ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Tuesday, December 31, 2019

የአዲስ አበባ ከተማ - የከተማዋን ነዋሪ ስነ-ልቦና ፣ዓለም አቀፍና አህጉራዊ ማዕከልነትን ታሳቢ ያደረገ የፖሊስ ኃይል ያስፈልጋታል።


ጉዳያችን  GUDAYACHN  
ታህሳስ 21/2012 ዓም (ዴሰምበር 31/2019 ዓም)

የአራዳ ዘበኛ  

አዲስ አበባ በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመርያውን የፖሊስ ሥራ ያስተዋወቀች ከተማ ነች።ዘመኑ 1901 ዓም ነበር አዲስ አበባ የመጀመርያውን የፖሊስ ሰራዊት ጥንስስ የአራዳ ዘበኛ በሚል ስም ያደራጀችው።የኢትዮጵያ የፖሊስ ሰራዊት ታሪክ ጥንስስም እዚህ ላይ ይጀምራል።በወቅቱ ንጉሰ ነገስት ምንሊክ የመጀመርያውን የኢትዮጵያ ፖሊስ የአራዳ ዘበኛ በሚል ለሕዝቡ ሲያስተዋውቁ ያወጡት አዋጅ እንዲህ የሚል እንደነበር ጳውሎስ ኞኞ 'አጤ ምንሊክ' በተሰኘው መፅሐፉ ላይ ጠቅሶታል።


ሞዓ አንበሳ ዘእምነገደ ይሁዳ
ምኒልክ ስዩመ እግዚአብሄር
ንጉሰ ነገስት ዘኢትዮጵያ

አዋጅ!
ለሊት ሌባ እንዳይበዛ፣ ቀን አነባብሮ እንዳያነሳ፣ በተረፈ ክፉን ነገር ሁሉ የሚጠብቅ ዘበኛ ብናቆም ሁሉም ዘበኛ ነኝ እያለ እንዳይዝ ቁጥር እና ባንዲራ ያለበት በራስ ላይ የሚደረግ ምልክት አበጅቻለሁ። ያንን ምልክት ያደረገ ዘበኛ ቢይዝህ መያዝ ነው እንጂ ይህን ጥሰህ የተጣላህ ሰው ትቀጣለህ።
ሚያዝያ ፳፱ ቀን ፲፱፻፩ አመተ ምህረት አዲስ አበባ ከተማ። ይላል።

የአራዳ ዘበኛ ኮፍያው ላይ 'የምስጢር ዘበኛ' የሚል ፅሁፍም ነበረው።

የአራዳ ዘበኛ እስከ 1928 ዓም ጣልያን ኢትዮጵያን እስኪወር ድረስ ዘለቀ።ጣልያን ከኢትዮጵያ ተባሮ ከወጣ ከ1934 ዓም ጀምሮ የኢትዮጵያ ፖሊስ አዲስ ምዕራፍ ተከፈተለት።ሰራዊቱ በአዋጅ ቁጥር 6/1934 በወቅቱ ስሙ አባዲና ፣የኢትዮጵያ ፖሊስ ኮሌጅ መመስረት ጋር ተከትሎ የፖሊስ ሥራ ሳይንሳዊ በሆነ መልክ የሚሰሩ መኮንኖች ሰራዊቱን መቀላቀል ጀመሩ።

የፖሊስ ሰራዊት የህዝብን ፀጥታ የማስከበር ሥራ እስከ 1967 ዓም ድረስ የሚያስከብርበት የተለያየ መንገድ ይጠቀም ነበር።ለምሳሌ የሚሊሻ ታጣቂዎች ከፖሊስ ጋር እንዲሰሩ ማድረግ፣አውጣጭኝ በሚል ሕብረተሰቡን ሰብስቦ በአንድ አካባቢ ሰብስቦ ወንጀል እንዲጋለጥ ከማድረግ ጀምሮ እስከ ፖሊስ እና ርምጃው የሚል ጋዜጣ እና የራድዮ ፕሮግራም እያደገ መጣ።እስከ 1967 ዓም ድረስ የፖሊስ ሰራዊት ሥራ በኅብረተሰቡ ውስጥ የተከበረ ሙያ ነበር። ፖሊስ የሆነ ሰውም የማይዋሽ፣በሕዝቡም ውስጥ የተሻለ ተሰሚነት ነበረው።ከ1967 ዓም ለውጥ በኃላ በከፍተኛ የፖሊስ ሙያ የሰለጠኑ ባለሙያዎች ወደ ማዕከላዊ ምርመራ ተሳቡ የቀሩት ወደ ደርግ የምድር ጦር እና የፖሊስ ሰራዊት መኮንኖች ውስጥ ሲዋቀር የፖሊስ ኃይሉም የሰለጠነ የሰው ኃይል ተዳከመ።ደርግ የህዝቡን መብት ለማፈን የፖሊስ ኃይሉ በቂ ስላልነበር የፖሊስን ሥራ የአብዮት ጠባቂ እና የደህንነት ክፍሉ አፋኝ ቡድን ወሰደው።በመቀጠል ፖሊስ ለትንንሽ የሌብነት ስራዎች ወይንም የፖለቲካ ጉዳይ የለባቸውም ለሚባሉ ወንጀሎች ብቻ የሚፈለግ ሆነ።

በ1983 ዓም ኢህአዴግ ስልጣን ሲይዝ በአራዳ ዘበኛ ጥንስስ የተጀመረው የፖሊስ ሥራ በየክልሉ እንዲከፋፈል ተፈረደበት።የፖሊስ ኃይሉ በክልሎች ደረጃ ሲዋቀር የፖሊስ ማሰልጠኛዎችም በየክልሉ የመክፈት ሥራ ቢይታይም በጥራት እና በደረጃ ግን ዘመኑን የተከተለ ሳይሆን በቂ ስልጠና የሌለው ፖሊስ ሰራዊቱን መቀላቀል ጀመረ።

አዲስ አበባ የራሷ ፖሊስ ኃይል ለምን ተነፈገች?

በዘመነ ደርግ አዲስ አበባ በአብዮት ጥበቃ ስር ብትሆንም የአዲስ አበባ ፖሊስ እና የሸዋ ፖሊስ ዋና መስርያ ቤቱን ከካሳንቺስ ወረድ ብሎ የሚገኘውን ህንፃ ተከራይቶ ይሰራ ነበር።በዘመነ ኢህአዴግ ግን የአዲስ አበባ ፖሊስ ደካማ ሆኖ እንዲደራጅ ከመደረጉም በላይ የፈድራል ፖሊስ ከፍ ተደርጎ እንዲደራጅ ተደረገ።በእዚህ ሳብያ ዘመናዊነት የሚታይባት አዲስ አበባ የከተሜ ማዕረግ ያለው ፖሊስ እንዳማራት ዓመታት ነጎዱ።የኢትዮጵያ ፖሊስ በአባዲና ኮሌጅ በጀመረው አሰለጣጠን መንገድ ዛሬ በ21ኛው ክ/ዘመን የኮምፕዩተር እና ኢንተርኔት ዘመን በሚመጥን መልኩ በብዛት እና በጥራት ማሰልጠን  ይጠበቃል።

