ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Sunday, November 17, 2013

በዛሬውም ሆነ በመጪው ትውልድ የሚጠየቁ ሁለት ''ለምኖች''



1/ ለምን አንድ 


ኢትዮጵያውያን  በሳውዲ ባሉ ወገኖቻችን ችግር  ላይ ከዋሽግተን እስከ አውስትራሊያ ሰልፍ ሲሰለፉ ለምንድነው በየሀገሩ ያሉ  የኢትዮጵያ ኢምባሲዎች በሰልፉ ላይ ያልተገኙት? ወይንም  ለምሳሌ የዛሬውን የዋሽግተን ሰልፍ አስመልክቶ  ቪኦኤ  ለዋሽግተን ኢትዮጵያ ኢምባሲ ቢደውልም ምላሽ አላገኘሁም ብሏል። ይህ የሀገራችን ጉዳይ አይደለም እንዴ? ሰልፉ የሳውዲ ኤምባሲን  ያስከፋው እንጂ የኢትዮጵያን ኢምባሲ ከሰልፉ ጋር እንዳይተባበር የሚያደርገው ምን አይነት ሐረካት ነው?

2/ ለምን ሁለት 


አሁንም በሺህ የሚቆጠር ኢትዮጵያዊ ሲሰለፍ ሳውዲ አረብያን ሲቃወም የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን እና ራድዮ አንዲት እንዳይተነፍስ ያስገደደው ጉዳይ ምንድነው? ለቅሶው ለወገን፣እንባ መራጨቱ ለወገን፣ኢትዮጵይ ቴሌቭዥን ይህንን እነ ቢቢሲ፣ሲ ኤን ኤን፣ዋሽግተን ፖስት  የዘገቡትን የኢትዮጵያውያን የሳውዲ መንግስትን ተቃውሞ ለምን አላሳየም? ለምን? አዲስ አበባ ያለው የሳውዲ ኤምባሲ ሰራተኞች የአረብ ሻሂ ፉት እያሉ ስሙን የሳውዲ ቲቪ መባል እሩብ ጉዳይ የቀረውን ኢቲቪ ሲያደንቁት አይታያችሁም? ግን ለምን? ሼም  ኦን ኢቲቪ! ካለ ምንም ማጋነን ኢቲቪ ወቅታዊ አብሽቅ ነው።

እስኪ ደግሞ መጪውን ትውልድ እናስብ የዛሬ 30 ዓመት አንድ ኢትዮጵያዊ እንበል የዩንቨርስቲ ተመራቂ የመመረቅያ ፅሁፉን ''በኢትዮጵያ እና ሳውዳረብያ ግንኙነት ላይ''ሊሰራ ቢያስብ እና የሰሞኑን ሰልፎች ከቢቢሲ እና ሲ ኤን ኤን ላይ ወስዶ ከጠቀሰ በኃላ ኢቲቪ ስለሰልፎቹ  ምንም አለማለቱን ሲመለከት መደምደምያው ላይ ምን ብሎ ይፅፋል? ''ኢቲቪን የሳውዲ ገንዘብ ተቆጣጥሮት ነበር'' ብሎ? እስኪ አስቡት የት ነን? ማነው የሚገዛን? ያለቀስኩት- ከባዕድ ቆንስላ ፊት። የወቀስኩት- የውጭ መንግስትን። ኢቲቪ ምን ቤት ነው ድምፄን የሚያፍነው? ሳስበው ሳስበው ውስጤን እሬት እሬት አለኝ።

ጉዳያችን
ህዳር 9/2006 ዓም

No comments:

Beynouna Village - Ethiopia (Video) ባለፈው ሳምንት የተመረቀው መተሃራ እምብርት ላይ የተገነባው አስደናቄው የበይኑና ሪዞርት መንደር (ቪድዮ)

Beynouna Village - Ethiopia (Video) ባለፈው ሳምንት የተመረቀው መተሐራ እምብርት ላይ የተገነባው አስደናቄው የበይኑና ሪዞርት መንደር (ቪድዮ)