ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Tuesday, December 31, 2013

ስለ ዳግማዊ ምንሊክ የ'' ኒዎርክ ታይምስ '' ጋዜጣ (ኅዳር 7/1909 ዓም እ ኤ አቆጣጠር) የዛሬ 96 አመት የፃፈው ፅሁፍ ለአሁኑ ትውልድ ታሪካዊ ማስረጃ ነው


ጉዳያችን ጡመራ ታህሳስ 22/2006 ዓም
ዳግማዊ አፄ ምንሊክ ፎቶ 

ኢትዮጵያ በየዘመኗ በሕልውናዋ ላይ የተቃጣባት የመበታተን አደጋን ያለፈችበት መንገድ የጦርነት መንገድ ብቻ አይደለም።ሆኖም ግን ከነበሩን የግጭት ታሪኮች በዘለለ በሕዝብ ዘንድ ተወዳጅ የነበሩ እና በሕዝብ ዘንድም የተወደዱ  መሪዎች ነበሩን።ከእነኝህ ውስጥ ዳግማዊ ምንሊክ አንዱ ነበሩ። አፄ ምንሊክ ሀገር የማስተዳደር ጥበብን የተማሩት በአፄ ቴዎድሮስ እጅ ሆነው እድገታቸውን በንጉሡ ቤተመንግስት ማድረግ ከጀመሩበት ጊዜ ጀምሮ መሆኑን ብዙዎች ይስማማሉ።ንጉሡ የቀደሙ አባቶቻቸው አፄ ቴዎድሮስ እና አፄ ዮሐንስ ኢትዮጵያን አንድ የማድረግ አላማቸው እውን እንዲሆን ያደረጉ እድለኛ ንጉስም ናቸው።

አፄ ምንሊክ ኢትዮጵያን አንድ ከማድረግ አልፈው እስከ ኬንያ፣ሱዳን እና ሱማልያ ግዛት ድረስ ዘልቀው ገብተው በቅኝ ግዛት ይማቅቁ የነበሩ ህዝቦችን ነፃ ያወጣሉ የሚል ስጋት የነበረባቸው  እና በወቅቱ በእነኚሁ የጎረቤት ሃገራት  ላይ የጥቅም ፍላጎት የነበራቸው የአውሮፓ ሃገራት በብርቱ ተፈታትነዋቸው ነበር።በመሆኑም አዲስ የድንበር ውል ከኢትዮጵያ ጋር የመፈራረም ፍላጎት ከእንግሊዝ፣ፈረንሳይ እና ኢጣልያ በኩል ጥያቄ መነጻቱን የወቅቱ የታሪክ ድርሳናት ያወሳሉ።

ዛሬ ዛሬ በምንሊክ ላይ ታሪካዊ መሰረት የሌላቸው ቀድሞ አፄ ምንሊክ የቅኝ ግዛት ጥማታቸውን በገቱባቸው እና ቂም በያዙ ፀሐፊዎች የተፃፉ ናቸው ብለው ከሚነግሩን አስገራሚ ''የታሪክ'' ፅሁፎች ውስጥ ''በምኒሊክ ዘመን እስከ አስር ሚልዮን ኦሮሞዎች አለቁ'' የሚል ፅሁፍ በአንዳንድ የማህበራዊ ድህረ ገፆች ተለቀው ሲነበቡ መመልከት  አስገራሚ የሰሞኑ ክስተት ነው።በፖለቲካው አለም በቂ ርዕዮተ አለምም ሆነ ፖለቲካዊ ፍልስፍና የጠፋባቸው አንዳንድ ወገኖች ''ትርፋማ'' ብለው ያሰቡት የዘር ፖለቲካ በኢትዮጵያውያን መካከል መዝራት እና ከመቶ አመት በፊት  የሆነውን የታሪክ ክስተት የአሁኑን ትውልድ በመውቀስ ትኩረት ለማግኘት ሲታትሩ መመልከት የዘመኑ አስቂኝ ተውኔት ነው።ዳግማዊ ምንሊክ ገና ብዙ የሚጠና ፖለቲካዊ፣ማኅበራዊ እና ወታደራዊ ክህሎት ባለቤት ለመሆናቸው በወቅቱ ከወጡት የዓለማችን ድንቅ ጋዜጦች አንዱ የ ኒውዮርክ ታይምስን እትም መመልከት ይበቃል።

ከእዚህ በታች በሚገኘው የኒውዮርክ ታይምስ ኅዳር 7/1909 ዓም እ ኤ አቆጣጠር እትም ላይ የኢትዮጵያ ጠቅላላ ሕዝብ ብዛትን 7,000,000 (ሰባት ሚልዮን) መሆኑን ያስቀምጣል። እዚህ ላይ አንዳንድ እራሳቸውን የታሪክ ምሁራን ነን በሚል ባልተጨበጠ ይልቁንም በምኒሊክ የቅኝ ግዛት ህልማቸው ከተደናቀፈባቸው ቂመኛ ፀሐፊዎች አነበብን የሚሉት እና የኦሮምኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያንን ያማለሉ መስሏቸው  ''ምንሊክ 10 ሚልዮን ኦሮሞ ገደሉ'' እያሉ ኢትዮጵያ ከነበራት የህዝብ ብዛት (7 ሚልዮን) በላይ  ቁጥር ሲጠሩ እፍረት አልተሰማቸውም።

''ማን ያውራ የነበረ'' እንዲሉ የኒውዮርክ ታይምስ  ጋዜጣ ኅዳር 7/1909 ዓም እ ኤ አቆጣጠር እትም ላይ ጋዜጣው አዲስ አበባ በነበረ  በልዩ ዘጋቢው አማካይነት ስለንጉሡ እና ኢትዮጵያ ፖለቲካዊ እና ምጣኔ ሃብታዊ ሁኔታ ፅፎ ነበር።ጋዜጣው  አፄ ምንሊክ እና አስተዳደራቸውን ከገለፀበት አረፍተ ነገር  ውስጥ እነኝህ ይጠቀሳሉ  -

 - ኢትዮጵያን ወደ ህገመንግስታዊ የንጉሥ አስተዳደር ለመቀየር ሂደት ላይ መሆኗን፣

 - የኢትዮጵያ ህዝብ ብዛት 7 ሚልዮን መሆኑን፣

 - አፄ ምንሊክ ንጉሰ ነገስት ሲሆኑ ጦርነት የነበረው የአፄ ዮሐንስ ተተኪ  እሳቸው መሆናቸውን ካልተቀበሉት ጋር ብቻ እንደ ነበር፣

 - የአውሮፓውያንን ስልጣኔ ወደሀገራቸው ለማምጣት የባርያ ንግድን ከመዋጋታቸውም በላይ ነፃ ትምህርት ዕድል ዜጎች እንዲያገኙ መሰረት መጣላቸውን፣

 - ምንሊክ እራሱ ልዩ ችሎታ ያላቸው ሰው መሆናቸውን። ከችሎታዎቻቸው መካከል  ዲፕሎማት፣የፋይናንስ ባለሙያ እና  ወታደር የሚሉት እንደሚጠቀሱ እና

 - እንደ ዲፕሎማት እና ወታደር የጣልያንን ወረራ ኢትዮጵያ እንድታሸንፍ ያደረጉበት ጥበብ መሆኑን፣

 የሚሉ ይገኙበታል።የጋዜጣውን ሙሉ ፅሁፍ ከእዚህ በታች ያለውን ሊንክ ከፍተው ያንብቡ።

 የኒውዮርክ ታይምስ  ጋዜጣ ኅዳር 7/1909 ዓም እ ኤ አቆጣጠር እትም ለማንበብ ይህንን ሊንክ ይክፈቱ።

Published: November 7, 1909 Copyright © The New York Times

http://query.nytimes.com/mem/archive-free/pdf res=F50A12F63A5A15738DDDAE0894D9415B898CF1D3 



Friday, December 27, 2013

'' ሆድ ያባውን ንግግር ያወጣዋል''- የጀዋር መሐመድ እና መሰሎቹ ፅንፈኛ 'ሜጫዊ' አስተሳሰብ አላማው ህዝብን ማፋጀት ነው!

('ሜጫ' የሚለውን ቃል ከጀዋር ንግግር አገባብ መረዳት እንደሚቻለው ካራ፣ጎራዴ ለማለት ተጠቅሞበታል)
 በአሜሪካዋ ሚኒሶታ ግዛት ሁለቱ ''አክቲቪስት'' ጀዋር መሐመድ እና ሃጂ ነጂብ መሐመድ ያደረጉት ንግግር አስደንጋጭ እና አሳሳቢ ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያ በመጪው ግዚያት  የሚገጥሟትን ተግዳሮቶች የሚያመላክትም ጭምር ነው። የጀዋር መሐመድ ''ሙስሊም  ያልሆነውን'' እንደርሱ አገላለፅ እርሱ በተወለደበት አካባቢ ''በሜጫ አንገቱን እንደሚቀላ'' የተናገረበት እና ሃጅ ነጂብ መሐመድም በተራቸው ''ከኦሮሞ ተወላጅ ባብዛኛው (ከ80% በላይ) ሙስሊም ነው .....በኢትዮጵያም እንዲሁ ከ ሃምሳ ሚልዮን በላይ ነን.....'' ሲሉ ተደምጠዋል። ሁለቱም የሜኖሰታ ተናጋሪዎች ከእዚህ ቀደም በሙስሊም ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ላይ እየደረሰ ያሉትን መንግስታዊ የአስተዳደር በደሎች ለማስተጋባት ''ድምፃችን ይሰማ'' በሚሉ መድረኮችም ሆኑ ሌሎች መድረኮች በማስተጋባት መታወቃቸው ብዙ ግን አስፈላጊ ጥያቄዎች እንዲነሱ በር ከፍቷል።

በሀገራችን ካለው የፖለቲካ፣የሃይማኖት፣ወዘተ በደሎች አንፃር የእስልምና ወንድሞቻችን የሚያነሱዋቸው ጥያቄዎች በትክክለኛ በኢትዮጵያ አንድነት፣ነፃነት እና ዲሞክራሲ በሚያምኑ ወገኖች አማካይነት ሲነሳ እና ሲመራ ማየት የሁሉም ሀገር ወዳድ ወገን ፍላጎት ነው።ከእዚህ በዘለለ ግን ጉዳዩ የአክራሪነት እና የፅንፈኝነት ስሜት በያዙ ወገኖች እሳት ዳር እንደሚጫወት ሕፃን ያሻቸውን ሲያደርጉ መመልከት ደግሞ ተገቢ አይደለም።

ጉዳያችን ጡመራ ባለፈው አመት ጥቅምት 2004 ዓም ላይ ''የሙስሊሙ ጉዳይ'' በሚለው ርዕስ ስር እንቅስቃሴው ወዴት ሊያመራ ይችላል? በሚል ከእዚህ በታች ያለውን ሁለት ስጋቶች አስቀምጣ ነበር።

''ጉዳያችን ጡመራ'' ቀ 27 ወራት በፊት (ጥቅምት/2004 ዓም) የነበራት ስጋት

  • ''የ ሙስሊም ፅንፈኛ ቡድን'' የ ሙስሊሙን ጥያቄ  የመሪነት ሚና ለመያዝ ቀና ማለት 
አልፎ አልፎ ብቅ ሲል የነበረው በ ሙስሊሙ ሃይማኖት ስም የሚንቀሳቀሰው ''የ ሙስሊም ፅንፈኛ ቡድን'' ከ ቢጫ ቀጥሎ ይወሰዳል ለተባለው እርምጃ የመሪነት ሚናውን ለመያዝ ቀና ቀና ማለቱ አይቀርም።በ ኢትዮጵያ ከ ቅርብ አመታት ወዲህ በ ጅማ፣ሐረር፣እልባቦር እርሲ ወዘተ እነኝህ ፅንፈኛ ቡድኖች በ አብያተ ክርስትያናት እና ምእመናን ላይ ጥቃት ሲፈፅሙ እንደነበር ይታወሳል።በመሆኑም  የ ሙስሊም ወንድሞቻችን እና እህቶቻችንን የማይወክሉ ግን ለ እራሳቸውም እንግዳ ትምህርት ይዘው የመጡባቸው  ክፍሎች የ እዚህ አይነቱን  ቀይ ካርድ መምጣት ''ሰርግ እና ምላሽ '' አርገው እንደሚመለከቱት ሳይታለም የተፈታ ነው። እዚህ ላይ በ ነሐሴ ወር ላይ የ ''አልሸባብ'' ሰዎች ሳይሆኑ አይቀሩም የተባሉ በ ከፍተኛ ደረጃ የታጠቁ ቡድኖች  በሞያሌ ከተማ ላይ ያደረጉት ጥቃት አይዘነጋም።
  •  በ አፍሪካ ቀንድ ለዘመናት ችግር ሲፈጥር የነበረው አለም አቀፍ አክራሪ እስልምና መነቃቃት ይጀምራል።
  
 አፍሪካ ቀንድ ለዘመናት ችግር ሲፈጥር የነበረው አለም አቀፍ አክራሪ እስልምና በመነቃቃት  ኢትዮጵያውያን  ፅንፈኝነት አስተሳሰብ ያላቸውንሙስሊሞች  መንግስት ስልጣን ጥያቄ እንዲያነሱ እና ኢትዮጵያ ''እስላማዊ መንግስት'' እንዲኖራት ወደሚል ግብ እንዲሄዱ ይህን ካደረጉ ብቻ  ጎናቸውእንደሚቆም ግፊቱን ሊያደርግ ይችላል። ይህንን ደግሞ ብዙ ሙስሊም ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን አይደግፉትም።  እዚህም ነው ጥያቂያቸውን ጥንቃቄ እና  ሰላማዊ መንገድ ብቻ  ማቅረብ ብዙውን ሕዝብ ያስደመሙት።  እዚህ በተጨማሪ  አለም አቀፍ ፅንፈኛ  እስልምና እንቅስቃሴ ኢትዮጵያ ቦታ ካገኘ ሁለት መሰረታዊ ክስተቶች  ሀገራችን ላይ ሊያመጣ ይችላል። እነርሱም አንድ  ሃያላኑ መንግሥታት ጣልቃ ገብነት ቢያንስ  ቁሳቁስእና  ቴክኒክ እርዳታ ነገሩን ማወሳሰብ እና ሁለተኛው  እስልምና ውጭ በሆነው ኢትዮጵያዊ ጋር ከፍተኛ ፍጥጫ ውስጥ መክተቱ የሚሉት ይጠቀሳሉ።'' (ጉዳያችን ጡመራ ጥቅምት/2004 ዓም http://gudayachn.blogspot.no/2012/10/blog-post_5.html ) 

ዛሬ ጀዋርም ሆነ ሃጅ ነጂብ መሐመድ እያመላከቱን ያሉት ይህንኑ ነው።የዲሞክራሲ ጥያቄን በድምር የመመለስ አባዜ ማለትም ችግሩ የብሔር እገሌን ችግር መፍታት፣የሃይማኖት እገሌን ችግር መፍታታ፣ ወዘተ የሚሉ የአምባገነንነትን መጫኛ ፈረስ ማዘጋጀት የተበላ ዕቁብ ከመሆን አያልፍም።ጀዋርም ሆኑ ሃጅ ነጂብ መሐመድ በመኖሶታው መድረክ ሊነግሩን የፈለጉት ''ውሃ ቢወቅጡት እምቦጭ'' መሰል ላለፉት ሃያ አንድ አመት ስንሰማው የነበረውን ''ኢትዮጵያን በብሄር ከፋፍሎ አላማን ማሳካት'' የሚለውን ያፈጀ መዝሙር መሰል ማላዘን ነው።እነርሱ የጨመሩበት ነገር ቢኖር ''በኦሮሞ ስም የታሸ አዲስ እስልምና'' ያለ መሆኑን ለመናገር ደፋርነት ማሳየታቸው ነው። ይህ ሂደት በእራሱ በወንድማማችነት የኖረውን የእስልምናውን ሃይማኖት የሚጣረስ እና በሃይማኖቱ ብሔር ብቻ ሳይሆን የሀገር ድንበር የማይገድበውን በአለማችን ካሉት ታላልቅ አምነቶች አንዱ -እስልምናን እንደነርሱ አገላለፅ ''በኦሮሞነት'' ስር መሸበብ ነው።

በመሰረቱ የኢትዮጵያ የእውነተኛ ዲሞክራሲ ጥያቄ በግለሰቦች ''ሜጫዊ'' ''ቁረጠው!ፍለጠው!'' ንግግር እና ጣልያን ኢትዮጵያን ሲወር በተጠቀበት መርዛማ ንግግር ብሄርን ከብሄር አልያም የሃይማኖት ተከታይን ከሃይማኖት ተከታይ በማበላለጥ አይሰናከልም። በብሄር እና በሃይማኖት ለመከፋፈል የቆሙ የመኖራቸውን ያህል ለኢትዮጵያ አንድነት እና ለእምነቶች መከባበር የቆሙ ሚሊዮኖች ኢትዮጵያ እንዳላት መዘንጋት አይገባም።የጀዋር መሐመድ እና የሃጅ ነጂብ መሐመድ ንግግር ግን የመብት፣የዲሞክራሲ እና የአንድነት ትግሉን ጠልፎ ወደ አለተፈለገ አቅጣጫ የመግፋት የግል ስሜታቸውን ከመግለፅ ባለፈ የሚያመጣው አዲስ ነገር አይኖርም። ይልቁን ''ሆድ ያባውን ንግግር ያወጣዋል'' የሚል ስያሜ መስጠት ግን የሁለቱን ንግግሮች በበቂም ባይሆን በመጠኑ የሚገልፀው ይመለኛል።
 በመጨረሻም የጀዋር መሐመድ እና የሀጂ ነጂብ መሐመድን ንግግር ይመልከቱ።




ጉዳያችን GUDAYACHNgetachewb221@gmail.com

Thursday, December 26, 2013

ድንበር የማይቀዘቅዝ ትኩስ ደም ነው። የኢትዮጵያ እና የሱዳን የድንበር ውል ዝርዝር ጉዳይ ከሕዝብ ሊደበቅ አይገባም።

አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ከሁለት ሳምንት በፊት በሱዳን ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወቃል።በእዚህ ጉብኝት ላይ አቶ ኃይለማርያም ''እጅግ ለም የሆነ  የኢትዮጵያ መሬት ለሱዳን ለመስጠት ተስማምተዋል አሁን የቀረው ችካል ማስቀመጥ ነው'' የሚል ዜና በኢሳት ሲዘገብ ቀናት ነጉደዋል።ትናንት ታህሳስ 16/2006 ኢሳት በአለም አቀፍ ራድዮ ስርጭቱ ላይ የኢትዮጵያ የድንበር ጉዳይ የሚከታተሉ  'የኢትዮጵያ ድንበር ኮሚቴ' የተሰኘ ኮሚቴ አባላትን በቃለ መጠይቅ አቅርቦ ነበር።እንደ ኮሚቴው ገለፃ ከሆነ አሁን ''የኢትዮጵያ መንግስት ለሱዳን  ለመስጠት መስማማቱ የሚነገረው መሬት ከቀድሞ ጀምሮ በኢትዮጵያ ይዞታ ላይ ያለ አሁንም  ገበሬዎች የሚገኙበት እና ባዶው ቦታን ጨምሮ በትንሹ ካለምንም ማጋነን 15 ሚልዮን ሕዝብ አስፍሮ መመገብ የሚችል ቦታ ነው።15 ሚልዮን ልብ በሉ! 

