ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Sunday, June 2, 2013

አዲስ አበባ የኢትዮዽያን ጩኸት ጮኸች መንግስት አሁንም ለዲሞክራሲ ዝግጁ አይደለም (ከቪድዮ ዘገባ ጋር)

ዛሬ ግንቦት 25፣2005 ዓም የሰማያዊ ፓርቲ በጠራው ሰልፍ  መቶ ሺዎች  ተሰልፈዋል።ሰልፈኛው ባብዛኛው ወጣቱ መሆኑ ነገን የሚያመላክት ነው።   ሮይተር፣አፍቃሪ መንግስት ፋና ብሮድካስቲንግ፣ኢቲቪ እና ሰማያዊ ፓርቲ በድህረገፃቸው  ያሉትን  ከ እሳት ቲቪ ዘገባ ቪድዮ ጋር ይመልከቱ።

1/ ሮይተር  (ADDIS ABABA (Reuters) 

ሮይተር ከአዲስ አበባ በዘገበው ዘገባ '' ተቃውሞ ብዙም ባልተለመደባት ኢትዮጵያ ሺዎች ለመብታቸው ተሰለፉ''  (Thousands march for rights in rare Ethiopia protest) ሲል

2/ ፋና ብሮድካስቲንግ 

ፋና ብሮድካስቲንግ የኢህአዴግ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ሬድዋን ሁሴን ተናገሩት ያለው እንዲህ ነው ''የሃይማኖት አክራሪነትን አጀንዳው አድርጎ ሲንቀሳቀስ የነበረው ሰማያዊ የፖለቲካ ፓርቲ ጸረ ህገ መንግስታዊ እንቅስቃሴው ዛሬ በጠራው ሰልፍ ተጋልጧል ብሎ ኢህአዴግ እንደሚያምን የኢህአዴግ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ሬድዋን ሁሴን አስታወቁ።'' ብሎ አሳዝኖናል። 

4/ ኢቲቪ

 ኢቲቪ በዛሬው የእሁድ ምሽት ዜናው የተደናገጠ ዜና አቅርቧል  ''ሰማያዊ ፓርቲ በጠራው ሰልፍ ህገመንግስቱን የሚጣረስ ተግባር መፈፀሙን መንግስት ገለፀ'' ካለ በኃላ ''ሰልፈኞቹ የኢትዮጵያን ባንዲራ አይወዱም'' የሚል መሰል ዜና ሲያቀርብ እንዲህ አለ''ሰልፈኞቹ የኢትዮጵያን ባንዲራ አንይ ሲሉ ተስተውለዋል'' አሁን ኢቲቪ እንዲህ የወረደ ዜና ያቀርባል ብሎ ማን አስቦ ያውቃል? ኢቲቪ ግን አደረገው።

4/ አቶ ሽመልስ የመንግስት ቃል አቀባይም የነቆራው አካል

አቶ ሽመልስ የመንግስት ቃል አቀባይም የነቆራው አካል ነበሩ 'ሃይማኖት እና መንግስት' የሚል አርስት የያዘ ''ለክቸር'' መሰል ማለት ትችላላቸው ከሰጡ በኃላ ሰልፉን ''የፍትህ መጨናገፍ ሊፈጥሩ ያሰቡ'' ብለው ሲናገሩ ኢቲቪ አሳይቷል። ካለፈው ለመማር እራሱ ለካ መታደል ነው።አሁንም ይህ ሁሉ ሕዝብ አሽባሪ ሆኖ ይሆን?

3/ ሰማያዊ ፓርቲ 

ሰማያዊ ፓርቲ በድህረገፁ ላይ ያለው ግን አንዲት ነገር ነች። ፓርቲው እንደ ኢቲቪም ሆነ እንደ አቶ ሽመልስ ሐተታ አላበዛም። ድህረ ገፁን ስትከፍቱ ይህንን የሚል ቃል ታነባላችሁ ''እናመሰግናለን !!!'' የሚል ቃል ብቻ። በሰልፉ ለተሳተፋችሁ ሁሉ እናመሰግናለን ማለቱ ነው።

መንግስት ከ እዚህ ሰልፍ ካልተማረ ከምንም አይማርም።በዛሬው የኢቲቪም ሆነ የፋና ዘገባ እንዲሁም ከአቶ ሽመልስ ንግግር አንድ ነገር መረዳት ይቻላል።መንግስት አሁንም ለዲሞክራሲ ዝግጁ አይደለም።
የኢሳት  ልዩ ዘገባ 

No comments:

ኢትዮጵያ በዘመናዊ ታሪኳ ታላቅ ተልዕኮ የሚኖረው ሀገራዊ የምምክር ኮሚሽን በተመለከተ ምን ያህል እናውቃለን?

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ኮሚሽን አማካሪ ኮሚቴ አባላትን ከሁሉም የኢትዮጵያ ክፍል ባካተተ መልኩ አዋቅሯል። በእዚህ ጽሑፍ ስር የሚከተሉት ነጥቦች ምላሽ ያገኛሉ፡  ኮሚሽኑ እንዴት ተመሰረተ?  የኮሚሽኑ 11 ኮሚሽነሮች እንዴት ተመ...