ከ2010 ዓም  የለውጥ ሂደት በኃላ የአዲስ አበባ የራሷ ፖሊስ የማግኘት መብት አሁንም አልተከበረም።ሌላው ቀርቶ ከእዚህ ለውጥ በፊትም ሆነ ከለውጡ በኃላ በሕገ መንግስቱ የተቀመጠውን ክልሎች የራሳቸው የፖሊስ ኃይል እንደሚኖራቸው  የተጠቀሰውን መብትም ሳይቀር አዲስ አበባ ላይ ሲደርስ ታግቷል።ይህ ደግሞ አዲስ አበባ የፖለቲካ እና የምጣኔ ሃብቱ ማዕከል እንደመሆኗ መንግሥታት አዲስ አበባን በቀጥታ በሚመሩት የፀጥታ ኃይል ስር የማድረግ ፅኑ ፍላጎት ነው።

የአዲስ አበባ ከተማ - የከተማዋን ነዋሪ ስነ-ልቦና ፣ዓለም አቀፍና አህጉራዊ ማዕከልነትን ታሳቢ ያደረገ የፖሊስ ኃይል ያስፈልጋታል።

የፖሊስ ኃይል አባል አካባቢውን በደንብ የሚያውቅ መሆኑ ብዙ ጥቅም አለው።በመጀመርያ ደረጃ የህዝቡን ስነ ልቦና፣ማኅበራዊ ሕግ  እና አስተሳሰብ የሚረዳ የፖሊስ ኃይል የሚያደርገውን የሚያውቅ ብቻ ሳይሆን የችግር አፈታት መንገዱም አካባቢውን ከማያውቅ በተሻለ መንገድ ሕዝብ የማገልገል አቅም ይኖረዋል።

ከእዚህ አንፃር የአዲስ አበባን ሁኔታ ስንመለከት ደግሞ አዲስ አበባ ከሌሎች የኢትዮጵያ ከተሞች የተለየ ባህሪ እንዳላት እንመለከታለን።አዲስ አበባ በመጀመርያ ደረጃ ሕብረ ብሔራዊ ሕዝብ የሚኖርባት ከተማ ነች።የብሔር ፖለቲካ አንግቦ የሚመጣ ኃይል ለአዲስ አበባ የተናቀ ሥራ ነው።ፖሊስን አዲስ አበባ የምታውቀው ከአራዳ ዘበኛ ጀምሮ እስካሁን ድረስ ሌሎች በጎሳ ዓይን ሲመለከቷት ለአዲስ አበቤ ግን ፖሊስ ፖሊስ ነው።

በሌላ በኩል አዲስ አበባ ከህብረ ብሔር ከተማነቷ በላይ በዓለም ላይ ከኒውዮርክ እና ጀኔቫ ቀጥሎ  ከፍተኛ የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ የሚገኝባት  ከተማ ነች።የአፍሪካ ህብረት ዋና መቀመጫ፣የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአንድ መቶ አምስት በላይ ዓለም አቀፍ መዳረሻው መነሻው አዲስ አበባ ነች።በቅርቡ ደግሞ ኢትዮጵያ ለአፍሪካውያን ካለቪዛ የመግባት ፍቃድ  መስጠቷን ተከትሎ ያለውን ሁኔታ ሁሉ ስንቃኝ አዲስ አበባ በምን ያህል ደረጃ ከአዲስ አበባ ጋር የተናበበ የፖሊስ ኃይል  እንደሚያስፈልግ መረዳት ይቻላል።ሌላው ቀርቶ አሁን በአዲስ አበባ የሚያዙት ሌቦች ከአዲስ አበባ የመጡ ብቻ ሳይሆን ከኬንያ እና ታንዛንያ ጭምር የመጡ ወንጀለኞች እየታዩ ነው።ይህ ማለት በየትኛውም የአዲስ አበባ ፖሊስ ጣብያ ቢያንስ በእንግሊዝኛ በበቂ ሁኔታ ቃል ሊቀበል የሚችል የፖሊስ መኮንን ያስፈልጋል ማለት ነው።

ባጠቃላይ የአዲስ አበባ የራሷ ፖሊስ የመኖሩ ጉዳይ እጅግ አንገብጋቢ ጉዳይ ነው።የፒያሳ ልጆችን ፀባይ፣የቄራ ልጆችን ብሽሽቅ፣ የጉለሌ ልጆችን ዱላ፣የቦሌ ልጆችን አስተዳደግ፣የቀጨኔ ልጆችን አስተሳሰብ የሚረዳ የፖሊስ ኃይል ያስፈልጋታል። ከእዚህ ውጪ በክልል ሰልጥኖ ወደ አዲስ አበባ የሚገባ የፖሊስ ኃይል የአዲስ አበባን ስነልቦና የማይረዳ ብቻ ሳይሆን የአዲስ አበባ ልጅ በሙሉ የክልል ሰው የሚንቁ መስሎ የሚታየው እና በንግግር እና ሃሳብ ሊግባባ የማይችል ፖሊስ በአዲስ አበባ ላይ ማሰማራት በመንግስት እና በአዲስ አበባ ሕዝብ መሃል ያለውን ግንኙነት የሚያበላሽ ብቻ ሳይሆን አዲስ አበባ የፀጥታ ሁኔታዋ እንዳይበላሽ ያሰጋል። አሁንም ለመድገም የአዲስ አበባ ከተማ - የከተማዋን ነዋሪ ስነ-ልቦና ፣ዓለም አቀፍና አህጉራዊ ማዕከልነትን ታሳቢ ያደረገ የፖሊስ ኃይል ያስፈልጋታል።

አዲስ አበባ Addis Ababa City - New Flower of Ethiopia (ቪድዮ)ጉዳያችን GUDAYACHN
 www.gudayachn.com

ኢትዮጵያ ለሊብያ ሰላም እየሰራች ነው።የጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አማካሪ ሙ/ጥ/ዲ/ዳንኤል ክብረት ከሊብያ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያይተዋል።Ethiopia is working for the effort of peace in Libya

Advisor of Ethiopian PM Abiy Ahmed, Daniel Kibret and Libya FM Mohamed Sayala 

ጉዳያችን ዜና  GUDAYACHN News 
ታህሳስ 21/2012 ዓም (ዴሰምበር 31/2019 ዓም)
(Please read in English under Amharic version here below)

ኢትዮጵያ ለሊብያ የሰላም ስኬት እየሰራች መሆኗን ሊብያ ኦብሰርቨር የተሰኘው የድረ ገፅ ጋዜጣ በትናንትናው ዕለት ከሊብያ ዘግቧል።እንደዘገባው ከሆነ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አህመድ አማካሪ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ያለፈው እሁድ ሐምሌ 19/2012 ዓም የኢትዮጵያ መንግስት ልዑካንን በመምራት  በሊብያ ከውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከሞሀመድ ሳያላ  ጋር መወያየታቸውን እና ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ህብረት እና ከተባበሩት መንግሥታት ሉዑክ ጋር በመሆን ጥረቷን እንደምትቀጥል መግለጣቸውን ዘገባው ገልጧል።

