ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Friday, February 26, 2016

የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ያልያዙ ኢትዮጵያውያን ሰልፈኞች መንግስት ጎረቤቶቻቸውን እና የአገሩን ቀደምት ነዋሪዎችን እንዲገድልላቸው ጠየቁ።


''ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይጠባም'' ይላል ደጉ ኢትዮጵያዊ። አሁን አሁን መጪውን የመከራ ዘመን ለመቀበል እራሳቸውን ያዘጋጁ፣መካሪ ሽማግሌ ያጡ እና ጥጋብ የሚሰሩትን ያሳጣቸው በእሳት ሲጫወቱ ማየት የተለመደ ሆኗል።

ከእዚህ በላይ የምትመለከቱት ፎቶ አፍቃሪ ሕወሃቱ ፋና ብሮድካስቲንግ በድረ ገፁ ላይ የሰቲት ሁመራ ነዋሪዎች የአካባቢው ቀደምት ነዋሪዎች አማራ ነን ትግሬ አይደለንም  በማለታቸው ብቻ ትግሪኛ ተናጋሪዎች ሰልፍ መውጣታቸውን ከዘገበበት ገፅ ላይ የተወሰደ ነው።

በፎቶው ላይ እንደምትመለከቱት የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ የለም በሚባል ደረጃ ሁለት ወይንም ሶስት ብቻ ትመለከታላችሁ።የቀረው በሙሉ ከኢትዮጵያ ጡት ያደገ በማይመስል መልክ (ተገዶ መሆኑን የሚገልፁ አሉ) የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ተሽቀንጥሮ በህወሓት አርማ ሰቲት ሁመራ ላይ ተሰልፈዋል። 

ዜናውን ፋና እንዳለው ብቻ ላቅርበው እና ሰልፈኞቹ መንግስትን ጎረቤቶቻችንን ይግደልልን ማለታቸውን አንብባችሁ ፍረዱ።በመጀመርያ ደረጃ በሰቲት ሁመራ፣በታች አርማጮ የአማራ ተወላጅ ነን ትግርኛ ብንናገርም ባህላችን፣ለቅሷችን፣ ሁሉ በአማራ ባህል ነው።በሚል በሰላማዊ እና በሰለጠነ መልክ ለመጠየቅ አዲስ አበባ ድረስ ተወካይ የላከው የሁመራ ሕዝብ ተወካዮቹ ታፈኑበት።እንግዲህ ይህንን በሰላማዊ መንገድ ለተጠየቀ ጥያቄ ነው ሰልፍ ተወጥቶ እንደ ፋና አገላለፅ ሰልፈኞቹ  እርምጃ ይወሰድልን አሉ ያለን።እንዲህ ይነበባል: -

''ህዝቡ እነዚህን አካላት እስካሁን በትዕግስት ጠብቋቸዋል ያሉት ነዋሪዎቹ፥ ከአሁን በኋላ ግን መንግስት አስፈላጊውን ህጋዊ እርምጃ እንዲወስደባቸው ጠይቀዋል።'

በትዕግስት ጠበቃቸው የተባሉት ስለ ሁለት ነገር ነው ማለት ነው? አንዱ ቀድመው ነዋሪ ስለሆኑ ባህላችን ይጠበቅ በማለታቸው ሲሆን ሁለተኛው ይህንን መብታቸውን ደጋግመው በሰላማዊ መንገድ መጠየቃቸው ነው።

ለጥያቄው ምላሽ የሕወሃቱ የምስራቅ ትግራይ አስተዳዳሪ አቶ ኢሳያስ በምላሹ እንዲህ አሉ ይላል ፋና :- ''የህዝቡን ጥያቄ ለማክበርም በእነዚህ አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ እንወስዳለን''

በቀይ ሽብር ዘመን እርምጃ ወስደናል ማለት ገድለናል ማለቱ መሆኑን ማንም ያውቀዋል።በፋና ዘገባም ሕዝብ ''እርምጃ ይወሰድ'' አለ ማለት ''ይገደሉልን'' ማለቱ ሲሆን ''እርምጃ እንወስዳለን'' አሉ ሲል ደግሞ ''እንገላለን'' ማለት መሆኑ ነው።እነማንን ሲባል ጎረቤቶቻቸውን እና ቀደምት ነዋሪዎችን።ምክንያት ባህላችን ይከበር በግድ ከመሬታችን ተገፋን ስላሉ።

ይህ አይነቱ የለየለት መንግስታዊ ፋሺዝም በኢትዮጵያ ላይ ነግሶ ሰላም ይመጣል ማለት ዘበት ነው።በኦሮምያ በመቶ የሚቆጠሩ በጥይት እረግፈው እና የአስር እና አስራሁለት ዓመት ወጣቶች አደባባይ ወጥተው ድምፅ አሰሙ ብሎ ጥይት በተርከፈከፈባቸው እና መድረክ አዲስ አበባ ላይ ሰልፍ ለመጥራት ጠይቆ በተከለከለ ማግስት  ሁመራ ላይ የሕወሃትን ሰንደቅ አላማ የያዙ ሰልፈኞች ጎረቤቶቻችንን ግዴልልን ብለው መንግስትን ጠየቁ መንግስትም እሺ እንገላለን አለ።የሚል ዜና የሚገኘው ፋና ድረ-ገፅ ላይ ብቻ ነው።ሰልፈኞችም ባይሰልፉ ቢቀር መልካም ነበር።ሽማግሌዎች (ሽማግሌ ካለ) ተሰብስበው ቢነጋገሩ እና መላ ቢዘይዱም ጥሩ ነበር።ነበር ለማለት ነው እንጂ ለህወሓት ከሁሉ በላይ የሆነ ስለመሰለው ፋሽሽታዊ ልብሱን በደንብ እያጠለቀ ነው።ለነገሩ ከቁንጮ እስከ እግር ድረስ በአንድ አካባቢ ሰው የምትመራ አገር በፋሽሽት መሪዎች እጅ  ብትወድቅ  አይገርምም።  
ይህ ስርዓት ከትናንቱ ይልቅ መጪው ፋሽሽታዊ አላማው ከመቼውም ጊዜ በላይ አሁን በግልፅ ታይቷል።


