ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Tuesday, December 17, 2019

ምሁራዊ ጀሃድ በኢትዮጵያዊነት፣በታሪክ ምሁራን፣ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን እና በአገልጋዮቿ ላይ ዘመቻ ከፍቷል።ሁሉም ሊመክተው ይገባል።


Cartoon picture source = coast2coastmixtapes.com

ጉዳያችን / Gudayachn
ታኅሳስ 8/2012 ዓም (ዴሴምበር 18/2019 ዓም) 

እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር  ቅዳሜ፣ጥቅምት 13/2001 ዓም የወጣው የ''ኒውዮርክ ታይምስ'' ጋዜጣ ''The deep Intellectual Roots of Islamic Terror'' በሚል ርዕስ ስር ባሰፈረው ፅሁፍ ላይ እንዲህ የሚል ፅሁፍ ሰፍሮ ይገኛል።
     ፅንፈኛ የእስልምና ጀሃድ አባላት በ1981 ዓም እኤአ  የግብፁን መሪ  አንዋር ሳዳት ከገደለ በኃላ ''The Neglected duty'' (ችላ የተባለው ተግባር) በሚል ርዕስ ስር ባለ ሃምሳ አራት ገፅ  ሰነድ አሰራጭቶ ነበር።የሰነዱን ይዘት ይሄው የኒው ዮርክ ታይምስ ጋዜጣ ሲያብራራ ቡድኑ ለመግደሉ ''ትክክለኛነት'' ለማሳመን የተጠቀመበት ሰነድ ሲሆን እንደ ሰነዱ አባባል ''ትክክለኛ እስልምና'' የማይቀበሉ መንግሥታት ላይ ግድያ እና በሰዎች ላይ የሚደርስ ጭፍጨፋን ያበረታታል።የዓለማችን ቀንደኛ ሽብርተኛ ቢንላደን የእዚሁ ፅንፈኛ ቡድን አባል የሆነው ከዓመታት በፊት እንደነበር ጋዜጣው ያትታል።

አሁን ባለንበት ዘመን ጅሃድ በቀጥታ ንፁሃንን መግደል ብቻ አይደለም።ከመግደል የሚቀድም ''ምሁራዊ ጀሃድ'' ነው።

ምሁራዊ ጀሃድ ምንድነው?

በ1985 ዓም እኤአ ባል ስቴት ዩንቨርስቲ (Ball State University) ሊንዳ ኮሎኮትሮኒስ (Linda K.Kolocotronis)  ''An intellectual historical study of Islamic Jihad during the life of Muhammad and in the twentieth century" በሚል ርዕስ በፃፉት የየዶክትሬት ማሟያ ፅሁፋቸው ''አብስትራክት'' ላይ ጅሃድ በጦርነት ብቻ ሳይሆን ''ዲፕሎማሲያዊ ጀሃድ'' የዘመናዊው ዓለም መተግበርያ እንደሆነ ካተተ በኃላ ጀሃድ በፊት ለፊት ሰው ከመግደል ባለፈ ሌሎች ስልቶች እንዳሉት ያትታል።

ምሁራዊ ጀሃድ የፊት ለፊት ንፁሃንን ከመግደል በፊት የቀደመ ፕሮፓጋንዳ ነው።በተለይ በዘመናዊው የመገናኛ መንገድ ምሁራዊ ጀሃድ በረቀቀ መንገድ አገራት ላይ መረቡን እየዘረጋ የስነ ልቦና ጦርነት ያካሂዳል።ምሁራዊ ጀሃድ የሚከወነው በከፍተኛ ደረጃ በተማሩ እና የትምህርት ችሎታቸውን ግን ለተንኮል እና እውነተኛውን የአገራት ታሪክ በማጣመም፣ቀዳሚ የታሪክ እና የሃይማኖት ምሁራንን ስም ማጥፋት፣ ለዓላማቸው ማስፈፀምያነት የማይስማማቸውን መንግስት እና የመንግስት መሪ፣ፖለቲከኛ እና  ታዋቂ ጋዜጠኞች ላይ ጭምር በምሁር ቃላት የተከሸኑ የጥፋት ፕሮፓጋንዳ ይከፍታሉ። የምሁራዊ ጀሃድ አራማጆች የአፈፃፀም ስልቱን እና የሰው ኃይል ምልመላቸውን የሚያካሂዱት በረቀቀ መንገድ ከመሆኑም በላይ በገንዘብ ኃይል ከጀርባ ይደገፋሉ።