በሌላ በኩል የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ሞሐመድ ሳያላ በኢትዮጵያ እና በሱማልያ መካከል ያለው ግንኙነት በመልካም ሁኔታ መቀጠል እንዳለበት ገልጠው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አሕመድ ለሊብያ ቀውስ ሰላም ለማፈላለግ ለሚያደርጉት ጥረት ሁሉ ሊብያ በደስታ የምትቀበለው መሆኑን ገልጠዋል።ሊብያ ኦብሰርቨር የተሰኘው የድረ ገፅ ጋዜጣ ሊብያ ውስጥ ካሉት የድረ ገፅ ጋዜጦች ውስጥ በቀዳሚነት የሚገኝ የዜና ገፅ ነው።

==================================

Ethiopia backs efforts of peace in Libya

Adviser of the Ethiopian Prime Minister, "Dikon Daniel", confirmed on Sunday, during his visit with a government delegation to Libya, his country's desire to support efforts in bringing stability to Libya through a political solution, in coordination with the African Union and the UN mission.
Daniel discussed with Libyan Foreign Minister, Mohamed Sayala avenues of enhancing cooperation between the two countries in many fields.
For his part, Sayala commended the relationship between the two countries and welcomed the efforts of the Ethiopian Prime Minister "Abiy Ahmed" to contribute to solving the Libyan crisis.
Source - Libya Observer (https://www.libyaobserver.ly/inbrief/ethiopia-backs-efforts-peace-libya

 www.gudayachn.com

Thursday, December 26, 2019

ኡስታዝ አሕመዲን ጀበል የታክሲ ላይ ፖስተር ወስደው የሙስሊሙን ማኅበረሰብ ለመቀስቀስ የተጠቀሙበት መንገድ የኃይማኖት ሰው ናቸው ወይንስ የፖለቲካ አክቲቪስት? የሚል ጥያቄ ጭሯል።


ጉዳያችን / Gudayachn
ታሕሳስ 16/2012ዓም (ደሴምበር  26/2019 ዓም)

እንደአውሮፓውያን አቆጣጠር ታህሳስ 21/2019 ዓም ኡስታዝ አሕመዲን ጀበል በፌስ ቡክ ገፃቸው ላይ ይዘው የወጡት የአንድ ሚኒ ባስ ላይ የተለጠፈ ፖስተር ጠቅሰው ከሞጣ መስጂድ የቃጠሎ አደጋ ጋር ለማገናኘት የሄዱበት ርቀት አስደንጋጭ ሆኖ አግኝቼዋለሁ።ኡስታዝ አሕመድ ጀበል በሚኒ ባስ የውጪ ክፍል ላይ ተለጥፎ ያነሱት  ፎቶ እና እንደ ትልቅ ወንጀል ያብጠለጠሉበት  ፖስተር ''የአባቶቻችንን ታሪክ እንደግማለን '' የሚለውን  ፅሁፍ  ነው።

በቅድምያ በየትኛውም ቦታ የሚደረግ የሃይማኖት ቦታ የማቃጠል፣የመግደል እና የመንቀፍ ተግባር የሚወገዝ ብቻ ሳይሆን፣ይህንን የፈፀሙም ሆነ እንዲፈፀም የረዱ ለፍርድ መቅረብ አለባቸው።በሞጣ መስጂድም ሆነ በባሌ፣ሐረር እና ሲዳማ አብያተ ክርስቲያናት ላይ ቃጠሎ ያደረሱ በሙሉ ለፍርድ መቅረብ እና ተመጣጣኝ ቅጣት ማግኘት አለባቸው።ይህንን ኢትዮጵያውያን ሙስሊምም ሆነ ክርስቲያኑ ከአደባባይ ንግግር እስከ ማኅበራዊ ሚድያ ደጋግሞ የገለጠው እና ሁላችንም የምንስማማበት ጉዳይ ነው።

ለእዚህ ፅሁፍ መነሻ ያደረገኝ አደገኛ አካሄድ ግን የሐይማኖት ቀዳሚ ሰዎች ወደ አክትቪዝም መግባት አደገኛ አካሄድ ነው። ኡስታዝ አህመዲን ጀበል በፌስ ቡክ ገፃቸው ላይ በአንድ የሚኒባስ ታክሲ ውጪያዊ ክፍል ላይ የተመለከቱትን ''የአባቶቻችንን ታሪክ እንደግማለን'' የሚል ሌላ ቦታ የተፃፈ ጥቅስ ከሞጣ የመስጊድ ቃጠሎ ጋር አገናኝተው ለመቀስቀሻነት  ሲጠቀሙ  እንዲህ የሚል ዓረፍተ ነገር በፌስቡክ ገፃቸው ላይ ተጠቅመዋል።እንዲህ ይነበባል -''"የአባቶቻችንን ታሪክ እንደግማለን" ሲሉ የቱን ታሪክ ሊደግሙ ነው ብለህ መቁጠር ብትጀምር ባለፈው አንድ ዓመት ዉስጥ ብቻ  ብዙ መቁጠር ትችላለህ። ለምሳሌ ትናንት ምሽት በሞጣ ከተማ መስጂዶችን እና የሙስሊሞችን ንብረቶች አቃጥለው' ----' በማለት  ያብራራሉ።

የአባቶቻችን ታሪክ መልካም የሆነውን የማንደግመበት ምክያት ምንድን ነው? የኢትዮጵያን ነፃነት ለመጠበቅ ያደረጉት ተጋድሎ፣ኢትዮጵያን ከዓለም ቀዳሚ  ለማድረግ ከስነ ፅሁፍ እስከ ስነ ህንፃ የሰሩትን መልካም ሥራ፣ግጭቶችን በሰላም ለመፍታት ታቦትና ድንጋይ ተሸክመው ይቅር መባባላቸው  እና ሌሎቹን የማንደግመብት ምክንያት ምንድነው? ኡስታዝ አህመዲን በኢትዮጵያ መስራች አባቶች ላይም ሆነ ላለፉት ሁለት መቶ ዓመታት በኢትዮጵያ ፖለቲካዊ፣ማኅበራዊ እና ምጣኔ ሃብታዊ ጉዳዮች ላይ ወሳኝ ሚና የተጫወቱትን አባቶች ሁሉ መስጂድ ያቃጠሉ ይመስል በፈስቡክ ያብጠለጠሉበት  አግባብነት የሌለው አገላለጥ አደገኛ የታሪክ ትርክት ውስጥ እየገቡ እንደሆነ አመላካች ነው።አባቶቻችን የመሐመድን ቤተሰቦች  ያስጠጉ፣ አስጠግተውም በእምነታቸው ላይ ተፅዕኖ ሳይፈጥሩ በሰላም ወደ መካ የላኩ የተከበሩ አባቶች የነበሩባት ምድር ነች ኢትዮጵያ። አባቶቻችን ከሸህ ሁሴን ጀብሪል ጋር ተመራርቀው የኖሩ፣ከአባጅፋር ጋር ተመካክረው የኖሩ አባቶች ናቸው ያሉን።ይህንን መልካም ተግባር መድገም ጥፋቱ ምኑ ላይ ነው?

