣጠር ዳሄር አዌይስ በኢትዮጵያ ላይ ''ጀሃድ'' ያሉትን ጦርነት ማወጃቸውን በራድዮ ሲለፍፉ ተደምጠዋል።በእዚሁ አመት በህዳር ወር ላይ '' 'ታላቂቱ ሱማልያ' የአፍሪካን ቀንድ በሙሉ መያዝ ይገባታል'' የሚል ቃል በራድዮ መናገራቸውም አይዘነጋም። ሼህ ሁሴን ዳሂር አዌይስ ጦርነት ያወጁባት ኢትዮጵያም እያየቻቸው  የአፍሪካ ቀንድን በሙሉ የመያዝ ሕልምም ሳይሳካ ዛሬ ተይዘዋል። የሱማልያ መንግስት አዌይስን የያዘችውን የራስገዝ ግዛቷን ሂማን አሳልፋ እንድትሰጥ አሳስቧል።ሼሁ በአሁኑ ጊዜ በሰባዎቹ እድሜ ውስጥ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል።
ዜናውን የአሜሪካ ድምፅ ራድዮን ጨምሮ የኬንያ የዜና ዘገባዎች ዘግበውታል።

Monday, June 24, 2013

''አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሰው አልገደለም።'' አቶ ኦባንግ ሜቶ (ቪድዮ)

በእስራኤል የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን አቶ ኦባንግ ሜቶ ''የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ'' (http://www.solidaritymovement.org) ሊቀመንበርን ንግግር እንዲያደርጉ ጋብዘው ነበር።''ኢትዮጵያን እናድን አንድነት ማህበር በእስራኤል'' በሚል ማኅበር ስር የተሰባሰቡት ወጣት ኢትዮጵያውያንን በከበረ ሰላምታ በማቅረብ ንግግራቸውን የጀመሩት ኦባንግ ''አቶ መለስ የሚነዳው ባቡር የጥላቻ ባቡር ነው.....አሁን ባቡሩ እየቆመ ነው'' ብለዋል።አቶ ኦባንግ ባለፈው ሳምንት የአሜሪካ ምክርቤት የውጭ ፖሊስ ንዑስ ኮሚቴ ቀርበው በተናገሩት ንግግር የብዙ ኢትዮጵያውያንን ልብ አኩርተዋል። አቶ ኦባንግ በአሜሪካ ምክርቤት ቀርበው ''እኛ አሜሪካኖችንን ነፃነት እንዲሰጡን አንለምንም ይህንን እኛ ማድረግ እንችላለን'' ነበር ያሉት።


አቶ ኦባንግ በእስራኤል ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ያደረጉት ንግግር ቪድዮ ይመልከቱ።



ጉዳያችን GUDAYACHNgetachewb221@gmail.com

Monday, June 17, 2013

የዘመናችን ስልቭያ ፓንክረስት- ፖርቱጋላዊቷ አና ጎሚዝ

አና ማርያ ሮሳ ማርቲንስ ጎሜዝ  ባጭሩ ሚስስ አና ጎሜዝ ይባላሉ።የካቲት 9፣1954 የፖርቱጋሏ ዋና ከተማ ሊዝበን  ውስጥ ተወለዱ። በ 2004 ዓም የአውሮፓ ህብረት ምክርቤት አባልነት የሀገራቸውን የሶሻሊስት ፓርቲ እንዲወክሉ ተመረጡ። ከእዛ በፊት ግን ሀገራቸውን በተባበሩት መንግሥታት በሚወክሉት ቆንስላዎች ውስጥ በኒውዮርክ እና በጀኔቭ እንዲሁም በቶክዮ እና በለንደን የፖርቱጋል ኢምባሲ ሀገራቸውን ወክለው አገልግለዋል።ይህ ብቻ አይደለም የፖርቱጋልንና የኢንዶነዥያንን የሻከረ ግንኙነት ሕይወት በመዝራት ይሞገሳሉ።

የሊዝበን ዩንቨርሲቲ የሕግ ምሩቅ የሆኑት አና ጎሜዝ ከአዚህ ሁሉ በኃላ አለምአቀፍ ልምድ እና ተሞክሮ በኃላ ነበር በ1997 ዓም በኢትዮጵያ የተደረገውን ምርጫ ለመታዘብ የአውሮፓ ህብረትን  ልዑክ በመምራት ወደ ኢትዮጵያ መጡ። አናጎሚዝ በወቅቱ በመንግስት የተወሰደውን የምርጫ ሸፍጥ ሲያነሱ አሁን ድረስ ያንገበግባቸዋል።ሲናገሩ ''ለምን ይዋሻል?'' የሚለው ስሜት ከውስጣቸው ሲፈነቅላቸው ይታያል። 

አንዳንዶች የምርጫውን ማጭበርበር ከጊዜ ብዛት እየለመድነው መጥተን  በውሸት መናደድ ወደማቆም የደረስን እንኖር ይሆናል።ለአና ጎሚዝ ግን ይህ ጉዳይ የህሊና እረፍት ነስቷቸዋል።እራሳቸውን እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ አድርገው ነው የሚናገሩት። ኢትዮጵያ አውሮፓውያን ለመብቷ የሚቆሙላት እናቶች አጥታ አታውቅም። እንግሊዛዊቷ ሲልቭያ ፓንክረስ (የርቻርድ ፓንክረስት እናት) በጣልያን ወረራ ዘመን በመላው አለም የኢትዮጵያ ድምፅ እንዲሰማ ሙሉ ግዝያቸውን የሰጡ ብቻ ሳይሆን ሞታቸው እና ቀብራቸውም ኢትዮጵያ (አራት ኪሎ ቅድስት ስላሴ ቤተ ክርስቲያን) ሆኗል። አና ጎሚዝ ፖርቱጋላዊ የዘመናችን ስልቭያ ፓንክረስት ሆነው ብቅ ብለዋል። በነገራችን ላይ አና ጎሚዝ ዛሬም ለኢትዮጵያ መጮሃቸውን አላቆሙም።በመጪው እረቡዕ  ሰኔ 12፣2005 ዓም በብራሰልስ፣ቤልጅየም ኢትዮጵያውያን በሚያደርጉት ሰልፍ ላይ ይገኛሉ።ኢትዮጵያን የወዱቱን ያብዛልን።

አና ጎሚዝ ስለ ፍትህ፣እውነት እና ዲሞክራሲ ይናገራሉ (ቪድዮ ይመልከቱ)
part 1

part 2 

Friday, June 14, 2013

''እነሱ ከአባቶቻቸው አይበልጡም እኛም ከአባቶቻችን አናንስም!!!'' ሰማያዊ ፓርቲ በአባይ ግድብ እና በግብፅ ዛቻ ላይ አቋሙን አሳወቀ።


ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ

ምንጭ- የሰማያዊ ፓርቲ ድህረ-ገፅ  http://www.semayawiparty.org/እነሱ%20ከአባቶቻቸው%20አይበልጡም%20እኛም%20ከአባቶቻችን%20አናንስም%21%21%21 
ግብፅ በኢትዮጵያ ላይ ወረራና ደባ መፈፀም የጀመረችው ኢትዮጵያ ዛሬ በአባይ ላይ ግድብ ለመስራት ከመነሳቷ እጅግ በርካታ አመታት በፊት ጀምሮ ነው፡፡ ሀገራችን ከግብፅም ሆነ ከሌሎች የተቃጣባትን ተደጋጋሚ ወረራዎች በመመከትና ጠላቶቿንም ድባቅ በመምታት ነፃነቷን ጠብቃ መኖሯ ለጠላቶቿ መራር የሆነ እውነት ነው፡፡ በተለይም ከጥንት ጀምሮ የአባይን ምንጭ ለመቆጣጠር ጥልቅ ምኞት የነበራት ግብፅ በሃገራችን ላይ የፈፀመችውን ግልፅና ድብቅ ወረራ በመመከት ተደጋጋሚ ሽንፈትን አከናንበን መልሰናታል፡፡
ሀገራችንን በጦር አውድማዎች ማሸነፍ እንደማትችል በቂ ትምህርት የወሰደችው ግብፅ ከቅርብና ሩቅ ታሪካዊ ጠላቶቻችን ጋር በማበር ዛሬ በኤርትራና በኢትዮጵያ በስልጣን ላይ የተቀመጡ አማፅያንን በማስታጠቅና ሁለንተናዊ ድጋፍ በመስጠት ኤርትራ ከኢትዮጵያ እንድትገነጠልና ኢትዮጵያም እንድትዳከም ከፍተኛ ደባ ፈፅማለች ፡፡ ግብፅ ይህን ሁሉ ግልፅ እና ስውር ደባ የምትፈፅመው ኢትዮጵያ በወንዞቿ መጠቀም የማትችል ደካማ ሐገር እንድትሆን ለማድረግ ነው፡፡ ይህ ጥረቷ ግን ደካማ ኢትዮጵያን ለመፍጠር ከመሞከሯ ውጭ የምኞቷን ያህል አልተሳካላትም፡፡ ቢሆንም እኛን ኢትዮጵውያንን እርስ በእርሳችን በማናከስ በጦርነትና በክፍፍል ተጠምደን ወንዞቻችንን የመጠቀም አቅም በማሳጣት ለዘለዓለም ብቸኛ ተጠቃሚ ሆና መኖር ትፈልጋለች፡፡ ይህ ካልተሳካላት ቀጥተኛ ወረራ በመፈፀም የወንዞቻችን ምንጮች ለመቆጣጠር እንደምትመኝ የየዘመናት ሙከራዎቿ ያረጋግጣሉ፡፡
ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ የጀመረችውን ግድብ አስመልክቶ ሰሞኑን ከግብፅ በኩል የሚሰማው ዛቻና ማስፈራሪያም ከላይ የተገለፁት እውነታዎች ነፀብራቅ ነው፡፡ በመሠረቱ በአባይ ወንዝ ላይ የተጀመረው ግድብ ከሐገራዊ ጠቀሜታው ይልቅ የገዥውን ፓርቲ የስልጣን እድሜ ለማራዘም የታለመና ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ የሚደለቅ ከበሮ መሆኑን ፓርቲያችን ይገነዘባል፡፡ የግድቡ ሥራ የገዥውን ፓርቲ የተለየ አሣቢነትና ተቆርቋሪነት የሚያሳይ አድርጎ ለማቅረብ የሚደረገው ልፈፋ ከተራ ጩኸት በዘለለ የዜጎችን ልብ የሚያማልል አይደለም፡፡ በአንፃሩ ከገዥው ፓርቲ አመለካከት ውጭ ያሉ ዜጎችን የግድቡ ሥራ የማይመለከታቸው አድርጎ ለማቅረብ የሚደረገው የወሬ ክምር ልብን የሚሰብር ርካሽ ፕሮፓጋንዳ ነው፡፡ በመሆኑም ለኢትዮጵያ ክብርና ኩራት መሠዋት ለዜጎችም ጥቅም መጠበቅ እነማን ምን እንደከፈሉና እንደሚያስቡ ለታሪክ በመተው ሃገርን መክዳትና መጥላትን በሌሎች ላይ ለመለጠፍ የሚደረገው ሩጫ ግን እንዲታሰብበት እንመክራለን፡፡
የግድቡ ሥራ ከስም አወጣጥ ጀምሮ የፕሮጀክቱ አነዳደፍ፤ የፋይናንስ አሰባሰብ፣ ግንባታውን የሚያካሂዱ ድርጅቶች አመራረጥና ሌሎችም ጉዳዮች እጅግ ግልፅነት የጎደላቸውና ባለቤትነታቸውም ከኢትዮጵያ ህዝብ ተነጥቆ ለተወሰኑ ቡድኖች በተለይም ለገዥው ፓርቲ ፍላጎት ማሳኪያ እየዋለ መሆኑ ቀርቶ ሁሉንም ኢትዮጵያውያን በሚያስማማ ሁኔታ እንዲካሄድ ፓርቲያችን አጥብቆ ይጠይቃል፡፡
ሐገራችን ለሚያስፈልጋት ዓላማ ሁሉ በወንዞቿ መጠቀሟን በመቃወም በግብፅም ሆነ በሌላ በማንኛውም አካል የሚፈፀሙ ዛቻም ሆነ ሌሎች አሉታዊ ድርጊቶችን ፓርቲያችን አጥብቆ ያወግዛል፡፡ የሃገራችንን ጥቅም ለማስጠበቅም ማንኛውንም መሰዋዕትነት መክፈልን ከጀግኖች አባቶቻችን የወረስነው አኩሪ ታሪካችን በመሆኑ ይህን ቃል ኪዳን ማክበርና መጠበቅ የፓርቲያችን የፀና አቋም ነው፡፡
በመጨረሻም አሁን የተፈጠረው ውጥረት በውይይት እንዲፈታ የኢትዮጵያ መንግስት ጠንካራ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት እንዲያደርግ እያሳሰብን ነገር ግን ግብፅ ይህን አልቀበልም በማለት ፍላጎቷን በሃይል ለማስፈፀም የምትፈልግ ከሆነ የአባቶቻችንን ታሪካዊ አሸናፊነት የምንደግመው መሆኑን ከታሪክ እንድትማር ለማስታወስ እንገደዳለን፡፡
ሰኔ 7 ቀን 2005 ዓ.ም