ጉዳያችን GUDAYACHN
www.gudayachn.com 
የካቲት 19/2008 ዓም 

Thursday, February 25, 2016

Breaking News Ethiopia:- High tension between Ethiopia and Eritrea border (GUDAYACHN NEWS)



Armed opposition force,Patriotic-Ginbot 7 lead by Prof. Birhanu Nega (US educated economist) is a day to day talk in the capital Addis Ababa and other far remote areas of Ethiopia.On Thursday February 25/2016, Washington based Ethiopian Satellite Televicion   (Esat) stated as TPLF is pushing its army to the border area between Ethiopia and Eritrea.The army is approaching to the border in two different fronts namely HUMERA and BADIMA.Many believes the main expected target of TPLF in this particular movement is Patriotic-Ginbot 7 for peace,democracy and freedom movement. 


For the last two months, TPLF was in critical time with popular uprising in Oromia regions. The ethno-centric regime of Ethiopia has controlled the political, economical and military power of the country for the quarter- century of the past.The Ethiopian people is tired of the regime. The demand for democratic change, both at home and abroad, is highly and eagerly expected by most Ethiopians. If the clash between Patriotic-G7 and TPLF army is brake out, another and non-reversible popular uprising is expected in every corner of the nation.

It is recalled that few days back the United States and Norway embassies in Addis Ababa  were issued a press release to their citizens not to travel far from the capital, Addis Ababa.


ጉዳያችን GUDAYACHN 
www.gudayachn.com 

February 26/2016

Tuesday, February 23, 2016

La oss alle håpe at Norge Regjeringen vil vurdere Flyktninge tilfeller av etiopiere fra ulike perspektiver. ( Let us all hope that Norway Government will consider Refugee cases of Ethiopians from different perspectives)

Etiopiske kong Haile Selassie besøker til Norge, 1954
(Ethiopian king Haile Selassie visits to Norway, 1954) 


GUDAYACHN
February 24, 2016
(English version is attached below)

Sterke bånd mellom Etiopia og Norge ble dannet under den andre verdenskrig, da keiser Haile Selassie første av Etiopia og den norske kongefamilien møtte i London. Dette førte til gjensidige statsbesøk; keiseren besøkte Norge i 1954, og kong Olav besøkte Etiopia i 1966. Norge er en av de første etiopiske marinen opplæring assistanse leverandør, da Etiopia dannet sin moderne Navy kraft i Massawa og Assab.

Foreløpig er det ganske kjent at Etiopia er under diktatur og etnosentrisk regel Government.At resultat millioner på flukt og å være flyktning i hele verden. Etiopiske flyktninger venter mye fra demokratiske land som Norge å spille en sentral rolle i prosessen med etiopierne slite mot fred og demokrati.

I Norge en rekke etiopiske født flyktninger er bosatt. De som har fått asylstatus av UDI har en god oversikt over integrering med det norske samfunnet. Men andre flyktninger som sakene er ennå ikke få beskyttelse status er i en alvorlig problem. I går, februar 22,2016, avslørt NRK Tv som rundt 800 etiopiske flyktninger vil plikt til å gå hjem (se lenke NRK).

Dette er et paradoks som ikke vil definere de grunnleggende globale figuren av Norge. Norge er ganske kjent med sjenerøs og aktiv deltakelse i internasjonale humanitære kriser og håndtering av flyktninger saken skikkelig i noen del av konfliktsoner over hele verden. Etiopia politiske situasjonen er ikke bare spare for politiske flyktninger, men også bli farlig for vanlige borgere hjemme. Dette er bevist av Norge ambassaden pressemeldinger i Addis Abeba. Addis Abeba norske ambassaden varsel til sine innbyggere er igjen sikre som den politiske og sikkerhetsmessige forholdene i Etiopia nå går fra vondt til verre.

February 19/2016, leser norske ambassaden i Addis Abeba varsel til borgere som følger:
Oppdatert Reiseinformasjon Oromia
19.02.2016 // Det er Fortsatt en ustabil og uforutsigbar situasjon i Oromia-REGIONEN.

Norske borgere Som befinner SEG jeg, Eller vurderer Å Reise til Oromia, Inkludert Rundt Addis Abeba, oppfordres til Å hol SEG oppdatert om situasjonen.

Det er mottatt Informasjon om at biler Skal ha blitt Utsatt for angrep MED stein i Bulbula, på Hovedveien til Hawassa, og i urolighetene også Har spredd SEG til omradet Rundt Lake Langano.


Engelsk oversettelse lyder slik: -

Oppdatert reiseinformasjon Oromia
02/19/2016 // Det er fortsatt en ustabil og uforutsigbar situasjon i Oromia regionen.

Norske borgere som er i, eller vurderer å reise til Oromia, inkludert rundt Addis Ababa, oppfordres til å holde seg orientert om situasjonen.

Det er mottatt informasjon om at biler skal ha blitt utsatt for angrep med steiner i Bulbul, på hovedveien til Hawassa, og uroen har også spredd seg til området rundt Lake Mangano.

Her kommer paradokset igjen. Hvordan kunne etiopiske asylsøkere plikt til å forlate Norge i en slik kritisk tid? Faktisk er det helt sant at landet lov Norge er en endelig lov som må respekteres og ikke å bli krenket på noen måte. Hver kropp er enig med det. Men noen kritiske spørsmål er på stedet: hva om den andre dimensjonen av humanitære spørsmål? hvordan primær globale flyktning beskytter nasjon vil velge å sende politiske flyktninger til veldefinert "krigssone", som allerede er bekreftet av sitt eget utenrikskontor?

