ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Friday, November 15, 2013

ለፋሺሽት ግራዝያኒ ዘብ የቆመው ወያኔ-ኢህአዲግ ወገኖቻችንን በግፍ ለገደለው ለሳውዲ መንግስት ታማኝነቱን በተግባር አሳየ።ወያኔ ገበናው ከምንጊዜም በላይ ፈጦ ወጥቷል።ጥያቄው ኢትዮጵያዊነት ወይንም ሞት!ነው።


አዲስ አበባ ሳውዲ አረብያ ኢምባሲ ፊት ለፊት በሰማያዊ ፓርቲ ዛሬ የተጠራው ሰልፍ በከፊል 

ቀደም ብሎ በጣልያን አፍሌ ግዛት ሊሰራ የነበረውን የሮዶልፍ ግራዝያኒ ሐውልትን በመቃወም ኢትዮጵያውያን አዲስ አበባ ላይ ያደረጉትን ሰልፍ የወያኔ-ኢህአዲግ ፖሊሶች ሰልፈኞቹን መደብደባቸው እና ለእስር መዳረጋቸው ይታወሳል።
(ለኢትዮጵያ ማን ይናገርላት? ጉዳያችን GUDAYACHN http://gudayachn.blogspot.no/2012/11/blog-post.html)

ዛሬ ህዳር 6/2006 ዓም የሰማያዊ ፓርቲ በሳውዲ የሚገኙ ወገኖቻችን ላይ የሚደርሰውን ግፍ በመቃወም አዲስ አበባ በሚገኘው የሳውዲ አረብያ ኤምባሲ ፊት ለፊት የጠራው ሰልፍ በፖሊስ ከመቆሙም በላይ በርካታ ወጣቶች እና አዛውንቶች በፖሊስ ተደብድበዋል የሰማያዊ ፓርቲ አመራርን ጨምሮ በርካታ ሰልፈኞች መስቀል ፍላወር አካባቢ እና አራት ኪሎ አካባቢ የሚገኙት ፖሊስ ጣቢያዎች ታስረዋል።''ጠላትማ ምንጊዜም ጠላት ነው አስቀድሞ ማለት አሾክሿኪውን ነው''።ወያኔ ገበናው ከምንጊዜም በላይ ፈጦ ወጥቷል።ለነፃነት የሚደረገው ትግል ለማደናቀፍ የቆሙት ኃይላትንም ከምንጊዜውም በላይ እየታወቁ መምጣታቸው ሌላው ክስተት ሆኗል።
ጥያቄው ኢትዮጵያዊነት ወይንም ሞት! ሆኗል።

የኢሳት ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን ከጥቂት ሰዓታት በፊት በፌስ ቡክ ገፁ ላይ የለጠፈው እንዲህ የሚል ነበር-

'' በአዲስ አበባ ወሎ ሰፈር ሳኡዲ አረቢያ ኤምባሲ አከባቢ ከፍተኛ ድብደባ እየተፈጸመ ነው። አሁን በስልክ ያገኘኋቸው የሰማያዊ ፓርቲ ሌሎች አመራሮች በእንባ ታጅበው ሲቃ ይዟቸው ''የኢትዮጵያ አምላክ ይፋረደን'' ሲሉ ለኢትዮጵያ ህዝብ መልእክት አስተላልፈዋል። የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች ወጣት ይድነቃቸው ከበደ እና ወጣት ሀና ዋለልኝ ከፍተኛ ድብደባ ተፈጽሞባቸዋል። ወደ 50 የሚጠጉ የፓርቲው አባላትና የሰልፉ ታዳሚ ወደ እስርቤት ተወስደዋል። ''በህግ አምላክ! እያለን እየጮህን በፌደራል ፖሊስ ተቀጠቀጥን" አለ ወጣት ይድነቃቸው። ''ወገን አለቀ ሳኡዲ አረቢያ ከሚገደሉት ከሚቀጠቀጡት ባልተናነሰ እኛም በሀገራችን ግፍ ተፈጸመብን'' ብላለች ወጣት ሃና። ''ኢትዮጵያዊ መንግስት ከወዴት ነው ያለኧው?'' የዛሬው ከፍ ብሎ የሚሰማው ጩኧት!''