በሕዝብ ስም የሚደረግ ማንኛውም ውል ከህዝብ ሊደበቅ አይገባውም።ድንበር የማይቀዘቅዝ ትኩስ ደም ነው።ይህ ደም ደግሞ ለዘመናት የኢትዮጵያ አባቶች እና እናቶች ያፈሰሱት ደም ነው።ማንም መንግስት በሕዝብ ደም ሊደራደርም ሆነ ድንበር ሊሰጥ አይችልም።ለአንድ 'ኩርማ' መሬት 'ለባድሜ' በሺዎች ላረገፈ ጦርነት ክተት ያወጀ  መንግስት 15 ሚልዮን ሕዝብ የሚያሰፍር መሬት ለሱዳን ለመስጠት መነሳቱ በቁም እየተሸጥን ለመሆኑ ማሳያ ነው። በትዊተር በብዛት የሚታዩት ባለስልጣናት ከሌላው ዜና ይልቅ የእዚህ አይነቱን ቅድምያ ሊሰጡት በተገባ ነበር።ድንበር የማይቀዘቅዝ ትኩስ ደም ነው።
ፊልሙ  መጨረሻ ላይ ሲናገር የምትመለከቱት የስርዓቱ አቀንቃኝ ይመስላል።በጋራ ''አሸባሪዎችን ይዋጋሉ'' የሚለው ጌቶቹ መሬቱን ሸጠው እንደጨረሱ በገደምዳሜ እየነገረን ነው።በመጀመርያ እንደዚህ አይነት አካባቢ አገር ጎብኚ ሲመጣ  እንዲያስተናግድ የሚፈቀድለት የስርዓቱ  ሹም ነው።በመሆኑም በጋራ ድንበር እየጠበቁ ነው ይለናል።አገር ጎብኝዋ ግን ''እህ!'' በማለት ውሸቱን ማወቅ መቻሏን ትገልፃለች። 



ጉዳያችን GUDAYACHN BLOG

Wednesday, December 25, 2013

ከትዝታዬ


ከትዝታዬ የሚሉ በጣም አጫጭር ጽሁፎች አልፎ አልፎ ጣል ለማድረግ ማሰቤን ልግለጽና ለዛሬ ይህችን ላካፍላችሁ። በደርግ መውደቅያ ዘመን አካባቢ አዲስ አበባን የምናውቃት በታክሲ ውስጥ፣በትምህርት ቤት፡ መምህራን፣ ካፌ ቤት፣ሰራተኞች ከስራ ባልደረቦቻቸው ጋር  በነጻነት (ሌላውን ነጻነት ትተን) በትግርኛ፣ኦሮምኛ ድምጻቸውን ከፍ አድርገው ይናገሩ ነበር።

ከሚኒባሱ ጋቢና የተቀመጠ ሰው ከኋላ ለተቀመጠ ወዳጁ በትግርኛ ድምጹን ከፍ አድርጎ ያወራ ነበር።በአውቶቡስ ውስጥም ኦሮምኛ ሆነ ጉራጊኛ ህዝቡ ካለ አንዳች መሳቀቅ ይናገር ነበር። ሁሉም ተከባብሮ ይኖር ነበር።ሌላ ቋንቋ ለመናገሩ አንዳች መሳቀቅ አይሰማውም።

ዘመኑ በደንብ ትዝ ይለኛል 'ጋሽ ተስፋ ጽዮን' የሚባሉ የሳይንስ መምህር ትምህርት ቤታችን ውስጥ ቮሊቮል መጫወት ይወዱ ነበር።ሲጫወቱ በትግሪኛ እያውሩ ነበር ኳሱን የሚሰርቡት... ጋሽ መገርሳ የእስፖርት አስተማሪያችንን አልረሳቸውም ኦሮምኛ የሚችሉ ልጆች ጋር በኦሮምኛ ይቆጧቸው ነበር፣ ኮሜርስ ስገባ ጎይቶም የሚባል በጣም የማዝንለት ጓደኛ ነበረኝ።ጎይቶም የአክሱም ልጅ ነው።አባቱ በህወሃት እስር ቤት መሆኑን ከእናቱ ጋር ወደ አዲስ አበባ መምጣቱን ይነግረን ነበር።ጎይቶም ትግሪኛ ሲናገር ባይገባንም ጓደግኞቹ የተለየ ንግግ ር የተናገረ ያክል አይሰማንም።እርሱም ደስ ብሎት አውርቶ ቀጥሎ ወደ እኛ ዞሮ አማርኛ ያወራናል... አዲስ አበባ ንግድ ስራ ኮሌጅ ሬጅስትራር ክፍል ስንሄድ ኦሮምኛ የሚናገሩ ሰራተኞች ብዙ ነበሩ።ይህ ቢሮ ውስጥ ነው የማወራው። ማንም ቅር አይለውም።ልዩነትም የለውም።

... መከላከያ ፊት ለፊት ያለው ትልቁ ኢትዮዽያ ንግድ ባንክ ለስራ ልምምድ ስላክ ብዙ አለቆች የእረጅም ጊዜ የስራ ልምድ ያላቸው የተከበሩ አባቶች የሚባሉ የትግራይና የኤርትራ ተወላጆች ነበሩ።በሻይ ሰኣት ሁሉም ዘና ብለው በትግሪኛ ያወራሉ ይጫወታሉ።ሁላችንም 'ጋሼ እትዬ' ብለን የታዘዝነውን እንሰራ ነበር... ብላቴ ስንሄድ ብዙ የተለያዩ ቋንቋ ተናጋሪዎች በየቋንቋቸው ይናገሩ ነበር።
ይህ ውበት ዛሬ ኢትዮዽያ የራቃት ይመስለኛል። ህዝቡን ጎሰኞች ስለ ጎሳ ብዙ በማውራት አሳቀቁት። ዛሬ ስለ ጎሳ አብዝቶ የሚያወራው መንግስት ከመጣ ወዲህ ወገኔ ተሳቀቀ።ነቀምት ሲገባ አማርኛ መናገር፣ጉራጊኛ ማውራት ተሳቀቀ።አዲስ አበባ ሲገባ ከ አራዳ ቋንቋ ሌላ ማውራት የሚያሳቅቀው ሆነ። የጎሳን ነገር  መንግስት ቤተ መንግስት አስገብቶ እንደፈለገው አብኩቶ ህዝቡን አሳቀቀው።ህዝቡ የእራሱ የሆነ የመከባበር ዘይቤው ጠፋው።ዘረኞች ፋታ አገኙ።ህዝቡን ናኙበት።ዛሬ በነጻነት ድምጹን ከፍ አድርጎ የሚያወራው አዲስ አበባ ላይ  በስደት ላይ የሚገኙ ሱማሌዎች ብቻ ሆኑ።እነርሱ ታክሲ ውስጥም ጮክ ብለው ያወራሉ።ሌላው አፈረ።ይህች ነች የብሔር ብሄረሰብ መብት? ሕዝብ መከፋፈል ለስልጣን ጥበቃ።

ታህሳስ 16/2013 ዓም 


Sunday, December 22, 2013

የኢትዮዽያ መጪው ትውልድ ሳይንቲስቶች እና አላማዎቻቸው (ቪድዮ)




ከሰይፉ ፋንታሁን ኢቢኤስ ዝግጅት የተገኘ

ጉዳያችን GUDAYACHN BLOG

Thursday, December 19, 2013

ሰበር ዜና-በደቡብ ሱዳን የሪክ ማቸር ኃይሎች ውግያ ጀመሩ። ትናንት ምሽት ቁልፏን ከተማ ቦርን ተቆጣጠሩ።ኢትዮጵያና ዑጋንዳ በደቡብ ሱዳን አንፃር (ጉዳያችን አጭር ዘገባ ታህሳስ 10/2006 ዓም)


ደቡብ ሱዳን ቦር ከተማ (photo Reuters)

በደቡብ ሱዳን የተቃዋሚ ኃይሎች ከሀገሪቱ ዋና ከተማ ጁባ በ 200 ኪሎሜትር  እርቀት ላይ የምትገኘውን 'ቦር' የተሰኘችውን ቁልፍ የደቡብ ሱዳን ከተማ ተቃዋሚ ኃይሎች መቆጣጠራቸውን የከተማዋ ከንቲባ ንሂሃል ማጃክ ለቢቢሲ ረቡዕ ታህሳስ 9/2006 ዓም አስታውቀዋል።
ፊሊፕ አጐር የተሰኙ የመንግስት የጦር ኃይሉ ቃል አቀባይ በሌላ በኩል ''ወታደሮቻችን በከተማዋ የነበራቸውን የበላይነት ለሪክ ማቸር ኃይሎች አስረክበዋል'' ብለዋል።ሪክ ማቸር የቀድሞ የደቡብ ሱዳን ምክትል ፕሬዝዳንት እና በመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ተሳትፈዋል ተብለው በሱዳን መንግስት እየተፈለጉ መሆናቸው ይታወቃል።

በደቡብ ሱዳን ዋና ከተማ ከትናንት በስትያ በተሞከረ የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ እንደ ተባበሩት መንግሥታት ዘገባ 500 ሰዎች ሲገደሉ ከ 20 ሺህ የማያንሱት ከመኖርያ ስፍራቸው ተፈናቅለው በተባበሩት መንግሥታት ግቢ ውስጥ እንዲጠለሉ ያደረገ ሲሆን ቁጥሩ ከእዚህም እንደሚልቅ ይገመታል።

በደቡብ ሱዳን ካሉት ትልልቅ ጎሳዎች ውስጥ የኑዌር እና ዲንቃ ጎሳዎች ሲጠቀሱ። የመፈንቅል ሙከራውን ያደረጉት ሪክ ማቸር የኑዌር ጎሳ ሲሆኑ ከመንግስት በኩል የተሰለፉት አብዛኞቹ የዲንቃ ጎሳ መሆናቸው ይነገራል።ጎሳዎቹ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ፣ሰሜን ምዕራብ ኬንያ እና ሰሜናዊ ዑጋንዳ ጋር ድንበር ከመጋራት አልፎ ተመሳሳይ ጎሳዎች ከመኖራቸው አንፃር ሲታይ ጉዳዩ የአካባቢው ፖለቲካ ላይ የሚኖረው አንደምታ ቀላል ላይሆን ይችላል።

 በዑጋንዳ ካምፓላ የሚታተመው ትልቁ የዑጋንዳ ጋዜጣ ''ዘ ኒው ቪዥን'' በዛሬ ማለዳ እትሙ ላይ የዩጋንዳው ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሰቬኒ የደቡብ ሱዳንን ግጭት እንዲሸመግሉ የተባበሩት መንግሥታት መጠይቁን ዘግቧል።በደቡብ ሱዳን ጉዳይ ከሁሉ በተሻለ ተፅኖ የመፍጠር አቅም የሚኖራት ምናልባትም በጉዳዩ ላይ በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ እጇ ሊኖር ይችላል ተብሎ የሚገመተው ዑጋንዳ ነች።የዑጋንዳው ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ አሁን ውግያ ለጀመረው የርክ ማቸር ኃይል መጠለያ ለመስጠትም ሆነ ስንቅ እና ትጥቅ ለማቀበል ብቸኛ አማራጭ የመሆናቸው ዕድል ትልቅ ነው።

የኢትዮጵያን ሚና ስንመለከት ግን መንግስት በሁለት አጣብቂኝ ውስጥ የገባ ይመስላል። በአንድ በኩል የሰሜን ሱዳን ወዳጅነት እንዳይደፈረስ በሌላ በኩል በደቡብ ሱዳን ያለው ጥቅም እንዳያመልጥ።የኢትዮጵያ አየርመንገድ በረራን ጨምሮ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በጁባ ቅርንጫፍ እስከ መክፈት ድረስ የደረሰ የንግድ ግንኙነት ያላት ኢትዮጵያ የአሁኑን ሁኔታ በጥንቃቄ የምታየው ብቻ ሳይሆን ኢህአዲግ በሌለው ብቁ የአካባቢያዊ ፖለቲካ ትንተና ሁኔታ አንፃር  በነገሮች ላይ ውሳኔ የመስጠት ዘገምተኝነት እና የተንዛዛ የውሳኔ አሰጣጥ ሰንሰለት መርዘም ሊኖር እንደሚችል መገመት ይቻላል።

በአቶ መለስ ጊዜ ውሳኔዎችን እራሳቸው ስለሚሰጡ እና ግልፅ መስመር በማሳየት  በኩል የተሻለ ሁኔታ በአካባቢያዊ ዲፕሎማሲ ላይ ይታይ የነበረ ለመሆኑ የማይታበል ሀቅ ነው።የሱማሌው ጉዳይ ላይ አቶ መለስ የአሜሪካንን ፍላጎት የሚያረካ አቅጣጫ  የ1997 ዓም ምርጫ ማጭበርበር አንፃር ለተነሳው ሕዝባዊ አመፅ የአሜሪካንን ድጋፍ ያገኙበት መሆኑ የሚታወቅ ነው።

በደቡብ ሱዳን ጉዳይ ላይ የብዙ ጥቅም ተጋሪ የሆኑት የኢህአዲግ የጦር ሹማምንት እና አንዳንድ ባለስልጣናት ውሳኔውን ከንግድ ጥቅማቸው አንፃር ብቻ እንዳይመዝኑ እና ሃገርን ለባሰ ጉዳት እንዳይዳርጉ የብዙዎች ስጋት ነው።ከሰሜን ሱዳን ጋር ያለውን ወዳጅነት ለማቆየት ብዙ ለም መሬት በመስጠት የሚታወቀው ኢህአዲግ ደቡብ ሱዳን ላይ የሚይዘው አቅጣጫ በቅርቡ የሚታወቅ ይሆናል።

እዚህ ላይ ሊሰመርበት የሚገባው ጉዳይ ግን ምንም አይነት የመንግስት ለውጥ በደቡብ ሱዳን ውስጥ ቢፈጠር ወይንም ያለው መንግስት ለተወሰነ ጊዜ እየተንገዳገደም መቆየት ቢችል ኢትዮጵያ ከሰሜን ሱዳን ወይንም ከደቡብ ሱዳን አንዳቸውን የመደገፍ አዝማምያ ለማሳየት ባትፈልግም የምትገደድበት ሁኔታ ሊፈጠር ይችላል።አሜሪካ አንዳንድ ጊዜ ብዙም ሀብት እና ስትራተጅያዊ ጥቅም የላቸውም ላለቻቸው ለትልልቅ የህዝብ ስደት እና ግጭቶች ጆሮዋን የማትሰጠው ን ያክል ለደቡብ ሱዳን በከፍተኛ ባለሥልጣኗ አማካይነት በጉዳዩ ላይ ሃሳቧን ሰጥታለች።

አሜሪካ ለጊዜው ጉዳዩ ላይ በቀጥታ መግባት ባትችልም የአካባቢው ሃገራትን '' 'ቀኝ እጄን ሰጥቻለሁ'  እንደእኔ ሆነህ ይህንን አድርግ'' የምትለው ሀገር የሚታዩዋት ምናልባት ኢትዮጵያ እና ዑጋንዳ ብቻ ናቸው።ኢትዮጵያ ደግሞ በአሜሪካ ፍቃድ ብቻ ላለመሄድ የሚያደርጋት የሱዳን ፊት አለ።ሱዳን ተፅኖ ለመፍጠር በኤርትራ የሚገኙ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ኃይሎችን መሸጋገርያ እንዳትሰጥ ያሰጋል።በመሆኑም ኢትዮጵያ በደቡብ ሱዳን ጉዳይ እንደ ሱማሌው ችግር ሙሉ በሙሉ የመግባቷ አዝማምያ እምብዛም አይታይም።ለዑጋንዳው ዩዌሪ ሙሰቨኒ ግን ሰርግ እና ምላሻቸው ነው።