Midlertidige politiske problemer er alltid i ferd med å endre gjennom borgere kontinuerlig straggle for demokrati. Vi kan nevnes historien til Egypt og Tunisia. Disse diktator herskere er ikke mer strøm. Men den kontinuerlige generasjon er der og det er grunnlaget for lyd forhold skip med andre land som Norge. Norske og etiopiske lang sikt forholdet kan ikke bestemmes av diktatoriske etnosentriske regimer som dagens regime i Etiopia. La oss alle håpe at Norge Regjeringen vil vurdere Flyktninge tilfeller av etiopiere fra ulike perspektiver. 

Etiopiske kong Haile Selassie besøker til Norge i 1954
(Ethiopian king Haile Selassie visits to Norway in 1954) 

=====================================================================

We all hope that Norway Government will consider Refugee cases of Ethiopians from different perspectives


Strong ties between Ethiopia and Norway were formed during the second World War, when Emperor Haile Selassie first of Ethiopia and the Norwegian royal family met in London. This led to mutual state visits; the emperor visited Norway in 1954, and King Olav visited Ethiopia in 1966. Norway is one of the first Ethiopian Navy training assistance provider, when Ethiopia formed her modern Navy force in Massawa and Assab.

Currently, it is quite known that Ethiopia is under dictatorship and ethnocentric rule of Government.At the result millions displaced and being refugee in all over the world. Ethiopian refugees are expecting a lot from democratic countries like Norway to play a key role in  the process of  Ethiopians struggle towards peace and Democracy.

In Norway a number of Ethiopian born refugees are residing. Those who have got asylum status by UDI have a good record of integration with the Norwegian society. But other refugees whose  cases are not yet get protection status are in a serious problem. Yesterday, February 22,2016, NRK  Tv disclosed as around 800 Ethiopian refugees will obliged to go back home ( see the link NRK).

This is a paradox that will not define the basic global face of Norway. Norway is quite known with generous and active participation of international humanitarian crises and handling refugees case properly in any part of conflict zones  all over the globe. Ethiopia political situation is not only save for political refugees, but also  becoming dangerous for ordinary citizens at home. This is proved by the Norway Embassy press releases in Addis Ababa. Addis Ababa's Norwegian Embassy notice to its citizens  is again assuring as the political and security condition of Ethiopia by now is going from bad to worse.

On February 19/2016, Norwegian Embassy in Addis Ababa notice to citizens reads as follows:

Oppdatert reiseinformasjon Oromia

19.02.2016 // Det er fortsatt en ustabil og uforutsigbar situasjon i Oromia-regionen.
Norske borgere som befinner seg i, eller vurderer å reise til Oromia, inkludert rundt Addis Abeba, oppfordres til å holde seg oppdatert om situasjonen.
Det er mottatt informasjon om at biler skal ha blitt utsatt for angrep med stein i Bulbula, på hovedveien til Hawassa, og at urolighetene også har spredd seg til området rundt Lake Langano.

English translation reads as:-  

Updated travel information Oromia
02/19/2016 // There is still an unstable and unpredictable situation in Oromia region.

Norwegian citizens who are in, or are considering traveling to Oromia, including around Addis Ababa, are encouraged to keep abreast of the situation.

It's received information that cars should have been subjected to attacks with rocks in Bulbul, on the main road to Hawassa, and the unrest has also spread to the area around Lake Mangano.

Here comes the paradox again. How could Ethiopian Asylum seekers obliged to leave Norway in such critical time?  In fact it is quite true that the land law of Norway is an ultimate law which must be respected and not to be violated in any way. Every body agree with it. But a critical questions are on the spot: what about the other dimension of humanitarian issues? how the primary global refugee protector nation will decide to send political refugees to the well defined 'war zone', which is already confirmed by its own foreign office? 

Temporary political problems are always in the process of change through determined citizens continuous straggle for democracy. We can mentioned the history of Egypt and Tunisia. Those dictator rulers are no more on power. But the continuous generation is there and it is the base for sound relation ship with  other countries like Norway. Norwegian and Ethiopian long-run relationship could not be determined by dictatorial ethnocentric regimes like the current regime of Ethiopia. Let us all hope that Norway Government will consider Refugee cases of Ethiopians from different perspectives. 


==================================================================


ጉዳያችን GUDAYACHN
February 24/2016
Oslo, Norway

The writer is NMBU International Development studies MA student.
e-mail= getachewb221@gmail.com 

ህወሓት የገመደችው የጎሳ ፖለቲካ ጅራፍ እራሷን መግረፍ ጀመረ (የጉዳያችን አጭር ማስታወሻ)





አዲሱ 2008 ዓም ከገባ ስድስተኛ ወር ላይ ነን።የካቲት ወር ለኢትዮጵያ የፖለቲካ መድረክ በርካታ ገጠመኞችን ይዟል።በባርነት ቀንበር ልንወድቅ አፋፍ ላይ ሆነን የኢትዮጵያ ሕዝብ ከዳግማዊ አፄ ምንሊክ እና ጣይቱ ጋር አድዋ ላይ ተሞ ጣልያንን ድል ያደረገው በየካቲት 23 ቀን ነበር።በየካቲት 12/1929 ዓም ደግሞ ኢትዮጵያን ዳግመኛ የወረረው ኢጣልያ በአዲስ አበባ ሕዝብ ላይ ጭፍጨፋ የፈፀመበት እና የኢትዮጵያ ሕዝብ ወንድ ሴቱ ከአርበኞች ጋር ይበልጥ እንዲሰለፍ የቆረጠበት እለት ነው።በሌላ በኩል የካቲት 1966 ዓም የኢትዮጵያ ሕዝብ የመጀመርያ ግብታዊ  አብዮት ያቀጣጠለበት ወር ነበር።በእዚህ አብዮትም አሁን ድረስ ላለው ላልሰከነው የአገራችን ፖለቲካ መነሻ ሆኖ ቀጥሏል።ይህ የያዝነው የካቲት ወርም ከሰሜን እስከ ደቡብ የሕዝብ ፖለቲካዊ እና ምጣኔ ሃብታዊ ጥያቄ ዳግም የተነሳበት ነው። 


