ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Monday, February 1, 2016

ሰበር ዜና - አርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊቱ ከኤርትራ በተጨማሪ ኢትዮጵያ ውስጥ መኖራቸውን ገለጠ (ጉዳያችን ዜና)ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ (ፎቶ ዘሐበሻ ድረ-ገፅ)

በፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የሚመራው አርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ ሰራዊቱ በኢትዮጵያ ውስጥ እንደሚገኝ ገለጠ።የድርጅቱ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ትናንት ዕሁድ ጥር 22/2008 ዓም ዋሽንግተን፣ደብል ትሪ ሂልተን ላይ በተጠራ ሕዝባዊ ስብሰባ  ባደረጉት ንግግር “ወታደሮቻችን ያሉት ኢትዮጵያ ውስጥ ነው፤ ትግላችንን ለመቀላቀል ካሁን በኋላ  ለምትፈልጉ  ወደ  ሰሜን ብቻ  መሄድ  የለባችሁም”   ብለዋል።


የፕሮፌሰር ብርሃኑ ንግግር በበርካታ የኢትዮጵያውያን የአካባቢ ራድዮኖች፣የፓልቶክ እና ልዩ ልዩ ድረ-ገፆች የቀጥታ ስርጭት ሽፋን አግኝቷል። በእዚሁ በጭብጨባ በታጀበ ንግግራቸው ላይ ፕሮፌሰር ብርሃኑ በቀጥታ ስልክ እና በአካል ከተገኙ ታዳሚዎች ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሾችን ሰጥተዋል።የኢትዮጵያ ችግር (የብሔር ጥያቄዎችን ጨምሮ) መፍትሄ የሚያገኙት ሕዝብ የመረጠው እና የተስማማበት መንግስት ስልጣን ላይ ሲወጣ መሆኑን የገለጡት ፕሮፌሰር የሕዝቡ የብሔር ግንኙነትን  አስመልክቶ በአገር ቤት ያለው ከውጭው በተሻለ  የግንኙነት ሁኔታ ላይ  መኖሩን ጠቁመዋል።

በመቀጠልም ''መማር ማለት እኮ ዕውነትን መፈለግ ነው'' በማለት ምሁራንን አሳስበው፣ ምሁራን የሚያምኑበትን ለመፃፍ የሚፈሩበት ሁኔታ ከትምህርት ዓላማ ጋር ምን ያህል ተቃርኖ እንዳለው አፅንኦት ሰጥተው አስረድተዋል።በሌላ በኩል በኦሮምያ የተከሰተው የሕዝብ ጥያቄን ሁሉም ሊደግፈው እንደሚገባ እና ስርዓቱ ሕፃናት እና ነፍሴ ጡሮችን በመግደል ጭካኔውን እያሳየ እንደሚገኝ አብራርተዋል። 

በኤርትራ የሚደረገው ትግል አዋጪነት ላይ ለተነሳ ጥያቄ ''ለእኔ ደቡብ ሱዳን ከሚረዳኝ እንኳንም ኤርትራ እረዳን፣ እኛ ፈልገን በኤርትራ መንግስት ምክንያት የቀረብን አንዳችም ሥራ የለም።እኔ ኤርትራ 7 ወራት ተቀምጫለሁ።በኤርትራ እና በኢትዮጵያ መካከል ልዩነት ማግኘት አልቻልኩም። ጧት ስትነሳ የገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ድምፅ ትሰማለህ፣መንገድ ላይ አማርኛ ስታወራ ዘወር ብሎ የሚያይህ የለም'' ብለዋል።

በመጨረሻም ፕሮፌሰር ብርሃኑ በቀጥታ የስርጭት ቪድዮዎች  ላይ እንደሚታዩት  (የተሟላ ቪድዮ ገና አልተለቀቀም) ከእዚህ ቀደም ከነበራቸው ንቃት እጅግ በበለጠ መልኩ መታየታቸውን ብዙዎች የሚሰጡት አስተያየት ሆኗል።ፕሮፌሰር ብርሃኑ ከአንድ ወር በፊት በብራስልስ፣ቤልጅየም በአውሮፓ ህብረት ፊት ተገኝተው ንግግር ባደረጉ በቀናት ውስጥ የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ መንግስት ላይ አሳሪ  የሆነ የውሳኔ ረቂቅ አቅርቦ ማሳለፉ ይታወሳል።  

ጉዳያችን Gudayachn 
ጥር 23/2008 ዓም (ፌብሯሪ 1/2016)No comments:

ወቅታዊ የዓለም ሁኔታ እንድንነታረክ ዕድል የሚሰጥ አይደለም።ብንነቃ መልካም ነው።

========== ጉዳያችን ወቅታዊ ========== የዓለም ታሪክ እንደሚያስተምረን ዓለም በወሳኝ የእጥፋት(turning point) ታሪኮች ውስጥ አልፋለች። እነኝህ የእጥፋት ጊዜዎች የዋዛና የፈዛዛ ጊዜ አይደሉም።መላው ዓለ...