በኢትዮጵያ ለኤርትራ ስደተኞች ተጨማሪ ሰባተኛ ካምፕ መክፈቱን የተባበሩት መንግሥታት ስደተኞች ኮሚሽን ገለፀ።

አለምአቀፉ የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ኮሚሽን ሰኔ 6፣2005 ዓም በድህረገፁ በለቀቀው ዜና በሰሜናዊ ኢትዮጵያ በኩል ከኤርትራ የሚሰደዱት ስደተኞች ቁጥር በመጨመሩ ሳብያ ተጨማሪ አዲስ ሰባተኛ የስደተኞች ካምፕ ለመክፈት መገደዱን ገልጧል።ድርጅቱ አራት ካምፕ በትግራይ ክልል እና ሁለት ደግሞ በአፋር ክልል መኖሩን ጠቅሷል። 

አዲሱ የስደተኞች ካምፕ እስከ 20 ሺህ ስደተኞችን መቀበል የሚችል ሲሆን ከመከፈቱ 776 ስደተኞች መግባታቸውንም ዜናው አክሏል።በሌላ በኩል ድርጅቱ እንደገለፀው  ከኤርትራ በኩል የሚሰደዱት ስደተኞች በትምህርት የገፉት፣ወጣቶች እና ለአቅመ አዳም እና ለአቅመ ሔዋን ያልደረሱት ሲሆኑ ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡበት 16 የመግቢያ መስመሮች መኖራቸውን ያወሳል።
በመጨረሻም በእዚህ አመት በወር እስከ 600 የሚደርሱ ስደተኞች እየመጡ ሲሆን ይህ ቁጥር ባለፈው አመት እስከ 2,000 ደርሶ እንደነበር እና የኤርትራ ስደተኞችን በማስተናገድ ላይ የሚገኙ ብዙ ሃገራት ቢሆኑም  ቁጥራቸው በሱዳን ብቻ ከ 114,500 በላይ ሲሆኑ ኢትዮጵያ በ አራት ካምፖች ትግራይ ውስጥ ብቻ 71,833 ስደተኞች ተጠልለው እንደሚገኙ ዘገባው አክሎ ይገልፃል።
የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኮሚሽን ሙሉ ዘገባ ጉዳያችን ጡመራ ላይ ያንብቡ።

Source- UNHCR June 13,2013

Eritrean refugees in Ethiopia get new camp in north of country

News Stories, 13 June 2013

© UNHCR/K.GebreEgziabher
At the Endabaguna reception centre in northern Ethiopia, Eritrean refugees board a bus for transfer to a new refugee camp at Hitsats. Most of the refugees are young men from cities rather than women and children.
HITSATS, Ethiopia, June 13 (UNHCR)  The UN refugee agency has opened a new camp in northern Ethiopia to house the increasing number of Eritrean refugees entering the country. A total 776 Eritrean refugees have already been transferred to Hitsats Camp, which can house up to 20,000 refugees.
"This is a big step forward in the protection of Eritrean refugees in this area," said Michael Owor, head of UNHCR's sub-office in Shire, which has erected 200 family tents and dug a communal well to handle the arrival of the new refugees at the camp on land provided by the Ethiopian government.
The government has also set up a temporary medical clinic and reception facilities for arriving refugees.
So far this year, UNHCR and the government's refugee agency, the Administration for Refugee and Returnee Affairs (ARRA), have registered more than 4,000 Eritrean refugees, overwhelming the capacity of the existing three camps in the region, which house nearly 49,000 refugees. A large number of the new arrivals are unaccompanied minors who require special protection.
What is unusual is that most of the Eritrean refugees fleeing to Ethiopia are young educated men from cities, unlike most refugee situations where the majority of refugees are women and children.
The predominance of young men is a pattern observed throughout the region, where Eritrean refugees tell UNHCR staff they are fleeing indefinite military service for both men and women.
In eastern Sudan, the UN refugee agency has also seen a significant number of children arriving on their own, but the number of refugee arrivals has dropped to between 400 and 600 per month this year from 2,000 a month in 2012. The total number of Eritrean refugees in Sudan is more than 114,500.
In Djibouti, arrivals are holding steady, at 112 for the first five months of this year, practically the same as the 110 Eritreans who arrived in the same period last year.
Eritrean refugees cross into Ethiopia through 16 entry points from which they are collected and brought to a reception station for screening and registration. Before departure from the reception centre, the refugees are issued with basic assistance items, including sleeping mats, blankets, jerry cans, water buckets, soap and mosquito nets. They are also provided with tents and food rations once they get to the new camp.
As of the end of May, Ethiopia is hosting 71,833 Eritrean refugees in four camps in Tigray region and two others in the Afar region in north-eastern Ethiopia. Transfers to the new camp are taking place every second day.

Tuesday, June 11, 2013

ይህች ሰበርም ጠቃሚም ዜና ነች

የግብፅ ተቃዋሚዎች ''ፕሬዝዳንት ሞሐመድ ሞሪስ የአባይን ጉዳይ የሚያነሱት የውስጥ ተቃውሞን ለማድበስበስ እና የህዝብ ድጋፍ ለማግኘት እየተጠቀሙበት ነው።'' አሉ። በግንቦት ወር ተቃዋሚዎች ፕሬዝዳንቱ ስልጣን እንዲለቁ የሚጠይቅ  15 ሚልዮን  ፊርማ ለማሰባሰብ አቅደው በግንቦት 29/2013 ዓም  እ.ኤ.አቆጣጠር ብቻ የ 7 ሚልዮን  ሕዝብ ፊርማ ማሰባሰብ ችለዋል። ለሰኔ 30፣2013 ዓም ተቃዋሚዎች ፕሬዝዳንቱ ስልጣን እንዲለቁ የሕዝብ ንቅናቄ ለመፍጠር ዝግጅት ላይ ናቸው። የዜናው ምንጭ ''አልሃራም ኦንላይን'' የግንቦት 11፣2013 ዓም ዘገባ።

ከግብፅ ተቃዋሚዎች ምን እንማራለን? የግብፅ ተቃዋሚዎች ሕዝቡን እውነታውን በመንገር መተኮር የሚገባበትን ዘለቄታዊውን እና ዋናውን ጉዳይ ከበቂ ትንተና ጋር አቅርበው አሳይተዋል።ብዥታም እንዲጠራ አቅጣጫም እንዲያዝ በሚነሱ ጉዳዮች ላይ በቂ ማብራርያ እና  አቅጣጫ እያስያዙ ነው።ይህ እጅግ አስተማሪ ጉዳይ ነው።

Morsi using Ethiopia dam crisis to boost popularity: ‘Rebel’
Opposition campaign group dismisses President Morsi's calls for unity over Ethiopia dam crisis, vows to launch mass protests on election anniversary
Ahram Online , Tuesday 11 Jun 2013
Rebel Campaign
Campaigners sign confidence-withdrawal forms (Photo: Al-Ahram Arabic-language news website)
The president's speech on Monday calling for "national reconciliation" over Nile dam issue is an effort to distract the people's attention from other problems, Badr added.The president should resign, Badr insisted.
'Rebel' campaign central committee member Mohamed Abdel-Aziz said,“Morsi and his people are worried. They fear the popular support of the Rebel campaign and our will to mobilise on 30 June to bring down the president.”
“Morsi is using the Nile water crisis to combat his loss of popularity, people’s anger towards him and the opposition’s boycott [of his calls for dialogue],” Abdel-Aziz added.
At a conference on Monday organised by Islamist forces to discuss the issue, Morsi said, "The country demands that we stand united."
The 'Rebel' campaign was launched in May to "withdraw confidence" from President Morsi by collecting 15 million signatures by the anniversary of his inauguration on 30 June, topping the number of votes he won in the election. The campaign announced on 29 May that it has collected seven million signatures.

