.png)
ጉዳያችን - በጉዳያችን ሚድያ፣ኮምኒኬሽን እና ምክር አገልግሎት የሚዘጋጅ ሲሆን ከ2003 ዓም ጀምሮ በድረ-ገፅ ላይ የነበረ በአሁኑ ጊዜ ከአንድ ሚልዮን በላይ ጎብኚዎች ያሉት ገፅ ነው። Gudayachn is prepared by Gudayachn Multimedia, Communication and Consultant Organization. It has been online since 2011. Currently, Gudayachn is being visited by over One-million readers from all over the world.
Thursday, October 15, 2026
Monday, September 28, 2026
የመስቀል ደመራ በዓል በንግስት ዕሌኒ ሀገር በግሪክ ቅዳሜ መስከረም 16፣2019 ዓም በከፍተኛ ድምቀት ተከብሮ ዋለ።በግሪክ የምትገንኘው የአቴንስ ኪዳነምሕረት ቤተክርስቲያን ምእመናን ለቅዱስ ሲኖዶስ አቤቱታቸውን ደግመው አቀረቡ።
ልዩ ሪፖርታዥ
========
በእዚህ ርዕስ ስር የሚከተሉትን ንዑስ ርዕሶች ያገኛሉ።እነርሱም ፡
- የመስቀል ደመራ ለምን ይከበራል?
- ግማደ መስቀሉ ወደ ኢትዮጵያ እንዴት መጣ?
- የዘንድሮው የመስቀል ደመራ በዓል በአቴንስ፣ግሪክ የነበረው ገፅታ(ቪድዮ) እና ደመራውን ለማስተጓጎል የተደረገው ጥረት ክሽፈት።
- በደመራው ላይ ከምእመናን የተጠየቀው እና ለቅዱስ ሲኖዶስ በተለይ የሀገረ ስብከቱ ሊቀጳጳስ በተመለከተ የቀረበ ቅሬታ (ቪድዮ)
ግማደ መስቀሉ ወደ ኢትዮጵያ እንዴት መጣ?
የዘንድሮው የመስቀል ደመራ በዓል በአቴንስ፣ግሪክ የነበረው ገፅታ እና ደመራውን ለማስተጓጎል የተደረገው ጥረት ክሽፈት።
በአቴንስ ግሪክ የምትገኘው የኪዳነምሕረት ቤተክርስቲያን ለብዙ አስርተ ዓመታት የመስቀል ደመራን በዓል የምታከብረው በአቴንስ ከተማ ዛፕዮ አደባባይ ላይ ነው። በአደባባዩ በሺህ የሚቆጠር ምእመን በፍቅር እና በአንድነት የሚያከብርበት አደባባይ ሲሆን በዘንድሮው ዓመትም በተመሳሳይ በዓሉን ለማክበር የፈቃድ ወረቀት ቤተክርስቲያኒቱ ስትጠይቅ የሀገረ ስብከቱ ሊቀጳጳስ አቡነ ኤልያስ የቤተክርስቲያኒቱ ጥያቄ እንዳይሰማ ከእዚህ በፊት በቤተክርስቲያኒቱ ውስጥ ደም በማፍሰስ፣ቅዳሴ እንዳይቀደስ እና ኪዳን እንዳይደርስ ፊሽካ በመንፋት እና የቤተክርስቲያኒቱን ንብረት በመዝረፍ የሚታወቁ ግለሰቦች ጋር ባላቸው ቅርበት እነርሱ ለተደራጁበት ኪኖቲታ በሚል ለተመዘገቡ አደባባይ እንዲፈቀድ የግሪክ የሃይማኖት ሚኒስቴርን በተሳሳተ መረጃ በመጠየቃቸው ቤተክርስቲያኒቱ የመስቀል ደመራ በዓልን እንዳታከብር እንቅፋት መፍጠራቸው በሺህ የሚቆጠሩ ምእመናንን አሳዝኖ ሰንብቷል። ሊቀ ጳጳሱ ከእዚህ በፊትም ክረምቱን እነኝሁ ግለሰቦች በሆቴል እየሰበሰቡ ''የእኔ'' የሚሉት ስብስብ ለመፍጠር መሞከራቸውን እና ይህም ከአንድ ጳጳስ የማይጠበቅ መሆኑን ከሕዝቡ የተውጣጡ ግለሰቦች ጭምር በወቀሳ ካሉበት ሆቴል ድረስ ሄደው ቢነግሯቸውም፣ አሁንም ይህንኑ ምእመኑን የሚለያይ ተግባር ቀጥለውበት የዘንድሮውን የመስቀል ደመራ በዓል የአቴንስ ኪዳነምሕረት ቤተክርስቲያን ምእመናን እንዳያከብሩ እጅግ አሳዛኝ ተግባር ፈጽመዋል።
Saturday, September 5, 2026
The Ethiopian Orthodox Tewahedo Church is in turmoil in Athens, Greece.