ህወሓት የገመደችው የጎሳ ፖለቲካ  ጅራፍ እራሷን መግረፍ ጀመረ 

ህወሓት ሥልጣን ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ የኢትዮጵያ መለያ ከሆነው አደገኛ መንገድ ውስጥ ዋናው አገሪቱን በጎሳ መከፋፈል ነው።ህወሓት የኢትዮጵያ የሆኑ ነገሮችን በጎጥ ያልከፋፈላቸው እና በጎሳ በሽታ ያለከፋቸው እሴቶች የሉም። ከዋናው የአገሪቱ ምክርቤት ጀምሮ ሰንደቅ አላማ፣የእራድዮ እና የቴሌቭዥን ጣቢያ፣የሚኒስቴር መስርያ ቤቶች፣ ወዘተ በኢትዮጵያ ስም ሳይሆን በጎጥ እንዲከፈሉ አደረገ።እዚህ ላይ የጎጥ ክፍፍልን ከፈድራል አስተዳደር ጋር ለማመሳሰል መሞከር ፈፅሞ የተሳሳተ ነው።ፌድራል አስተዳደር ዓላማ አገርን በጎጥ የመከፋፈል ሳይሆን ሕዝብ እራሱ በመረጣቸው መሪዎች የመምረጥ እና የመተዳደር መብትን እና በማዕከል የተያዘውን አስተዳደር እታች ላለው ሕዝብ በቅርቡ አገልግሎቱን እንዲያገኝ ማድረግ ነው። የጎሳ ፈድራሊዝም ግን የበለጠ ሕዝብ አስጨናቂ እና  ብጥብጥ ፈጣሪ ሆኗል። ይህ ደግሞ ላለፉት 24 ዓመታት በአገራችን ተፈትኖ የወደቀ ነው።

ይህ ህወሓት የገመደው የጎጥ ጅራፍ እንደ ህወሓት አስተሳሰብ ሌላውን ኢትዮጵያዊ እየገረፈ ሊኖርበት እንጂ እራሱን የሚገርፍ ጅራፍ ይሆናል ብሎ አላሰበም ነበር።በፈድሬሽን ምክርቤት ጎሳዎች ሲጣሉ (ህዝቡ በእራሱ በመረጣቸው ሽማግሌዎች የሚፈታውን ችግር ) በመካከል እየገባ በርካታ የአገሪቱን ችግሮች በመንደር ደረጃ አወሳስቦታል። 

ህወሓት ስልጣን እንደያዘ በርካታ ምሁራን በቅንነት የጎሳ ፖለቲካ ውሎ አድሮ ችግር እንደሚያስከትል  ሲናገሩ ነበር። ህወሓት ግን አንድ ጊዜ ነፍጠኞች፣ሌላ ጊዜ የደርግ ርዝራዥ እያለ ሁሉንም አራቃቸው።ህወሓት ስልጣኑን ለመረከብ ብቃት እንደሌለው ነገር ግን በአገሪቱ የነበረው ሁኔታ እና ዓለም አቀፍ ሁኔታው ስልጣኑን ካለምንም ተቀናቃኝ እንዲረከብ እንዳደረገው ዘነጋው እና በእውቀት፣በምክንያታዊ እና በኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ ላይ የተመሰረተ መንግስት መመስረት አቃተው። አቶ መለስ ተቃዋሚዎቻቸውን በመሳርያ ኃይል ማራቃቸው የፈለጉትን የጎሳ ፖለቲካ በኢትዮጵያ ላይ ማስፈን ብቸኛ የስልጣን ዋስትና አድርገው ተመለከቱት።ስለሆነም የጎሳ ጅራፉን ገመዱት እና የእኛ አይደለም ባሉት ሕዝብ ሁሉ ላይ ያሳርፉት ጀመር።

በጎሳ ፖለቲካ ጅራፍ ሺዎች ከቀያቸው ተባረዋል፣ንብረታቸው ተወርሶ ተመፅዋች ሆነዋል፣እንደ እብድ ጫካ ለጫካ እየተባረሩ እንደ ውሻ ተገድለዋል፣ብዙዎች በጎሳ ፖለቲካ ከስራቸው ተፈናቅለዋል፣ከአገር ተሰደዋል።በጉርዳፈርዳ የተባረሩ  አማርኛ ተንጋሪ ኢትዮጵያውያን፣በምስራቅ ሐረር በሱማሌኛ ተናጋሪዎች የተባረሩ በሺህ የሚቆጠሩ የኦሮምኛ ተናጋሪዎች፣በእልባቦር እና ከፋ ከቀያቸው ተባረው በጥይት የተገደሉት ወዘተ ቤቱ ይቁጠራቸው።እነኝህ ሁሉ የህወሓት የጎሳ ፖለቲካ ጅራፍ ያረፈባቸው ናቸው።በደላቸውን ወደ መንግስት አቤት ለማለት ሲመጡ የህወሓት መንግስት ኢፍትሃዊ መልስ ሲሰጣቸው ቆይቷል።ጅራፉ በኢትዮጵያ ሕዝብ ጅራፍ ላይ አረፈ።ሆኖም ግን ችግሩ በእዚህ ብቻ አልቆመም።

ህወሓት ሰራሹ የጎሳ ጅራፉ አደገ ተመነደገ እና ነቃ! ለካ ህወሓት ቢሰራውም እራሱ ሰሪውን መግረፍ ይችላል። ህወሓት የኢትዮጵያን ፓርላማ መስከረም ወር ላይ ሲከፍት ኢትዮጵያዊ ለዛን አጥፍቶ የተጣፈ ሱሪ የመሰሉ በርካታ የክልል ባንዲራ የያዙ ሕፃናትን እያስያዘ የኢትዮጵያን የነበረ ሰንደቅ አላማ ስያኮስስ መኖሩ ይታወቃል።በትግራይ ከኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ በበለጠ ሕዝብ የህወሃትን አርማ የያዘ ጨርቅ የበለጠ እንዲከበር ሲያደርግ ታይቷል።አቶ መለስም የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ ''ጨርቅ ነው ከጨርቁ በስተጀርባ'' እያሉ ለማናናቅ የሞከሩት የህወሓት አርማን ለማጉላት የታሰበ ሃሳብ አካል ነው። 