ጉዳያችን ታህሳስ 10/2006 ዓም
የጉዳያችንን ዘገባ በድህረ ገፅዎ ላይ ሲያወጡ ያገኙበትን ምንጭ  መግለፅ ጨዋነት ነው።

Wednesday, December 18, 2013

የኢትዮጵያ ኢንተርኔት አገልግሎት የዘመኑን ሉላዊነት (globalization) የመወዳደር አቅሙ በአሳዛኝ ደረጃ ወርዷል።



በአንድ ወቅት ላይ ያለ መንግስት የሚሰራው ስህተት ወይንም ብቃት በሌለው አሰራር ሳብያ የሚያስከትለው ችግር አሁን ካለው ትውልድ ተሻግሮ ለመጪው ዘመናትም የማይለቅ ተከታታይ ችግሮችን ይዞ መምጣቱ አይቀርም።ባለፈው ወር ላይ አዲስ አበባ ላይ በተደረገ የአፍሪካ  የኃይል አጠቃቀም ላይ አንድ ምሁር ባቀረቡት የጥናት ፅሁፍ ላይ የተናገሩት በአንድ ትውልድ ዘመን ያለ መንግስት ደካማ አሰራር ምን ያህል ተከታታይ ትውልዶች ላይ ጠባሳ እንደሚያስከትል የሚያመላክት ነው።ምሁሩ ''አፍሪካ'' ይላሉ ''አፍሪካ የኢንዱስትሪው አብዮት ተሳታፊ ሳትሆን አለፋት፣ቀጥሎም የመረጃ ቴክኖሎጂ (information technology-IT) በአግባቡ ሳይደርሳት አለፈ አሁን ደግሞ አረንጓዴ ኃይል ዘርፍ ተጠቃሚ ሳትሆን እንዳያልፋት ያሰጋል'' ብለዋል። ይህ ጉዳይ ኢትዮጵያንም ይመለከታል።

የኢንተርኔት አገልግሎት ቁልፍ እና የሁሉም የምጣኔ ሀብት ዘርፎችን የማንቀሳቀስ አቅሙ ቀላል አይደለም።የኢንተርኔት ዘርፉ ቢያንስ በውጭ የሚኖሩ እና በሀገር ውስጥ ያለ የግል ዘርፉን የማሳተፍ እድሉ በእጅጉ ከመጥበብ አልፎ እጅግ አደገኛ በሆነ መንገድ እና  ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ለቻይና ኩባንያዎች ስራውን እያስተላለፈ መምጣቱ ሌላው አሳሳቢ ተግባር ነው።

ጂ-4 የተባለው የአራተኛው ትውልድ ቴክኖሎጂ ሥራ ጨምሮ ቻይና ሙሉ በሙሉ እጇን በኢትዮጵያ ውስጥ አስገብታለች።ሲሶው እጅ በቻይና መንግስት ሽርክና መያዙ የሚነገርለት የቻይና የቴሌኮምዩኒኬሽን  ዜድቲ ኢ (ZTE)  ለኔትዎርክ ሥራ ብቻ እስከ 1.3 ቢልዮን ዶላር የሚደርስ ውል እንዲፈርም መደረጉ የሚታወስ ነው።የእዚህ አይነት ትልልቅ ፕሮጀክቶችን በአግባቡ ዓለም አቀፍ ጨረታ አውጥቶ ደረጃቸውን የጠበቁ ኩባንያዎችን ከማሳተፍ ይልቅ ግልፅነት የጎደላቸው ጨረታዎች ሥራ ላይ መዋላቸው ተለምዷል።ይህ አይነቱ ድርጊት እራሳቸውን የቻሉ ተያያዥ ችግሮችን ብቻ ሳይሆን ለተከፈለው ክፍያ ተገቢው እና ጥራቱን የጠበቀ አገልግሎት ለመገኘቱ ዋስትና መጥፋቱ ሌላው ችግር ነው።ከእዚህ በተጨማሪ ቻይና የሀገራችንን የፖለቲካም ሆነ ምጣኔ ሃብታዊ ጉዳዮች ላይ እጅ የመጠምዘዝ አቅሟን የማሳደጉ ጉዳይ ሳይረሳ ነው።

ይህ ሁሉ ሆኖም ግን የ 2013 ዓም ''ፍሪደም ሃውስ'' ዓለም አቀፍ የመረጃ መረብ እና ዲጂታል መገናኛ ዳሰሳ ሪፖርቱ መሰረት ኢትዮጵያን ከመጨረሻዎቹ ተርታ ሃገራት መካከል ፈርጇታል። የመረጃ መረብ እና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ  የዘመኑን  የሉላዊነት ተግዳሮትን ለማሸነፍ ቁልፍ ከመሆኑ አንፃር ሪፖርቱ  ለሀገራችን ብዙ ማለት ለመሆኑ አያጠራጥርም።ከሰማንያ ሃገራት ውስጥ የመንን ብቻ እንደምንበልጥ መስማት ሌላው እራስ ምታት ነው።በሀገርቤት በኢህአዲግ እና በኢቲቪ የሚቀርበው ሪፖርት ግን ፈፅሞ እውነታውን አያመላክትም።በነገራችን ላይ ሪፖርቱ መረጃቸው ያልተገኘ ያላቸው ጥቂት ሃገራትን አላካተተም።ከእነዚህም ውስጥ ኤርትራ ትገኝበታለች።

ሙሉውን ሪፖርት ለማንበብ ይህንን ድህረ ገፅ ይክፈቱ።
http://freedomhouse.org/sites/default/files/resources/FOTN%202013_Full%20Report_0.pdf 

Tuesday, December 17, 2013

''ኢትዮጵያ ማንዴላን አዳነች'' የደቡብ አፍሪካ ኤስ ኤ ቢሲ ቲቪ ልዩ ቃለ መጠይቅ ከሻምበል ጉታ ዲንቃ ጋር (ቪድዮ) Ethiopia saved Mandela-SABC TV VIDIO

In 1962 Former President Nelson Mandela secretly travelled to Ethiopia for military political and spiritual training under the name of David Motsamai. Haile Selassie's Ethiopian army, on the orders of Haile Selassie himself first trained and armed Nelson Mandela in his struggle against apartheid South Africa.

On the personal orders of his Majesty, the Ethiopian Colonel in charge of Mandela's military training gave him a gun with which he was to bring down the ignoble and unhappy apartheid regime still thriving at that time in South Africa. Mandela went back to South Africa to continue his struggle. The rest is history.

One of the things that Madiba recently learned is that while he was in Ethiopia , the aparheid government knew where he was and had paid his menders to kill him.We are joined now by Captain Guta Dinka who not only looked after Madiba while he was in Ethiopia but was ordered to kill Madiba. He is with Prof Mamo Muchie who will do the translation for us.



ጉዳያችን GUDAYACHN BLOG

Sunday, December 15, 2013

''ፖለቲካ ሀጢአት ነው ወይ? '' የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሊቅ አጭር እና ግልፅ ምላሽ

በሳምንቱ መጨረሻ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ማኅበረ ቅዱሳን ወደ ደብረዘይት ደብረ መድሃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስያን  ባዘጋጀው የመንፈሳዊ ጉዞ ላይ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ምዕመናን ተሳትፈዋል።መርሃግብሩ ላይ ከምዕመናን እና በቀጥታ በማኅበራዊ ድህረገፆች ለአባቶች የጥያቄ እና መልስ መርሃግብር ተዘጋጅቶ ነበር። ለተነሱ ጥያቄዎች ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ምላሽ መስጠታቸው ከማኅበሩ የፌስ ቡክ ገፅ ላይ የተገኘው መረጃ ይገልፃል።ምእመናን ከእንደዚህ አይነት መርሃግብሮች እና ከሊቃውንቱ ቀጥተኛ እና  ትክክለኛ መረጃ ማግኘታቸው  ትልቅ ዋጋ ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ ነው።

ከገፁ ላይ የተገኘውን ከእዚህ በታች እንዲህ ይነበባል-

''ቀጥሎ የሚኖረን መርሐ ግብር የጥያቄና መልስ መርሐ ግብር ሲሆን ሊቃውንቱ መልአከ ታቦር ተሸመ ዘሪሁን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የሊቃውንት ጉባኤ አባል፤ መጋቤ ሐዲስ ደጉ ዓለም ካሣ የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የሐዲሳት ትርጓሜ መምህር፤ መጋቤ ሐዲስ እሸቱ አለማየሁ በቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ የብሉይና የሐዲስ ትርጓሜ መምህር፤ ሲሆኑ ከምዕመናን ለሚቀርቡ ጥያቄዎች ደግሞ በዲ/ን ያረጋል አበጋዝ አቅራቢነት ያስተናግዳሉ፡፡ በዚህ አጋጣሚ ይመለስልን የምትሉት ጥያቄ ካላችሁ በውስጥ መስመራችንም ሆነ በ ኢ-ሜላችን ብትሉክልን እናስተናግደዋለን፡፡
……………………

ጥያቄ 2 . ቅዱስ ጳውሎስ ሀገራችን በሰማይ ነው ስላለ እኛ ክርስቲያኖች በምድራዊት ሀገራችን ላይ እንዴት እንስራ?


እግዚአብሔር ሰማይ ዙፋኔ ምድርም የእግሬ መረገ ናት እንዳለ አሁን ዛሬ ተቀምጠን የምንዘምርበት፣ የምንማርበት፣ የምናመሰግንበት፣ ይሄ ምድርም የእግዚአብሔር ፍጥረት ስለሆነ ሰው ለሀገሩም ሊሰራ ሊሞት ይገባዋል፡፡ ለዚህም ማሳያ የሚሆነው በአድዋ ድል የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያንን ሱታፌ ማስታወስ በቂ ነው፡፡ መልአከ ታቦር ተሸመ ዘሪሁን የሊቃውንት ጉባኤ አባል
……………………..

ጥያቄ 4 ፡ ፖለቲካ ሀጢአት ነው ወይ?

ሰው በዚህ አለም ሲኖር ከሀጢአት በቀር በአለም ያለው ሁሉ ይመለከተዋል፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ እነ ዳዊት፣ እነሰሎሞን ፖለቲከኞች ነበሩ ስለዚህ ሀጢአት አይደለም ሀጢአት የሚሆነው አያያዙን ማወቅ ሲያቅት ነው፡፡ ወተት መጠጣት ሀጢአት አይደለም በረቡዕ ከተጠጣ ግን ሀጢአት ይሆናል፣ ቢላዎ ባለሞያ ሴት ካገኘችው ያገለግላል ባለጌ ካገኘው ሰው ይጎዳበታል ፖለቲካም አያያዙን ካወቅንበት ሀጢአት አይደለም፡፡ መጋቢ ሐዲስ እሸቱ ዓለምዓየሁ በቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ የብሉይና የሐዲስ ትርጓሜ መምህር።''
በጉባኤው ላይ ከታደሙት ምዕመናን በከፊል 



ምንጭ - https://www.facebook.com/mkidusan



Saturday, December 14, 2013

የአኝዋክ ጎሳን እልቂት ችግር ጉዳይ ከባዕዳን እጅ እንዲወጣ የኢትዮጵያውያን ንቁ ተሳትፎ ያስፈልጋል፣ የአቶ ኦባንግ ሜቶ ክቡር ተግባርም ሊደገፍ ይገባል።ማስታወሻው የአቶ ኦባንግ ሜቶን ቪድዮ ቃለመጠይቅ ይዟል።

 አቶ ኦባንግ ሜቶ

በጋምቤላ አኝዋክ ጎሳ ላይ በጅምላ እልቂት የተፈፀመበት እና ከ 400 በላይ አኝዋኮች የተገደሉበት( ታህሳስ 13/2003 ዓም እ ኤ አቆጣጠር) አስረኛ ዓመቱን ደፍኗል።በተለያዩ ወገኖች ስለ እልቂቱ የሚዘገቡት ዘገባዎች የድርጊቱ እጅግ ዘግናኝነት ያወሳሉ።ጉዳዩን ነፃ የዲሞክራሲ ስርዓት በሀገራችን ቢኖር ኖሮ በግልፅ ውይይት ከእየጎሳው የተውጣጡ ሽማግሌዎችን በማደራጀት በካሳ እና በይቅርታ በጉዳዩ ላይ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የተሳተፉ ወንጀለኛ ባለስልጣትና (በየትኛውም የስልጣን እርከን ላይ ቢሆኑ) ለፍርድ እንዲቀርቡ በማድረግ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ በደሉን ለመዝጋት መሞከር ከአስተዋይ መንግስት የሚጠበቅ ተግባር ነበር።ይህ ግን አልሆነም።ይልቁን በመንግስት በኩል ችግሩን የባሰ ማድበስበስ እንደአማራጭ ተወስዷል።

ይህ እልቂት ከኢትዮጵያውያን ይልቅ በባዕዳን ብዙ ሲባልለት ይሰማል።ሆኖም ግን የእራሳችንን ችግር እና የሰብአዊ መብት ጉዳይ በተገቢው መንገድ ማሰብ መዘከር የሚገባን እኛው ነን።ባዕዳን ጉዳዮችን የሚያነሱበት መንገድ እራሱን የቻለ ችግር ይዞ ይመጣል። ምክንያቱም ችግሮቻችንን፣ህመማችንን እና ቁስላችንን የሚነግሩን ከእራሳቸው ስልታዊ ጥቅም አንፃር ነው።በመሆኑም በተለይ በባህር ማዶ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የአኝዋክን እልቂት ሻማ በማብራት ከተጎዱት ጎን በመሆን ማፅናናት እና በመሳሰሉት መርሃግብሮች ማሰብ የወቅቱ  አንገብጋቢ ተግባራቸው መሆን ይገባዋል።

አቶ ኦባንግ ሜቶ በጋምቤላ አኝዋኮች ላይ የተፈፀመውን ግፍ ለዓለም ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ከሚያሰሙት መካከል ናቸው።አቶ ኦባንግ ጉዳዩን የሚያነሱበት ጥግ እራሱ ከጎሳ ጉዳይ አውጥተው ''ችግሩ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ነው።የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ችግር ሲፈታ የጋምቤላውም፣ የአፋሩም ወዘተ ችግር ይፈታል'' ብለው የሚያምኑ ታላቅ ኢትዮጵያዊ ናቸው።አቶ ኦባንግ ሜቶ ይህንን ሃሳባቸውን ወደ ተግባር ለመቀየር ''የአዲሲቱ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ'' የተሰኘ ብሔራዊ አላማ ያለው ድርጅት መስርተው ይንቀሳቀሳሉ።

የአኝዋክ ጉዳይ የሁላችንም ጉዳይ ነው።ከዋሽግተን እስከ አውስትራልያ ያሉ ኢትዮጵያውያን ቢያንስ ይህንን እልቂት ሻማ በማብራት መዘከር ይገባቸዋል።በሀገርቤትም ያሉ  ችግሩ መነሻው ከጎሳ ግጭት ተነስቶ መንግስት ወገን የያዘበት ጉዳይ መሆኑ ከትውልድ ወደትውልድ  ሲቆይ ይዞ የሚመጣው የእራሱ የሆነ ቅርፅ በተለይ ባዕዳን በአካባቢው ካላቸው የሀብት ፍላጎት አንፃር ለማወሳሰብ መጣራቸው ስለማይቀር የሲቪል ማህበራት እና የሃይማኖት ተቅዋማት ችግሩን በሽምግልና ለመፍታት ቢያንስ ሂደቱን ዛሬ መጀመር ይገባቸዋል።

ከእዚህ በታች ባለ ቪድዮ ላይ የተከበሩ አቶ ኦባንግ ሜቶ ስለ ኢትዮጵያ  ይናገራሉ።ቃለ መጠይቁ  በኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቭዥን (ኢሳት) ''ምን አለሽ  መቲ'' ከተሰኘ መርሃ ግብር የተወሰደ ነው።



ጉዳያችን GUDAYACHNgetachewb221@gmail.com

Thursday, December 12, 2013

አንዳንድ አፍቃሪ ወያኔዎች በአፄ ምንሊክ ላይ በአድዋ ጦርነት ወቅት ወደ ኢትዮጵያ ከዘመቱት የኢጣልያ መኮንኖች እኩል ጥላቻ አላቸው የታህሳስ 3/2006ዓም (አጭር ማስታወሻ)


ዛሬው ታህሳስ 3/2006 ዓም የንጉሰ ነገስት ዳግማዊ አፄ ምንሊክ 100ኛ ዓመት እና የፊት አውራሪ ሃብተ ጊዮርጊስ ዲነግዴ 87ኛ ዓመት የእረፍት መታሰብያ እለት ነው።

-  በፌስ ቡክ እና በሌሎች የማህበራዊ መገናኛ መስመሮች መንግስት እና የመንግስት ደጋፊዎች በዳግማዊ ምንሊክ ላይ የስድብ ውርጅብኝ ሲያወርዱ ውለዋል።ለምሳሌ ዳንኤል ብርሃነ የተሰኘ የኢህአዲግ ካድሬ (በኢቲቪ ሚድያ ዳሰሳ ላይ ላይ በክብር ካድሬነት ይቀርባል) በፌስ ቡክ ገፁ ላይ  አሳፋሪ ቃላትን እየፈለገ የእርሱን የጨብሲ ውሎ በሚያሳብቅ መልክ ሲሳደብ ውሏል።

-  ይህ ብቻ አይደለም ዳንኤል ብርሃነ ሰሞኑን ቴዲ አፍሮ ስለ ምንሊክ በማቀንቀኑ ሰፊ የስም የማጥፋት ዘመቻ ከግብረ አበሮቹ ጋር አብሮ  ከፍቶበት ሰንብቷል።

- ዳንኤል የሚያስብባት ትንሽዬ ማሰብያ ጭንቅላት የመንግስት መሆኑን የምትረዱት የምሽቱ የ 2 ሰዓቱን ኢቲቪ አንዳች ነገር ስለ አፄ ምንሊክ 100ኛ ዓመት እረፍት በዓል አለመተንፈሱን ስትመለከቱ ነው።

- ይህ ብቻ አይደለም ከምንገምተው በላይ ኢህአዲግ/ወያኔ በሀገር ጥላቻ ባህር  ውስጥ እየዳከረ  መሆኑን ለመረዳት የዛሬውን ቀን የአንድ የመኪና አደጋ ዜና ያክል ቦታ ሳይሰጠው ማለፉ ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያን የወከሉ ባለስልጣናት ዛሬ በነፃነት በአዲስ አበባ እንዲፏልሉ ያደረጋቸው አፄ ምኒልክ የመሩትን የአድዋ ድል እረስተው አንዳች ትኩረት እንዳይሰጠው አድርገዋል።ምናልባት ባለስልጣናቱ ጊዜ ላይኖራቸው ይቻላል ምክንያት ዛሬ ጣልያን ኤምባሲ የራት ግብዣ ይኖርባቸው ይሆናላ!