- The Greek Department of Religious Affairs under the Greek Ministry of Education has not responded adequately to the clear and protocol-based letters of the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church's Holy Synod and the Holy Patriarch, which were sent a year ago.
- The department has been giving undue weight to the letters of the temporary Archbishop of the Diocese, Abune Elias, who is currently in conflict with Ethiopian Orthodox Church followers in Greece and is acting against the EOTC's Holy Synod decisions.
Thousands of Ethiopian Orthodox Tewahedo Church believers are deeply saddened by the actions of the temporary Archbishop of EOTC in Greece, Elias. Last month, Archbishop Elias's trip to Athens caused a stir among followers of the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church in Greece. Although the Archbishop said he was in Athens to preach the Gospel, he spent weeks in a hotel and was said to have given a sermon in a hotel, which is completely contrary to Orthodox tradition, and this action of his has become a topic of talk of the town in Athens among Ethiopian Orthodox Tewahedo Church followers.
Not only this, but the Archbishop also accused the Orthodox community in Greece, the ''Somatio'' Organization, of improper opening of the prayer house in Spata; and the Archbishop accused the head of the Greek police in Spata of being involved in assisting Ethiopian Orthodox Christians.
That is why thousands of Ethiopian Orthodox Tewahedo Church believers in Greece are deeply saddened by the actions of the Archbishop, Elias.
Having said that, the main reasons for putting the Ethiopian Orthodox Tewahedo church in Greece in turmoil are:
- The Greek Department of Religious Affairs under the Greek Ministry of Education has not responded adequately to the clear and protocol-based letters of the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church's Holy Synod and the Holy Patriarch, which were sent a year ago.
- The department has been giving undue weight to the letters of the temporary Archbishop of the Diocese, Abune Elias, who is currently in conflict with Ethiopian Orthodox Church followers in Greece and is going against the EOTC's Holy Synod decisions.
Therefore, according to Gudayachn's analysis, to solve the problem of EOTC in Greece, the following measures should be taken with all concerned parties. These are:
Hundreds of Greek citizens living in Ethiopia have been using a church in Addis Ababa that has been preserved for more than half a century. However, in Athens, Greece, the believers of the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church have been facing problems and have not even been able to celebrate the Easter holiday this year. Therefore, the Ministry of Religion should meet with the Holy Synod of the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church to respect the right of Ethiopians to have a church, at least by lifting the ban on their own property in Spata.
3/ The Holy Synod of the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church should appoint a suitable diocesan bishop for Greece. It is easy to understand that Archbishop Elias, who is over ninety years old, is not only incapable of properly governing or leading the believers in Greece, but also has been accused of deliberately complicating matters in the Swedish court where he lives, and that he cannot lead the church in Greece. Therefore, appointing a new bishop for Greece is a task of the Holy Synod of the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church and is one of the key issues in the solution. In addition to that, Archbishop Elias should also stop his relations with individuals who have corrupted the church and whose cases are still pending in Greek courts.
Friday, August 28, 2026
የኢትዮጵያ ወዳጅ ንጉስ ልጅ ዛሬ ከእዚህ ዓለም አረፉ። ለኖርዌይ ትልቅ የሃዘን ቀን ሆኗል።Norway's King Harald V has died at the age of 89
- ስለ ንጉስ ሃራልድ በጥቂቱ
- የንጉስ ሃራልድ አባት ንጉስ ኦላቭ እና ቀዳማዊ አፄ ኃይለሥላሴ የት ተዋወቁ?