Monday, June 10, 2013

ግልፅ በሆነው በአባይ ጂኦ-ፖለቲካዊ ጉዳይ መንግስትም ተቃዋሚዎችም ዝምታቸውን ያቁሙ!

 የአባይ ወንዝ  በግብፅ አፈር ላይ ሳተላይት ፎቶ(NASA)

ግብፆች  ከበሮ እየደለቁ ነው።ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬም ሲዝቱ ተሰምተዋል።ዝርዝሩ ቢያንስ ለእዚህ ማስታወሻ አይጠቅምም።የኢትዮጵያ ሕዝብ ግን መረጃው አይነገረውም።በአንድ ፓርቲ ስር ተሸብቦ በአባይ ሰበብ እበላሃለሁ እያለ የሚደነፋበትን ሀገር ጉዳይ እንዳይወያይ እድሉን አጥቷል።ሀገር የሚጠበቀው በአንድ ፓርቲ ብቻ አይደለም።ግልፅነት፣ነፃ የመረጃ ልውውጥ፣ወቅታዊ መረጃ ለሕዝቡ መስጠት ያስፈልጋል።መንግስት እና ተቃዋሚዎች ሊወያዩበት ሊነጋገሩበት የሚገባ አጀንዳ አባይ ካልሆነ ምን ሊሆን ይችላል? ባለፉት ሶስቱም መንግሥታት ውስጥ በአፄ ሃይለስላሴ፣በደርግ እና በኢህአዲግ የሚያስማማ ጉዳይ የአባይ ጉዳይ ነው።አባይ መገደብ እንዳለበት ሁሉም መንግሥታት ያምኑ ነበር።ይህ ከፊት ለፊት የተቀመጠ ሀቅ ነው። ኢህአዲግ ደርግ የጀመረውን ''የጣና በለስ'' ፕሮጀክት ለእርድ ቢያቀርበውም ቅሉ።

በአንድ በኩል ኢህአዲግ ''ግብፅ ልትዋጋ አትችልም'' ሲል በሌላ በኩል  ተቃዋሚዎች ''ኢህአዲግም ሆነ ግብፆች የውስጥ ችግራቸውን ለማስቀየር የሚጠቀሙበት ስልት ነው ሲሉ'' ስናደምጥ ይሄው የግብፅ ፉከራ አንድ ሳምንት ዘለቀ።ይህ ጉዳይ የሚያሳየው አንገብጋቢ በሆነ በሀገራችን ጉዳይም ኢቲቪ  ህዝብን እንደማያወያይ አንድምሁር ለመጠየቅም የቻለ ወይም የተፈቀደለት ልበለው ሪፖርተር ጋዜጣ  ብቻ መሆኑን ነው። እኛ በሀገራችን ጉዳይ በሀገር ቤት ሚድያ ለምንድነው እንድንወያይ የማይደረገው? ግብፆች ኢቲቪም  ሆነ አራት ኪሎ  ውስጥ አሉ እንዴ? ነው ወይስ ጅብ እግሬን ሲቆረጥም ''አመመኝ'' ማለት ያለብኝ ኢቲቪ ወይንም መንግስት ሲፈቅድልኝ ብቻ ነው?

ተቃዋሚዎችስ የግብፅ እና የአባይ ጉዳይ ለዘመናት የታወቀ ጉዳይ መሆኑ እየታወቀ።ብዙ ጥራዝ የሚወጣቸው ፅሁፎች ቢሮዎቻቸውን አጣበውት ''ችግር የለውም ጉዳዩ መንግሥታቱ  ከውስጥ ለሚነሳባቸው ተቃውሞ አቅጣጫ  ማስቀየርያ ነው'' እያሉ ከሚነግሩን ጉዳዩን እንዴት እንደሚያዩት፣ ለሀገር ያለውን አደጋ፣ሕዝብ ምን ማድረግ እንዳለበት ከእነመፍትሄው ማቅረብ ይገባቸዋል። ለግንቦት 20 በዓል አስመልክተው የተቃውሞ መግለጫ የሚያወጡ የተቃዋሚ ድርጅቶች እንዴት ይህን ትልቅ አካባቢያዊ ፣ሃገራዊ እና አለማቀፋዊ  ጉዳይ ላይ  ለሕዝቡ ያልተደናበረ አቅጣጫ አመላካች ሃሳብ መስጠት ያቅታቸዋል? እኔ በግሌ ይህ ጉዳይ  በጣም የሚያም  እንደሆነ ይሰማኛል።የብዙ ነገሮችም አመላካችም ነው።እንደምንኖርበት ጅኦ-ፖለቲካዊ አቀማመጥ ከእዚህ በዘለለ ብዙ ችግሮች ወደፊት ሊገጥሙን ይችላሉ። የምኖርበት አለም ተለዋዋጭ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ በእራሱ ፈጣን ግን ትክክለኛ ውሳኔ  ከፖለቲካ ድርጅት የሚጠበቅ ነው።የመፍትሄ ሀሳቦችም በእዚሁ ፍጥነት መሰጠት ይገባቸዋል።

የአባይ ጉዳይም ምንም አይነት ውስብስብ ገፅታ ቢሰጠውም ሕዝብ ግን የኢህአዲግ መንግስት ከህዝብ ጋር የተራራቀበትን ጉዳይ ሁሉ ከጥገናዊ ለውጥ በዘለለ መሰረታዊ ለውጥ አድርጎ ያለፈ ስህተትን የሚያርምበት የመጨረሻውን  መጨረሻ ዕድልን ሊጠቀምበት ይገባል እያለ ነው።ተቃዋሚዎችም 'ሰላሳ ትንንሽ ከመሆን አንድ ትልቅ መሆን' ከእዚህ ባለፈም የግብፅን ጉዳይ በተመለከተ ቢያንስ የመፍትሄ የሚሆን ሃሳብ  ማመንጨት እና ሕዝብ ሊይዘው የሚገባውንም አቅጣጫ ማመላከት ያላቸው ብቸኛ መንገድ ይመስለኛል።