- በአዲስ አበባ በዓታ ለማርያም ቤተክርስቲያን ካህናት የዳግማዊ አፄ ምንሊክን እና የፊት-አውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ ዲነግዴ 87ኛ ዓመት  የእረፍት መታሰብያ በፀሎት አስበዋል።

- የሰማያዊ ፓርቲ ልዩ የፎቶግራፍ አውደ-ርዕይ በፅህፈት ቤቱ ከፍቶ ለሕዝብ አሳይቷል።

-  ሸገር ኤፍ ኤም  በዜና ሽፋኑ ላይ የባዕታውን የፀሎት መርሃግብር ቀንጭቦ ከማሰማቱም በላይ  ''ታሪክን የኃሊት'' በተሰኘ ማስታወሻው ላይ  እንዲህ ብሏል-''አፄ ምኒልክ የተለዩ ሰው የሚያደርጋቸው ለሀብት እና ንብረት የማይጨነቁ ይልቁን ከቤተመንግስት ውጭ አንዳችም እርስት እና ንብረት የሌላቸው እና ለልጆቻቸውም አለማውረሳቸው ነው።''

 ከዛሬ 100 ዓመት በፊት በአዲስ ዓለም ኦሮሞዎች 'እምዬ' የተባሉት ንጉስ ምንሊክ ዛሬ ቂም የሚይዝ፣ከንፈር የሚነክስ መንግስት ስልጣን ይዞ ዳግማዊ ምንሊክን ኢትዮጵያ በብሔራዊ ደረጃ መዘከር ባትችል በዜና መልክም ሳትናገር አለፈች።ምንሊክ የቅኝ ገዢዎች እና የባንዳዎች ጠላት ነበሩ።በእዚህ እንስማማለን።

ግን ማስታወሻዬን ከመደምደሜ በፊት አንድ ጥያቄ ልጠይቅ ኢህአዲግ/ወያኔ የእዚህን ያክል ተራ ቂም፣ዘረኝነት፣ሸር እና ተንኮል  አናቱ ላይ እየጨፈሩበት እንዴት ብሎ  ነው ኢትዮጵያን ያክል ሀገር እና ሕዝብ መምራት ይችላል?

ጉዳያችን ታህሳስ 3/2006 ዓም 

Wednesday, December 11, 2013

ዳግማዊ አፄ ምኒልክን ሳስብ የሚገርሙኝ ሶስት አስገራሚ ችሎታዎቻቸው፣የዳግማዊ ምኒልክ እውነተኛ ድምፅ (ኦድዮ) እና አፄ ምኒልክ የነዷት የመጀመርያዋ እውነተኛ መኪና(ቪድዮ)

 ዳግማዊ አፄ ምኒልክ የጥቁር ህዝቦችን የቅኝ ግዛት ታሪክ ተረት ያደረጉ ብቸኛ የዓለማችን መሪ ናቸው።ያረፉበት 100ኛ ዓመት ታህሳስ 3/2006 ዓም በሰማያዊ ፓርቲ እና በኢትዮጵያ ሕዝብ ዘንድ ይታሰባል።ዕለቱ የዳግማዊ አፄ ምኒልክ ብቻ ሳይሆን የፊት-አውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ ዲነግዴ 87ኛ እረፍት መታሰብያም ነው።ይህ በዓል ሊከበር የሚገባው በብሔራዊ ደረጃ ነበር።ሆኖም ግን ጉዳዩ የተገላቢጦሽ ሆኖ ኢትዮጵያ ጀግኖቿን እና ታሪክ የሰሩ እውነተኛ ልጆቿ የሚገፉበት ወቅት ሆነ።ይህንን በዓል ለማክበር ሰማያዊ ፓርቲ በጃን ሜዳ ለመሰብሰብ የጠየቀው ጥያቄ እንዳልተፈቀደ ገልጧል።ፓርቲው ግን ዝግጅቱን ቀጥሏል።

ኢትዮጵያውያን በሀገር ቤት የግራዝያኒን ሃውልት መሰራት ተቃውመው ሲወጡ በፖሊስ ተደበደቡ።በሳውዲ በወገኖቻችን ላይ የደረሰውን ግፍ አስመልክተው በሳውዲ ኤምባሲ ለመቃወም ሲሰለፉ እንዲሁ ለፖሊስ ዱላ እና ለእስር  ተዳረጉ።ዘንድሮ ደግሞ የዳግማዊ አፄ ምኒልክ 100ኛ  እና የፊት-አውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ ዲነግዴ 87ኛ እረፍት መታሰብያ ለማዘጋጀት ጃን ሜዳ እንሰብሰብ ሲሉ አሁንም ተከለከሉ።

የእዚህ አይነቱ ታሪካችንን በአግባቡ እንዳንዘክር የማድረጉ ተግባር ባዕዳንን ሊያስፈነድቅ ይችላል።ለኢትዮጵያውያን ግን በመጪው ታሪካችን ሁሉ በጥቁር ቀለም ተፅፎ የምናነበው አሳዛኝ ታሪክ ነው።ካለፈው ታሪካችን ጋር በእዚህ አይነት ደረጃ የተቃረነ መንግስት ያጋጠመን አይመስለኝም።

እኔ ግን ሁል ጊዜ ዳግማዊ ምኒልክን ሳስብ  የሚገርሙኝ  ሶስት አስገራሚ ችሎታዎቻቸውን መጥቀስ እፈልጋለሁ።

1/ የዲፕሎማሲ ችሎታ

በወቅቱ የነበረው የአውሮፓውያን የቅኝ ግዛት የመስፋፋት ፖሊሲ ከእንግሊዝ ጋር በኬንያ አና ሱዳን በኩል ከኢጣልያን ጋር በሱማሌ እና በኤርትራ በኩል ከፈረንሳይ ጋር በጅቡቲ በኩል የነበሩትን ቁርሾዎች እናስብ።በወቅቱ የነበሩትን ንግግሮች፣ደብዳቤዎች፣ሉዓላዊነትን የማስከበር ሂደቶች ሁሉ ማሰብ ይቻላል።ድንቅ እና ለዘመናዊው ዓለም መማርያ የሚሆኑ ብዙ ትምህርቶች ይገኙበታል።

2/ ዘመናዊ አስተተሳሰብ የመቀበል አቅም 

ከአውሮፓውያን ጋር በነበሩ ግንኙነቶች ሉዓላዊነትን ከማስጠበቅ ጎን ለጎን ዘመናዊ አሰራርን የመቀበል ሂደት።የመጀመርያ ዘመናዊ መኪና፣ካቢኔ፣ባቡር፣ስልክ፣ፖስታ፣ሆቴል፣ሲኒማ ቤት ወዘተ የተጀመሩበትን ሂደት እናስብ።በወቅቱ ዘመናዊ አሰራርን ንጉሡ ባይቀበሉ ኖሮ አዲሱ መኪና ላይ እንዳይወጡ ያወገዙ እንደነበሩ አለመዘንጋት ነው።ምኒልክ ግን ዘመናዊ አሰራርን ተቀበሉ።

3/ የአካባቢ ጥበቃ ጠበቃ 

አፄ ምኒልክ ዛሬ የዓለማችን ትልቅ ችግር የአካባቢ ጥበቃ ጉዳይ ያሳሰባቸው ገና በጧቱ ነበር።የደን መመናመን ጉዳይን በቤተመንግስታቸው በአጀንዳነት የተወያዩ እና መፍትሄ ያስገኙ ቆይቶም ባህር ዛፍ ከአውስትራሊያ በማስመጣት እንዲተከል ያደረጉ የአካባቢ ጥበቃ ተሟጋች ነበሩ።

ይህ ሁሉ የሆነው ከአንድ መቶ አመታት በፊት ነው።ይህ ሁሉ የሆነው ዓለም በመረጃ ባልተሳሰረበት እና ዘወትር ለመማር ዝግጁ በሆኑት እለት እለት እራሳቸውን በሚሰሙት፣በሚያነቡት እና በሚያማክሯቸው ሰዎች እራሳቸውን በእውቀት ባበለፀጉት ንጉስ ምኒልክ ነው።

አፄ ምኒልክ የነዷት መኪና(ቪድዮ)



የዳግማዊ ምኒልክ እውነተኛ ድምፅ (ኦድዮ) ድምፁን በሞባይ መስማት ያልቻላችሁ ሞባይላችሁ ላይ የፕሮግራም አለመጫን ስለሚሆን በቤት ኮምፕዩተር ይክፈቱት።


Monday, December 9, 2013

Mr Mandela's military training in Ethiopia-just before he arrest on 5 August 1962

General Tadesse Birru (Ethiopian army officer) gave a pistol to Nelson Mandela as he returned to South Africa(BBC photo)


By Penny Dale
BBC Africa, Addis Ababa
9 December 2013 Last updated at 09:52 GMT

….In July 1962, Col Fekadu Wakene taught South African political activist Nelson Mandela the tricks of guerrilla warfare - including how to plant explosives before slipping quietly away into the night.

Mr Mandela was in Ethiopia, learning how to be the commander-in-chief of Umkhonto we Sizwe - the armed wing of the African National Congress (ANC).

The group had announced its arrival at the end of 1961 by blowing-up electricity pylons in various places in South Africa.
Mr Mandela was in Ethiopia at the invitation of the emperor, an ardent supporter of Africa's decolonisation and African unity.

At the time, Ethiopia had one of the strongest armed forces on the continent.

Its troops were part of the UN peacekeeping operation during the Congo crisis in 1960 and a decade earlier Ethiopian soldiers had fought in the Korean war.

And the emperor had invited many other African liberation struggle fighters to be trained on Ethiopian soil….
Read more on BBC.co.uk link-  http://www.bbc.co.uk/news/world-africa-23515879 


Saturday, December 7, 2013

''የዓለም ማዕበል ጎርፍ ያላናወጣት ፍቅሯ ያልለወጠ በፈተና ብዛት'' (ኦድዮ)

የአባቶቻችን አምላክ ወዴት ነህ? ኢትዮጵያን ተመልከት!



Thursday, December 5, 2013

ኔልሰን ማንዴላ ከእስር ሲፈቱ እና ዓለም አቀፍ አቀባበል ሲደረግላቸው ለመላው የዓለም ሕዝብ ያደረጉት የመጀመርያው ታሪካዊ ንግግር (ቪድዮ) Nelson Mandela first speech as he released from prison (full speech)

እረጅሙ ጉዞ ወደ ነፃነት!
ኔልሰን ማንዴላ ነፍስህን በገነት ያኑርልን።
LONG WALK TO FREEDOM!
RIP NELSON MANDELA WE WILL NEVER FORGET YOU.



''ኢትዮጵያ ልዩ ስፍራ የምሰጣት እና የማልማት ሀገር ነች።ፈረንሳይን፣እንግሊዝን እና አሜሪካንን ጎብኝ ከምትሉኝ ኢትዮጵያን መጎብኘት እመርጣለሁ።ኢትዮጵያን መጎብኘት ማለት አፍሪካዊ ያደረገኝን ስረ-መጥነቴን የጎበኘሁ ያክል ይሰማኛል።ቀዳማዊ ሃይለስላሴን አግኝቼ እጃቸውን የጨበጥኩ ጊዜ ታሪክ እራሱን የጨበጥቁ ያክል ነበር''
ኔልሰን ማንዴላ ከፃፉት ''እረጅሙ ጉዞ ወደ ነፃነት'' ከተሰኘው መፅሐፋቸው የተወሰደ።

''Ethiopia has always held a special place in my own imagination and the prospect of visiting Ethiopia attracted me more strongly than a trip to France, England and America combined. I felt I would be visiting my own genesis, unearthing the roots of what made me an African. Meeting the Emperor( Emperor Haileselassie I of Ethiopia) himself would be like shaking hands with history.” Nelson Mandela on his Book -Long Walk to Freedom


 Photo-Haile Selassie Mediating between southern Sudanese insurgents (the Anya Nya) and the Sudan government in Addis Ababa, 72; His mediation efforts were responsible for 11 years of relative peace in the Sudan. This scene was later replicated by reggae singer Bob Marley on his “One Love Peace Concert” in April of 78, when he asked rival political leaders of 'the Jamaican Labor Party' and 'the People's National Party' on stage and managed to get them to shake hands. )
ጉዳያችን GUDAYACHN

Wednesday, December 4, 2013

ሰበር ዜና - የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት የሳይንስ እና የባህል ኮሚሽን(UNESCO) በኢትዮጵያ የሚከበረውን የመስቀል ደመራ በዓል ዓለም ዓቀፍ እንክብካቤ እና ጥበቃ እንዲደረግለት በዓለም ቅርስነት ዛሬ መዘገበ!!



የምዝገባ ሂደቱን በተመለከተ ከእዚህ በፊት በጉዳያችን ጡመራ ላይ የወጣውን ለመመልከት ይህንን ይጫኑ - http://gudayachn.blogspot.no/2013/09/blog-post_26.html 

የዩኔስኮ (UNESCO) በቅርስነት የመዘገበበትን ዜና ከድርጅቱ ድህረ-ገፅ ላይ ለማንበብ ይህንን ይጫኑ - http://www.unesco.org/culture/ich/en/RL/00858

Decision 8.COM 8.11
The Committee (…) decides that [this element] satisfies the criteria for inscription on the Representative List of the Intangible Cultural Heritage of Humanity, as follows:
R.1: Rooted in the religious and cultural traditions of Ethiopia and passed on from generation to generation, the festival of Maskel promotes social unity, integration and diversity across the nation;
R.2: Inscription of the festival of Maskel on the Representative List could enhance the visibility of intangible cultural heritage and promote inter-cultural dialogue among the multi-ethnic population of Ethiopia, as well as other communities internationally;

ኢህአዲግ በእውቀት ላይ የተመሰረተ ሥራ እየሰራ ላለመሆኑ አይነተኛ ማስረጃ - በደርግ እና በኢህአዴግ መካከል ለብሄር ብሔረሰቦች የሚውል ገንዘብ አመዳደብ ልዩነት


ደርግ በብዙ አምባገነናዊ ድርጊቱ ይጠቀሳል።በብሄር ብሄርሰቦች ጉዳይ ግን ከኢህአዴግ ጋር ምን ይለያቸዋል? እስኪ በሃሳቤ የመጡልኝን ስር የያዙ የምላቸውን ነጥቦች ላንሳ

ደርግ 

1/ ''የብሔር ብሔርሰቦች ኢንስቲትዩት'' የተሰኘ ትልቅ የምርምር ኢንስቲትዩት መስርቶ የታወቁ የታሪክ ምሁራን እነ ፕሮፌሰር ላጵሶ ገልዴቦ እነ ፕሮፌሰር ታደሰ ታምራትን እና ሌሎችም ታላላቅ ስራዎችን እንዲሰሩ አደረገ።ኢንስቲትዩቱ የብሔር ብሔረሰቦች ባህል፣ስር አመጣጥ፣በጋራ የሚያስተሳስራቸው ኢትዮጵያዊነት ወዘተ ላይ ጥናቶች አጥንቷል።የተለያዩ የምርምር ፅሁፎችን፣ዎርክሾፖችን ወዘተ አዘጋጅቷል።ኢንስቲትዩቱ ከሀገር ውስጥ አልፎ የውጭ ዓለም አቀፍ ምሁራንን እየጋበዘ የጥናት ወረቀቶችን ያሰራ ነበር።

2/ ለኢቲቪ ከ 40ሺህ ብር በላይ በጀት መድቦ ''ተጓዥ ካሜራችን'' የሚል በሳምንት አንድ ጊዜ በጋዜጠኛ ብዙ ወንድም አገኘሁ አዘጋጅነት የሚቀርብ  የሚናፈቅ ፕሮግራም ጀምሮ የተረሱ ብሄረሰቦችን  የአኗኗር  ባህላቸውን እና ታሪካቸውን ያስተምር ነበር።ብዙዎቻችን በልጅነት ጊዜ ይህንን ፕሮግራም እናስታውሳለን።

3/ የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን በ'ህብረት ትርኢት' ፕሮግራም ላይ የሁሉንም ብሔሮች ዘፈኖች ሕዝብ እንዲመለከት ያደርግ ነበር። ይህም በተለይ ለታዳጊው ወጣት የሁሉንም  ባህል እንዲረዳ እና እንዲያከብር ያደርግ ነበር።የቲያትር ቤቶች የሚኖራቸው የኪነት ቡድን የብዙዎቹን ብሔሮች ውዝዋዜ መለማመድ ግዴታቸው ነበር።

ኢህአዲግ 


1/ ስለ ብሔር ብሄረሰብ ብዙ ይናገራል፣በሕገ መንግስቱ አንቀፅ 29 ከፈለጉ መገንጠል እንደሚችሉ ያትታል።

2/ የብሔር ብሄርሰቦች ቀን ብሎ ብዙ ዘፈን፣ምግብ፣መጠጥ፣ያዘጋጃል፣ከየብሄሩ ለመጡ አባላቱ ያበላል፣ያጠጣል በብዙ ሺህ የሚቆጠር ብር ያወጣል።


3/ የቴሌቭዥን ፕሮግራሞች አንዱ የአንዱን እንዳይቀላቅል የሚቀርቡትን  ዘፈኖችን ብንመለከት በአማርኛው ላይ የኦሮምኛ እንዳይቀርብ፣በትግርኛው ላይ የአማርኛው እንዳይቀርብ ወዘተ ሆኗል።ይህም ቀድሞ አማርኛ ፕሮግራም ላይ ኦሮምኛው፣ትግርኛው ይቀርብ ስለነበር ሕዝብ እርስ በርሱ አንዱ የአንዱን ባህል የማወቅ ዕድል ነበረው። የእነ ኪሮስን፣አሊብራን የመሰሉ ከያንያን ዝናን ያተረፉት አንድ ለእናቱ በነበረው ቲቪ ህዝቡ እየተመለከተ ነው እንጂ የትኛው ኤፍ ኤም ነው ያስተዋወቀው?