Friday, August 14, 2026
የኢትዮጵያ ወቅታዊ ፖለቲካ፣ የአፈጀው የአዛውንቶች ክበብ፣ ''ፅንዶ'' እና ቅምጥሎቹ ''ባንዳ'' ዩቱበሮች በአውሮፓና አሜሪካ።
Tuesday, August 11, 2026
የኢትዮጵያ የባሕር ኃይል አዛዥ ኮሞዶር ጌታቸው ስዩም በምፅዋ የኢትዮጵያ የባሕር በር ላይ እጅ አልሰጥም ብለው ያፈሰሱት ደም ዛሬም በባሕሩ ዳር ላይ ይጣራል።
Monday, August 3, 2026
በግሪክ የምትገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጉዳይ ዛሬም ከምንጊዜውም በላይ የቅዱስ ሲኖዶስን የአፈጻጸም ጥብቅ ክትትል ትፈልጋለች።በሺህ የሚቆጠሩ ምእመናን ችግር ላይ ናቸው።
=============
ኢትዮጵያና ግሪክ
- አቴንስ ፖሊጎኖ የምትገኘው ለአራት አስርተ ዓመታት ምእመናን ሲገለገሉባት የነበረችው የኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን በአጽራረ ቤተክርስቲያን በሆኑ በቤተክርስቲያን ውስጥ ፊሽካ ከመንፋት እስከ ደም ማፍሰስ ወንጀል በፈጸሙ እና አሁንም ጉዳያቸው በሕግ የተያዘ ግልሰቦች እና እራሱን ኪኖቲታ በማለት በሚጠራ የዕድር አደረጃጀት በፈጠሩት ሁከት አማካይነት ቤተክርስቲያኒቱ በግሪክ መንግስት እንድትዘጋ ሆነ።
- ቤተክርስቲያኒቱ ከተዘጋች ወዲህ በአቴንስ የሚኖሩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሚያስቀድሱበት ቦታ በተለይ በአቴንስ ከተማ ውስጥ አለመኖሩና ቤተክርስቲያኒቱን በግሪክ በሕጋዊነት እንዲያገለግሉ የተመደቡት ሊቀስልጣናት አባ ኪሮስ ጸጋዬ ወደ ግሪክ በቶሎ አለመምጣት መጪው የፍልሰታ የፆም ወቅት ሳይቀር ምእመናን ተቸግረው እንደሚያሳልፉ ቅዱስ ሲኖዶስም የሚያውቀው ጉዳይ ነው።
- ይህ በእንዲህ እያለ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ በአቡነ ኤልያስ ቤተክርስቲያኒቱን ያወከውን የዕድር አደረጃጀት (ኪኖቲታን) ማዕከል ያደረገ በሆቴል ያደረጉት ''ጉባዔ'' አይደለም ሌላ የራሱ የኪኖቲታ ስር ናችሁ የተባሉ ምእመናንን ሳይቀር ማሰባሰብ ያልቻለ ብቻ ሳይሆን በቅዱስ ሲኖዶስም ምንም እውቅና የሌለው የጉባዔው ምንነት እና ሆቴል የተመረጠበትም ምክንያት ሳይታወቅ ተድበስብሶ ይሄው ሳምንታት ነጎዱ።
- ቤተክርስቲያኒቱ በስሟ የተገዛውን ከስድስት ሺህ ካሬ በላይ ስፋት ያለው በአውሮፓ የመጀመርያዋ የሆነውን ገዳም በተመለከተ ምን ደረሰ፣ይህ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ንብረት ነው ብሎ የሚከታተለው ሊቀጳጳስም ሆነ ሀገረስብከት ሳይኖረው ስምንት ዓመታትን ያሳለፈበት እውነታ ዛሬም መሬት ላይ ያለ ዕውነታ ነው።