ኡስታዝ አሕመዲን የዛሬ ዓመት ገደማ ለ'ኢትዮ ቱብ' በሰጡት ቃለ መጠይቅ ላይ ኢትዮጵያን እስር ቤት ከመግባታቸው  በፊት በደንብ እንደማያውቁ እና እስር ቤት ከገቡ በኃላ እንዳወቁ አብራርተው ነበር።በእርግጥ እርሳቸው መጅሊሱ አካባቢ ባሉ አለመግባባቶች ውስጥ ለረጅም ጊዜ የሄዱበት ጉዳይ እንዳለ ይሰማል።ይህ በራሱ ጉዳዩን በሚያውቁ ቢብራራ ይሻላል።ኡስታዝ አህመዲን ግን ከእስር ከተፈቱ በኃላስ የኢትዮጵያን ሕዝብ ያውቁታል ወይ? ካወቁትስ ቀረብ ብለው ተረድተውታል ወይ? ሙስሊም ከክርስቲያኑን ለማጋጨት ይህ ትውልድ ያልኖረውን የአባቶቹን ታሪክ እየጠቀሱ ያውም በ16ኛው ክ/ዘመን አንድ ሙስሊም ተገድሎ ነበር በሚል አገላለጥ ከላይ የጠቀስኩትን የታክሲ ፖስተር ጋር አያይዘው ግራ እና ቀኙን ያልለየ  ምስኪን ኢትዮጵያዊ ሙስሊም እና ክርስቲያን ላይ ለምን የሞት አዋጅ የሚጠራ የቅስቀሳ ፅሁፍ ይፅፉበታል? ለምን? ይህ ከአንድ የሃይማኖት  አስተምሮ እንዳለው ከሚናገር ሰው የሚጠበቅ አይደለም።አሁንም ርጋታ፣ማስተዋል እና ወደ በጎ ህሊና መመለስ ጠቃሚ ነው።

በያዝነው ሳምንት ውስጥ ከአንድ ሙስሊም የተላለፈ ታላቅ ምክር፤ ለኢትዮጵያ ክርስቲያኖች እና ሙስሊሞች (ቪድዮ)

ምንጭ = አደባባይ ሚድያ 
ጉዳያችን GUDAYACHN
 www.gudayachn.com

Thursday, December 19, 2019

የምስራች! ኢትዮጵያ የመጀመርያዋን ሳተላይት ወደ ጠፈር አምጥቃለች። Ethiopia’s first remote sensing satellite, ETRSS-1, launched to space this morning at 03:21 GMT December 20/2019.(ቪድዮ ይመልከቱ)


ጉዳያችን /Gudayachn

ታህሳስ 10/2012 ዓም (ዴሰምበር 20/2019 ዓም)

የምስራች! ኢትዮጵያ የመጀመርያዋን ሳተላይት ወደ ጠፈር  አምጥቃለች። 
Ethiopia’s first remote sensing satellite, ETRSS-1, launched to space this morning at 03:21 GMT December 20/2019.

According to African News this morning the 70 kg multi-spectral civil Earth observation will provide data for Ethiopia’s authorities and research institutions to monitor the environment and study weather patterns for better agricultural planning, early warning for drought, mining activities and forestry management.

ሳተላይቷ -
- በምድር ላይ ያለ 13 ሜትር ርዝመት ያለውን ነገር ሳይቀር ከጠፈር ላይ ለይታ መረጃ ትልካለች
- የምልከታዋ ፍጥነት መሬት በራሷ ዛብያ ላይ ከምትዞርበት በፈጠነ መልክ መረጃ ትልካለች 
- በአራት ቀናት መላዋ ኢትዮጵያ ያለውን መረጃ መሰብሰብ ትችላለች።
- በሃምሳ አምስት ቀናት መላው ዓለም ያለውን መረጃ የመሰብሰብ አቅም አላት፣
- ኪሎዋ 70 ኪሎ ነው።
- ከምድር 700 ኪሜትር ከፍታ ላይ ትገኛለች።
- በማዕድን፣የአየር ንብረት፣በደን ሽፋን፣ ብዙ አልተወራም እንጂ ለፀጥታ ጉዳይ ሁሉ ጥቅሟ ብዙ ነው።
- የመቆጣጠር ሥራው ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያውያን በእንጦጦ ተራራ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ህዋ ምርምር ጣብያ ይከናወናል።
- በቀጣይ አስር ዓመት ኢትዮጵያ እስከ አስር የሚደርሱ ሳተላይት ወደ ጠፈር ለመላክ እቅድ እንዳላት አንድ ከፍተኛ የኢኖቨሽን እና ሳይንስ ባለስልጣን አስታውቀዋል።

ቪድዮ ይመልከቱ 


ጉዳያችን GUDAYACHN
 www.gudayachn.com

Tuesday, December 17, 2019

ምሁራዊ ጀሃድ በኢትዮጵያዊነት፣በታሪክ ምሁራን፣ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን እና በአገልጋዮቿ ላይ ዘመቻ ከፍቷል።ሁሉም ሊመክተው ይገባል።


Cartoon picture source = coast2coastmixtapes.com

ጉዳያችን / Gudayachn
ታኅሳስ 8/2012 ዓም (ዴሴምበር 18/2019 ዓም) 

እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር  ቅዳሜ፣ጥቅምት 13/2001 ዓም የወጣው የ''ኒውዮርክ ታይምስ'' ጋዜጣ ''The deep Intellectual Roots of Islamic Terror'' በሚል ርዕስ ስር ባሰፈረው ፅሁፍ ላይ እንዲህ የሚል ፅሁፍ ሰፍሮ ይገኛል።
     ፅንፈኛ የእስልምና ጀሃድ አባላት በ1981 ዓም እኤአ  የግብፁን መሪ  አንዋር ሳዳት ከገደለ በኃላ ''The Neglected duty'' (ችላ የተባለው ተግባር) በሚል ርዕስ ስር ባለ ሃምሳ አራት ገፅ  ሰነድ አሰራጭቶ ነበር።የሰነዱን ይዘት ይሄው የኒው ዮርክ ታይምስ ጋዜጣ ሲያብራራ ቡድኑ ለመግደሉ ''ትክክለኛነት'' ለማሳመን የተጠቀመበት ሰነድ ሲሆን እንደ ሰነዱ አባባል ''ትክክለኛ እስልምና'' የማይቀበሉ መንግሥታት ላይ ግድያ እና በሰዎች ላይ የሚደርስ ጭፍጨፋን ያበረታታል።የዓለማችን ቀንደኛ ሽብርተኛ ቢንላደን የእዚሁ ፅንፈኛ ቡድን አባል የሆነው ከዓመታት በፊት እንደነበር ጋዜጣው ያትታል።

አሁን ባለንበት ዘመን ጅሃድ በቀጥታ ንፁሃንን መግደል ብቻ አይደለም።ከመግደል የሚቀድም ''ምሁራዊ ጀሃድ'' ነው።

ምሁራዊ ጀሃድ ምንድነው?