ዛሬ ግን የህወሓት ጅራፍ አድጎ ጥያቄ አነሳ! በኦሮምያ በተነሳው ሕዝባዊ አመፅ የጅራፍ ገማጁን የአቶ መለስን ፎቶ ግራፍ አውርዶ የኦነግ አርማ የያዘ ጨርቅ ተሰቀለ።የጎሳ ፖለቲካ ጅራፍ ሲሆን መጀመርያ አለመግመድ ጥሩ ነበር።ከገመዱም ቶሎ አቁሞ የኢትዮጵያን ሕዝብ መከፋፈል ማቆም እና የአገሪቱን አንድነት የሚጠብቅ ሥራ ላይ ማትኮር፣ዲሞክራሲን በእውነት ማስፈን፣ ሕዝብ የመናገር እና ሃሳቡን የመግለጥ መብቱን ማክበር ለእዚህ ጊዜ ይጠቅም ነበር።

ባጭሩ ህወሓት የጎሳ ፖለቲካ ጅራፍ ገምዳ  የኢትዮጵያን ሕዝብ እገርፍበታለሁ ብላ አሰበች።ጅራፉ ግን አድጎ እና ተመንድጎ እራሷን ሕወሃትን አደጋ ላይ ጣላት።ቅንነትን መሰረት ያደገ፣  የሕዝብን አንድነት የሚጠብቅ እና ከጎጥ ፖለቲካ የራቀ ፖለቲካ መከተል ጥቅሙ ለኢትዮጵያ ብቻ አይደለም ለእራሷ ለሕወሃትም ይበጃት ነበር።ክፋቱ ግን ህወሓት የገመደው ያቀጣጠለው የጎሳ ፖለቲካ ጅራፍ ለኢትዮጵያም ሌላ ፈተና እንዳያመጣ አሁንም ሁሉም ወገኖች የማንነት ክብርን ጠብቆ የዜግነት ፖለቲካን ማራመድ ብቸኛው መውጫ መሆኑን ማወቅ አለባቸው።ዛሬ ላይ ሆነው የጎጥ ጅራፍ የሚገምዱቱም  ነገ እንደህወሓት መልሶ እንደሚገርፋቸው ማወቅ አለባቸው።ከማትወጡበት ማጥ ከመግባት በፊት ከህወሓት ከእራሷ ተማሩ።



ጉዳያችን GUDAYACHN
www.gudayachn.com
የካቲት 15/2008 ዓም (ፈብሯሪ 23/2016)

Friday, February 12, 2016

''አርጋኖን'' እና ''ኦርጋን'' ምን አገናኛቸው? ሰውን እንፈር፣እግዚአብሔርንም እንፍራ! (የጉዳያችን ማስታወሻ)

ኦርጋን የሙዚቃ መሳርያ 
   
   
       የአባ ዘጊዮርጊስ ድርሰት መፅሐፈ አርጋኖን  


ባለፈው ሰሞን ከወደ አሜሪካ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አውደ ምህረት ላይ ''በኦርጋን መዘመር ይቻላል''።የሚል እንግዳ ንግግር ተሰምቷል።የምንኖረው በምዕራቡ ዓለም ነው እና ማንም የመሰለውን ሃሳብ መስጠት ይችላል።ሆኖም ግን አሁንም የምንኖረው በምዕራቡ ዓለምም ነውና ማንም ግን ካለማንም ፍላጎት የግል ሃሳቡን በሌላ ላይ መጫን አይችልም። ስለ ኦርጋን የተነገረው  ከግል አስተያየትነት አያልፍም።ይህ ማለት ግን ትክክል ነው ማለት ግን አይደለም።ስንት የሚሰራ ሥራ ያላትን ቤተ ክርስቲያን ከስርዓቷ ውጭ የሆነ ተግባር እንድትፈፅም ለመጫን መሞከር መዘዙ ብዙ ነው።

አገረ አሜሪካ፣ ይሄው ሃሳብ የተሰነዘረባት አገር በርካታ የቤተ ክርስቲያኒቱ ሊቃውንት የሚገኙባት ነች።በተለይ በስደት የሚገኙ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ፓትርያሪክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ከሁለት አስርተ ዓመታት በላይ በስደት የሚገኙት አሁንም አሜሪካ ነው።አቡነ መርቆርዮስም ሆኑ በስደት የሚገኘው ሲኖዶስ ኦርጋን በየቤተ ክርስቲያን ይግባ የሚል ውሳኔ አላሳለፈም። በአገር ቤት የሚገኘው ሲኖዶስ ይልቁንም ከሃያ አመታት በፊት የቤተ ክርስቲያኒቱ የመዝሙር መሣርያዎች ምን ምን እንደሆኑ ለይቶ በቀኖና (ህገ ቤተክርስቲያንነት)  ወስኗል። በሁለቱ ማለትም በውጭ እና በአገር ቤት በሚገኙ አባቶቻችን መካከል ምንም አይነት የሃይማኖታዊ ዶግማዊም ሆነ ቀኖናዊ ልዩነት የለም።በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንም መሰረታዊ የሆነ የልዩነት ነጥብ አልተከሰተም።በእርግጥ በአንዳንድ አጥብያዎች ስርዓተ ቤተ ክርስቲያን ከሚፈቅደው ውጭ የሚታዩ ማዘንበሎች የአገር ቤቱንም ሆነ በውጭ በስደት የሚገኘውን ሲኖዶስ መገለጫ ሊሆኑ አይችሉም።

