አቶ መለስ ካረፉ አንደኛ አመታቸው አልፏል።አንዳንዶች ቀለል አድርገው ለማየት ይሞክራሉ።ጉዳዩ ግን የዲሞክራሲ መታፈንን ደረጃ የሚያሳይ ነው። ለእኔ ግን የብዙ ነገር አመላካች ነው።ከአንድ አመት በኃላም እንዳስገረመኝ አለ። አቶ መለስ-
እንዴት እንደሞቱ?
በምን ህመም እንደሞቱ?
የህመሙ ምክንያት ምን እንደነበር?
የት ሆስፒታል እንደሞቱ?
የት ሀገር እንደሞቱ?
እስካሁኗ ደቂቃ ድረስ የሀገራችን ቴሌቭዥንም ሆነ መንግስት አልነገረንም።
በድፍኑ ''በውጭ ሀገር በህክምና ሲረዱ ቆይተው'' ከመባል ውጭ። ይህንን የመጠየቅ መብት እንዳላቸው በቅጡ የተገነዘቡ ቁጥራቸው ስንት ደርሶ ይሆን?
በድፍኑ ''በውጭ ሀገር በህክምና ሲረዱ ቆይተው'' ከመባል ውጭ። ይህንን የመጠየቅ መብት እንዳላቸው በቅጡ የተገነዘቡ ቁጥራቸው ስንት ደርሶ ይሆን?
አንድ የውጭ ዜጋ ''መሪያችሁ በምን ህመም እንደታመመ፣የት እንደታከመ ሌላው ቀርቶ አስከሬን ከየት ሀገር እንደገባ ያልተነገራችሁ...ምስኪን ጭቁን ህዝቦች፣የህወሓት አባላት፣የኦህዴድ አባላት፣የብአዴን አባላት ሆይ! እስኪ መልሱልኝ? '' ብሎ ቢጠይቅ መልስ ያለው አለ? ይህ የሚያመላክተን አንድ እና አንድ ነገር ብቻ ነው። ይሄውም የነፃነታችንን እና የመብታችንን ባዶነትን ነው የሚያሳየው። ''እያበበ'' ነው የተባለው ዲሞክራሲ ለእዚች ትንሽ ጥያቄ ካልሰራ የት ይሆን የሚሰራው?
ጌታቸው
ኦስሎ