እርግጥ ነው የግብፁ ፕሬዝዳንት ሞሐመድ ሞሪስ ተቃዋሚዎችን ሰብስበው ሲነጋገሩ ኢህአዲግ ግን ገና አፉ ሲተሳሰር መታየቱ ከውስጡ ትክክለኛ ጊዜ ላይ አስፈላጊ መፍትሄ መስጠት በማይችሉ አመራር መሞላቱን ያሳያል።በግትርነት የተመራ ሀገር የለም። ህዝብንም ሀገርንም ይዞ ለመጥፋት ካልታሰበ በቀር። ችግሩ ገፍቶ ሲመጣ ሕዝብ እግር ስር ወድቆ መማፀን ላይቀር ዛሬ ከመረጃም ከመፍትሄም እርቆ መቀመጥ ለመንግሥትም ለሀገራችንም  አያዋጣም። 

ዝምታው ይሰበር።ብሔራዊ ሉአላዊነታችን  አደጋ ላይ የሚወድቅባቸው ብዙ እንቅፋቶች ተዘርግተው ይታያሉ። እነኝህ እንቅፋቶች ሊ ነቀሱ የሚችሉት ወሳኝ በሆነ ለውጥ ነው።የግድቡ የገንዘብ ማሰባሰብ ሥራ በተለያዩ ሃገራት የገጠመው ተቃውሞ በግብፃውያን አይደለም። በኢትዮጵያውያን ነው። ኢትዮጵያውያን የሚጠይቁት ጥያቄዎች ደግም ይታወቃሉ።የሚገርመው ነገር ኢህአዲግ  ይህን ፅሁፍ በፃፍኩበት ቀን (ግብፅ ያዙኝ ልቀቁኝ በምትልበት ቀን) በካናዳዋ ከተማ ካልጋሪ  ላይ በተመሳሳይ መንገድ የገቢ ማሰባሰብያ መርሃግብር  ተሞክሮ መክሸፉ እየተነገረ ነው።መንግስት ''የኔ'' የሚላቸው ሰዎችን በእየ ሆቴሉ እየሰበሰበ የተቀረው የእንጀራ ልጅ ይመስል እየተገፋ በሚዋጣ ገንዘብ አይሰራም።ሁሉም ከልብ በመነጨ ስሜት ሊሳተፍበት ይገባል።ይህንን ለማድረግ ደግሞ መንግስት የተጠየቀውን ''ከድብብቆሽ ለውጥ'' በዘለለ መመለስ ሲችል ነው። ግድቡ በመንግስት ዘንድ  ከልብ ከታሰበበት ለምን ቢያንስ በሕዝብ የተነሱት ጥያቄዎች አይመለሱም? ለምን ነገ የጦርነት ድግሱ በር ላይ ሲደርስ  እግሩ ስር ወድቆ መንግስት አድነኝ ብሎ የሚማፀነውን ሕዝብ ጥያቄ ከወዲሁ መፍትሄ አይሰጠውም?
 
ጦርነት የለም የሚለው ጭፍን ድምዳሜ ለመድረስ ድፍረት የለኝም።ግብፅን ቢያንስ ኢትዮጵያን እንድታዳክም በሞራልም ሆነ በማተርያል የሚደግፉ ጠላቶች እንዳሉን ለማወቅ ብዙ መመራመር አይጠበቅም። አልጀዚራ ግብፅ ውስጥ የነበረውን የኢትዮጵያውያንን በተባበሩት መንግሥታት በር ላይ ያደረጉትን ሰልፍ እንዴት አድርጎ ሐረጋት መዞ ዜና እንደሰራበት ከተረዳን  ግብፅ አንዳንድ የአፍሪካ ቀንድን ለመቆጣጠር የዘመናት ሕልም የነበራቸውን  የመካከለኛ ምስራቅ ሃገራትን ማሰለፍ እንደምትችል ፍንጭ ይሰጠናል።

የአባይ ጉዳይ የዘመናት ቁስል ነው። ቀላል ነው ተብሎ እንደሚነገረው አይደለም።መንግሥታቱ የውስጥ ቅራኔዎችን ለማስታገስ ብለው ነው ብለን የምንዘብትበትም ጉዳይ አይደለም።ቢያንስ ጉዳዩ ዛሬ ባይሆን ነገም የማይለቀን ጉዳይ ነው።የዛሬው ትውልድ ውሳኔ የነገውም ዕድል ወይንም ፈተና መሆኑ አይቀርም።ዝምታ ግን ውርስ የለውም።ዝምታ መጨረሻው መፍትሄ ያልሆነ ግን መፍትሄ መሰል ነገር መወርወር ብቻ ይሆናል።ይህ ደግሞ በአሁኑ ትውልድ ላይ ብቻ ሳይሆን በመጭውም ትውልድ ላይ ለመፍረድ መደፋፈር ይሆናል።

አበቃሁ 
ጌታቸው 
ኦስሎ

መረጃ አይናቅም -ግብፅ በአባይ ጉዳይ ላይ ስትከተላቸው የነበሩት ሶስቱ ስልቶች (ስትራቴጂዎች) በአቶ መለስ ዜናዊ (ቪድዮ)





Saturday, June 8, 2013

የሰኔ 1፣1997 ዓም ሰማዕታት የተመለከተ ልዩ ጥናታዊ (ዶክመንተሪ) ፊልም በጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና

 ዛሬ ሰኔ 1 ነው።በዛሬዋ ዕለት 1997 ዓም በትንሹ ከአንድ መቶ ዘጠና ዘጠኝ ቤቶች በላይ ውስጥ አስከሬን የወጣበት ቀን በሺህ የሚቆጠሩ ዘመዶች፣ወዳጆች  ኢትዮጵያውያን   በሃዘን ሲያስቡ ይውላሉ።

ሕዝብ ጥያቄውን በሰላማዊ ሰልፍ ሲያቀርብ የጥይት አረር ለመለሱ መንግሥታትም ሆነ ትዛዙን ላስተላለፉ መሪዎች አለማችን ቦታ የላትም።
የግብፁ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ሁስኔ ሙባረክ አሁን ከተከሰሱበት ክስ መካከል አንዱ እና ዋናው በታህሪር አደባባይ ለተሰለፉት ሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ የኃይል እርምጃ በመውሰዳቸው ነው።በተመሳሳይ መንገድ ጎረቤት ሀገር ኬንያ ፕሬዝዳንቷ ጭምር በአለምአቀፍ ፍርድቤት ደረጃ ክስ የተመሰረተባቸው እ.አ.አቆጣጠር በ2007 ዓም የተካሄደውን  ምርጫ ተከትሎ በተነሳው ግጭት የኃይል እርምጃ እንዲወሰድ በመደረጉ ነው።