በ1985 ዓም እኤአ ባል ስቴት ዩንቨርስቲ (Ball State University) ሊንዳ ኮሎኮትሮኒስ (Linda K.Kolocotronis)  ''An intellectual historical study of Islamic Jihad during the life of Muhammad and in the twentieth century" በሚል ርዕስ በፃፉት የየዶክትሬት ማሟያ ፅሁፋቸው ''አብስትራክት'' ላይ ጅሃድ በጦርነት ብቻ ሳይሆን ''ዲፕሎማሲያዊ ጀሃድ'' የዘመናዊው ዓለም መተግበርያ እንደሆነ ካተተ በኃላ ጀሃድ በፊት ለፊት ሰው ከመግደል ባለፈ ሌሎች ስልቶች እንዳሉት ያትታል።

ምሁራዊ ጀሃድ የፊት ለፊት ንፁሃንን ከመግደል በፊት የቀደመ ፕሮፓጋንዳ ነው።በተለይ በዘመናዊው የመገናኛ መንገድ ምሁራዊ ጀሃድ በረቀቀ መንገድ አገራት ላይ መረቡን እየዘረጋ የስነ ልቦና ጦርነት ያካሂዳል።ምሁራዊ ጀሃድ የሚከወነው በከፍተኛ ደረጃ በተማሩ እና የትምህርት ችሎታቸውን ግን ለተንኮል እና እውነተኛውን የአገራት ታሪክ በማጣመም፣ቀዳሚ የታሪክ እና የሃይማኖት ምሁራንን ስም ማጥፋት፣ ለዓላማቸው ማስፈፀምያነት የማይስማማቸውን መንግስት እና የመንግስት መሪ፣ፖለቲከኛ እና  ታዋቂ ጋዜጠኞች ላይ ጭምር በምሁር ቃላት የተከሸኑ የጥፋት ፕሮፓጋንዳ ይከፍታሉ። የምሁራዊ ጀሃድ አራማጆች የአፈፃፀም ስልቱን እና የሰው ኃይል ምልመላቸውን የሚያካሂዱት በረቀቀ መንገድ ከመሆኑም በላይ በገንዘብ ኃይል ከጀርባ ይደገፋሉ።

ምሁራዊ ጀሃድ በኢትዮጵያ ስራውን ከጀመረ ቆየት ያለ ጊዜ አለው።ይህ በአካል ንፁሃን ክርስቲያኖችን በመጨፍጨፍ እና አብያተ ክርስቲያናትን ለሚያቃጥለው የጥፋት ኃይል የተኩስ ሽፋን በመስጠት ለእኩይ ድርጊቱ የሐሰት ፍትሃዊ ፅሁፎች በማጉረፍ ለድርጊቱ ሌላ ምክንያት በመስጠት ሟቾች መሞት እንደነበረባቸው ለመተረክ የሚደፍር አይን አውጣ ቡድን ነው። የምሁራዊ ጀሃድ አባላት እንደማንኛውም ሰው ህዝቡ ውስጥ ገብተው የሚኖሩ አንዳንዶቹ በስልጣን እርከን ውስጥ ተሰግስገው የመንግስትን መዋቅር በማዳከም እና ሕዝብ በመንግስት እንዲማረር ሌት ተቀን የሚደክሙ ናቸው።በሌላ በኩል ምሁራዊ ጀሃድ  አባላት በዩንቨርስቲ ውስጥ ከታሪክ ምሁርነት እስከ ፅንፈኛ የጎሳ ሚድያዎች ውስጥ ተሰግስገው የሚሰሩ ናቸው። የእዚህ ቡድን አባላት ከሚሰሯቸው የጥፋት ስራዎች ውስጥ የሚከተሉት ተጠቃሽ ናቸው። እነርሱም -

  • የኢትዮጵያን ታሪክ እያጥላሉ በማኅበራዊ ሚድያ መልቀቅ፣
  • ኢትዮጵያ የምትባል አገር የለችም፣ኢትዮጵያ ጥንት የሚባለው ምስራቅ አፍሪካ በሙሉ ነበር የሚል ትርክት በመተረክ የታሪክ አሻራ የሌላት አገር አድርጎ ማቅረብ፣
  • በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ላይ የማጥላላት ዘመቻ በመክፈት እና ከአንድ ብሔር ጋር እያያዘ ለመነጠል መሞከር፣ቤተ ክርስቲያን ኢትዮጵያን ወደ ኃላ ያስቀረች አስመስሎ የሚያቀርብ የውሸት ጥናት መሰል ፅሁፍ ማዥጎድጎድ፣
  • ባለፈው ማንነቱ የማይኮራ ትውልድ ለመፍጠር የውሸት ትርክት ማስፋፋት፣
  • የኢትዮጵያ ጥቅም በሆኑ ጉዳዮች ላይ ሁሉ በተቃዋሚ ስም በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ ማጥላላት እና ማጠልሸት፣
  • በኢትዮጵያዊነታቸው የሚያምኑ እና ይህንኑ በሥራ ያስመሰከሩ ጋዜጠኞች፣ምሁራን እና የሃይማኖት ምሁራን ላይ በቀጥታ የስም ማጥፋት ዘመቻ መክፈት። እዚህ ላይ ሰሞኑን በሙሐዘ ጥበባት ዲ/ን ዳንኤል እና ''አክራሪ እስልምና በኢትዮጵያ'' የተሰኘው መፅሐፍ አዘጋጅ በመልአከ ኤዶም ቀሲስ ኤፍሬም እሸቴ ላይ የተከፈተው የማኅበራዊ ሚድያ ዘመቻ መጥቀስ ይቻላል፣
  • ከፅንፈኛ የመካከለኛው ምስራቅ አገሮች ጋር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በመገናኘት በአገር ውስጥ ላላቸው ሕዋስ እና  የፅንፍ መገናኛ ብዙሃን ድጋፍ በማግኘት በአገር ውስጥ በጎሳዎች መሃል ግጭት እንዲፈጠር ማሴር እና 
  • ፖለቲካዊ፣ማኅበራዊ እና ምጣኔ ሃብታዊ ቀውስ ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲፈጠር ካደረጉ በኃላ የፖለቲካ ስልጣን ለመያዝ መስራት የሚሉ ተጠቃሾች ናቸው።
የምሁራዊ ጀሃድ ዋና አንቀሳቃሾች በአሁኑ ወቅት በአክትቪስትነት ተከስቷል።ለስውር ስራው ሽፋን ደግሞ አንድ ጊዜ በጎሳ ፅንፈኛ ኃይሎች ስም በመደራጀት፣ሌላ ጊዜ ደግሞ በቀጥታ የኢትዮጵያን አንድነት በመፃረር በአገሪቱ ውስጥ የፅንፍ እስልምና እንቅስቃሴ ሲያበረታታ ይታያል። በኢትዮጵያ ውስጥ የምሁራዊ ጀሃድ ሥራ ላይ የተሰማራው ቡድን ረዘም ላለ ጊዜ እራሱን ለመደበቅ በመሞከር ለሚሰራቸው የቅሰጣ ስራዎች የጎሳ ፖለቲካ እና የብሔር ግጭቶችን እንደሽፋን ሲጠቀም እና በእዚህም እያስታከከ ኢትዮጵያዊነትን ሲያጥላላ፣ኢትዮጵያዊነት ላይ የሚኖሩትን ሲያሳድድ እና በቅርቡ ደግሞ ለረጅም ጊዜ በፕሮፓጋንዳ  ሲሰራበት የነበረውን ኢትዮጵያን እና የኢትዮጵያን ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ሲያጥላላ  ኖሮ የፀጥታ ችግር በተፈጠረባቸው ክፍተቶች ሁሉ ባገኘው አጋጣሚ ክርስቲያኖችን ሲገድል እና አብያተ ክርስቲያናትን ሲያቃጥል  በግልጥ ታይቷል።የምሁራዊ ጀሃድ ዋና ተግባር ኢትዮጵያን ማናጋት ነው።ለእዚህ ደግሞ ዋና ምክንያቱ  ከትርምሱ እንደሚያተርፍ ያስባል።ትርምሱ ሲቀጥል ኢትዮጵያን ከስር ወደላይ ለመገልበጥ በሰይፍ ዓላማውን ለማስፈፀም ያሰፈሰፈ  የጥፋት ቡድን ነው።

