- በፌስ ቡክ እና በሌሎች የማህበራዊ መገናኛ መስመሮች መንግስት እና የመንግስት ደጋፊዎች በዳግማዊ ምንሊክ ላይ የስድብ ውርጅብኝ ሲያወርዱ ውለዋል።ለምሳሌ ዳንኤል ብርሃነ የተሰኘ የኢህአዲግ ካድሬ (በኢቲቪ ሚድያ ዳሰሳ ላይ ላይ በክብር ካድሬነት ይቀርባል) በፌስ ቡክ ገፁ ላይ አሳፋሪ ቃላትን እየፈለገ የእርሱን የጨብሲ ውሎ በሚያሳብቅ መልክ ሲሳደብ ውሏል።
- ይህ ብቻ አይደለም ዳንኤል ብርሃነ ሰሞኑን ቴዲ አፍሮ ስለ ምንሊክ በማቀንቀኑ ሰፊ የስም የማጥፋት ዘመቻ ከግብረ አበሮቹ ጋር አብሮ ከፍቶበት ሰንብቷል።
- ዳንኤል የሚያስብባት ትንሽዬ ማሰብያ ጭንቅላት የመንግስት መሆኑን የምትረዱት የምሽቱ የ 2 ሰዓቱን ኢቲቪ አንዳች ነገር ስለ አፄ ምንሊክ 100ኛ ዓመት እረፍት በዓል አለመተንፈሱን ስትመለከቱ ነው።
- ይህ ብቻ አይደለም ከምንገምተው በላይ ኢህአዲግ/ወያኔ በሀገር ጥላቻ ባህር ውስጥ እየዳከረ መሆኑን ለመረዳት የዛሬውን ቀን የአንድ የመኪና አደጋ ዜና ያክል ቦታ ሳይሰጠው ማለፉ ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያን የወከሉ ባለስልጣናት ዛሬ በነፃነት በአዲስ አበባ እንዲፏልሉ ያደረጋቸው አፄ ምኒልክ የመሩትን የአድዋ ድል እረስተው አንዳች ትኩረት እንዳይሰጠው አድርገዋል።ምናልባት ባለስልጣናቱ ጊዜ ላይኖራቸው ይቻላል ምክንያት ዛሬ ጣልያን ኤምባሲ የራት ግብዣ ይኖርባቸው ይሆናላ!
- በአዲስ አበባ በዓታ ለማርያም ቤተክርስቲያን ካህናት የዳግማዊ አፄ ምንሊክን እና የፊት-አውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ ዲነግዴ 87ኛ ዓመት የእረፍት መታሰብያ በፀሎት አስበዋል።
- የሰማያዊ ፓርቲ ልዩ የፎቶግራፍ አውደ-ርዕይ በፅህፈት ቤቱ ከፍቶ ለሕዝብ አሳይቷል።
- ሸገር ኤፍ ኤም በዜና ሽፋኑ ላይ የባዕታውን የፀሎት መርሃግብር ቀንጭቦ ከማሰማቱም በላይ ''ታሪክን የኃሊት'' በተሰኘ ማስታወሻው ላይ እንዲህ ብሏል-''አፄ ምኒልክ የተለዩ ሰው የሚያደርጋቸው ለሀብት እና ንብረት የማይጨነቁ ይልቁን ከቤተመንግስት ውጭ አንዳችም እርስት እና ንብረት የሌላቸው እና ለልጆቻቸውም አለማውረሳቸው ነው።''
ከዛሬ 100 ዓመት በፊት በአዲስ ዓለም ኦሮሞዎች 'እምዬ' የተባሉት ንጉስ ምንሊክ ዛሬ ቂም የሚይዝ፣ከንፈር የሚነክስ መንግስት ስልጣን ይዞ ዳግማዊ ምንሊክን ኢትዮጵያ በብሔራዊ ደረጃ መዘከር ባትችል በዜና መልክም ሳትናገር አለፈች።ምንሊክ የቅኝ ገዢዎች እና የባንዳዎች ጠላት ነበሩ።በእዚህ እንስማማለን።
ግን ማስታወሻዬን ከመደምደሜ በፊት አንድ ጥያቄ ልጠይቅ ኢህአዲግ/ወያኔ የእዚህን ያክል ተራ ቂም፣ዘረኝነት፣ሸር እና ተንኮል አናቱ ላይ እየጨፈሩበት እንዴት ብሎ ነው ኢትዮጵያን ያክል ሀገር እና ሕዝብ መምራት ይችላል?
ጉዳያችን ታህሳስ 3/2006 ዓም
No comments:
Post a Comment