የሲሳይ አጌና የሰኔ 1፣1997 ዓም እልቂት የሚያስታውስ ልዩ ጥናታዊ (ዶክመንተሪ) ፊልም በኢትዮጵያ የዲሞክራሲ ጥያቄ ያነሱ ግን የጥይት አረር ሰለባ የሆኑ  ኢትዮጵያውያንን ታሪክ በትትክል ይዘግባል።ጉዳዩን መንግስት እራሱ በመሰረተው አጣሪ ኮሚሽን ያልተመጣጠነ እርምጃ መወሰዱን 8 ለ 2 ድምፅ ወስኖ ለምክርቤት ቢቀርብም የጉዳዩ ተዋናዮች ዛሬም ለፍርድ አልቀረቡም። 

ከአሁን በኃላ በሰላማዊ ሰልፍ ለሚጠየቁ ጥያቄዎች ተመሳሳይ ስህተት ለመስራት ሞራል ያለው ፖሊስም ሆነ ''የግደሉ'' ትዕዛዝ ለማስተላለፍ የሚደፋፈር  ባለስልጣን ባይኖረን እንመርጣለን።ለቀደመውም ተዋናይ የነበሩት ለፍርድ እንዲቀርቡ በሕይወት ያለነው መጠየቅ ባንችልም የሞቱት ግን ለፈጠራቸው አምላክ መጮሃቸው አይቆምም።ለሰማዕታቱ እረፍተ ነፍስን  ለቤተሰብ፣ለወዳጅ ዘመድ መፅናናትን ይስጥልን።





ጉዳያችን GUDAYACHNgetachewb221@gmail.com

Thursday, June 6, 2013

ከፍልጥ ፈሊጥ ይቅደም! የግብፅ እና የኢትዮጵያን ጉዳይ በተመለከተ (የጉዳያችን ጡመራ ማስታወሻ)

(የግብፅ ፕሬዝዳንት ከተቃዋሚዎቻቸው ጋር ያደረጉት ሚስጥራዊ የተባለ ግን  በቀጥታ በቴሌቭዥን  ይተላለፍ የነበረ ቪድዮ ከፅሁፉ መጨረሻ ይመልከቱ) 

የግብፁ ፕሬዝዳንት ሞሐመድ ሞርሲ ''የሳላፍስት ኑር'' ፓርቲ መሪ ዮንስ ማክሆን፣የሊበራል ፖሊቲካ ኮመንታተር አምር ሃምዛዊ  ያሳተፈ  ስብሰባ በኢትዮጵያ አባይ ግድብ ዙርያ ባለፈው ሰኞ(26/05/2005 ዓም) ስብሰባ አድርገው ነበር።በስብሰባው ላይ የብሔራዊ ሳልቨሽን ግንባር በፕሬዝዳንቱን ስብሰባ እንደማይገኝ የገለፀው ስብሰባው ግልፅነት እና ብዙም ውጤት የማይጠብቅበት መሆኑን በመግለፅ ነበር።


በሌላ በኩል የግብፅ ''የሙስሊም ወንድማማማቾች ነፃነት እና ፍትህ ፓርቲ'' መሪ ሞሐመድ  ኤልካታንቴ  ግንቦት 28፣2005ዓም ለአረብኛው ''አልሃራም'' ጋዜጣ እንደተናገሩት ''የግብፅን ሕዝብ ሳናማክር ወታደራዊ ግጭት ውስጥ ከኢትዮጵያ ጋር አንገባም'' ካሉ በኃላ ቀጥላ ግብፅ ስለምታደርገው ጉዳይ ሲናገሩ '' በመጀመርያ  የዲፕሎማሲ ጥረት እናደርጋለን ይህ ካልተሳካ አለምአቀፍ ገልጋዮች ጉዳዩን እንድያዩት እናደርጋለን በመቀጠል ብዙ አማራጮች አሉን ይህም አካባብያዊ ድርጅቶች እንደ አረብ ሊግ አለም አቀፍ ድርጅቶች እንደ የተባበሩት መንግሥታት ያሉት በጉዳዩ እንዲገቡ እንጋብዛለን'' በማለት ገልፀዋል።

ግብፅ በአባይ ወንዝ አጠቃቀም ኢትዮጵያን ያገለለ ሱዳን እና ግብፅን ብቻ የሚጠቅመውን (በግብፅ እና ሱዳን ብቻ የተፈፀመውን) የ 1959 እ.አ.ቆጣጠር  ውል   እንዲከበርላት ለዘመናት ስትታትር ተስተውላለች።ሆኖም ግን ውሉን ኢትዮጵያ በሶስቱም መንግሥታት በቀዳማዊ አፄ ሃይለስላሴ፣በደርግ እና በአሁኑ መንግስት ተቀባይነት አላገኘም። የአባይ ወንዝ ፍትሃዊ አጠቃቀም ላይ  በተለይ የታችኛው ተፋሰስ ሃገራት ተብለው በሚጠሩት ኢትዮጵያ፣ሩዋንዳ፣ቡሩንዲ፣ዲሞክራቲክ ሪፑብሊክ ኮንጎ፣ታንዛንያ፣ኬንያ፣ዑጋንዳ፣ደቡብ ሱዳን፣ሰሜን ሱዳን፣ግብፅን ያካተተ ውይይት ሲደረግ ቆይቶ በ 2010 እኤአ ቆጣጠር  ከግብፅ እና ከሱዳን በቀር ሌሎች ሃገራት በፊርማም ሆነ በአዎንታዊ መልኩ የተቀበሉት ውል ተረጋገጠ። ውሉም  ''የኢንተቤ ውል'' በመባል ይታወቃል።

የእዚህ አይነቱ የታችኛው ተፋሰስ ሃገራት መስማማት ግብፅ ከጉዳዩ ጋር ብዙ ለመጮህ ሳይመት ቀረ።ይህ በእንዲህ እያለ ኢትዮጵያ የአባይን ግድብ ስትጀምር ግብፅ ''የህዝብ ዲፕሎማስን'' ማጠናከር ላይ አተኮረች። ለእዚህም አይነተኛ ማስረጃ የኮፕቲክ ቤተክርስቲያን ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነቷን ማጠናከር፣ከግብፅ አብዮት በኃላ ከወጣቶች የተውጣጡ ልዑካን ኢትዮጵያን መጎብኘት ወዘተ ተጠቃሽ ነበሩ። ይህ እንግዲህ የግብፅ አብዮት ወዴት እንደሚሄድ ሳይታወቅ በነበረበት ደረጃ መሆኑ ነው።