የሰማያዊ ፓርቲም ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ባወጣው መግለጫ እንዲህ ብሏል።


''በሳውዲ አረቢያ በሚገኙ ዜጎቻችን ላይ እየደረሰ ያለው በደል እና ስቃይ መጠኑ ከመጨመር አልፎ ሕይወትን እስከማሳጣት መድረሱ የሚታወቅ ነው፡፡ ይህን በደል እና ስቃይ ለመቃወም እና ሀዘናችንን ለመግለፅ በዛሬው ዕለት ማለትም ህድር 6 ቀን 2006 ዓ.ም አዲስ አበባ በሚገኘው በሳውዲ አረቢያ ኢምባሲ ፊት ለፊት ሰላማዊ ሰልፍ የተጠራ ቢሆንም በመንግሥት ታጣቂዎች በተወሰደ በአሰቃቂ እርምጃ ሰልፉ ሊካሄድ አልቻለም፡፡
እኛ ኢትዮጵያን በውጭ በሚገኙ ዜጐቻችን ላይ የሚደርሰው በደልና ግፍ እንዲቆም፣ ይህንንም ድርጊት የፈፀሙት ለሕግ እንዲቀርቡና የተጐዱ ዜጐች ተገቢውን ካሳ እንዲያገኙ፤ የኢትዮጵያ መንግሥትም በዜጐቹ ላይ ያሳየውን ቸልተኝነት በአስቸኳይ በማቆም ተገቢ የሆነውን የመንግሥት ኃላፊነት እንዲወጣ ቢጠየቅም፤ ሰልፉ በተቃራኒው በመንግሥት ታጣቂዎች በተወሰደ አሰቃቂ እርምጃ ተጠናቋል፡፡
በሳውዲ እየተፈፀመ ያለውን በደል በመቃወም በዓለም አቀፍ ደረጃ ኢትዮጵያዊያን ድምፃቸውን በማሰማት ላይ ቢሆኑም እኛ ኢትዮጵያዊያን ግን በገዛ ሀገራችን ድምፃችንን እንኳን እንዳናሰማ ታፍነናል፡፡ በዚህም እንቅስቃሴ ላይ የተሳተፉ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች፣ አባላት፣ ደጋፊዎችና ሌሎች የኅብረተሰብ ክፍሎች ከፍተኛ ድብደባ፣ እንግልትና እስር ተፈፅሞባቸዋል፡፡
የመንግሥት ፖሊሶች የራሳቸውን ዜጋ በመደብደብና በማሰቃየት ብሎም በማሰር በሳውዲ በሚገኙ ኢትዮጵያዊ ወገኖቻችን ላይ የተፈፀመውን በደል ሀገር ውስጥ በሚገኙ ንፁሐን ወገኖቻቸው ላይ ደግመውታል፡፡
ይህ በውሸት ዲሞክራሲ ስም የተደበቀው አምባገነን መንግሥት ሕዝብን ለማሸማቀቅ የወሰደውን እርምጃ ወደ ጐን በመተው የኢትዮጵያ ሕዝብ ቅድም አያቶቹን በማስታወስ ያስረከቡትን ክብር ከማስመለስ ወደ ኋላ እንደማይል እርግጠኛ መሆናችንን እንገልፃለን፡፡
ፓርቲያችን እንዲህ አይነቱን የለየለት የመንግሥት ሕገ ወጥ ተግባር ትኩረት ሰጥቶ የሚመለከተው መሆኑን እየገለፅን፤ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብና መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ከጐናችን እንዲቆም በአፅንኦት ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡

ህዳር 6 ቀን 2006 ዓ.ም''




/////////////////////////////////።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።//////////////////////////////።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

 -






No comments:

ህወሓት ሰሜን ወሎ ራያን ወርሮ የገጠር ወረዳዎችን እየዘረፈ ነው። ህዝብ ሲዘረፍ እና በአስር ሺዎች ሲፈናቀሉ የመንግስት የፖለቲካም ሆነ የወታደራዊው አመራሮች ዝምታቸው ከተጠያቂነት አያድናቸውም።

በሰሞኑ የህወሓት ወረራ ቆቦ ተፈናቅለው የገቡ የሰሜን ወሎ ተፈናቃዮች  በከፊል ፎቶ፡ ቢቢሲ ሚያዝያ 20፣2024 እኤአ ''ቅጥ አምባሩ የጠፋው'' የፕሪቶርያው ውል   ''ስኩዌር ዋን&#...