4/ በኢትዮጵያ ታሪክ ታይቶ የማይታወቁ የብሄሬ ድንበር፣ወሰን ተጣሰ ስሞታዎች እና ግጭቶች ተበራክተዋል።ለእዚህም መንግስት ጉዳዩን ለብቻው የሚመለከት አካል እስከመመደብ የደረሰው በእዚሁ ስለ ብሔር ብሔረሰቦች ብዙ በምዘፈንበት ጊዜ ነው።

ባጠቃላይ 

 ለኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ብዙ ሺህ ብር እያወጣ ምግብ የሚበላ መንግስት ነው ጥሩ አደረገ የሚባለው ወይንስ ገንዘብ መድቦ የብሔር ብሄርሰቦች ኢንስቲትዩት የመሰረተ? በእየ ዓመቱ የብሔር ብሄርሰቦች ቀን ተብሎ የሚባክነው ብር ስንት ሥራ ለብሄር ብሄርሰቦቻችን በሰራ ነበር። ኢህአዲግ በእውቀት ላይ የተመሰረተ ሥራ እየሰራ ላለመሆኑ አይነተኛ ማስረጃ ይህም ነው።  እነሆ ዘንድሮም ጅጅጋ ላይ እንደጉድ ይዘፈናል። ያ የብሔር ብሔረሰቦች ኢንስቲትዩትን ያያችሁ? አሁን አለ? 

Monday, December 2, 2013

ኢትዮጵያ ''ብሔር ብሄረሰብ'' እያለች እንድትዘምር ሲፈረድባት ጎረቤቶቿ ግን በብሄር ስም የፖለቲካ ድርጅት መመስረትን በሕግ ከልክለው በአንድ ገንዘብ ለመጠቀም ስምምነት ላይ ደረሱ



ኢትዮጵያ ያረጀ ያፈጀውን የማርክሲስት አስተሳሰብ ''ብሔር ብሄረሰብ'' ርዕዮት እንድትዘምር ተፈርዶበታል።ህዳር 29 ቀን ጅጅጋ ላይ የቀለጠ ድግስ ተዘጋጅቷል።የእዚህ አይነት ዝግጅት በኢትዮጵያ ወጣቶች መካከል ለምሳሌ በትምህርት ቤቶች መካከል የሚደረግ ከፖለቲካዊ ይዘት የራቀ ግን ወጣቶች የሚቀራረቡበት መልክ ቢኖረው ብዙ ፍሬ ባፈራ ነበር።የኢህአዲግ ዝግጅት ግን ኢትዮጵያውያን አንድ የሚያደርጋቸው እልፍ ነገሮችን ማውሳት ትቶ  የሚለያዩበት ነገር እየተነቀሰ የሚነገርበት መርሃ ግበር መሆኑ ነው አሳዛኙ ነገር።

ኢትዮጵያ ውስጥ ይህ ይሁን እንጂ ጎረቤቶቻችን ግን በሀገራቸው በብሄር ስም የፖለቲካ ድርጅት መመስረትን በሕግ ከልክለው  በአንድ ገንዘብ ለመጠቀም ስምምነት ላይ ደረሱ ።ቅዳሜ ህዳር 21/2006 ዓም የኬንያ፣ዩጋንዳ፣ታንዛንያ፣ቡሩንዲ እና ሩዋንዳ መሪዎች በዩጋንዳ ዋና ከተማ ካምፓላ ተገናኝተው በአስር ዓመት ውስጥ የጋራ መገበያያ ገንዘብ እንዲኖራቸው የፕሮቶኮል ስምምነት ተፈራርመዋል። ይህ ማለት ኢትዮጵያን የሚቀናቀን ትልቅ ገበያ እንደሚፈጥሩ ይታመናል።ኢትዮጵያ በእዚህ ጊዜ ቢያንስ በታዛቢነት አለዝያም ከደቡብ ሱዳን፣ጅቡቲ፣ሱማልያ ወዘተ ጋር የጋራ ገበያ የምትፈጥርበትን ሁኔታ ማመቻቸት ይገባት ነበር።ከእዚህ ይልቅ ''ምኑ ቀርቶብኝ በወጉ በኮነነኝ'' እንደሚባለው የጎረቤት የጋራ ገበያ ቀርቶ  ጠንካራ ሃገራዊ አንድነት እንዳትፈጥር  በብሄር እንድታስብ ተፈርዶባታል።ህዳር 29 በቴሌቭዥን እያዘፈነች እበላ ባይ አፈጮሌ ካድሬዎቿ ስሽሞነሞኑ ማየት የሰሞኑ አሳዛኝ ድርጊት ነው።

የአምስቱ የምስራቅ አፍሪካ ሃገራት መሪዎች የቅዳሜ ስብሰባ ይዘትን ከእዚህ በታች ጉዳያችን ጡመራ ላይ ይመልከቱ።
Burundi, Kenya, Rwanda, Tanzania and Uganda will establish common currency

Nov 30, 2013
The presidents of Burundi, Kenya, Rwanda, Tanzania and Uganda met Saturday in the Ugandan capital, Kampala, to sign a protocol for the creation of a monetary union to be established in 10 years. This will be a major change and breakthrough for international trade and tourism alike.

The EAC began 13 years ago with the goal of creating a common customs union, market, monetary union and a political federation of East African states.

Progress has been slowed, however, due to concerns of the member countries about the impact of the bloc's decisions on their individual economies.

The five countries in the East African Community regional economic bloc agreed on the following:
5TH ORDINARY SUMMIT OF HEADS OF STATE OF THE EAST AFRICAN COMMUNITY
COMMUNIQUÉ

1.THE EAST AFRICAN COMMUNITY HEADS OF STATE, THEIR EXCELLENCIES PRESIDENT UHURU KENYATTA OF THE REPUBLIC OF KENYA, PRESIDENT JAKAYA MRISHO KIKWETE OF THE UNITED REPUBLIC OF TANZANIA, PRESIDENT YOWERI KAGUTA MUSEVENI OF THE REPUBLIC OF UGANDA, PRESIDENT PIERRE NKURUNZIZA OF THE REPUBLIC OF BURUNDI AND PRESIDENT PAUL KAGAME OF THE REPUBLIC OF RWANDA HELD THE 15TH ORDINARY SUMMIT OF THE EAST AFRICAN COMMUNITY HEADS OF STATE AT THE SPEKE RESORT AND CONFERENCE CENTRE IN KAMPALA, UGANDA ON 30TH NOVEMBER 2013. THE HEADS OF STATE AND GOVERNMENT MET IN A WARM AND CORDIAL ATMOSPHERE.
2. THEBUREAUOFTHESUMMITWASCHANGEDWHEREBYTHEREPUBLIC OF KENYA TOOK OVER FROM THE REPUBLIC OF UGANDA AS
2
CHAIRPERSON AND THE UNITED REPUBLIC OF TANZANIA TOOK OVER FROM THE REPUBLIC OF BURUNDI AS THE RAPPORTEUR. THE INCOMING CHAIRPERSON EXPRESSED HIS GRATITUDE TO THE OUTGOING CHAIRPERSON FOR HIS STEWARDSHIP OF THE INTEGRATION PROCESS DURING THE LAST ONE YEAR.
3. THE SUMMIT EXPRESSED ITS SOLIDARITY WITH THE PEOPLE OF THE REPUBLIC OF KENYA FOLLOWING THE BARBARIC ATTACK BY THE AL- SHABAAB TERRORISTS ON WESTGATE MALL, NAIROBI AS A RESULT OF WHICH PEOPLE LOST THEIR LIVES AND PROPERTY DESTROYED, AND BUSINESS DISRUPTED. THE SUMMIT REITERATED ITS COMMITMENT TO THE COLLECTIVE SAFEGUARD OF THE PEACE AND SECURITY FOR THE PEOPLE OF EAST AFRICA. THE SUMMIT ALSO EXPRESSED ITS SYMP ATHY WITH THE PEOPLE OF THE REPUBLIC OF KENY A FOLLOWING THE DISASTROUS FIRE AT THE JOMO KENYATTA INTERNATIONAL AIRPORT AND DIRECTED TO ESTABLISH RELIABLE MECHANISMS FOR DISASTER RESPONSE AND RISK MANAGEMENT FOR THE EAC REGION.
4. THE SUMMIT RECEIVED THE ANNUAL REPORT OF THE COUNCIL OF MINISTERS COVERING THE PERIOD NOVEMBER 2012 – NOVEMBER 2013 AND NOTED THE STEADY PROGRESS MADE IN THE COMMUNITY IN PARTICULAR ON PROGRESS ON REMOVAL OF NON-TARIFF BARRIERS. THE SUMMIT COMMENDED THE COUNCIL FOR THE PROGRESS MADE IN DIFFERENT PROGRAMMES OF THE COMMUNITY.
5. THESUMMITCONSIDEREDAMECHANISMFORTHEIMPLEMENTATIONOF OUTSTANDING SUMMIT DECISIONS AND:-
3
a) DIRECTED THE SECRETARY GENERAL IN CONSULTATION WITH THE RELEVANT HEADS OF STATE TO REPORT REGULARLY ON THE IMPLEMENTATION OF DECISIONS INCLUDING NON-COMPLIANCE AND DECIDED THAT THE STATUS OF IMPLEMENTATION REMAINS A STANDING ITEM ON THE AGENDA OF THE SUMMIT.
b)UNDERTOOK TO REPORT ON INDIVIDUAL PARTNER STATES’ IMPLEMENTATION OF DECISIONS INVOLVING THEIR RESPECTIVE COUNTRIES AT EVERY ORDINARY SUMMIT
c) DIRECTED THE SECRETARIAT TO PREPARE A COMPREHENSIVE LIST ON NON IMPLEMENTATION OF ALL DECISIONS FOR CONSIDERATION AT THE 12TH EXTRAORDINARY SUMMIT IN APRIL 2014.
d)DIRECTED THE COUNCIL TO PRESENT A REPORT ON ALTERNATIVE FINANCING MECHANISM INCLUDING THE OPTION OF 1% OF IMPORTS FROM OUTSIDE THE EAST AFRICAN COMMUNITY IN PRINCIPLE OF FINANCIAL SOLIDARITY AND EQUITY AND REPORT TO THE SUMMIT AT ITS 12TH EXTRA-ORDINARY MEETING IN APRIL 2014.
e) DIRECTED THE COUNCIL TO SUBMIT PROGRESS REPORTS IN IMPLEMENTATION OF MAJOR DECISIONS AND DIRECTIVES OF THE COUNCIL AND THE SUMMIT EVERY SIX MONTHS.
6. THE SUMMIT DIRECTED THE COUNCIL TO CONCLUDE THE EAC INSTITUTIONAL REVIEW AND REPORT TO THE SUMMIT AT THE 12TH EXTRA-ORDINARY MEETING IN APRIL 2014; AND
4
7. THE SUMMIT APPOINTED DR. EMMANUEL UGIRASHEBUJA FROM THE REPUBLIC OF RWANDA JUDGE OF THE EAST AFRICAN COURT OF JUSTICE (APPELLATE DIVISION) TO REPLACE HON. LADY JUSTICE EMILY RUSERA KAYITESI WHO RESIGNED. THIS APPOINTMENT TAKES EFFECT FROM 1ST DECEMBER 2013.
8. THE SUMMIT APPOINTED HON. LADY JUSTICE MONICA MUGENYI FROM THE REPUBLIC OF UGANDA JUDGE OF THE EAST AFRICAN COURT OF JUSTICE (FIRST INSTANCE DIVISION) TO REPLACE HON.LADY JUSTICE MARY STELLA ARACH AMOKO, DEPUTY PRINCIPAL JUDGE WHO IS RETIRING. THIS APPOINTMENT TAKES EFFECT FROM 1ST DECEMBER 2013.
9. THE SUMMIT DESIGNATED HON. MR. JUSTICE ISAAC LENAOLA AS DEPUTY PRINCIPAL JUDGE TO REPLACE HON. LADY JUSTICE MARY STELLA ARACH AMOKO. THIS DESIGNATION TAKES EFFECT FROM 1ST DECEMBER 2013.
10.THE SUMMIT RECEIVED THE REPORT ON THE ATTAINMENT OF THE SINGLE CUSTOMS TERRITORY. THE SUMMIT NOTED THAT THE FRAMEWORK FOR THE OPERATIONALISATION OF THE SINGLE CUSTOMS TERRITORY HAD BEEN FINALISED AND ADOPTED BY THE COUNCIL. THE SUMMIT DIRECTED THAT THE SINGLE CUSTOMS TERRITORY COMMENCES ON 1ST JANUARY 2014 AND THAT ALL OPERATIONAL REQUIREMENTS BE FINALISED BY JUNE 2014.
11.THE SUMMIT RECEIVED THE PROGRESS REPORT ON THE NEGOTIATIONS FOR THE ADMISSION OF THE REPUBLIC OF SOUTH
5
SUDAN INTO THE EAST AFRICAN COMMUNITY. THE SUMMIT OBSERVED THAT THE COUNCIL OF MINISTERS HAD ESTABLISHED A HIGH LEVEL NEGOTIATION TEAM TO CONDUCT THE NEGOTIATIONS AND ENABLE THE SUMMIT MAKE A DECISION ON THE MATTER AT THE 12TH EXTRA- ORDINARY SUMMIT IN APRIL 2014.
12.THE SUMMIT RECEIVED THE PROGRESS REPORT ON THE VERIFICATION OF THE APPLICATION OF THE REPUBLIC OF SOMALIA TO JOIN THE EAST AFRICAN COMMUNITY. THE SUMMIT NOTED THAT THE TERMS OF REFERENCE FOR THE VERIFICATION PROCESS HAD BEEN DEVELOPED AND A VERIFICATION COMMITTEE PUT IN PLACE. THE SUMMIT DIRECTED THE COUNCIL OF MINISTERS TO SUBMIT PROGRESS REPORT ON THE VERIFICATION EXERCISE AT THE 16TH ORDINARY SUMMIT IN NOVEMBER 2014.
13.THE SUMMIT RECEIVED THE PROGRESS REPORT ON THE ROADMAP FOR THE ESTABLISHMENT OF THE EAST AFRICAN FEDERATION. THE SUMMIT NOTED THAT THE REVISED MODEL STRUCTURE, ROAD MAP AND ACTION PLAN WILL BE CONSIDERED BY THE COUNCIL OF MINISTERS AND SUBMITTED TO THE 12TH EXTRA-ORDINARY SUMMIT MEETING IN APRIL 2014.
14.THE SUMMIT APPROVED AND SIGNED THE PROTOCOL ON THE ESTABLISHMENT OF THE EAST AFRICAN MONETARY UNION AND DIRECTED THAT:
a) ALL PARTNER STATES SHOULD CONCLUDE THE RATIFICATION PROCESS OF THE EAMU PROTOCOL BY JULY, 2014;
6
b) THE COUNCIL OF MINISTERS SHOULD IMPLEMENT THE ROADMAP TO SINGLE CURRENCY AS INDICATED IN THE SCHEDULE ON THE EAMU PROTOCOL;
c) THE FOLLOWING INSTITUTIONS NECESSARY FOR THE IMPLEMENTATION OF THE EAMU BE ESTABLISHED:-
i) THE EAST AFRICAN MONETARY INSTITUTE
ii) THE EAST AFRICAN STATISTICS BUREAU TO BE RESPONSIBLE
FOR STATISTICS
iii) THE EAST AFRICAN SURVEILLANCE, COMPLIANCE AND
ENFORCEMENT COMMISSION TO BE RESPONSIBLE FOR
SURVEILLANCE, COMPLIANCE AND ENFORCEMENT; AND
iv) THE EAST AFRICAN FINANCIAL SERVICES COMMISSION TO BE
RESPONSIBLE FOR FINANCIAL SERVICES.
d) THE COUNCIL OF MINISTERS DEVELOPS THE BILLS FOR THE ESTABLISHMENT OF THE INSTITUTIONS PROVIDED IN THE PROTOCOL FOR CONSIDERATION BY THE EAST AFRICAN LEGISLATIVE ASSEMBLY AS PROVIDED FOR IN THE ROAD MAP;
e) THE COUNCIL OF MINISTERS APPRISES THE SUMMIT ON THE PROGRESS MADE ON IMPLEMENTATION OF THE ROADMAP TO SINGLE CURRENCY AT EVERY ORDINARY SUMMIT.
15.THE SUMMIT NOTED THAT THE SECTORAL COUNCIL ON FINANCE AND ECONOMIC AFFAIRS WILL BE RESPONSIBLE FOR THE IMPLEMENTATION OF THE MONETARY UNION PROTOCOL.
16.THE SUMMIT APPROVED THE COUNCIL RECOMMENDATION TO EXTEND THE JURISDICTION OF THE EAST AFRICAN COURT OF JUSTICE TO
7
COVER TRADE AND INVESTMENT AS WELL AS MATTERS ASSOCIATED WITH THE EAST AFRICAN MONETARY UNION. ON HUMAN RIGHTS MATTERS AS WELL AS CRIMES AGAINST HUMANITY, THE SUMMIT DIRECTED THE COUNCIL OF MINISTERS TO WORK WITH THE AFRICAN UNION ON THIS MATTER.
17.THE SUMMIT DIRECTED THAT THE INTERNATIONALIZED NEW GENERATION EAST AFRICAN PASSPORT BE LAUNCHED BY NOVEMBER 2015.
18.THE SUMMIT DISCUSSED THE PREVAILING SECURITY SITUATION AND THE NEED FOR CONCERTED EFFORTS TOWARDS COMBATING TERRORISM AND NEGATIVE FORCES IN THE REGION AND REAFFIRMED ITS COMMITMENT TO THE PEACE AND SECURITY IN THE REGION.
19.THE SUMMIT NOTED WITH CONCERN THE RECENT POLITICAL AND SECURITY DEVELOPMENTS IN SOMALIA AND URGED ALL PARTIES TO EMBRACE DIALOGUE AND CREATE AN ENVIRONMENT CONDUCIVE FOR THE IMPLEMENTATION OF SOMALIA’S VISION 2016 AND FACILITATE THE ELECTIONS BY 2016.
20.THE SUMMIT TOOK NOTE OF THE UN SECURITY COUNCIL RESOLUTION 2124 ADOPTED ON 12TH NOVEMBER 2013 REGARDING ENHANCING THE MILITARY CAPACITY OF THE AMISOM AND THE SOMALI NATIONAL FORCES AND CALLED FOR THE REVIEW OF THE RESOURCE PACKAGE TO ASCERTAIN ITS ADEQUACY TO FACILITATE CONTINUITY AND STRENGTHENING OF THE MILITARY CAMPAIGN AGAINST AL-SHABAAB.
8
21.THE SUMMIT REITERATED ITS CONTINUED SUPPORT FOR THE GOVERNMENT OF SOMALIA AND CALLED UPON REGIONAL BODIES AND THE INTERNATIONAL COMMUNITY TO COME FORWARD AND SUPPORT ECONOMIC, SOCIAL AND POLITICAL INTERVENTIONS GEARED TOWARDS ENHANCING THE CAPACITY OF THE SOMALI GOVERNMENT AND ITS GOVERNANCE INSTITUTIONS TO FULFIL ITS MANDATE AND MEET THE EXPECTATIONS OF ITS CITIZENS.
22. THE SUMMIT REAFFIRMED THEIR SUPPORT FOR THE EFFORT OF THE ICGLR/SADC MEMBER STATES AND THE INTERNATIONAL COMMUNITY ON THE ONGOING PEACE INITIATIVES AIMED AT STABILIZING EASTERN DRC, AND IN THAT REGARD, ENCOURAGED THE EAC PARTNER STATES TO SUPPORT THE ONGOING POLITICAL PROCESS (KAMPALA DIALOGUE), WHICH SHOULD BE CONCLUDED AS SOON AS POSSIBLE.
23.THE SUMMIT NOTED THE JUSTIFIABLE CAUSE FOR THE NEED TO HARMONISE THE TERMS AND CONDITIONS OF SERVICE FOR THE ELECTED MEMBERS OF THE EAST AFRICAN LEGISLATIVE ASSEMBLY WITH THOSE OF ALMOST EQUAL STATUS WITHIN THE COMMUNITY. THE SUMMIT APPROVED A LUMPSUM INCREMENT OF USD 1,206 PER MEMBER WITH EFFECT FROM 1ST JULY 2014.
24.THE SUMMIT COMMENDED THE INITIATIVE BY THE MEDIA IN THE REGION TO FORM A BODY THAT WILL REPRESENT THEIR INTEREST AND PLAY A MORE ROBUST ROLE IN PROPAGATING THE INTEGRATION ISSUES.
9
25.THE SUMMIT DIRECTED THE COUNCIL OF MINISTERS TO STUDY THE MODALITIES OF INCLUDING FRENCH AS A LANGUAGE OF THE COMMUNITY IN ADDITION TO ENGLISH AND KISWAHILI.
26.THEIR EXCELLENCIES, PRESIDENT PAUL KAGAME OF THE REPUBLIC OF RWANDA, PRESIDENT, UHURU KENYATTA OF THE REPUBLIC OF KENYA, PRESIDENT JAKAYA MRISHO KIKWETE OF THE UNITED REPUBLIC OF TANZANIA, AND PRESIDENT PIERRE NKURUNZIZA OF THE REPUBLIC OF BURUNDI THANKED THEIR HOST, HIS EXCELLENCY PRESIDENT YOWERI KAGUTA MUSEVENI OF THE REPUBLIC OF UGANDA, FOR THE WARM AND CORDIAL HOSPITALITY EXTENDED TO THEM AND THEIR RESPECTIVE DELEGATIONS DURING THEIR STAY IN UGANDA.
DONE AT KAMPALA, THIS 30TH DAY OF NOVEMBER 2013