የግብፅ አብዮት በውድም ይሁን በግድ በመደራጀቱ ብቻ ቀድሞ የተገኘው ''የእስላማዊ ወንድማማቾች ህብረት'' እጅ ሲወድቅ አለምአቀፉ ህብረተሰብም ሆነ የግብፅ ሊበራል አሰሳሰብ ያላቸው ወገኖች በግብፅ ጉዳይ ስጋት ላይ ወደቁ።በተለይ ''የእስላማዊ ወንድማማቾች ህብረት'' በፅንፈኛ አመለካከቱ ብቻ ሳይሆን የግብፁን ፕሬዝዳንት ሁስነ ሙባረክን አዲስ አበባ ላይ ለአፍሪካ ህብረት ስብሰባ ከቦሌ አየርማረፍያ ወደ ቤተመንግስት ሲሄዱ ለመግደል ሙከራ ያደረገ መሆኑ ስለሚታወቅ የሀገሪቱ የወደፊት ዕጣ ያሰጋቸው ቢኖሩ አይፈረድባችውም። በ አሜሪካ ዩንቨርሲቲ የምህንድስና ትምህርታቸውን ያጠናቀቁት የእስላማዊ ወንድማማቾች ህብረት እጩ እና የአሁኑ የግብፅ ፕሬዝዳንት ሞሐመድ ሞሪስ ለአሜሪካም ሆነ ለእስራኤል እንደ ሙባረክ የማይመቹ መሆናቸውን ለመተንበይ ብዙ ሊቅ መሆን የማይይቅ ሆነ።

በእዚህ ሁሉ ሁኔታ ነው እንግዲህ የአባይ ግድብ በኢትዮጵያ የተጀመረው እና አሁን  21% የተሰራ መሆኑ የተነገረው። እዚህ ላይ የሰሞኑ የግብፆች ግርግር ለምን አዲስ ሆነ? የሚል ጥያቄ ሊነሳ ይችላል። መልሱ የግብፆችን ልማድ እንዳለ ትተን  እኛም ዲፕሎማስያዊ ጥበብ ያነሰን መሆኑን ማንሳት አንዱ ምላሽ ሊሆን ይችላል ። የማይለቀን ''የካድሬ ምክር መስማት'' ኢትዮጵያን መጉዳቱን ቀጥሏል።ግድቡ ስራውን እየቀጠለ ሳለ ግንቦት 20ን ጠብቆ ውሃውን መንገድ አስቀየርኩት ማለት ይህንንም በቴሌቭዥን በቀጥታ ማስተላለፍ የነበረው ጥቅም አይታየኝም።ለግብፁ ፕሬዝዳንት ግን ህዝባቸውን ለማስደንበር ተጠቅመውበታል። ''የኢንተቤን ውል'' ዙርያ ከመከራከር ይልቅ አዲስ ድንጋፄ ፈጥረው ግብፅ በቶሎ ግድቡን እንድታስቆም ይሻሉ። ኢትዮጵያ ይህንን የግንቦት 20 ስነ-ስዓት  የተወሰኑ ካድሬዎች ከኢትዮጵያውያን ዲፕሎማቶች ጋር ሳይወያዩ የሰሩት ድርጅታዊ ሥራ ይመስላል።በሙያዊ ጉዳዮች መግባት የካድሬዎች ሥራ ባይሆን እና ዲፕሎማውን ለባለሙያው ተውልን ባማረ ነበር።በእውቀት ላይ ያልተመሰረተ ''ብሔራዊ ጀግና'' ለመባል ብቻ የሚሰሩ የካድሬ ፕሮፓጋንዳ መሰል ችግሮች አንዳንዴ የሚያስከፍሉት ዋጋ የትየለሌ ስለሚሆን ከፍልጥ ፈልጥ የሚያስቀድሙት ባለሙያዎች ቢደመጡ ለሀገራችን የሚበጅ ብቸኛ መንገድ ነው።

ግብፅ ለዘመናት የኖረ ጭፍን ሃሳቧን ታቆማለች ማለት አይቻልም።የእኛ የቤታችን ሥራ ግን አለ። በግድቡ ሂደት ላይ የኢትዮጵያ ሕዝብ በበለጠ የሚሳተፍበትን  መልክ ማስያዝ እና ግልፅነትን የተላበሰ ስራውን ከካድርያዊ አሰራር መለየት እና ሁሉንም በሚያባብል መልክ ማቅረብ አስፈላጊ ነው።ስለአባይ ግድብ ገንዘብ መሰብሰብ የሚገባው አምባሳደር ሳይሆን ሕዝብ ያውም ተራው ሕዝብ ነው።የእዚህን ጊዜ ነው የእኔነት ስሜት የሚዳብረው። ፖለቲካን ከልማት ሥራ መለየት (ምንም ተያያዥነት ቢኖራቸውም) እና ሕዝብ ካለአንዳች ተፅኖ እንዲሰራው ማድረግ ተገቢ ነው። ከፍልጥ ፈልጥ ቀደመ ማለትም ይህ ነው። የሆነው ቢሆን ግን ግብፅ እስከ አራት ኪሎ ድረስ ገብታ እንድትፈተፍት የሚፈቅድላት ኢትዮጵያዊ አይኖርም።የቤታችንን ጉዳይ ለእኛ ተዉት -ግብፆች እና አጋሮቻችሁ ማለት  ኢትዮጵያዊነት ነው።

አበቃሁ 
ጌታቸው 
ኦስሎ 






ጉዳያችን GUDAYACHNgetachewb221@gmail.com

Wednesday, June 5, 2013

ሰበር ዜና - ኢትዮጵያ ለግብፅ ምላሽ ሰጠች- ''ግብፅ የቀን ሕልም ላይ ነች'' አቶ ጌታቸው ረዳ የጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ቢሮ ቃል አቀባይ

ሰበር ዜና 

ኢትዮጵያ ለግብፅ ምላሽ ሰጠች- ''ግብፅ የቀን ሕልም ላይ ነች'' አቶ ጌታቸው ረዳ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ቢሮ ቃል አቀባይ

''አህራም ኦን ላይን'' የተሰኘው የግብፅ ድህረ ገፅ ጋዜጣ በዛሬው ግንቦት 28፣2005 ዓም ባወጣው ዘገባ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ቢሮ ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ ግብፅ ኢትዮጵያን ለማተራመስ ብዙ ያልተሳካ  ሙከራ ማድረጓን መግለፃቸውን እና  አሁን ''በኢትዮጵያ ላይ ወረራ ማድረግ እና ሴራ ማድረግ'' የሚሉ አስተያየቶች ጊዜ ያለፈባቸው የከሸፉ ሃሳቦች  ''old failed concept." እና የቀን ሕልም "day dreaming." ከመሆን ያልዘለለ መሆኑን አክለው መናገራቸውን ዘግ ቧል።