እውነታው እንግዲህ ይህ ሆኖ ሳለ በአሜሪካን አገር ስለ ኦርጋን በአውደ ምሕረት አንድ አባት ተናገሩ ተብሎ እንደ ስርዓት የተደነገገ ያክል የሚናገሩ  እና  አልፈው ተርፈውም ኦርጋንን ከአባ ዘጊዎርጊስ ድርሰት ጋር እያመሳሰሉ የሚፅፉ ግለሰቦች ሰው ይታዘበናል አለማለታቸው እየገረመኝ ነው።

ከሁሉ በፊት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስርዓት ቀኖና በአስተያየት፣በአውደ ምህረት ላይ ንግግር ወይንም አንድ አባት ስለፃፈ ሕግ ይሆናል ማለት አይደለም።በአገራችን አንድ ባህታዊ ከቤተ ክርስቲያን ደጅ ላይ ከወገቡ በላይ እራቁቱን ሆኖ እራሱን በሰንሰለት እየገረፈ የሚናገረውን እንደ ሲኖዶስ ውሳኔ የሚወሰድበት አጋጣሚ መኖሩ በእራሱ አሳዛኝ ሆኖ ሳለ በውጭ የሚኖረው ምዕመን ሕግ እና ስርዓት ቤተ ክርስቲያኒቱ በማን እና እንዴት እንደምታወጣ የማያውቅ ይመስል ኦርጋን እና አርጋኖን እየተባለ ሲወናበድ ማየት አሳዛኝ ነው።አሁን አሁን  የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫን አርጋኖን የተሰኘውን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን የሚያመሰግነውን መፅሐፍ  ኦርጋን ከተባለው የሙዚቃ መሳርያ ጋር እያመሳሰሉ የሚፅፉ ሰዎች ለህሊና የሚከብድ ውሸት ሲዋሹ መመልከት ተለምዷል።

ይህንን ፅሁፍ እንድፅፍ ያነሳሳኝ ዛሬ በማኅበራዊ ድረ-ገፅ ላይ ያነበብኩት አንድ ፅሁፍ  በርካታ በተረታ ተረቶች  የተሞሉ ፅሁፎች ታጭቆበት ስለተመለከትኩ ነው።ለነገሩ ተረት ብቻ ሳይሆን ''አይን ያወጣ'' በሚባል ደረጃ በውሸት የተሞላ ነው። ከፅሁፉ ውስጥ ሶስቱን ውሸቶች ብቻ ልጥቀስ:-

ውሸት አንድ - ''ኦርጋን የመዝሙር መምነሽነሽያ ነበር''

ውሸት ሁለት -''ኦርጋን ከአባይ ዳር ነው የተገኘው''

ውሸት ሶስት -''ቅዱስ ያሬድ ቅዱስ ኤፍሬም እና አባ ሕርያቆስ ኦርጋን ይጠቀሙ ነበር።ቅዱስ ያሬድ ኦርጋን ብሏል።'' የሚሉ ይገኙበታል።

እዚህ ላይ ኦርጋን የተባለውን የሙዚቃ መሳርያ ከአሥራ አራተኛው ክ/ዘመን ኢትዮጵያዊው ሊቅ እና ቅዱስ አባ ዘጊዮርጊስ ዘጋስጫ ድርሰት የሆነው ''አርጋኖን'' ጋር አንድ ነው የሚለው አባባል ሌላው አስቂኝ የማሞኛ ግን ደግሞ ምንም የማያውቁ ምዕመናንን ለማሳሳት የሚሞከረው ሙከራ  አደገኛ መሆኑን መግለጡ ተገቢ ነው።ለመሆኑ ኦርጋን የሙዚቃ መሳርያ ከሆነ አርጋኖን ምንድነው? 

ስለ አርጋኖን እና አባ ጊዮርጊስ የተፃፈው ፅሁፍ እንዲህ ይነግረናል:-

''የአባ ዘጊዮርጊስ ዘጋስጫ የመጀመርያው ድርሰቱ አርጋኖን  የተሰኘውና በቅኔ ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የሚያመሰግነው መጽሐፉ ነው፡፡ ስለ አርጋኖን ድርሰቱ ገድሉ በሚከተለው መንገድ ይገልጠዋል «ወሰመዮ በሠለስቱ አስማት ዘውእቶሙ አርጋኖነ ውዳሴ፣ ወመሰንቆ መዝሙር ወእንዚራ ስብሐት - በሦስት ስሞችም ሰየማቸው እነርሱም አርጋኖነ ውዳሴ፣ መሰንቆ መዝሙርና እንዚራ ስብሐት  ይባላሉ፡፡» ይህ አገላለጥ አንድ ነገር እንድናስተውል ያደርገናል፡፡ ይሄውም ስለ አርጋኖን መጽሐፍ ይዘት ነው፡፡ በገድሉ ላይ አርጋኖን መጽሐፍ አንድ ሆኖ ሦስት ክፍሎች ያሉት ነው፡፡ .... አርጋኖን ከሰኞ እስከ ዓርብ ላሉት ዕለታት ተከፋፍሎ የተዘጋጀ ሲሆን፣ እንዚራ ስብሐት ግን ከ«ሀ » እስከ «ፖ» ያሉትን ፊደላት በመክፈያነት በመጠቀም የተዘጋጀ ነው፡፡ ይህም አርጋኖንን አባ ጊዮርጊስ ሲያዘጋጀው አንድ ሆኖ በኋላ ግን በየክፍሉ እየተጻፈ የተባዛ ይመስላል፡፡እመቤታችን አርጋኖንን ስለ ወደደችለት ዚማት  በሚባለው ሀገር በነበረ ጊዜ «ከድርሰቶችህ ሁሉ እንደ አርጋኖን የምወደው የለም»  ብላዋለች፡፡ ዐፄ ዳዊትም ድርሰቱን በጣም ከመውደዱ የተነሣ በወርቅ ቀለም እንዳጻፈው ገድሉ ይገልጣል፡፡አባ ጊዮርጊስ የተወለደው በ1357 ዓም ነው።ወላጆቹ ልጅ ስለሌላቸው ዘወትር እያዘኑ ይኖሩ ነበር።አባ ጊዮርጊስ የተወለደው በቅዱስ ዑራኤል ብስራት መሆኑን ድርሳነ ዑራኤል ይተርክልናል።'' +