- አቡነ ኤልያስ በግሪክ የሃይማኖት ሚኒስቴር በኩል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በግሪክ ያላቸው የኃላፊነት ደረጃ በግልጽ እንዲነገረው በአዲስ አበባ የሚገኘውን የግሪክ ኤምባሲ ቤተክሕነት ድረስ ሄዶ እና የሚመለከተውን መምርያ ተገናኝቶ እንዲገለጽለት ጠየቀ።
- የግሪክ የሃይማኖት ሚኒስቴር ይህንን ጥያቄ ያቀረበበት ምክንያት አቡነ ኤልያስ ተደጋጋሚ ደብዳቤ በተለይ ወደ የግሪክ የሃይማኖት ሚኒስቴር በመላክ በግሪክ ያለውን ጉዳይ እኔ የምቆጣጠረው ነው በሚል ከጊዜያዊ አስተዳዳሪ ምደባ ጀምሮ በሚልኳቸው ደብዳቤዎች የሚኒስቴር መስርያቤቱ ግራ ስለተጋባ ነበር።
- በእዚህ መሰረትም መስመር ኤምባሲው ወደ ቤተክሕነት ልዑክ ልኮ የአቡነ ኤልያስ የኃላፊነት መጠን በቤተክርስቲያን ሲጋበዙ መባረክ ብቻ መሆኑ ተገለጸለት።ይህ የማጣራት ሂደት በግሪክ የሃይማኖት ሚኒስቴር ከደረሰው በኋላ አቡነ ኤልያስ በግሪክ በተጋበዙበት ቦታዎች የመባረክ ተግባራትን እንጂ በግሪክ የምትገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በተመለከተ ማናቸውም ጉዳዮች የሚከወኑት እና የተፈጻሚነት ደብዳቤዎች የሚመጡት ከቅዱስ ሲኖዶስ ብቻ መሆኑን የሃይማኖት ሚኒስቴር አረጋገጠ።
- በእዚህም መሰረት ምንም እንኳን እንደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ስርዓት እና ደንብ መሰረት የሃገረስብከቱ ሊቀጳጳስ ሚና ከፍተኛ ቢሆንም ከግሪክ አንጻር ግን የሃይማኖት ሚኒስቴር ባረጋገጠው የሕግ ተቃርኖ ትንተና መሰረት አቡነ ኤልያስ በአሁኑ ጊዜ በግሪክ ቤተክርስቲያን የመመስረትም ሆነ የማስቀጠል እንዲሁም በሃይማኖት ሚኒስቴር በኩል አስተዳዳሪ የመሾም መብት እንደሌላቸው በግሪክ የሃይማኖት ሚኒስቴር በኩል የታወቀ ነው።
- ለእዚህም ነው አንዳንድ በኪኖቲታ በኩል ያሉ ምእመናን ወንድሞች እና እህቶች ቤተክርስቲያን ልንገዛ ነው፣ገንዘብ አዋጡ ስትባሉ ሁለቴ አስቡ። አሰራሩ እንደዛ አይፈቅድም ገንዘቡን ለመዝረፍ ያሰፈሰፉ ዙርያችሁን አሉ እያልን ደጋግመን የምንመክረው።
- በግሪክ ለምትገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ የሚመደበው በቅዱስ ሲኖዶስ ብቻ መሆኑ ለግሪክ የኃይማኖት ሚኒስቴር በድጋሚ ግልጽ ስለሆነ አሁንም ቅዱስ ሲኖዶስ የመደባቸው ሊቀ ስልጣናት አባ ኪሮስ ጸጋዬ ሲመጡ ብቻ ነው ቤተክርስቲያኒቱ በግሪክ ያላት የማስፈጸም አቅም የሚከፈተው።ይህ በግሪክ ያለው ተጨባጭ ሁኔታ ነው።
- የሊቀስልጣናት አባ ኪሮስ ጸጋዬ የግሪክ ጉዞ በተመለከተ ቅዱስ ሲኖዶስ ልዩ ክትትል በሚከተሉት ሁለት መንገዶች መከታተል እና ማስፈጸም ይችላል።