የጋዜጣውን አጭር ዜና ከእዚህ በታች በጉዳያችን ጡመራ ላይ ያንብቡ።


Ethiopia: Egypt attack proposals 'day dreaming'
Ethiopia's official says Egyptian politicians suggestions of sabotaging Renaissance dam is 'day dreaming'
AP, Wednesday 5 Jun 2013
Share/Bookmark
Views: 335
A spokesman for Ethiopia's prime minister is downplaying suggestions by Egyptian politicians that Egypt should sabotage Ethiopia's new Nile River dam.
Political leaders in Egypt on Monday proposed carrying out hostile acts against Ethiopia. Egypt, which is dependent on the Nile, fears a diminished flow.
Getachew Reda, a spokesman for Ethiopian Prime Minister Hailemariam Desalegn, said late Tuesday that Egyptian leaders in the past have unsuccessfully tried to destabilize Ethiopia. He called the suggestions of attack or sabotage an "old failed concept." He also labeled it "day dreaming."
Ethiopia last week ago began diverting the flow of the Nile toward its $4.2 billion hydroelectric plant that has been dubbed the Grand Ethiopian Renaissance Dam. The project, currently about 20 percent complete, has raised concerns in Nile-dependent Egypt.

Monday, June 3, 2013

መጪው ትውልድን ለማወቅ (ቪድዮ)

አሁን ያለው ትውልድ አደራውን ይወጣል። መጪው ትውልድ ደግሞ እየተዘጋጀ ነው። መጪው ትውልድን ለማወቅ የእዚህን ሕፃን በቃሉ የሚያሰማውን ግጥም ሰምቶ መገረም ይጠይቃል።ቪድዮው ከማህበራዊ ድህረ-ገፅ(ፌስ ቡክ)  የተወሰደ።






ጉዳያችን GUDAYACHNgetachewb221@gmail.com

Sunday, June 2, 2013

አዲስ አበባ የኢትዮዽያን ጩኸት ጮኸች መንግስት አሁንም ለዲሞክራሲ ዝግጁ አይደለም (ከቪድዮ ዘገባ ጋር)

ዛሬ ግንቦት 25፣2005 ዓም የሰማያዊ ፓርቲ በጠራው ሰልፍ  መቶ ሺዎች  ተሰልፈዋል።ሰልፈኛው ባብዛኛው ወጣቱ መሆኑ ነገን የሚያመላክት ነው።   ሮይተር፣አፍቃሪ መንግስት ፋና ብሮድካስቲንግ፣ኢቲቪ እና ሰማያዊ ፓርቲ በድህረገፃቸው  ያሉትን  ከ እሳት ቲቪ ዘገባ ቪድዮ ጋር ይመልከቱ።

1/ ሮይተር  (ADDIS ABABA (Reuters) 

ሮይተር ከአዲስ አበባ በዘገበው ዘገባ '' ተቃውሞ ብዙም ባልተለመደባት ኢትዮጵያ ሺዎች ለመብታቸው ተሰለፉ''  (Thousands march for rights in rare Ethiopia protest) ሲል

2/ ፋና ብሮድካስቲንግ 

ፋና ብሮድካስቲንግ የኢህአዴግ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ሬድዋን ሁሴን ተናገሩት ያለው እንዲህ ነው ''የሃይማኖት አክራሪነትን አጀንዳው አድርጎ ሲንቀሳቀስ የነበረው ሰማያዊ የፖለቲካ ፓርቲ ጸረ ህገ መንግስታዊ እንቅስቃሴው ዛሬ በጠራው ሰልፍ ተጋልጧል ብሎ ኢህአዴግ እንደሚያምን የኢህአዴግ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ሬድዋን ሁሴን አስታወቁ።'' ብሎ አሳዝኖናል። 

4/ ኢቲቪ

 ኢቲቪ በዛሬው የእሁድ ምሽት ዜናው የተደናገጠ ዜና አቅርቧል  ''ሰማያዊ ፓርቲ በጠራው ሰልፍ ህገመንግስቱን የሚጣረስ ተግባር መፈፀሙን መንግስት ገለፀ'' ካለ በኃላ ''ሰልፈኞቹ የኢትዮጵያን ባንዲራ አይወዱም'' የሚል መሰል ዜና ሲያቀርብ እንዲህ አለ''ሰልፈኞቹ የኢትዮጵያን ባንዲራ አንይ ሲሉ ተስተውለዋል'' አሁን ኢቲቪ እንዲህ የወረደ ዜና ያቀርባል ብሎ ማን አስቦ ያውቃል? ኢቲቪ ግን አደረገው።

4/ አቶ ሽመልስ የመንግስት ቃል አቀባይም የነቆራው አካል

አቶ ሽመልስ የመንግስት ቃል አቀባይም የነቆራው አካል ነበሩ 'ሃይማኖት እና መንግስት' የሚል አርስት የያዘ ''ለክቸር'' መሰል ማለት ትችላላቸው ከሰጡ በኃላ ሰልፉን ''የፍትህ መጨናገፍ ሊፈጥሩ ያሰቡ'' ብለው ሲናገሩ ኢቲቪ አሳይቷል። ካለፈው ለመማር እራሱ ለካ መታደል ነው።አሁንም ይህ ሁሉ ሕዝብ አሽባሪ ሆኖ ይሆን?

3/ ሰማያዊ ፓርቲ 

ሰማያዊ ፓርቲ በድህረገፁ ላይ ያለው ግን አንዲት ነገር ነች። ፓርቲው እንደ ኢቲቪም ሆነ እንደ አቶ ሽመልስ ሐተታ አላበዛም። ድህረ ገፁን ስትከፍቱ ይህንን የሚል ቃል ታነባላችሁ ''እናመሰግናለን !!!'' የሚል ቃል ብቻ። በሰልፉ ለተሳተፋችሁ ሁሉ እናመሰግናለን ማለቱ ነው።

መንግስት ከ እዚህ ሰልፍ ካልተማረ ከምንም አይማርም።በዛሬው የኢቲቪም ሆነ የፋና ዘገባ እንዲሁም ከአቶ ሽመልስ ንግግር አንድ ነገር መረዳት ይቻላል።መንግስት አሁንም ለዲሞክራሲ ዝግጁ አይደለም።
የኢሳት  ልዩ ዘገባ 

በኢትዮጵያ የእገታ ወንጀል ተሳታፊ አራት አካላት ናቸው። ለችግሩ የመፍትሄ አካላት ሁለት ናቸው።ሁለቱ አካላት ምን ይስሩ?

======= ጉዳያችን ======= በኢትዮጵያ ዜጎችን እያገቱ ገንዘብ የሚቀበሉ ወንጀለኞች ከተራ ወንጀለኝነት አልፎ በታጣቂ ቡድኖች የገንዘብ ማግኛነት መዋል ብቻ ሳይሆን ዜጎችን የማሸበርያ ፋሺሽታዊ ተግባር ሆኗል። እገታ የ...