ኢትዮጵያዊ ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ 

ስለዚህ አርጋኖን ድርሰት ነው።ኦርጋን ደግሞ የሙዚቃ መሳርያ ነው። አሁን በ21ኛው ክ/ዘመን ሰዎች እንዲህ የማይገናኙ ነገሮችን አምታተው ፅፈው ሕዝብ ያታልላሉ ብሎ ማን ይጠብቃል? እየሆነ ያለው ግን ይህ ነው።

የኦርጋንን የሙዚቃ መሳርያ በተመለከተ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጋር አያይዞ የተሰጠው አስተያየት ጋር ተዛምዶ በማኅበራዊ ድረ-ገፅ የሚፃፉትን በተመለከተ መታወቅ ያለባቸው ሶስት ነጥቦችን አንስቼ ፅሁፌን ልደምድም።

1/ ቤተ ክርስቲያን መድረክ ላይ በሚሰጡ የግል ሃሳቦች ቀኖና አትቀንንም 

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የምትመራባቸው መሰረታዊ መመርያዎች ምንጮች ሁለት ናቸው።አንዱ መሰረተ እምነቷ የሆነው ዶግማ ሲሆን ሁለተኛው አባቶች የሰሩላት ሥርዓቷ ወይንም ቀኖና ነው።

ዶግማን ሐዋርያውቅዱስ ጳውሎስም “ነገር ግን እኛ ብንሆን ወይም ከሰማይ መልአክ፥ ከሰበክንላችሁ ወንጌል የሚለይ ወንጌልን ቢሰብክላችሁ፥ የተረገመ ይሁን።አስቀድመን እንዳልን እንዲሁ አሁን ሁለተኛ እላለሁ፥ ከተቀበላችሁት የተለየውን ማንም ቢሰብክላችሁ የተረገመ ይሁን። ” በማለት እንዳወገዘው (ገላ፩፣  -) ማንም ማን ቢሆን የማይቀይረው መሰረተ ዕምነት ነው።ለምሳሌ የክርስቶስ ፍፁም አምላክነት ዶግማ ነው።ቀኖና  ግን የቤተ ክርስቲያኒቱን መሰረተ ዕምነት፣የመፅሐፍ ቅዱስ ትዕዛዛትን እና ቀደም ያሉ የቅዱሳን አበው ድንጋጌዎችን መሰረት አድርጎ የተሰራ ነው። ቀኖና በአውደ ምሕረት ላይ አንድ አባት ሃሳብ ስለሰጡ ''አይሻሻልም'' አሁንም የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ይፈልጋል።ቅዱስ ሲኖዶስ ደግሞ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ስለሚመራ የሚወስናቸው ውሳኔዎች በዘፈቀደ አይደለም።

በመሆኑም የኦርጋን ጉዳይ በውጭ ባለው ሲኖዶስም ሆነ በአገር ቤቱ ሲኖዶስ  የቤተ ክርስቲያን መሳርያ ነው የሚል ነገር የለም።ይልቁንም በአገር ቤት ሲኖዶስ በቤተ ክርስቲያኒቱ መንፈሳዊ መሳርያነት ተቀባይነት አላገኘም።በአገር ቤት እና በውጭ ባለው ሲኖዶስ መካከል ደግሞ የዶግማም ሆነ የቀኖና ልዩነት የለም።ይህንን በሁለቱም በኩል ያሉ አባቶች ደጋግመው ተናግረዋል።

2/ ኦርጋንን የሚከለክለው ማኅበረ ቅዱሳን ነውን ?

አሁን አሁን የተያዘው ፈሊጥ ኦርጋንን የሚከለክለው ማኅበረ ቅዱሳን ነው የሚል ነው።እንግዲህ ይህንን ለመረዳት በተራ ቁጥር አንድ ላይ ቤተ ክርስቲያኒቱ እንዴት ስርዓት እንደምታወጣ ከተመለከትን ከቤተ ክርስቲያን መዋቅር ስር በሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ ስር የሚገኘው ማኅበረ ቅዱሳን በምን ስልጣኑ ነው ስለ ቀኖና መቀነን ሥራ ገባ የተባለው።ደግሞስ በእዚህ ዘመን ስንት ያላመኑ ለማሳመን እንደመጣር በእየጭፈራ ቤት ማድመቅያ የሆነውን የሙዚቃ መሳርያ ከቤተ ክርስቲያን ካልገባ ብሎ ያዙኝ ልቀቁኝ ምን የሚሉት ፈሊጥ ነው? በእዚህም ሳብያ የቤተ ክርስቲያን ሌላ እራስ ምታት ለመሆን መሮጥ ምን አይነት አለመታደል ነው?

3/ ለምን ኦርጋን ተፈለገ?