H.E. UHURU KENYATTA
PRESIDENT OF THE REPUBLIC OF KENYA
H.E. YOWERI KAGUTA MUSEVENI
PRESIDENT OF THE REPUBLIC OF UGANDA
H.E. JAKAYA MRISHO KIKWETE
PRESIDENT OF THE UNITED REPUBLIC OF TANZANIA
H.E. PIERRE NKURUNZIZA
PRESIDENT OF THE REPUBLIC OF BURUNDI
H.E. PAUL KAGAME
PRESIDENT OF THE REPUBLIC OF RWANDA

source - http://www.eturbonews.com/40192/burundi-kenya-rwanda-tanzania-and-uganda-will-establish-common-c  

ኢህአዲግ/ወያኔ ከግንቦት ሰባት የሰላም፣የፍትህ እና የነፃነት ንቅናቄ ጋር ድርድር ላድርግ ስላለው ግንቦት 7 ፈፅሞ እንዳይበርደው እንዳይሞቀው (vidio)

ኢህአዲግ/ወያኔ ግንቦት ሰባትን ዛሬ ልደራደር ስላለው እንዳይበርደው እንዳይሞቀው ያስፈልጋል።ምክንያት ግንቦት ሰባት ኢህአዲግ /ወያኔ ከእዚህ ቀደም ድርድር ካደረገባቸው ከኦጋዴን ወዘተ ድርጅቶች አያንስም።ብዙም ሳይገረሙ መራመዱ ብቻ ነው ለሀገር የሚበጀው።ለኢህአዲግ/ወያኔ መንገዱን ጨርቅ ያድርግላችሁ ከማለት ''ትንሽ ነው ያሉት እንዲህ ቁጭ ብድግ ያስደርጋል እና በአንክሮ ታስቦበት ከልብ የፖሊሲ ለውጥ ላይ አተኩሮ ፍፁም ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር ላይ ማተኮሩ የሚበጅ ነው። በብረት ተማምኖ ስልጣን ላይ መቆየት እንደማይቻል ታሪክ አስተምሯል።ሃሳቤን የምትገልፀው ቪድዮ ይህች ነች።





ጉዳያችን GUDAYACHNgetachewb221@gmail.com

Saturday, November 30, 2013

በእዚህ ዘመን ካሉት ከአዋቂዎቹ ይልቅታዳጊ ህፃናቱ የኪነጥበብ ባለሙያዎች የተሻለ የሀገር ፍቅር ያንፀባርቃሉ(ቪድዮ)

በእዚህ ዘመን አርቲስቶቻችን በእራሳቸው ምህዋር ውስጥ እየዞሩ ሀገራቸውን ባብዛኛው የዘነጉበት፣ለሙያ፣ለእውነት እና ለሕዝብ ፍቅር ከሚሰሩ ስራዎች ይልቅ ብዙ ብር የሚያስገኙ ስራዎች የተወደዱበት እና በሕዝብ ከመወደድ ይልቅ ከሚሊንየሮች ጋር ሸራተን መታየት የበለጠባቸው ዘመን እየሆነ ነው።እርግጥ ነው እንደ እነ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) አይነቶች በባትሪ ተፈልገው የተገኙ አልጠፉም።ኢትዮጵያ ግን የጥበብ ስራዋ በእዚህ አይነት ደረጃ ህዝብን እና ብሔራዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ስራዎች የወደቁበት ወቅት አሁን ነው።

እዚህ ላይ የኢትዮጵያ የኪ-ነጥበብ   እድገት እና ውድቀት ትንተና ላይ አይደለሁም።ሕዝብን፣ሃገርን የተመለከቱ ያለፈውን እና መጪውን የሚያማትሩ ስራዎች ግን በፈጣን ገንዘብ አስገኚ ስራዎች ተተክተዋል።ፊልሞች ወጣቶችን በፍቅር ታሪክ በማማለል ተሳክቶላቸው ይሆናል።ወጣቶቹ ወዴት እንደሚሄዱ፣ከየት እንደመጡ፣የጋራ ሃገራዊ እሴታቸው ምን እንደሆነ ግን አይነግሩም።ይህ በጣም ጥቅል እና በወፍ በረር የታየ ሃሳብ ይሆናል።በእዚህ ዘመን ካሉት አዋቂዎቹ ታዳጊ ህፃናቱ የኪነጥበብ ባለሙያዎች የተሻለ የሀገር ፍቅር ያንፀባርቃሉ።

ለናሙን ከእዚህ በታች ያሉትን የሸገር ራድዮ ለወጣት ሴቶች በራስ መተማመን ዙርያ የሚያስተምርበት ''የኛ'' የተሰኘ ተከታታይ ተውኔት ላይ የሚሰሙ ዜማዎች ናቸው። ቀደም ብሎ የወጣው ''አቤት'' የተሰኘው ዜማ የ2005 ዓም የዓመቱ ምርጥ ዜማ ተብሎ በሕዝብ ተመርጧል።በቅርቡ በተቀረፀው ''እቴጌ'' በተሰኘው ዜማ  ላይ ደግሞ ታዳጊ ህፃናቱ አስቴር አወቀ እንድትሳተፍበት አድርገዋል።ይመልከቷቸው።





Wednesday, November 27, 2013

ሰበር ዜና በሰሜናዊ ኢትዮጵያ በሁመራ ቃፍታ ወረዳ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር የሰነዘረውን ጥቃት ከመንግስት አካል በኩል ተረጋገጠ


በሰሜናዊ ኢትዮጵያ በሁመራ ቃፍታ ወረዳ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ከጋምቤላ ሕዝብ ነፃነት ንቅናቄ ጋር በመሆን  የሰነዘረውን ጥቃት የወረዳው የፀጥታ ኃላፊ ገዛይ ዳኘው ለአካባቢው ራድዮ ማመናቸውን ቪኦኤ የአማርኛው አገልግሎት ዛሬ ህዳር 18/2006 ዓም አስታወቀ።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሽምቅ ውግያ ሂደቶች ከሰሜናዊ ኢትዮጵያ በኩል እየተሰማ ነው።''የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል'' እና ''የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር'' ያሰለጠኗቸውን ሰራዊቶች ማስመረቃቸውን በእዚሁ በያዝነው ህዳር ወር ላይ ማስታወቃቸው ይታወቃል።

በእዚሁ ወር ኢሳት ለወራት በኢህአዲግ-ወያኔ ሲቀናበር የነበረ ኤርትራ በሚገኙ  በግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል አመራሮች ላይ ግድያ ለመፈፀም የተሸረበ ሴራ መጋለጡ መዘገቡ ይታወቃል።የሴራው ሂደትም ኢህአዲግ-ወያኔ በቁጥር አንድ ያስጨነቀው ጉዳይ ወደ ትጥቅ ትግል የገቡ ኃይሎች መሆናቸውን ያመላከተ አይነተኛ ማስረጃ መሆኑን ብቻ ሳይሆን የአሁኑ ሂደት ከእዚህ በፊት ከነበሩት ሁኔታዎች የተለየ ነባራዊ ሁኔታ መኖሩን ብዙዎች ይስማማሉ።

ዛሬ ቪኦኤ የመንግስት መዋቅር የትግራይ ምዕራባዊ ዞን ቃፍታ ወረዳ የፀጥታ ኃላፊ ውግያውን ማመናቸውን ለአካባቢው ራድዮ መናገራቸውን ከመግለፁም በላይ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር የውጭ ግንኙነት ኃላፊ አርበኛ ኑር ጀባን ቃለ መጠይቅ አድርጎላቸዋል።አርበኛ ኑር ጀባ ስለውግያው ሲናገር  በ24ኛ ክፍለ ጦር ላይ ጉዳት ማድረሱን እና በርካታ ቀላል እና ከባድ የጦር መሳርያዎችን መማርኩን ገልጧል።በነገራችን ላይ ኢሳት በትናንትናው እለት ቀደም ብሎ ዜናውን ማወጁ ይታወቃል።በውቅቱም ጦርነቱ የተደረገው ህዳር 13/2006 ዓም መሆኑ ተዘግቦ ነበር።

ከእዚሁ ጋር በተያያዘ ሰሞኑን ኢትዮጵያ ውስጥ በሌለበት ፍርድ ቤት ተከሶ የነበረው በአሁኑ ወቅት የግንቦት ሰባት ሕዝባዊ ኃይል አመራር ካሴ ዘመነ ''ከወያኔ ጋር ከአሁን በኃላ የምንገናኘው ቃሊቲ ወይም እስር ቤት ሳይሆን ጦር ሜዳ ነው እዝያው እንገኛኛለን'' ያለውም በእዚሁ በያዝነው ሳምንት ነው።

ዛሬ ግንቦት 19/2006 ዓም ዘግይቶ በወጣ ዘገባ ራድዮ ፋና በድህረገፁ ጥቃቱን አምኗል።

ጉዳያችን
ህዳር 19/2006 ዓም

Monday, November 25, 2013

ኢትዮጵያዊ ቆስሎም እንዲህ ይከበር ነበር።በኮርያ ዘመቻ ላይ ተሳትፈው ለቆሰሉ ሰላሳ የኢትዮጵያ ወታደሮች ቀዳማዊ አፄ ኃይለስላሴ በተኙበት የጀግና ሜዳልያ ሲሸልሟቸው (ታሪካዊ ፎቶ)

ኢትዮጵያዊ ቆስሎም እንዲህ ይከበር ነበር።በኮርያ ዘመቻ ላይ ተሳትፈው ለቆሰሉ ሰላሳ የኢትዮጵያ ወታደሮች ቀዳማዊ አፄ ኃይለስላሴ በተኙበት የጀግና ሜዳልያ ሲሸልሟቸው (ታሪካዊ ፎቶ)

በኮርያ ዘመቻ የዘመቱት የኢትዮጵያ ወታደሮች አስከሬንም ሆነ ቁስለኛ 9,252 ኪሎ ሜትሮች ተጉዞ ለሀገሩ አፈር ይበቃ ነበር። ዛሬ ዓለም በሰለጠነበት እና መገናኛ በተስፋፋበት ዘመን ሳውዲ ውስጥ ወገኖቻችን አሳራቸውን የሚያዩት በ 1,900 ኪሎሜትር ማለትም የሁለት ሰዓት ተኩል የአይሮፕላን በረራ እርቀት ላይ ሆነው ነው።


Saturday, November 23, 2013

በዓለም ላይ በሳውዳረብያ በወገኖቻችን ላይ የደረሰውን ሰቆቃ ለመቃወም ሰልፍ የከለከለች ብቸኛ ሀገር-ኢትዮጵያ ነች። ይህ እንቅልፍ ያስወስዳል?

አዲስ አበባ ፌድራል ፖሊስ የሳውዲን መንግስት ለመቃወም ሰልፍ የወጡትን ሲደበድብ 

በዓለም ላይ በሳውዳረብያ በወገኖቻችን ላይ የደረሰውን ሰቆቃ ለመቃወም ሰልፍ የከለከለች ብቸኛ ሀገር-ኢትዮጵያ ነች።
ኢትዮጵያውያን በሳውዲ አረብያ በወገኖቻችን ላይ የደረሰውን ሰቆቃ አስመልክተው

ሰሜን አሜሪካ 

 - የተለያዩ ግዛቶች

 በአውሮፓ-

በጀርመን፣

እንግሊዝ፣

ጣልያን፣

ስዊድን፣

ኖርዌይ፣

 ካናዳ-

የተለያዩ ግዛቶች 

 አውስትራሊያ


መካከለኛው ምስራቅ 

- እስራኤል፣
- ቤሩት 

አፍሪካ 

 ደቡብ አፍሪካ፣

 ዑጋንዳ ፣

እስያ 

 ደቡብ ኮርያ፣

 በሚገኙ የሳውዳረብያ ኤምባሲ ፊት ለፊት ሰልፍ አድርገዋል።በለቅሶ በቁጭት እንባ ተራጭተዋል።ኤርትራውያን ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን አብረው ተሰልፈው ተላቅሰዋል ቁጣቸውን ገልፀዋል።

ቀሪ ሰልፎች ለምሳሌ በቤልጅየም ብራስልስ እና ሌሎችም ሀገሮች ይቀጥላሉ።
በዓለም ላይ የሳውዲን መንግስት ተቃውመው ዜጎች ሰልፍ እንዳይወጡ የከለከለች ብቸኛ ሀገር የጉዳዩ ባለቤት ኢትዮጵያ ብቻ ነች።ሌላ ማንም ሀገር አልከለከለም።

ኢትዮጵያ የሳውዲን ኢ-ሰብአዊ ድርጊት ተቃውመው ሰልፍ የወጡ እንቡጥ እና ለጋ ወጣቶችን፣አረጋውያንን፣አዛውንቶችን በፖሊስ እየደበደበች ብዙዎችን አካለ ስንኩል አደረገች።የቀሩትን  ሰልፉ የተደረገበት ቀን ሳትውል ሳታድር ወደ እስር ቤት ወረወረች።ይህንን የሚቀበል እንዴት አይነት ህሊና ነው?
ኢህአዲግ-ወያኔዎች ሆይ! ይህ ጠረንጴዛችሁ ላይ ያለ ያልተመለሰ ምን ጊዜም ልንረሳው የማንችለው ግን መልስ የሚሻ አጀንዳ ነው።

ጉዳያችን 

ህዳር/ 2006 ዓም 

Friday, November 22, 2013

አስር ጊዜ ከንፈር ከመምጠጥ ኢሳትን መርዳት!


የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቭዥን -ኢሳት ከተመሰረተ ገና ሶስት አመታትን ቢያስቆጥርም በኢትዮጵያ ፖለቲካዊ፣ማህበራዊ እና ምጣኔ ሃብታዊ ጉዳይ ላይ ቁጥር አንድ ተፅኖ ፈጣሪ ሆኖ ወጥቷል።ዛሬ ዛሬ ኢሳት ባይኖር ኖሮ ስንት ሕዝብ ሊሰማቸው የሚገቡ ጉዳዮች ሳይሰሙ ሊቀሩ የመቻላቸውን ሁኔታ ስንመለክት ኢሳት ወሳኝ መሆኑን እንረዳለን።

በቅርቡ ከተከሰቱት የሙስሊሞች ጥያቄ፣በቤንሻጉል የጉርዳፈርዳ ነዋሪዎች መፈናቀል፣ሰሞኑን በሳውዲ አረብያ በወገኖቻችን ላይ የተፈፀመውን ግፍ ለሕዝብ በማድረስ በኩል ሁሉ የኢሳትን ታላቅ የስራ ክንውኖች የሚገልፁ ናቸው።ኢሳትን  ኢትዮጵያን የሚወድ ሁሉ ሊደግፈው የሚገባ ነው።የመረጃ  መታፈን ቁጥር አንድ ሉዓላዊነታችንን የሚያሳጣን መሆኑን የተገነዘበው ስንት ሰው እንደሆነ አላውቅም።ይህንን ስንረዳ የመገናኛ ብዙሃንን አስፈላጊነት እንረዳዋለን።ይህንን በደንብ የተረዳ የስርዓቱ ደጋፊ ቢሆንም ኢሳትን ለመርዳት ግዴታው ነው ብዬ አስባለሁ።ዛሬ ኢሳት እና ኢቲቪ ለሕዝብ በሚያቀርቡት ይዘት ተለያዩ እንጂ ሁለቱም የህዝብ ንብረት ናቸው።

ነገን አማትረን ስናይ ግን ኢትዮጵያ መንገዷ ሲሰምርላት ትልቅ አለማቀፍ የዜና አውታር እንደሚሆኑ አንጠራጠርም።ለእዚህ ሁሉ ግን ዛሬ ላይ ሆኖ ኢሳትን ማገዝ ከኢትዮጵያውያን የሚጠበቅ ትልቅ ቁምነገር ነው።ኢሳት በውጭ ከሚኖረው ሕብረተሰብ ማግኘት የሚገባውን ያህል እያገኘ አለመሆኑ በተደጋጋሚ የተገለፀ ጉዳይ ነው።አሁንም ጥያቄው ስንቶች በወር ሻይ ሲጠጡ ጉርሻ የሚሰጡትን ሃያ ዶላር በአግባቡ ይሰጣሉ? ነው።በቀን 2 ዶላር ብንሰጥ በወር 60 ዶላር መሆኑን ሳንረሳ ማለት ነው።አሁን የተጠየቀው በትንሹ 20 ዶላር ነው።ኢሳት በመጪው እሁድ ህዳር 15/2006 ዓም (ኖቬምበር 24/2013) ''እሳት የእኔ ነው'' የተሰኘ በቀጥታ ስርጭት ልዩ መርሃግብር አዘጋጅቷል።በዝግጅቱ ላይ በቀጣይነት የሚከፍሉ አባላትን ለማፍራት አስቧል።ቢያንስ ከቤት ሆኖ ይህንን መርሃግብር መሳተፍ ትንሿ ማንም ሰው ሊያደርገው የሚችለው ሥራ ነው።አስር ጊዜ ከንፈር ከመምጠጥ ኢሳትን መርዳት።ደግሞ መርዳት አይደለም ግዴታን መወጣት ነው።

ጉዳያችን
ሕዳር/2006 ዓም







Thursday, November 21, 2013

በሳውዲ አረብያ ያሉ ወገኖቻችን ጉዳይ ብዙ እርቀት መሄድ ይፈልጋል። ገጠራማው የሳውዳረብያ ግዛት የኢትዮጵያውያንን ሰቆቃ እያስተናገደ ነው።



ሳውዲ አረብያ ያሉ ወገኖቻችን ችግር ገና አልተቀረፈም።እስካሁን ባብዛኛው የታየው በከተሞች አካባቢ ያሉት ነው።ቢጮሁ የማይሰማበት ማንም የማይሰማቸው በገጠራማ የሳውዲ ግዛቶች ያሉ ብዙ ሺህ ወገኖቻችን ድረሱልን እያሉ ነው።ከከተማ እየጠለፉ የሚወስዷቸውን እህቶቻችንን የሚደብቁባቸው ቦታዎች እነኚሁ ከከተማ ራቅ ያሉ ቦታዎች ናቸው።

በኢሳት አስተባባሪነት የተመሰረተው ዓለም አቀፍ ግብረሃይል ለሳውዲ ንጉስ፣የደህንነት እና የፖሊስ መስርያቤት ግልፅ ደብዳቤ ፅፏል።ይህ የስራው መጀመርያ ነው።ግብረ ኃይሉ ከዲፕሎማሲ ሙያ ጀምሮ የተለያየ ሙያ ያላቸው ኢትዮጵያውያንን የያዘ ለእራሳችን ችግር መፍትሄዎቹ እኛው ነን የሚለውን ብሂል በተግባር ያመላከተ ድንቅ ጅምር ነው።በቀጣይ ጊዜ ለሚኖሩ የስራ ዝርዝሮች እንደሚኖሩት ይጠበቃል። የእዚህ አይነቱ ግብረ ኃይል በተጠናከረ መልክ በቀጣይነት ሊኖር የሚገባው እና ለሌሎች ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዊነትን ለሚገዳደሩ ተግዳሮቶች ሁሉ ምላሽ የሚሰጥ እና አቅም የሚያጎለብት እንዲሆን የሁሉም ኢትዮጵያዊ ኃላፊነት ነው።

በሌላ በኩል ወደሀገር ቤት በመንግስት እየተመለሱ መሆናቸውን ኢቲቪ እያሳየ ነው።ስደተኞቹ በሲቪል ሰርቪስ ግቢ በግዝያዊነት ያረፉ እንዳሉ ተነግሯል። ሆኖም ግን በሺህ የሚቆጠር ኢትዮጵያዊ  ስደተኛ ሃሳሩን ከሚያይባት ሳውዲ አረቢያ መንግስት እስካሁን ሀገርቤት አድርሻለሁ ያለው ቁጥር ግራ እያጋባ ነው።ለምሳሌ  የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ፣የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ትዊተር ገፅ እና ኢቲቪ የተናገሩት የተምታታ ቁጥር ነው።ለምሳሌ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ ዲና  4,961 ወደ ሀገርቤት አስገብተናል ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዶ/ር ቴዎድሮስ በትዊተር ገፃቸው ላይ የተመለሱትን ቁጥር 10,707 ናቸው ብለዋል።ዛሬ ኢቲቪ ደግሞ 13,000 ሰው ተመልሷል ብሏል።በዚህን ያህል ቁጥር የአንድ መንግስት ድርጅቶች እንዴት ይለያያሉ? በቁጥር ነገር መቸም መንግስትን ማመን እንደማይቻል ብዙ ምሳሌዎችን መጥቀስ ይቻላል።

የችግሩ ግዝፈት ግን ወደ ሀገር የማስገባት ሥራ ብቻ አይደለም። በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን በገጠራማ የሳውዲ ግዛቶች ውስጥ ይኖራሉ።በአንድ የዓለም ባንክ በአለማችን ላይ በገጠራማ ቦታዎች የሚኖሩ ህዝቦች ቁጥር በሚያሳይ ዘገባው ላይ ሳውዳረብያ በ 2012 ዓም እ ኤ አ ወደ 5ሚልዮን የሚጠጋ ህዝቧ ከከተማ እርቆ ነው የሚኖረው።(http://data.worldbank.org/indicator/SP.RUR.TOTL) እንግዲህ ስንት እህቶቻችን እና ወንድሞቻችን የሚሰማቸው አጥተው በየገጠሩ ሃሳራቸውን እያዩ ነው? ምን ያህል ኢትዮጵያውያን በሳውዳረብያ እንደሚኖሩ የኢትዮጵያ ኢምባሲ የጠራ መረጃ የለውም። አሁን ብዙዎቻችን ትኩረት የሰጠነው እና ስለችግሩ እየሰማን ያለነው በሪያድ እና ጅዳ አካባቢ ነው።በሌሎቹ አካባቢ ያሉት ወገኖች ጋር ለመድረስ ግን ምናልባት ጥቂት ሳምንታት ብሎም ወራት ልፈልግ ይቻላል።

 በሳውዲ መንግስት ላይ አስፈላጊው ዓለም አቀፍ ተፅኖ ለማድረግ ከተቻለ እና ተከታታይ እረፍት የለሽ ወቀሳዎች ከተሰነዘሩ ሳውዳረብያ ወደመሰላቸቱ ብቻ ሳይሆን በሃገሯ ካለባት ውስጣዊ ችግሮች አንፃር ለችግሩ መፍትሄ የማትሰጥበት ምክንያት የለም።ዓለም አቀፉ የኢትዮጵያውያን ግብረ ኃይል ግን ተከታታይ የስራ ሪፖርቶቹን ለሕዝብ እየገለፀ የራሱ የሆነ በጎ ተፅኖ መፍጠሩ አይቀርም። ከእዚህ በዘለለ በሌሎች የአረብ ሃገራት ላሉት ወገኖችም አንድ አይነት ማዕከልን የጠበቀ እርዳታ ለማድረግም ሆነ መብታቸውን እዲያስከብሩ ገንቢ ሃሳቦችን የማቅረብ ብሎም በየሀገራቱ የሚከራከርላቸው አካል ለመመስረት ይችላል።

ከእዚህ በታች የተለጠፈው የሩስያ ቲቪ (RT) ሳውዲን የተመለከተ ልዩ ዘገባ ሀገሪቱ ያለባትን የውስጥ ችግር ያመላክታል።የሀገሪቱን ኢ-ሰብአዊ አያያዝ ብቻ ሳይሆን የመንግስት መዋቅር ጭምር  ወጣቱ ንጉሳዊው ቤተሰብ የነቀፉበት አግባብን ዘገባው ይጠቁማል።



ጉዳያችን GUDAYACHNgetachewb221@gmail.com

Tuesday, November 19, 2013

Monday, November 18, 2013

ከሰሞኑ ጉዳይ መነሻነት ኢትዮጵያውያን ያላከናወናቸው ሁለት አበይት ተግባራት




ኢትዮጵያውያን ሰሞኑን በሳውዲ እየደረሰ ያለውን ችግር መፍትሄ እንዲኖረው  በአውሮፓ እና በአሜሪካ ከተሞች እንዲሁም ትናንት አርብ በአዲስ አበባ (በግፍ በእስር እና በድብደባ እስኪቆም ድረስ) በመሰለፍ ተቃውሟቸውን ገልፀዋል። ከእዚህ ሁሉ ሂደት የነጠሩ እና ወደፊት ሊነጥሩ የሚችሉ ነገሮችን ማውሳት ተገቢ መሰለኝ።

 በቅድምያ ግን ከሂደቱ የተረዳነው ጉዳይ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ችግሮች በተለይ ኢትዮጵያዊ ያልሆነ መንግስትን ከመደገፍ እና አይዞህ ባይነት ጋር በተያያዘ በቀጥታ እጃቸውን ያስገቡ መንግሥታት መኖራቸው ከምንጊዜውም በላይ ግልፅ ሆኗል።ኢሕአዲግ-ወያኔም ገንዘብ እና ድጋፍ ለሰጡት ሁሉ መታዘዙን እና ከስልጣኑ በላይ ምንም የሚያስቀድመው ነገር እንደሌለ በድጋሚ አስመስክሯል።ለእዚህም የማይካድ ሀቅ ሆኖ የወጣው የሳውዳረብያ መንግስት ምን ያህል በሀገራችን የፖለቲካ እና ምጣኔ ሀብት ጉዳይ ገብቶ እየፈተፈተ እና እያዘዘ መሆኑ በትናንትናው እለት በአዲስ አበባ በሰልፈኞች ላይ የደረሰው ድብደባ እና እስር ጥሩ ማሳያ ነው።

ከሰሞኑ ሰልፎች ጋር ተያይዞ ኢትዮጵያውያን ልናከናውናቸው የሚገቡ ሁለት አበይት ተግባራት


1/ በውጭ የሚኖረው ሕብረተሰብ አደረጃጀት ተፅኖ ፈጣሪ ማድረግ 


በውጭ የሚኖረው ሕበረተሰብ አሁን ካለበት አደረጃጀት በተሻለ እና ዓለማቀፋዊ መልክ በያዘ፣ በህብረተሰቡ ውስጥ ያሉ በትምህርትም ሆነ በገንዘብ አቅም የደረጁትን ብሎም አዳዲስ ሃሳብ የሚያፈልቁትን በማሰባሰብ አሁን ባለው የኢትዮጵያ ችግርም ሆነ ዘመን ተሻግሮ (ከለውጥ በኃላም) ኢትዮጵያን ለማንሳት ወሳኝ መሆኑን መገንዘብ ተገቢ ነው። በውጭ የሚኖረው ሕብረተሰብ አሁን አንዳንድ ችግሮች ሲፈጠሩ በተቃውሞ ሰልፍ ከመግለፅ ባለፈ ተፅኖ የመፍጠር አቅሙ በበለጠ መደራጀት አለበት።

ለምሳሌ በየሀገራቱ ያሉት የኢትዮጵያ ማህበረሰቦች (Communities) ለምን በዓለም አቀፍ ወይንም በአህጉር አቀፍ ደረጃ የመተዳደርያ ደንብ ቀርፀው የጋራ ሃገራዊ ራዕይ ቀርፀው በአጭር ጊዜ አይደራጁም? ይህ መደራጀት በፖለቲካ፣በኢኮኖሚ ማለት በውጭ ባሉ የንግድ ስራዎች እና በማህበራዊው በተለይ ባህላዊ እና ታሪካዊ እሴቶቻችንን በመጠበቅ እና ለቀሪው ዓለም በማሳወቅ ብሎም ባህሉ ለውጭው ዓለም ባህል እንዲሆን በመጣር ብዙ ተፅኖ የመፍጠርያ መንገዶችን ለመቀየስ ይቻላል። እናም ይህንን ሥራ በአፋጣኝ መስራት ሁሉም በውጭ ያለ ማሕበረሰብ  አባል እንዲሆን ማድረግ ይቻላል።

እዚህ ላይ የፖለቲካ እና የዘር አስተሳሰብ ችግሮች ያደናቅፉታል የሚሉ አስተሳሰቦች እንደሚኖሩ አስባለሁ። እነኝህ ችግሮች ግን በመተዳደርያ ሕጉ ሃገራዊ እና ኢትዮጵያዊ ራዕይ ላይ ከተመሰረተ ብዙ አንድ የሚያደርጉን ነጥቦችን ብቻ ለማጉላት ይረዳል።''ኢትዮጵያዊ አይደለሁም ወደፊትም አላስብም'' ያለ ወደ ኢትዮጵያዊነት እስኪመጣ ኢትዮጵያውያን ሥራ አይሰሩም ማለት አይቻልም እስከ ዕለተ ምፃትም ድረስ ሁሉ አንድ አይነት አስተሳሰብ እንብድኖረው እና ሃሳብ እንዲያመነጭ አይጠበቅም።ዛሬ ችግሩን የተረዳው ሥራ መስራት ይጀምራል ሌላው ይቀጥላል።

2/ ቀድመው ለሚጠብቁን የተቀነባበሩ የስነ-ልቦና ዘመቻዎች አለመጋለጥ 


ሰሞኑን ኢትዮጵያውያን ያደረጉትን የተቃውሞ ሰልፍ በማስመልከት ምን ሊደረግ እንደሚችል ቀድሞ መረዳት ተገቢ ነው።እንደ ጣኦት የሚመልኩት የሳውዲ ንጉሳውያን እና ልዑላን ምንም ማለት እንዳልሆኑ ኢትዮጵያውያን በተቃውሞ ሲናገሩ ማየት ለእራሳቸው ንጉሳውያን ቤተሰብ ብቻ ሳይሆን ለሚንቀጠቀጥላቸው  ሕዝብ ማስደንገጡ እና ማናደዱ አይቀርም።ይህ ማለት ሳውዲ አረብያ ባላት መንገድ እና መዋቅር ሁሉ ከወዳጆቿ ጋር ሆና ስሟን ለማደስ ከምትጠቀምበት መንገድ አንዱ ''ኢትዮጵያውያን በየሄዱበት ሕግ አያከብሩም'' ለማስባል እዚህም እዝያም ኢትዮጵያውያንን ስም ለማጉደፍ የሚሰሩ ቀላል የሚመስሉ ግን በዓለም አቀፉ ሕብረተሰብ ዘንድ በጊዜ ብዛት ተፅኖ የሚኖራቸው ተግባራት ሊኖሩ እንደሚችሉ መጠርጠሩ አይከፋም።ለምሳሌ በእየሃገራቱ ጋዜጦች ላይ አርቲክሎች የሚፅፉ ማዘጋጀት፣የቆዩ ቁርሾዎችን ማጉላት፣ኢህአዲግ- ወያኔን ትክክል እንደሆነ ለመሳል መሞከር ወዘተ ሊሆኑ ይችላሉ።

ለእዚህ ተግባር ደግሞ የሚተባበሩ የኢትዮጵያ ስም ሲጎድፍ የእነርሱ የሚተልቅ የሚመስላቸው ከቅርብም ሆነ ከሩቅ አይጠፉም። እዚህ ላይ እራሱ ኢህአዲግ-ወያኔም ተባባሪ እንደሚሆን ማረጋገጥ ይቻላል።በውጭ የሚኖረውን ሕብረተሰብ እንደ ጦር የሚፈራው እና የምጠላው ወያኔ-ኢህአዲግ ለምሳሌ ከሳውዲ መንግስት ጋር ሲነጋገር- ''ይህንን አመፅ የፈጠሩት በመሳርያ ኃይል ያስወገድኩት  የነፍጠኛ፣አክራሪ ክርስትያኖች፣ ፀረ አረብ አመለካከት ያላቸው ናቸው። የእነርሱ ወደ ስልጣን መምጣት ፀረ አረብ ስልጣን ያዘ ማለት ነው'' የሚል የሐሰት ገበያ ሊያደራ ይችላል።

