ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Wednesday, June 26, 2013

ሰበር ዜና - ሼህ ሁሴን ዳሄር አዌይስ ዛሬ ሰኔ 19/2005ዓም ተያዙ።Sheikh hassan dahir aweys captured

ሼህ ሁሴን ዳሄር አዌይስ (photo  FILE | NATION MEDIA GROUP)


ሼህ ሁሴን ዳሄር አዌይስ ቀንደኛ የሱማልያ ''አልሸባብ'' አመራር እና ''የእስላማዊ ፍርድቤቶች ህብረት'' መስራች ዛሬ ሰኔ 19/2005ዓም ተያዙ።

አዌይስ ''ኦጋዴንን ከኢትዮጵያ እገነጥላለሁ ''የሚለው እና በአዲስ አበባ፣በድሬዳዋ እና በጅጅጋ ለደረሱ ጥቃቶች ተጠያቂ የሆነውን ''አል-ኢታድ አል-ኢስላምያ'' በ 1990 ዎቹ ሲመራ የነበረ ግለሰብ መሆኑ ይታወቃል። 

በማከላዊ ሱማልያ የራስ ገዝ ግዛት በሆነችው በ ሂማን ግዛት እንደተያዙ የተነገርላቸው አዌይስ በ2011 ዓም በአሜሪካ መንግስት በቀንደኛ አሸባሪነት ዝርዝር ውስጥ የገቡ ናቸው።ግለሰቡ አሜሪካ እንደምትለው በታንዛንያ እና በኬንያ የአሜሪካ ኢምባሲ ለደረሰው ጥቃት ተጠያቂ የተደረገው ''አልቃይዳ'' ጋር ንክኪ እንዳላቸው በሰፊው ስትገልፅ የነበረ መሆኑ ይታወቃል።

በሐምሌ ወር 2006 ዓም እኤአቆጣጠር ዳሄር አዌይስ በኢትዮጵያ ላይ ''ጀሃድ'' ያሉትን ጦርነት ማወጃቸውን በራድዮ ሲለፍፉ ተደምጠዋል።በእዚሁ አመት በህዳር ወር ላይ '' 'ታላቂቱ ሱማልያ' የአፍሪካን ቀንድ በሙሉ መያዝ ይገባታል'' የሚል ቃል በራድዮ መናገራቸውም አይዘነጋም። ሼህ ሁሴን ዳሂር አዌይስ ጦርነት ያወጁባት ኢትዮጵያም እያየቻቸው  የአፍሪካ ቀንድን በሙሉ የመያዝ ሕልምም ሳይሳካ ዛሬ ተይዘዋል። የሱማልያ መንግስት አዌይስን የያዘችውን የራስገዝ ግዛቷን ሂማን አሳልፋ እንድትሰጥ አሳስቧል።ሼሁ በአሁኑ ጊዜ በሰባዎቹ እድሜ ውስጥ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል።
ዜናውን የአሜሪካ ድምፅ ራድዮን ጨምሮ የኬንያ የዜና ዘገባዎች ዘግበውታል።

No comments:

ወቅታዊ የዓለም ሁኔታ እንድንነታረክ ዕድል የሚሰጥ አይደለም።ብንነቃ መልካም ነው።

========== ጉዳያችን ወቅታዊ ========== የዓለም ታሪክ እንደሚያስተምረን ዓለም በወሳኝ የእጥፋት(turning point) ታሪኮች ውስጥ አልፋለች። እነኝህ የእጥፋት ጊዜዎች የዋዛና የፈዛዛ ጊዜ አይደሉም።መላው ዓለ...