ለማጠቃለል የምሁራዊ ጀሃድ ቡድን በፅንፍ የጎሳ ፖለቲካ ከኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ እስከ ቤንሻንጉል፣ከባሌ ዶሎ መና እስከ አርሲ የተሞከረው የጎሳ እልቂት ድግስ ባለመሳካቱ በግልጥ የነበረ እውነተኛ መልኩን ማለትም የኢትዮጵያ ሙስሊም ወገኖቻችን ፈፅመው የማይቀበሉትን ኢትዮጵያዊነትን እና ኦርቶዶክስ ሃይማኖትን ለመናድ በማኅበራዊ ሚድያ በግልጥ ለመምጣት ተገዷል። በነገራችን ላይ የምሁራዊ ጀሃድ አራማጅ ቀደም ብሎ በአሜሪካ የፅንፈኛው ኃይል መንገድ ሜንጫ  መሆኑን ሳያውቀው የተነፈሰው ፈልጎት አልነበረም።ድንገት ሳያውቀው የወጣበት ሚስጥር ነው።ሰሞኑን በኢትዮጵያ ታሪክ ላይ  ደካማ እና የተረት ተረት ወግ ጥረቃ ፅሁፎች በማኅበራዊ ሚድያ ላይ የመለቀቅ እውነተኛ ምስጢር ተስፋ የመቁረጥ ውጤት ነው።በታሪክ እና የሃይማኖት ምሁራን ላይ የስም ማጥፋት ዘመቻ መከፈቱም ሌላው የመደናገጥ እና የመደናበር ውጤት ነው። ይህ ማለት ግን የሕግ እና ስርዓት የማስከበር ኃላፊነት ያለበት መንግስት የምሁራዊ ጀሃድ አራማጆችን እና የህዝቡን ፀጥታ ለማወክ በሚንቀሳቀሱ ላይ ሕጋዊ ሥራ መስራት አለበት።ጉዳዩን በቸልተኝነት ሊያልፈው አይገባም። ሕዝቡም ካለምንም ማመንታት የጀሃድ ምሁራን ቡድኖችን በየትኛውም የተቃውሞ አክትቪዝም ስራም ሆነ የፖለቲካ ተቃዋሚ ወይንም የመንግስት መዋቅር ውስጥ ቢገኙ ማጋለጥ እና ለሕግ እንዲቀርቡ ማድረግ ይገባዋል። በሌላ በኩል ኃላፊነት የሚሰማው ኢትዮጵያዊ ምሁር በሙሉ የምሁራው ጀሃድ አራማጆችን ፅሁፍ እግር በግር እየተከታተለ ማምከን እና የውሸት መጋረጃ በአደባባይ ማጋለጥ አለበት።  
ጉዳያችን GUDAYACHN 
 www.gudayachn.com

Monday, December 16, 2019

የኢትዮጵያ የመንግስት ራድዮ እና ቴሌቭዥን ዜና ይዘት ስብጥር ጉዳይ ካልተስተካከለ ለአገር አንድነት አደጋ አለው (ጉዳያችን ሃሳብ)

ጉዳያችን / Gudayachn
ታኅሳስ 6/2012 ዓም (ዴሰምበር 16/2019 ዓም)

በኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙኃን በአገሪቱ ማኅበራዊ እና ፖለቲካዊ አስተሳሰቦች ላይ የራሳቸውን አሻራ በአጭር እና በረጅም ጊዜ ማስቀመጣቸው የማይካድ ሀቅ ነው።ጥያቄው ግን የመገናኛ ብዙሃኑ ተፅኖ በምን ያህል መጠን እየሄደ ነው? ተፅኖው አዎንታዊ ነው ወይንስ አዎንታዊ? የሚለውን ጥያቄ የሚመልስ ከስር ከስር እየተከታተለ የሚያጠና አካል አለመኖሩ ጉዳት አለው።የሚከታተለ እና ሪፖርቱን ለሕዝብ የሚያቀርብ አካል አለመኖሩ ግን የመገናኛ ብዙኃኑን አዎንታውም ሆነ አሉታዊ ተፅኖ ከመፍጠር ግን የሚገታቸው አይደለም። እዚህ ላይ መንግሥታዊው የመገናኛ ብዙኃን ኤጀንሲን አልዘነጋሁትም።ይህ ድርጅት ግን ብዙውን ጊዜ ከፖሊሲ እና መመርያ አንፃር የመገናኛ ብዙሃንን ከመከታተል ባለፈ ጠለቅ ያለ ጥናት አስጠንቶ ለሕዝብ ሲያቀርብ አልገጠመኝም።

በአሁኑ ወቅት ያለው ዜና በመንግስት መገናኛ ብዙሃን ምን ይመስላል?


የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ከ2010 ዓም የኢህአዴግ የለውጥ ጅማሬ በፊት ከነበሩበት አቀራረብ በብዙ ተቀይረዋል።ከተቀየሩበት መንገድ አንዱ በተቻለ የተለያየ የኅብረተሰብ ክፍል ይነካል ያሉትን ዜና ለማካተት ጥረት አለ።ለምሳሌ በቀድሞ ጊዜ ከነበረው የደረቀ ፕሮፓጋንዳ አሁን በቴክኒክም ሆነ በአቀራረ የተሻለ ሁኔታ አለ።ለምሳሌ ቀድሞ ከአራት ኪሎ ብቻ ለሚወጡ  ምናልባት የፓርላማውን መክፈቻ ብቻ ያውም ከስንት አንዴ በመንግስት ከታዘዙ ብቻ የቀጥታ ስርጭት ይሸፍኑ የነበሩ የመገናኛ ብዙኃን አሁን በበርካታ ክንውኖች ላይ የቀጥታ ስርጭት ያሳያሉ።በሌላ በኩል የዜና ዝግጅቶች በተመሳሳይ ሰዓት በቀጥታ በማኅበራዊ ሚድያ መታየታቸው እና በዩቱብ መጫናቸው ቀደም ብሎ የተጀመረ ቢሆንም አሁን ግን ካለምንም መቆራረጥ እና በዕለቱ ማግኘት የሚቻልበት ሁኔታ አለ።ይህም ሆኖ ግን የዜና ሽፋኞቹ  በክልል የታጠሩ እና አንዱ ስለሌላው በሚገባ እንዲያውቅ የሚያደርግ አይደለም።


 የኢትዮጵያ የመንግስት ራድዮ እና ቴሌቭዥን ዜና ይዘት ስብጥር ጉዳይ ካልተስተካከለ ለአገር አንድነት አደጋ አለው

በእዚህ አነስተኛ ፅሁፍ ለማንሳት የምሞክረው  ዋናው ጉዳይ የመንግስት ራድዮ እና ቴሌቭዥን ዜና ይዘት መላው ኢትዮጵያን የካለለ አለመሆኑ በአጭርም ሆነ በረጅም ጊዜ የሚፈጥረው አደገኛ የመለያየት ጥፋት ይኖራል።ለእዚህ መነሻዬ የተጠና መረጃ ኖሮኝ አይደለም።ነገር ከራሴ ምልከታ ነው።ምልከታው ግን ትክክል እንደሆነ እና የአደጋው ውጤት በራሱ ከገመትኩትም በላይ ሊሆን ይችላል።