ምሁራዊ ጀሃድ በኢትዮጵያ ስራውን ከጀመረ ቆየት ያለ ጊዜ አለው።ይህ በአካል ንፁሃን ክርስቲያኖችን በመጨፍጨፍ እና አብያተ ክርስቲያናትን ለሚያቃጥለው የጥፋት ኃይል የተኩስ ሽፋን በመስጠት ለእኩይ ድርጊቱ የሐሰት ፍትሃዊ ፅሁፎች በማጉረፍ ለድርጊቱ ሌላ ምክንያት በመስጠት ሟቾች መሞት እንደነበረባቸው ለመተረክ የሚደፍር አይን አውጣ ቡድን ነው። የምሁራዊ ጀሃድ አባላት እንደማንኛውም ሰው ህዝቡ ውስጥ ገብተው የሚኖሩ አንዳንዶቹ በስልጣን እርከን ውስጥ ተሰግስገው የመንግስትን መዋቅር በማዳከም እና ሕዝብ በመንግስት እንዲማረር ሌት ተቀን የሚደክሙ ናቸው።በሌላ በኩል ምሁራዊ ጀሃድ  አባላት በዩንቨርስቲ ውስጥ ከታሪክ ምሁርነት እስከ ፅንፈኛ የጎሳ ሚድያዎች ውስጥ ተሰግስገው የሚሰሩ ናቸው። የእዚህ ቡድን አባላት ከሚሰሯቸው የጥፋት ስራዎች ውስጥ የሚከተሉት ተጠቃሽ ናቸው። እነርሱም -

  • የኢትዮጵያን ታሪክ እያጥላሉ በማኅበራዊ ሚድያ መልቀቅ፣
  • ኢትዮጵያ የምትባል አገር የለችም፣ኢትዮጵያ ጥንት የሚባለው ምስራቅ አፍሪካ በሙሉ ነበር የሚል ትርክት በመተረክ የታሪክ አሻራ የሌላት አገር አድርጎ ማቅረብ፣
  • በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ላይ የማጥላላት ዘመቻ በመክፈት እና ከአንድ ብሔር ጋር እያያዘ ለመነጠል መሞከር፣ቤተ ክርስቲያን ኢትዮጵያን ወደ ኃላ ያስቀረች አስመስሎ የሚያቀርብ የውሸት ጥናት መሰል ፅሁፍ ማዥጎድጎድ፣
  • ባለፈው ማንነቱ የማይኮራ ትውልድ ለመፍጠር የውሸት ትርክት ማስፋፋት፣
  • የኢትዮጵያ ጥቅም በሆኑ ጉዳዮች ላይ ሁሉ በተቃዋሚ ስም በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ ማጥላላት እና ማጠልሸት፣
  • በኢትዮጵያዊነታቸው የሚያምኑ እና ይህንኑ በሥራ ያስመሰከሩ ጋዜጠኞች፣ምሁራን እና የሃይማኖት ምሁራን ላይ በቀጥታ የስም ማጥፋት ዘመቻ መክፈት። እዚህ ላይ ሰሞኑን በሙሐዘ ጥበባት ዲ/ን ዳንኤል እና ''አክራሪ እስልምና በኢትዮጵያ'' የተሰኘው መፅሐፍ አዘጋጅ በመልአከ ኤዶም ቀሲስ ኤፍሬም እሸቴ ላይ የተከፈተው የማኅበራዊ ሚድያ ዘመቻ መጥቀስ ይቻላል፣
  • ከፅንፈኛ የመካከለኛው ምስራቅ አገሮች ጋር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በመገናኘት በአገር ውስጥ ላላቸው ሕዋስ እና  የፅንፍ መገናኛ ብዙሃን ድጋፍ በማግኘት በአገር ውስጥ በጎሳዎች መሃል ግጭት እንዲፈጠር ማሴር እና 
  • ፖለቲካዊ፣ማኅበራዊ እና ምጣኔ ሃብታዊ ቀውስ ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲፈጠር ካደረጉ በኃላ የፖለቲካ ስልጣን ለመያዝ መስራት የሚሉ ተጠቃሾች ናቸው።
የምሁራዊ ጀሃድ ዋና አንቀሳቃሾች በአሁኑ ወቅት በአክትቪስትነት ተከስቷል።ለስውር ስራው ሽፋን ደግሞ አንድ ጊዜ በጎሳ ፅንፈኛ ኃይሎች ስም በመደራጀት፣ሌላ ጊዜ ደግሞ በቀጥታ የኢትዮጵያን አንድነት በመፃረር በአገሪቱ ውስጥ የፅንፍ እስልምና እንቅስቃሴ ሲያበረታታ ይታያል። በኢትዮጵያ ውስጥ የምሁራዊ ጀሃድ ሥራ ላይ የተሰማራው ቡድን ረዘም ላለ ጊዜ እራሱን ለመደበቅ በመሞከር ለሚሰራቸው የቅሰጣ ስራዎች የጎሳ ፖለቲካ እና የብሔር ግጭቶችን እንደሽፋን ሲጠቀም እና በእዚህም እያስታከከ ኢትዮጵያዊነትን ሲያጥላላ፣ኢትዮጵያዊነት ላይ የሚኖሩትን ሲያሳድድ እና በቅርቡ ደግሞ ለረጅም ጊዜ በፕሮፓጋንዳ  ሲሰራበት የነበረውን ኢትዮጵያን እና የኢትዮጵያን ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ሲያጥላላ  ኖሮ የፀጥታ ችግር በተፈጠረባቸው ክፍተቶች ሁሉ ባገኘው አጋጣሚ ክርስቲያኖችን ሲገድል እና አብያተ ክርስቲያናትን ሲያቃጥል  በግልጥ ታይቷል።የምሁራዊ ጀሃድ ዋና ተግባር ኢትዮጵያን ማናጋት ነው።ለእዚህ ደግሞ ዋና ምክንያቱ  ከትርምሱ እንደሚያተርፍ ያስባል።ትርምሱ ሲቀጥል ኢትዮጵያን ከስር ወደላይ ለመገልበጥ በሰይፍ ዓላማውን ለማስፈፀም ያሰፈሰፈ  የጥፋት ቡድን ነው።