- በአዲስ አበባ የሚገኘው የግሪክ አምባሳደርን ቅዱስ ፓትርያሪካችን ጠርተው ቤተክርስቲያኒቱ የመደበቻቸው አባት ወደ ግሪክ ተጉዘው በፍጥነት አገልግሎት እንዲጀምሩ እንዲያደርጉ ውይይት ማድረግ እና ለግሪክ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንም ደብዳቤ በመጻፍ ቤተክርስቲያኒቱ ቅሬታዋን ማቅረብ አለባት።
- የግሪክ ሀገረ ስብከት አንዱ የገጠማት ችግር ሀገረስብከቱን አስተባብሮ የቤተክርስቲያንን ችግር ከመፍታት ይልቅ በግል እና የሀገረስብከቱን መዋቅራዊ አቅም ባገለለ መልክ ከግለሰቦች ጋር በሚደረግ ግንኙነት ብቻ ለመምራት የሚሞክሩት የሀገረ ስብከቱ ሊቀጳጳስ አካሄድ መሆኑ ፀሐይ የሞቀው እና ሊቀጳጳሱን የሚቀርቡ ሁሉ እጅግ ያዘኑበት ጉዳይ ነው። በመሆኑም ሀገሩን እና ዘመኑን የዋጀ የሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ምደባ አሁንም በግሪክ የምትገኘው የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ከቅዱስ ሲኖዶስ የምትጠብቀው አሁንም አንገብጋቢው ጉዳይ እና ቅዱስ ሲኖዶስም ከእዚህ አንጻር የጉዳዩን አንገብጋቢነት ለመረዳት መዘግየቱ አሁንም ድረስ በቅርብም ሆነ በሩቅ ያሉ የቤተክርስቲያኒቱን አባቶችም ሆነ ምእመናንን ግራ ያጋባ ጉዳይ ነው።
- በግሪክ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ ምደባ ጉዳይ ከቤተክርስቲያን ጉዳይነት በዘለለ የሀገር ገጽታ፣ ከእዚያም ሲያልፍ የኢትዮጵያና የግሪክ የረጅም ጊዜ ትስስር ነጸብራቅም ስለሆነ የኢትዮጵያ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር የአውሮፓ ዴስክ እና በጣልያን የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲም በጥብቅ ተከታትሎ ሊያስፈጽመው የሚገባ ጉዳይ ነው።በውጪ የሚኖረው ማኅበረሰብ የራሱን ኃይማኖት በተገቢ መንገድ ማከናወን አለመቻሉ ከቤተክሕነትም አልፎ የኢትዮጵያውያን ጉዳይ ያገባኛል የሚል ማናቸውም ቢሮ ይመለከተዋል። ስለሆነም የተጠያቂነቱ አድማስ በቀላሉ የሚወሰን አይደለም።
Tuesday, July 14, 2026
የክፍለዘመናችን የኢትዮጵያ የስልጣኔ ማማ መለኪያ የሆነው ታላቁ የኢትዮጵያ ጉባዔ ነገ በአዲስ አበባ ይከፈታል። ህልውናችን፣መጪው ስልጣኔያችን፣ሰላማችን እና ዕድገታችን በእዚህ ጉባዔ ውጤትና ሒደት ይወሰናል።
- የቻልን በሀሳብ እና በጸሎት፣ ያልገባን እና የተምታታብን ደግሞ እኪገባን በዝምታ በመቆየት ኢትዮጵያን እናግዛት።
Wednesday, July 8, 2026
Tuesday, June 2, 2026
7ኛው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ግንቦት 24፣2018 ዓም በከፍተኛ የሕዝብ ተሳትፎ ተጠናቋል።
- ስለምርጫው ዝርዝር ጉዳይ ምን ያውቃሉ?