የዜና ስብጥሩ ችግሩ እና መፍትሄው 


ስለአንድ የጋራ አገር የተለያየ መረጃ የደረሰው ትውልድ ነገ ይጣላል።ለዛሬው  የወጣቶች በዩንቨርስቲ ግቢ ውስጥ ፀብ አንዱ መነሻ ትናንት የተሰጠው የመገናኛ ብዙሃን በአንድ አገር ውስጥ የተለያየ መረጃ መሰጠቱ ነው።በመንግስት መገናኛ ብዙሃን በአማርኛ፣ኦሮምኛ፣ትግርኛ፣ሱማልኛ፣አፋርኛ የሚተላለፉ ዜና ለሁሉም ኢትዮጵያዊ ይደርሰዋል? ለምሳሌ ሁሉም ዜና በተለያየ ልሳን ሲያቀርቡ ቀዳሚ የሚያደርጉት በመንግስት ቀዳሚ የሆነውን ዜና ለምሳሌ በጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ ወይንም የተወካዮች ምክርቤት የተደረገ እና ሌላም ዜና በተመሳሳይ መልክ ያቀርባሉ።ይህ ተገቢ ነው የዕለቱ ቀዳሚ አጀንዳ ለሁሉም ልሳን ዜና መቅረቡ ተገቢ ነው። 


የመረጃ ክፍተቱ የሚመጣው ግን እዚህ ላይ አይደለም።ወደ ክልሎቹ ስመጣ ነው ችግሩ። የአማርኛ ልሳን ዜና ላይ ስለ አዲስ አበባ እና ከክልሎችም በጣም ተመርጠው የጎሉ የተባሉት ይቀርባሉ።በኦሮምኛ ልሳን የሚነበበው ደግሞ በቀዳሚ የመንግስት የዕለቱን ዜና ካወራ በኃላ በዝርዝር ወደ ኦሮምያ ክልል ያሉ ዜናዎች ያወራል። የትግርኛውም፣የሱማለውም ሆነ የአፋሩ ተመሳሳይ እንደ አማርኛው፣ኦሮምኛው እና ትግርኛው በዝርዝር ስለክልላቸው የሚዘግቡትን ያህል የአማርኛው ስለ አዲስ አበባ ያለውን ዝርዝር ለኦሮምኛው ልሳን አድማጭ አይነግሩትም፣የአማርኛው ዜና ላይም በዕለቱ አምቦ ከተማ ምን እንደተደረገ ከኦሮምኛው ወስዶ ለአማርኛ ልሳን ሰሚው አያወራም።ሁሉም ላይ የሚታየው ችግር ይህ ነው።ለእዚህ ደግሞ ዋናው ምክንያት አንዳቸው ከአንዳቸው በእየእለቱ ዜና አይቀያየሩም።ስለ ኦሮምያ ክልል መረጃ ለማግኘት ከአማርኛው ዜና አጠናቃሪ በተሻለ የኦሮምኛ ክፍሉ የልሳኑ ተናጋሪ  በመሆኑ የበለጠ ዝርዝር መረጃ የማግኘት ዕድል አለው።በሌላውም እንዲሁ ነው። ሁሉም በየራሱ ልሳን ያጠናቀረውን ዜና ያቀርባል እንጂ የሌላውን ዝርዝር ገብቶበት ለሌላው አይነግረውም።በእዚህም አዲስ አበቤ በአንድ መቶ ኪሎ ሜትር ርቀት ስለምትገኘው አዳማ (ናዝሬት) መረጃ ያጥረዋል።የአዳማ ነዋሪም ስለ ባህርዳር ለማወቅ የአማራ መገናኛ ብዙሃን ልያስስ ነው ለእዛውም የልሳን ማወቅ እና አለማወቅ ካልገደበው። በጠገላብጦሽም ብናየው ተመሳሳይ ነው። 


ይህ ጉዳይ ደግሞ ከፍተኛ የመረጃ ክፍተት በአንድ አገር በሚኖር ሕዝብ መሃከል ፈጥሯል።ይህ የመረጃ ክፍተት ደግሞ ፖለቲካውን፣ማኅበራዊ  ኑሮውን እና ምጣኔ ሃብቱን ሳይቀር በአጭር እና በረጅም ጊዜ ይጎዳዋል።ጉዳቱ ደግሞ በአጭር ጊዜ ብቻ ሳይሆን በረጅም ጊዜ አገር የሚለያይ እና የተለያየ አስተሳሰብ ያለው ትውልድ የመፍጠር አደጋ አለው።

 የመንግስት የመገናኛ ብዙሃን ዋናውን ብሔራዊ ዜና በጋራ ካዘጋጁ በኃላ የአማርኛው ልሳን ከኦሮምኛው እና ትግርኛው ልሳን ያሉትን ዜናዎች  አስተርጉሞ በዝርዝር ስለ ኦሮምያ ክልል ትግራይ ክልል እና ሌሎችም ያሉትን ዝርዝር ጉዳዮች በዜና እንዲያቀርብ እንፈልጋለን። የአፋር፣የሱማለውም ሆነ የሌላው እንዲሁ የአማርኛ ዜናዎች የያዙትን የዕለቱን ይዘት  በዝርዝር ተርጉመው ለአድማጮቻቸው ማስደመጥ አለባቸው።ኢትዮጵያውያን እርስ በርስ የተሳሰሩ ናቸው።ባህርዳር ያለው ስለ ደምቢዶሎ ውሎ ማወቅ ይፈልጋል።አሳይታ ያለው ስለሞያሌ ውሎ ማወቅ ይፈልጋል።አዲስ አበቤ ስለ ዶሎ መና ያለው የአንዲት መንደር መንገድ ጠረጋ ዜናም ቢሆን መስማት ይፈልጋል።ከዜናው ትንሽነት እና ትልቅነት አይደለም ጉዳዩ። ሕዝብ የሚተነትንበት የራሱ አይን አለው።አንዱ ስለአንዱ በዝርዝር ካወቀ ችግሩንም ሆነ ጉዳቱን፣ደስታውንም ሆነ ሀዘኑን ይረዳል።በመረዳት ብቻ አይቆምም ርዳታ ሲፈልግ ይደርስለታል።አሁን ያለውሁኔታ ግን ሁሉም እንደ ጋሪ ፈረስ በየልሳኑ የምቀለውን  የአካባቢውን ዜና እያቀረበ ሌላው ሳይሰማው እንደ ጋሪ ፈረስ ሕዝብ በእየአካባቢው እንዲያስብ የሚያደርግ አደገኛ አካሄድ ነው። እዚህ ላይ ሁሉም ዜና በየልሳኑ የተወሰነ ስለሌላው አያወራም እያልኩ አይደለም።ጥልቀት ያንሰዋል።ጫፍ ጫፉን ነው የምትንነግሩን፣ባለ ልሳኑ የሚያወራውን ዜና ያህል የጠለቀ ዝርዝር እኩል እንወቅ እያልን ነው። በእርግጥ በአንድ የዜና ሽፋን ጊዜ ሁሉን መሸፈን አይቻል ይሆናል።ነገር ግን ሁለት አማራጭ አለ። አንዱ በእየለቱ ሁሉም በልሳኑ የሌላው ልሳን ያዘጋጀው ዜና ላይ ጉልህ የሆኑትን ከሁሉም ክልሎች የማቅረብ ግድታ ቢገባ የሚለው ሲሆን፣ ሌላው ከዋና የዜና እወጃ በተለየ በሳምንት ሁለት ወይንም ቢያንስ አንድ ቀን ሰፊ የክልሎች ዜና በስፋት ሁሉም የዜና እወጃ በልሳኑ በጥልቀት እንዲዘግብ እና ዘገባው ደግሞ ሁሉንም ክልሎች የሳምንት ዜና  የሸፈነ እንዲሆን ማድረግ ነው።የመረጃ ክፍተቱ የሚፈጥረው አደጋ ይታየን።