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተ ክርስቲያን ኦርጋን እንድትጠቀም የሚወተወትበት በተለይ በባእዳን በኩልም ጭምር የሚቀነቀነው ከሶስት ፍላጎቶች አንፃር ነው።
አንደኛው የቤተ ክርስቲያንም ሆነ የኢትዮጵያ መለያ እና ብቸኛ ባለቤት የሆነው የያሬዳዊ ዜማን ለማስጣል እና አገሪቱን ካለ አንዳች መለያ ማስቀረት፣ 
ሁለተኛ፣ በእዚህ ሳብያ የኢትዮጵያ ታሪክን በዋናነት የያዘችው ቤተ ክርስቲያንን መሰረታዊ መለያ መበረዝ የኢትዮጵያን ህልውና ማሽመድመድ ነው ከሚል እሳቤ አፍሪቃዊቷን ቤተ ክርስቲያን አውሮፓዊ ካባ ለማልበስ የሚደረግ እሩጫ እና 
ሶሥተኛው ምክንያት በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ከፍተኛ መተራመስ ለመፍጠር የሚንቀሳቀሰው ለባዕዳን በማደር እና ጧት ማታ ባዕዳንን በማድነቅ የቤተ ክርስቲያንን እና አባቶች ያቆዩትን ስርዓት ለመናድ የሚጣጣረው እና  ባለፈው ሰኔ/2007 በርካታ ገፆች አትሞ በድብቅ የነበረውን ስራውን በይፋ ማውጣቱን የገለፀው ''የተሃድሶ እንቅስቃሴ'' በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ልዩነት የመፍጠርያ ነጥብ ያገኘ መስሎት ስለሚያራግበው ነው።

ከእዚህ በታች ''አንድ አድርገን'' ድረ-ገፅ ላይ የያረዳዊ የቤተ ክርስቲያናችንን ዜማ በባዕዳን መቀየር የሚመክሩትን አስመልክቶ ከሁለት ዓመት በፊት የወጣ ፅሁፍ የድርጊቱን እኩይ አላማ ስለሚያሳይ እንዳለ አቀርበዋለሁ።



''ከአበው ከወረስናቸው በርካታ መንፈሳዊ ርስቶቻችን አንዱ መንፈሳዊው ዜማ ነው።ይህ መንፈሳዊ ዜማ አባቶቻችን ከእግዚአብሔር የተቀበሉትና ከእርሱ ጋር የተገናኙበትእኛም ተግተን ብንጠብቀው ወደ ሰማያዊ ኅብረት የምንነጠቅበት መሰላል ነው። መንፈሳዊው ዜማ በዓለም ካሉት ሀገራት ይልቅ ለኢትዮጵያ ተለይተው ከተሰጡሃብታት አንዱ ነው። ኢትዮጵያ ከታላቁ አባት ከቅዱስ ያሬድ የተቀበለችው የዜማርስትም ጣዕሙን ለሚያውቀው በጦር መወጋትን እንኳን  ህመሙን ያስረሳ ነው (በቅዱስ ያሬድ ዜማ የተመሰጡት አፄ ገብረ መስቀል በጦር  የቅዱስ ያሬድ እግር ላይ በትረ መስቀላቸውን መትከላቸው እና  ሁለቱም ተመስጠው ሲነቁ መመልከታቸው) ፡፡ይህን የዜማ ርስት ግንበዚህ ዘመን አልሰጥም ብሎ እንደ ናቡቴ የሚጠብቅ አልተገኘም ፤ ንጉሥ አክዓብለናቡቴ ያቀረባቸውን ሁለት አማራጮችም በዘመናችን ትውልዱ በደስታ ተቀብሎትይገኛል፡፡
ለናቡቴ የቀረበው የመጀመሪያው ምርጫ የአባቶችን ርስት ወስጄ ሌላ ርስትንልስጥህ › የሚል ነበር።በዚህ ዘመንም ከአባታችሁ ከቅዱስ ያሬድየተቀበላችሁትን ዜማ ትታችሁ ሌላ ያሬዳዊ ያልሆነ ዜማን እናሰማችሁ ባዩ በዝቷል።ይህንንም ጥሪ ተቀብሎ ያሬዳዊ ያልሆነን ዜማ ማድመጥና ማድነቅ የተለመደ ሆኗል፡፡
ሁለተኛው የናቡቴ ምርጫ ደግሞ ‹ገንዘብ ልስጥህ ርስትህን ስጠኝ› ነበር።ይህን አይነቱንም መንገድ ዛሬ ብዙዎች የቀደመውን የዜማ ርስታችንን ለመጣላችን መንስኤነው።የናቡቴና የእኛ ዘመን ነገር ልዩነቱ ናቡቴ በንጉሥተገድዶም እንኳን ርስቱን ሳይሰጥ የሞተ ሲሆን ይህ ትውልድ ደግሞ በራሱ ፍላጎትርስቱን እየሸጠና እየለወጠ መሆኑ ነው።ያሬዳዊ ዜማ የአንድ ወገን ባሕል ሳይሆን እግዚአብሔር በቀጥታ ለቤተ ክርስቲያን ዘኢትዮጵያ የሰጠው መንሳዊ ጸጋ ነው።ያሬዳዊውን ዜማ ማጣጣልና መቃወም ቤተ ክርስቲያኒቱን መቃወም እንጂ የተወሰኑግለሰቦችን መቃወም አይደለም፡፡'' 

በመጨረሻም ፅሁፌን ለመደምደም የምፈልገው በአንድ አረፍተ ነገር ነው።ሰውን መውደድ፣ አባትን መውደድ ወይንም ማድነቅ አንድ ነገር ነው።የሚወዱትን አባት የሚለውን ሁሉ የቤተ ክርስቲያኒቱ ቀኖና አስመስሎ ለምዕመናን ማቅረብ ግን የቤተ ክርስቲያንን ስርዓት አለማወቅ ነው።አርጋኖን እና ኦርጋን ምን አገናኛቸው? ሰውን እንፈር፣እግዚአብሔርንም እንፍራ!

ጉዳያችን GUDAYACHN
www.gudayachn.com

የካቲት 5/2008 ዓም  (ፈብሯሪ 13/2016)

ማጣቀሻ 

+  አንድ አድርገን ድረ-ገፅ 2006 ዓም 
+  መፅሐፍ ቅዱስ 
+  አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ልዩ መርሐ ግብር ግንቦት 10 እስከ 12 www.danielkibret.com 



ሐያ ገዳማት የሚገኙበት በግሪክ የሚገኘው የአቶስ ተራራ ገዳማውያን አኗኗር (ቪድዮ)

ገዳሙ ከሰርብያ፣ሮማንያ፣ቡልጋርያና ሩስያ የመጡ ዓለምን የናቁ መነኮሳት ገድመውበታል።