ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Wednesday, December 4, 2013

ኢህአዲግ በእውቀት ላይ የተመሰረተ ሥራ እየሰራ ላለመሆኑ አይነተኛ ማስረጃ - በደርግ እና በኢህአዴግ መካከል ለብሄር ብሔረሰቦች የሚውል ገንዘብ አመዳደብ ልዩነት


ደርግ በብዙ አምባገነናዊ ድርጊቱ ይጠቀሳል።በብሄር ብሄርሰቦች ጉዳይ ግን ከኢህአዴግ ጋር ምን ይለያቸዋል? እስኪ በሃሳቤ የመጡልኝን ስር የያዙ የምላቸውን ነጥቦች ላንሳ

ደርግ 

1/ ''የብሔር ብሔርሰቦች ኢንስቲትዩት'' የተሰኘ ትልቅ የምርምር ኢንስቲትዩት መስርቶ የታወቁ የታሪክ ምሁራን እነ ፕሮፌሰር ላጵሶ ገልዴቦ እነ ፕሮፌሰር ታደሰ ታምራትን እና ሌሎችም ታላላቅ ስራዎችን እንዲሰሩ አደረገ።ኢንስቲትዩቱ የብሔር ብሔረሰቦች ባህል፣ስር አመጣጥ፣በጋራ የሚያስተሳስራቸው ኢትዮጵያዊነት ወዘተ ላይ ጥናቶች አጥንቷል።የተለያዩ የምርምር ፅሁፎችን፣ዎርክሾፖችን ወዘተ አዘጋጅቷል።ኢንስቲትዩቱ ከሀገር ውስጥ አልፎ የውጭ ዓለም አቀፍ ምሁራንን እየጋበዘ የጥናት ወረቀቶችን ያሰራ ነበር።

2/ ለኢቲቪ ከ 40ሺህ ብር በላይ በጀት መድቦ ''ተጓዥ ካሜራችን'' የሚል በሳምንት አንድ ጊዜ በጋዜጠኛ ብዙ ወንድም አገኘሁ አዘጋጅነት የሚቀርብ  የሚናፈቅ ፕሮግራም ጀምሮ የተረሱ ብሄረሰቦችን  የአኗኗር  ባህላቸውን እና ታሪካቸውን ያስተምር ነበር።ብዙዎቻችን በልጅነት ጊዜ ይህንን ፕሮግራም እናስታውሳለን።

3/ የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን በ'ህብረት ትርኢት' ፕሮግራም ላይ የሁሉንም ብሔሮች ዘፈኖች ሕዝብ እንዲመለከት ያደርግ ነበር። ይህም በተለይ ለታዳጊው ወጣት የሁሉንም  ባህል እንዲረዳ እና እንዲያከብር ያደርግ ነበር።የቲያትር ቤቶች የሚኖራቸው የኪነት ቡድን የብዙዎቹን ብሔሮች ውዝዋዜ መለማመድ ግዴታቸው ነበር።

ኢህአዲግ 


1/ ስለ ብሔር ብሄረሰብ ብዙ ይናገራል፣በሕገ መንግስቱ አንቀፅ 29 ከፈለጉ መገንጠል እንደሚችሉ ያትታል።

2/ የብሔር ብሄርሰቦች ቀን ብሎ ብዙ ዘፈን፣ምግብ፣መጠጥ፣ያዘጋጃል፣ከየብሄሩ ለመጡ አባላቱ ያበላል፣ያጠጣል በብዙ ሺህ የሚቆጠር ብር ያወጣል።


3/ የቴሌቭዥን ፕሮግራሞች አንዱ የአንዱን እንዳይቀላቅል የሚቀርቡትን  ዘፈኖችን ብንመለከት በአማርኛው ላይ የኦሮምኛ እንዳይቀርብ፣በትግርኛው ላይ የአማርኛው እንዳይቀርብ ወዘተ ሆኗል።ይህም ቀድሞ አማርኛ ፕሮግራም ላይ ኦሮምኛው፣ትግርኛው ይቀርብ ስለነበር ሕዝብ እርስ በርሱ አንዱ የአንዱን ባህል የማወቅ ዕድል ነበረው። የእነ ኪሮስን፣አሊብራን የመሰሉ ከያንያን ዝናን ያተረፉት አንድ ለእናቱ በነበረው ቲቪ ህዝቡ እየተመለከተ ነው እንጂ የትኛው ኤፍ ኤም ነው ያስተዋወቀው?

4/ በኢትዮጵያ ታሪክ ታይቶ የማይታወቁ የብሄሬ ድንበር፣ወሰን ተጣሰ ስሞታዎች እና ግጭቶች ተበራክተዋል።ለእዚህም መንግስት ጉዳዩን ለብቻው የሚመለከት አካል እስከመመደብ የደረሰው በእዚሁ ስለ ብሔር ብሔረሰቦች ብዙ በምዘፈንበት ጊዜ ነው።

ባጠቃላይ 

 ለኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ብዙ ሺህ ብር እያወጣ ምግብ የሚበላ መንግስት ነው ጥሩ አደረገ የሚባለው ወይንስ ገንዘብ መድቦ የብሔር ብሄርሰቦች ኢንስቲትዩት የመሰረተ? በእየ ዓመቱ የብሔር ብሄርሰቦች ቀን ተብሎ የሚባክነው ብር ስንት ሥራ ለብሄር ብሄርሰቦቻችን በሰራ ነበር። ኢህአዲግ በእውቀት ላይ የተመሰረተ ሥራ እየሰራ ላለመሆኑ አይነተኛ ማስረጃ ይህም ነው።  እነሆ ዘንድሮም ጅጅጋ ላይ እንደጉድ ይዘፈናል። ያ የብሔር ብሔረሰቦች ኢንስቲትዩትን ያያችሁ? አሁን አለ? 

No comments:

Beynouna Village - Ethiopia (Video) ባለፈው ሳምንት የተመረቀው መተሃራ እምብርት ላይ የተገነባው አስደናቄው የበይኑና ሪዞርት መንደር (ቪድዮ)

Beynouna Village - Ethiopia (Video) ባለፈው ሳምንት የተመረቀው መተሐራ እምብርት ላይ የተገነባው አስደናቄው የበይኑና ሪዞርት መንደር (ቪድዮ)