ለማተቃለለ ይህ ጉዳይ ጊዜ የሚሰጠው አይደለም።በነገራችን ላይ  ህዝቡ የቪኦኤ እና ዶቼቬሌ ራድዮን የሚከታተለው የተለየ ነገር ሆኖ አይደለም።የዜና ሽፋናቸው አብዛኛውን ክልል ስለምሸፍን ነው።መረጃዎች ከባህር ማዶ ሲመጡ ደግሞ ከውጭ አገር ማሰራጫው ፖሊሲ ጋር የተያያዘ ስለሆነ በራሱ የጠራ አይደለም። የመንግስት መገናኛ ብዙኃን ይህንን ቢያስቡበት ተገቢ ነው።

የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን  በ1955 ዓም ሲከፈት (ቪድዮ )ጉዳያችን GUDAYACHN
 www.gudayachn.com

Thursday, December 12, 2019

ኢትዮጵያን በተመለከተ በኦስሎ፣ኖርዌይ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ የተከፈተውን ዓውደ ርዕይ (ኤግዚብሽን) በቪድዮ ይጎብኙ።
ኢትዮጵያን በተመለከተ በኦስሎ፣ኖርዌይ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ የተከፈተውን የኖቤል ዓውደ ርዕይ (ኤግዚብሽን) በቪድዮ ይጎብኙ።
ትናንት ታህሳስ 1/2012 ዓም በክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ዓቢይ አህመድ በኦስሎ ኖርዌይ የተከፈተው Cross Roads Ethiopia a country in transition የተሰኘውን የኖቤል ኤግዚቢሽን ይጎብኙ። 

ቪድዮውን ለመከታተል ይህንን ሊንክ ይጫኑ ዩቱብ ሊንክ ይክፈቱኝ 

 https://www.youtube.com/watch?v=NGjYDcgSjp0&feature=youtu.be

On December 12/2019 Nobel Peace Center Cross Roads Ethiopia a country in transition Exhibition was officially opened by Ethiopian Prime Minster Abiy Ahmed in Oslo.Here is Nobel Peace Center Exhibition live visit by Gudayachn editor Getachew Bekele
To watch the video Click here 

ጉዳያችን (https://www.youtube.com/watch?v=NGjYDcgSjp0&feature=youtu.be)
ጉዳያችን GUDAYACHN
 www.gudayachn.com

Wednesday, December 11, 2019

ሰበር ዜና - የጥምቀት በዓል በዩኔስኮ በዓለም አቀፍ ቅርስነት ተመዘገበ።UNESCO decided to inscribe TIMKET on the List of the Intangible Cultural Heritage of Humanityዛሬ ረቡዕ ታህሳስ 1/2012 ዓም የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣የሳይንስ እና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በእየዓመቱ ጥር 11 ቀን የሚከበረውን የጥምቀት በዓል በዓለም አቀፍ የማይዳሰስ ቅርስነት እንደመዘገበው ገልጧል።ድርጅቱ ይህንን ውሳኔ ያደረገው በኮሎምቢያ፣ቦጎታ እያካሄደ ባለው ስብሰባው ነው።የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ካሏት ሁለት ዓመታዊ ክብረ በአሏች ውስጥ ከእዚህ በፊት መስቀል በዓለም ቅርስነት መመዝገቡ ይታወሳል።

UNESCO decided to inscribe TIMKET on the List of the Intangible Cultural Heritage of Humanity. 
According to UNESCO website,Ethiopian Epiphany was expressed as follows -
''Ethiopian Epiphany is a colorful festival celebrated all over Ethiopia to commemorate the baptism of Jesus Christ. The commemoration starts on the eve of the main festival, when people escort their parish church TABOT, a representation of the Tables of the Law, to a pool, river or artificial reservoir. Celebrants then attend night-long prayers and hymn services, before taking part in the actual festival the following day, when each TABOT is transported back to its church. The Ethiopian Epiphany is a religious and cultural festival whose viability is ensured through continuous practice and the pivotal contribution of the Orthodox clergy''.

ጉዳያችን GUDAYACHN
 www.gudayachn.com

Friday, December 6, 2019

በጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ ቢሮ የተጀመረው ምቹ የስራ ቦታን የመፍጠር ሳይንስ (ኤርጎኖሚክስ) የኢትዮጵያን የመንግስት ቢሮዎች እና የሰራተኞችን ምቾት በሚያስደንቅ መልኩ ቀይሮታል። (ቪድዮ)

ኢትዮጵያ ያሉትን የመንግስት ቢሮዎች ከእዚህ በፊት የምታውቁ ይህንን ቪድዮ ተመልክቶ ካለምንም ማጋነን አለመደመም አይቻልም።ጉዳያችን በእውነት በጣም ረክታበታለች።


ጉዳያችን GUDAYACHN
www.gudayachn.com

Tuesday, December 3, 2019

የኖቤል የሰላም ሽልማት በተመለከተ በኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ምን አሉ? (ዛሬ የተለቀቀ አዲስ የኢሳት ቴሌቭዥን ዝግጅት) Etiopiere i Oslo kommenterer 2019s Nobels fredspris som vil bli gitt til statsminister Abiy 10. desember 2019.


ስለ ኖቤል መርሐግብር አዳዲስ መረጃ ለመከታተል  ይህንን የፈስቡክ ሊንክ ይጫኑ >> ኖቤል 2019 ለሌሎች ያካፍሉ።


ምንጭ - ኢሳት

Ethiopian Satellite TV (ESAT TV) 


ጉዳያችን GUDAYACHN
www.gudayachn.com

Sunday, December 1, 2019

ሰበር ዜና - የብልፅግና ፓርቲን የተቀላቀሉ ድርጅቶች የስምምነት የፊርማ ስነ-ስርዓት ዛሬ ዕሁድ ህዳር 21/2012 ዓም በአዲስ አበባ ሲደረግ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ያደረጉት አስደናቂ ንግግር ይመልከቱ።

እኛን ብቻ መተቸት በቂ አይደለም።አማራጭ ሃሳብ ማምጣት ያስፈልጋል።  ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አህመድ ዛሬ የተናገሩት።
ሙሉውን ንግግር  ይመለክቱ።ጉዳያችን GUDAYACHN
 www.gudayachn.com