ባጠቃላይ 


በመሆኑም ኢትዮጵያውያን በያሉበት ያሉትን የህዝብ ለሕዝብ ግንኙነት፣ጨዋነት፣ስነ-ምግባር እና ሌላውን የመረዳት ባህላችንን በጥንቃቄ ከመቸውም በበለጠ መልክ መያዝ ይገባናል።ከእዚህ በበለጠ ደግሞ ወደፊት የሚቀነባበሩልንን የስነ-ልቦና ዘመቻዎች ሰለባ ላለመሆን ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል።የስነ-ልቦና ዘመቻዎቹ እንደለመደብን ''ኢትዮጵያዊ በመሆኔ አፈርኩ'' የሚሉ ቃላትን ደጋግመን እንድንናገር ያደርገን እና መጨረሻው አደገኛ ወደ ሆነ  ትንታኔ ይወስደናል።ኢትዮጵያ ዛሬም እጅግ ሃብታም በተፈጥሮ የበለፀገች ሀገር ነች።ይህንን አሁንም ልንጠራጠር አይገባንም።ይህ ሕዝብ ታላቅ ሕዝብ ነው። የቀረን እና መከናወን ያለበት በዘር እና በጎሳ ከፋፍሎ እና ከባዕዳን ጋር ተባብሮ ወደ መጨረሻው ፈተና የሚገፋትን ስርዓት አንስቶ  በአፈራችን ላይ የመኖር መብታችንን ማስከበር ነው።ለእዚህም ኢትዮጵያዊ የፖለቲካ ራዕይ ማስቀመጥ እና ከወዲሁ ማዳበር ዛሬ  ጠንካራ የሆነ እንደ ''አለማቀፍ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ'' ሁሉን አቀፍ ድርጅት መመስረት እና የፖለቲካ ፓርቲዎችን አቅጣጫ በማህበረሰቡ ፍላጎት እና ራዕይ ላይ ተመስርቶ አቅጣጫ መስጠት፣የሚ ታገዙትን ማገዝ አስፈላጊ የሆንበት ወቅት ላይ ነን። ለእዚህ ሁሉ ተግባራት ደግሞ ዘመኑ እራሱ አጋዥ ነው።ተግባሩን ለማከናወንም ሆነ ለማፋጠን የመገናኛ ቴክኖሎጂዎች ብዙ ፋይዳ አላቸው።

ጉዳያችን
ህዳር 7/2006

Sunday, November 17, 2013

በዛሬውም ሆነ በመጪው ትውልድ የሚጠየቁ ሁለት ''ለምኖች''



1/ ለምን አንድ 


ኢትዮጵያውያን  በሳውዲ ባሉ ወገኖቻችን ችግር  ላይ ከዋሽግተን እስከ አውስትራሊያ ሰልፍ ሲሰለፉ ለምንድነው በየሀገሩ ያሉ  የኢትዮጵያ ኢምባሲዎች በሰልፉ ላይ ያልተገኙት? ወይንም  ለምሳሌ የዛሬውን የዋሽግተን ሰልፍ አስመልክቶ  ቪኦኤ  ለዋሽግተን ኢትዮጵያ ኢምባሲ ቢደውልም ምላሽ አላገኘሁም ብሏል። ይህ የሀገራችን ጉዳይ አይደለም እንዴ? ሰልፉ የሳውዲ ኤምባሲን  ያስከፋው እንጂ የኢትዮጵያን ኢምባሲ ከሰልፉ ጋር እንዳይተባበር የሚያደርገው ምን አይነት ሐረካት ነው?

2/ ለምን ሁለት 


አሁንም በሺህ የሚቆጠር ኢትዮጵያዊ ሲሰለፍ ሳውዲ አረብያን ሲቃወም የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን እና ራድዮ አንዲት እንዳይተነፍስ ያስገደደው ጉዳይ ምንድነው? ለቅሶው ለወገን፣እንባ መራጨቱ ለወገን፣ኢትዮጵይ ቴሌቭዥን ይህንን እነ ቢቢሲ፣ሲ ኤን ኤን፣ዋሽግተን ፖስት  የዘገቡትን የኢትዮጵያውያን የሳውዲ መንግስትን ተቃውሞ ለምን አላሳየም? ለምን? አዲስ አበባ ያለው የሳውዲ ኤምባሲ ሰራተኞች የአረብ ሻሂ ፉት እያሉ ስሙን የሳውዲ ቲቪ መባል እሩብ ጉዳይ የቀረውን ኢቲቪ ሲያደንቁት አይታያችሁም? ግን ለምን? ሼም  ኦን ኢቲቪ! ካለ ምንም ማጋነን ኢቲቪ ወቅታዊ አብሽቅ ነው።

እስኪ ደግሞ መጪውን ትውልድ እናስብ የዛሬ 30 ዓመት አንድ ኢትዮጵያዊ እንበል የዩንቨርስቲ ተመራቂ የመመረቅያ ፅሁፉን ''በኢትዮጵያ እና ሳውዳረብያ ግንኙነት ላይ''ሊሰራ ቢያስብ እና የሰሞኑን ሰልፎች ከቢቢሲ እና ሲ ኤን ኤን ላይ ወስዶ ከጠቀሰ በኃላ ኢቲቪ ስለሰልፎቹ  ምንም አለማለቱን ሲመለከት መደምደምያው ላይ ምን ብሎ ይፅፋል? ''ኢቲቪን የሳውዲ ገንዘብ ተቆጣጥሮት ነበር'' ብሎ? እስኪ አስቡት የት ነን? ማነው የሚገዛን? ያለቀስኩት- ከባዕድ ቆንስላ ፊት። የወቀስኩት- የውጭ መንግስትን። ኢቲቪ ምን ቤት ነው ድምፄን የሚያፍነው? ሳስበው ሳስበው ውስጤን እሬት እሬት አለኝ።

ጉዳያችን
ህዳር 9/2006 ዓም

Friday, November 15, 2013

የኢትዮጵያይውያን ተቃውሞ በ ኦስሎ፣ኖርዌይ ህዳር 5/2006 ዓም (ቪድዮ )

Ethiopians residing in Norway Demonstration against inhuman treatment of Saudi Arabia and EPRDF poor diplomatic enforcement November 14/2013 Oslo




ጉዳያችን GUDAYACHNgetachewb221@gmail.com

ለፋሺሽት ግራዝያኒ ዘብ የቆመው ወያኔ-ኢህአዲግ ወገኖቻችንን በግፍ ለገደለው ለሳውዲ መንግስት ታማኝነቱን በተግባር አሳየ።ወያኔ ገበናው ከምንጊዜም በላይ ፈጦ ወጥቷል።ጥያቄው ኢትዮጵያዊነት ወይንም ሞት!ነው።


አዲስ አበባ ሳውዲ አረብያ ኢምባሲ ፊት ለፊት በሰማያዊ ፓርቲ ዛሬ የተጠራው ሰልፍ በከፊል 

ቀደም ብሎ በጣልያን አፍሌ ግዛት ሊሰራ የነበረውን የሮዶልፍ ግራዝያኒ ሐውልትን በመቃወም ኢትዮጵያውያን አዲስ አበባ ላይ ያደረጉትን ሰልፍ የወያኔ-ኢህአዲግ ፖሊሶች ሰልፈኞቹን መደብደባቸው እና ለእስር መዳረጋቸው ይታወሳል።
(ለኢትዮጵያ ማን ይናገርላት? ጉዳያችን GUDAYACHN http://gudayachn.blogspot.no/2012/11/blog-post.html)

ዛሬ ህዳር 6/2006 ዓም የሰማያዊ ፓርቲ በሳውዲ የሚገኙ ወገኖቻችን ላይ የሚደርሰውን ግፍ በመቃወም አዲስ አበባ በሚገኘው የሳውዲ አረብያ ኤምባሲ ፊት ለፊት የጠራው ሰልፍ በፖሊስ ከመቆሙም በላይ በርካታ ወጣቶች እና አዛውንቶች በፖሊስ ተደብድበዋል የሰማያዊ ፓርቲ አመራርን ጨምሮ በርካታ ሰልፈኞች መስቀል ፍላወር አካባቢ እና አራት ኪሎ አካባቢ የሚገኙት ፖሊስ ጣቢያዎች ታስረዋል።''ጠላትማ ምንጊዜም ጠላት ነው አስቀድሞ ማለት አሾክሿኪውን ነው''።ወያኔ ገበናው ከምንጊዜም በላይ ፈጦ ወጥቷል።ለነፃነት የሚደረገው ትግል ለማደናቀፍ የቆሙት ኃይላትንም ከምንጊዜውም በላይ እየታወቁ መምጣታቸው ሌላው ክስተት ሆኗል።
ጥያቄው ኢትዮጵያዊነት ወይንም ሞት! ሆኗል።

የኢሳት ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን ከጥቂት ሰዓታት በፊት በፌስ ቡክ ገፁ ላይ የለጠፈው እንዲህ የሚል ነበር-

'' በአዲስ አበባ ወሎ ሰፈር ሳኡዲ አረቢያ ኤምባሲ አከባቢ ከፍተኛ ድብደባ እየተፈጸመ ነው። አሁን በስልክ ያገኘኋቸው የሰማያዊ ፓርቲ ሌሎች አመራሮች በእንባ ታጅበው ሲቃ ይዟቸው ''የኢትዮጵያ አምላክ ይፋረደን'' ሲሉ ለኢትዮጵያ ህዝብ መልእክት አስተላልፈዋል። የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች ወጣት ይድነቃቸው ከበደ እና ወጣት ሀና ዋለልኝ ከፍተኛ ድብደባ ተፈጽሞባቸዋል። ወደ 50 የሚጠጉ የፓርቲው አባላትና የሰልፉ ታዳሚ ወደ እስርቤት ተወስደዋል። ''በህግ አምላክ! እያለን እየጮህን በፌደራል ፖሊስ ተቀጠቀጥን" አለ ወጣት ይድነቃቸው። ''ወገን አለቀ ሳኡዲ አረቢያ ከሚገደሉት ከሚቀጠቀጡት ባልተናነሰ እኛም በሀገራችን ግፍ ተፈጸመብን'' ብላለች ወጣት ሃና። ''ኢትዮጵያዊ መንግስት ከወዴት ነው ያለኧው?'' የዛሬው ከፍ ብሎ የሚሰማው ጩኧት!''

የሰማያዊ ፓርቲም ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ባወጣው መግለጫ እንዲህ ብሏል።


''በሳውዲ አረቢያ በሚገኙ ዜጎቻችን ላይ እየደረሰ ያለው በደል እና ስቃይ መጠኑ ከመጨመር አልፎ ሕይወትን እስከማሳጣት መድረሱ የሚታወቅ ነው፡፡ ይህን በደል እና ስቃይ ለመቃወም እና ሀዘናችንን ለመግለፅ በዛሬው ዕለት ማለትም ህድር 6 ቀን 2006 ዓ.ም አዲስ አበባ በሚገኘው በሳውዲ አረቢያ ኢምባሲ ፊት ለፊት ሰላማዊ ሰልፍ የተጠራ ቢሆንም በመንግሥት ታጣቂዎች በተወሰደ በአሰቃቂ እርምጃ ሰልፉ ሊካሄድ አልቻለም፡፡
እኛ ኢትዮጵያን በውጭ በሚገኙ ዜጐቻችን ላይ የሚደርሰው በደልና ግፍ እንዲቆም፣ ይህንንም ድርጊት የፈፀሙት ለሕግ እንዲቀርቡና የተጐዱ ዜጐች ተገቢውን ካሳ እንዲያገኙ፤ የኢትዮጵያ መንግሥትም በዜጐቹ ላይ ያሳየውን ቸልተኝነት በአስቸኳይ በማቆም ተገቢ የሆነውን የመንግሥት ኃላፊነት እንዲወጣ ቢጠየቅም፤ ሰልፉ በተቃራኒው በመንግሥት ታጣቂዎች በተወሰደ አሰቃቂ እርምጃ ተጠናቋል፡፡
በሳውዲ እየተፈፀመ ያለውን በደል በመቃወም በዓለም አቀፍ ደረጃ ኢትዮጵያዊያን ድምፃቸውን በማሰማት ላይ ቢሆኑም እኛ ኢትዮጵያዊያን ግን በገዛ ሀገራችን ድምፃችንን እንኳን እንዳናሰማ ታፍነናል፡፡ በዚህም እንቅስቃሴ ላይ የተሳተፉ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች፣ አባላት፣ ደጋፊዎችና ሌሎች የኅብረተሰብ ክፍሎች ከፍተኛ ድብደባ፣ እንግልትና እስር ተፈፅሞባቸዋል፡፡
የመንግሥት ፖሊሶች የራሳቸውን ዜጋ በመደብደብና በማሰቃየት ብሎም በማሰር በሳውዲ በሚገኙ ኢትዮጵያዊ ወገኖቻችን ላይ የተፈፀመውን በደል ሀገር ውስጥ በሚገኙ ንፁሐን ወገኖቻቸው ላይ ደግመውታል፡፡
ይህ በውሸት ዲሞክራሲ ስም የተደበቀው አምባገነን መንግሥት ሕዝብን ለማሸማቀቅ የወሰደውን እርምጃ ወደ ጐን በመተው የኢትዮጵያ ሕዝብ ቅድም አያቶቹን በማስታወስ ያስረከቡትን ክብር ከማስመለስ ወደ ኋላ እንደማይል እርግጠኛ መሆናችንን እንገልፃለን፡፡
ፓርቲያችን እንዲህ አይነቱን የለየለት የመንግሥት ሕገ ወጥ ተግባር ትኩረት ሰጥቶ የሚመለከተው መሆኑን እየገለፅን፤ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብና መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ከጐናችን እንዲቆም በአፅንኦት ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡

ህዳር 6 ቀን 2006 ዓ.ም''




/////////////////////////////////።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።//////////////////////////////።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

 -






Thursday, November 14, 2013

የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ በኖርዌይ (Ethiopian Community in Norway) በሳውዲ አረብያ የሚኖሩ ወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ላለው ሰቆቃ ያዘጋጀው ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄደ


የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ በኖርዌይ (Ethiopian Community in Norway) ዛሬ ህዳር 5/2006 ዓም በሳውዲ አረብያ የሚኖሩ ወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ላለው ሰቆቃ ያዘጋጀው ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ቁጥሩ  ከፍተኛ የሆነ ሕዝብ በተገኘበት በኖርዌይ ዋና ከተማ በኦስሎ በሚገኘው የሳውዲ አረብያ ኢምባሲ ፊት ለፊት ተካሄደ።


ከቀትር በኃላ  በ10 ሰዓት የተጀመረው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ  በርካታ ወጣቶች፣ በእድሜ የገፉ አረጋውያን እና እድሜያቸው  ከአንድ ዓመት ያልዘለሉ ሕፃንትን የያዙ እናቶች ሁሉ የታደሙበት ነበር።እስከ ምሽቱ 12 ሰዓት ድረስ በቆየው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ -

- የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች ተወካዮች እና ሲቪክ ማህበራት ተወካዮች አጫጭር ንግግሮች አድርገዋል፣

- የሳውዲ አረብያ መንግስት በሀገሩ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ላይ የሚያደርሰውን በደል የሚያጋልጡ በማህበራዊ ድህረ ገፆች የተለቀቁት ፎቶዎች በትልቁ ታትመው እንዲታዩ ተደርገዋል፣

- የተለያዩ መፈክሮች ተሰምተዋል፣

-  ለሳውዲ አረብያ ኢምባሲ የተዘጋጀው የተቃውሞ ደብዳቤ ተሰጥቷል፣

-  የሳውዲ አረብያ መንግስት ንጉሳውያን ቤተሰቦች የያዘ ፎቶግራፍን  እንዲቃጠል በማድረግ ሰልፈኛው ተቃውሞውን ከመግለጡም በላይ የኢትዮጵያ መንግስት ጉዳዩን በቸልታ እና ተገቢውን የዲፕሎማቲክ ግንኙነትን ያልጠበቀ አያይዝ ኢትዮጵያውያኑን በእጅጉ አስቆጥቷቸዋል። በሰልፉ ላይ ከተነገሩት ንግግሮች ውስጥ የኢህአዲግ ወያኔ መንግስት ለዜጎቹ የሚሰጠው ዋጋ በእጅጉ ያነሰ መሆኑ በተደጋጋሚ ከመወሳቱም በላይ አንድ ተናጋሪ '' ዛሬ ወገኖቻችን ሥራ ፍለጋ በእየ አረብ ሃገራቱ የሚሰደዱት ከ 40 ቢልዮን ብር በላይ በመዘረፉ መሆኑን መዘንጋት የለብንም ለእዚህም ተጠያቂው እራሱ ወያኔ ነው'' በማለት በምሬት ተናግረዋል።

በመጨረሻም  በሰሞኑ የሳውዲ ፖሊስ እና ወጣቶች  ተግባር የተጎዱ ኢትዮጵያውያንን  ፎቶ ሰልፈኛው ''ስራቸውን ይመልከቱት በማለት ኢምባሲው አጥር ላይ እንዲቀመጥ ከተደረገ በኃላ የሰልፉ ስነ ስርዓት ፍፃሜ ሆኗል።

የሰልፉን ገፅታ በከፊል የሚያሳየውን ፎቶ ከእዚህ በታች ይመልከቱ።














ሐያ ገዳማት የሚገኙበት በግሪክ የሚገኘው የአቶስ ተራራ ገዳማውያን አኗኗር (ቪድዮ)

ገዳሙ ከሰርብያ፣ሮማንያ፣ቡልጋርያና ሩስያ የመጡ ዓለምን የናቁ መነኮሳት ገድመውበታል።