✓ ሰባተኛው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ 42 ፓርቲዎች እና 73 የግል ተወዳዳሪዎች ለተለያዩ ምክር ቤቶች ዕጩዎች የቀረቡበት ነው።
✓ በዚህ ምርጫ በአጠቃላይ 2,198 ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲሁም 8,736 ለክልል ምክር ቤቶች መቀመጫዎች በዕጩነት ቀርበው ተወዳድረዋል።
✓ በዚህም በምርጫው የተወዳደሩት አጠቃላይ ዕጩዎች ቁጥር 10,934 ዕጩዎች መሆናቸውን የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መረጃ ያመለክታል።
✓ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና ለክልል ምክር ቤቶች ከፍተኛውን ዕጩዎች ያቀረቡት ሦስት ፓርቲዎች ናቸው።
✓ በዚህም ገዢው ብልጽግና 2,950 ዕጩዎችን በማቅረብ ቀዳሚ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) 1,256 እና ሦስተኛው ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት 1,032 አቅርበዋል
✓ ሌሎች ፓርቲዎች እና የግል ተወዳዳሪዎችም በተለያየ ቁጥር ለተለያዩ ምክር ቤቶች መቀመጫ ለማግኘት ዕጩዎችን በምርጫው ላይ እንዲወዳደሩ አቅርበዋል።
✓ በአማራ ክልል ከሚገኙ 138 የምርጫ ክልሎች መካከል በስምንቱ ምርጫ እንደማይደረግ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ቀደም ብሎ ማስታወቁ ይታወሳል።
✓ በአማራ ክልል ድምጽ የማይሰጥባቸው 8ቱ የምርጫ ክልሎች በደቡብ እና ምዕራብ ጎንደር፣ በአምባሰል እንዲሁም በደጋ ዳሞት የሚገኙ መሆናቸው ተገልጿል።
✓ በትግራይ ክልል ከሌሎች የአገሪቱ ክልሎች ጋር በአንድ ላይ ምርጫ አልተካሄደም።
✓ የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢዋ ወ/ሮ ሜላተወርቅ ሰኞ ዕለት ድምጽ በማይሰጥባቸው ስምንት የምርጫ ክልሎች ወደፊት እንዲመርጡ እንደሚደረግ ገልጸዋል።
✓ በትግራይም 38 ወንበሮች ክልሉ በምርጫ ቦርድ በተቀመጠው የምርጫ ሒደትና ሕግ መሰረት የሚካሔድና ወንበሮቹ ክፍት ሆነው ይጠብቃሉ።
✓ ትናንት ግንቦት 24፣2018 ዓም የተደረገው ብሔራዊ ምርጫ 501 ዕጩዎችን ወደ የሕግ መወሰኛው ወይንም የተወካዮች ምክርቤት የሚያስገባና ምስክርም 25፣2019 ዓም በሚከፈተው የኢትዮጵያ ምክርቤት አዲሱ መንግስት ሥራ ይጀምራል።
✓ በእዚህ ምርጫ የኢትዮጵያን የመንግስት ስሪት ምርጫውን በማደናቀፍ ዕቅድ ተግባር የሸረቡ የቅርብና የሩቅ ቡድኖች በኢትዮጵያ ሕዝብ ጥንቁቅና የቆረጠ የምርጫ ተሳትፎ በእጅጉ ተበሳጭተዋል።
በሰባተኛው የኢትዮጵያ ምርጫ የተሳተፉ ብሔራዊና የክልል ፓርቲዎች ዝርዝር:-
ምንጭ:- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድምንጭ:- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
Friday, May 29, 2026
ከሰባተኛው የኢትዮጵያ ምርጫ በቀጣይ የሚታዩ የሚታዩት ሦስት እውነታዎች
Thursday, April 30, 2026
በአቴንስ፣ግሪክ የምትገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ የኪዳነምሕረት ቤተክርስቲያን ላለፉት 40 ዓመታት በላይ ስትጠቀምበት የነበረውን ፖሊጎኖ የሚገኘው ቤተክርስቲያን በፖሊስ ታሸገ።የቅዱስ ሲኖዶስ አፋጣኝ ምላሽ እየተጠበቀ ነው።
-
በቀሲስ መንግሥቱ ጐበዜ ሉንድ ዩንቨርሲቲ ፣ ስዊድን (ቀሲስ መንግስቱ ጎበዜ በአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ አርኪኦሎጂ እና ቅርስ አስተዳደር ትምህርት ክፍል መምህር እና በሉንድ ዩንቨርስቲ የዶክትሬት...
-
The Ethiopian herald News Paper August 20 , 2020 BY STAFF REPORTER Addis Ababa ************************** (EPA) ADDIS ABABA - Over sixty-mil...
-
አድሚራል ጄምስ ስታርቪድስን =============== ጉዳያችን /Gudayachn =============== ብሉምበርግ የተሰኘው የአሜሪካ ድረገፅ በፖለቲካ እና ፖሊሲ አምድ ስር የአድሚራል ጄምስ ስታርቪድስን አሜሪካ ኢትዮጵ...
.png)
.png)
.png)




