ለማጠቃለል የምሁራዊ ጀሃድ ቡድን በፅንፍ የጎሳ ፖለቲካ ከኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ እስከ ቤንሻንጉል፣ከባሌ ዶሎ መና እስከ አርሲ የተሞከረው የጎሳ እልቂት ድግስ ባለመሳካቱ በግልጥ የነበረ እውነተኛ መልኩን ማለትም የኢትዮጵያ ሙስሊም ወገኖቻችን ፈፅመው የማይቀበሉትን ኢትዮጵያዊነትን እና ኦርቶዶክስ ሃይማኖትን ለመናድ በማኅበራዊ ሚድያ በግልጥ ለመምጣት ተገዷል። በነገራችን ላይ የምሁራዊ ጀሃድ አራማጅ ቀደም ብሎ በአሜሪካ የፅንፈኛው ኃይል መንገድ ሜንጫ  መሆኑን ሳያውቀው የተነፈሰው ፈልጎት አልነበረም።ድንገት ሳያውቀው የወጣበት ሚስጥር ነው።ሰሞኑን በኢትዮጵያ ታሪክ ላይ  ደካማ እና የተረት ተረት ወግ ጥረቃ ፅሁፎች በማኅበራዊ ሚድያ ላይ የመለቀቅ እውነተኛ ምስጢር ተስፋ የመቁረጥ ውጤት ነው።በታሪክ እና የሃይማኖት ምሁራን ላይ የስም ማጥፋት ዘመቻ መከፈቱም ሌላው የመደናገጥ እና የመደናበር ውጤት ነው። ይህ ማለት ግን የሕግ እና ስርዓት የማስከበር ኃላፊነት ያለበት መንግስት የምሁራዊ ጀሃድ አራማጆችን እና የህዝቡን ፀጥታ ለማወክ በሚንቀሳቀሱ ላይ ሕጋዊ ሥራ መስራት አለበት።ጉዳዩን በቸልተኝነት ሊያልፈው አይገባም። ሕዝቡም ካለምንም ማመንታት የጀሃድ ምሁራን ቡድኖችን በየትኛውም የተቃውሞ አክትቪዝም ስራም ሆነ የፖለቲካ ተቃዋሚ ወይንም የመንግስት መዋቅር ውስጥ ቢገኙ ማጋለጥ እና ለሕግ እንዲቀርቡ ማድረግ ይገባዋል። በሌላ በኩል ኃላፊነት የሚሰማው ኢትዮጵያዊ ምሁር በሙሉ የምሁራው ጀሃድ አራማጆችን ፅሁፍ እግር በግር እየተከታተለ ማምከን እና የውሸት መጋረጃ በአደባባይ ማጋለጥ አለበት።  




ጉዳያችን GUDAYACHN 
 www.gudayachn.com

No comments:

በኢትዮጵያ የእገታ ወንጀል ተሳታፊ አራት አካላት ናቸው። ለችግሩ የመፍትሄ አካላት ሁለት ናቸው።ሁለቱ አካላት ምን ይስሩ?

======= ጉዳያችን ======= በኢትዮጵያ ዜጎችን እያገቱ ገንዘብ የሚቀበሉ ወንጀለኞች ከተራ ወንጀለኝነት አልፎ በታጣቂ ቡድኖች የገንዘብ ማግኛነት መዋል ብቻ ሳይሆን ዜጎችን የማሸበርያ ፋሺሽታዊ ተግባር ሆኗል። እገታ የ...