ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Saturday, November 9, 2013

በሳውዳረቢያ ያሉ ወገኖች ሁኔታ እጅጉን ተባብሷል....ሶስት ደረጃ ያላቸው መፍትሄዎች ይታዩኛል። የአዲስ አበባ ሕዝብ እና በውጭ የምንኖር ዜጎች በቀጣዮቹ ጥቂት ሰዓታት መስራት ያለብን ።


በማህበራዊ መገናኛ ከተለጠፈ የድረሱልን ጥሪ ቅዳሜ ጥቅምት 30/2006 ዓም 

በሳውዲ አረብያ ያሉ ወገኖቻችን ሁኔታ ከሶስት ቀናት በፊት ከነበረበት ሁኔታ እጅግ ወደ ባሰ ሁኔታ እየተሸጋገረ ይመስላል።ባለፉት 48 ሰዓታት ውስጥ የተከሰተው አዲስ ነገር ኢትዮጵያውያን መከራ ሲበዛባቸው እራሳቸውን ወደመከላከሉ ሲ ያዘነብሉ የሳውዲ ወጣቶችም አበሻውን እየመረጡ ማጥቃት ጀምረዋል።ሁኔታው በእዚሁ ከቀጠለ ከእዚህ በኃላ ተይዘው እስር ቤት የሚገቡት ኢትዮጵያውያን በእስር ቤት ከገቡ በኃላ ምንም አይነት የሚድያ ሽፋን በማታገኘው ሳውዲ አረብያ ታላቅ መከራ ይወድቅባቸዋል።

መንግስት ምክትል አምባሳደሩን አነጋገርኩ፣ ዜጎችን የማስወጣት ሥራ ልጀምር ነው ወዘተ የሚሉ የማረጋግያ ንግግሮችን ቢያሰማም ሁኔታውን ግን ከእዚህ በላይ የሚሄድበት አይመስልም።እንደ እውነቱ ከሆነ የእዚህ አይነቶቹ ሁኔታዎች በመንግስት ቀደም ብለው መታየት የነበረባቸው ሁኔታዎች ነበሩ።ለምሳሌ የዜጎች በሳውዲ አረብያ የሚሄዱበት ሁኔታ እና ነገሩ ከቁጥጥር ውጭ ከመውጣቱ በፊት የዜጎችን ችግር ለመፍታት በተጠና መንገድ አለመታሰቡ ዛሬ ለገጠመን ችግር የእራሱ የሆነ አሉታዊ ተፅኖ አምጥቷል።

አሁን ያንን ማውራቱ ሞት በራቸው ላይ ለቆመባቸው ወገኖቻችን አንዳች ነገር አይፈይድም።ከሳውዲ አረብያ ውጭ ያለን ኢትዮጵያውያን (ማለትም በሀገር ቤት እና ባህር ማዶ ያለነው) ማድረግ ያለብን አንድ ነገር ያለ ይመስለኛል።በመጀመርያ ደረጃ መንግስት ኢትዮጵያውያኑን አወጣለሁ ያለውን ወደተግባር ለመቀየር በቅርብ ይችላል ብሎ ማለት አይቻልም።ምክንያቱም ፓስፖርት የሌላቸውን በሺህ የሚቆጠሩትን ይለፍ መስጠት(ዜግነታቸውን ማረጋገጥ)፣ነፃ የትራንስፖርት ወጪ መመደብ እና ሀገር ቤት ወደየቀያቸው እስኪመለሱ  ቢያንስ ለጥቂት ቀናት የሚሆናቸው ገንዘብ ያስፈልጋል።አሁን ብዙዎች ንብረታቸውን እየተነጠቁ ናቸው።እነኝህን ስራዎች ባጭር ጊዜ የመስራት አቅሙም ሆነ የሎጀስቲኩ ዝግጅት ከመንግስት ሊገኝ ይችላል የሚል ግምት የለኝም።መንግስትን በመጠየቅ ሕይወት ስቀጠፍ ማየት በራሱ ሌላ እራስ ምታት ነው።


ስለዚህ ምን እናድርግ? 

እኔ አሁን የሚታዩኝ ሶስት ደረጃ ያላቸው ድርጊቶች ናቸው።


1/  ድርጊት አንድ 


አዲስ አበባ የሚገኘውን የሳውዲ ኤምባሲን  በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ወጥተው  በተቃውሞ ድምፃቸውን ማሰማት አለባቸው።የአዲስ አበባው ሰልፍ በውጭ ከሚኖሩት በበለጠ ትልቅ ድምፅ አለው።ሰልፉ የዓለም አቀፍ የዜና ዘጋቢዎች ሰሞኑን አዲስ አበባ ለተደረጉት ስብሰባዎች የመገኘታቸውን አጋጣሚ መጠቀም ያስፈልጋል።ሳውዲ አረብያም ከኢትዮጵያ ጋር የሚኖራትን ጥቅም እንደሚጎዳው ትረዳለች።እራሳችንን አሳንሰን አንመልከተው ከእርሻ ጀምሮ ሌሎች የንግድ ዘርፎች ላይ ሳውዳረብያ ኢትዮጵያ ውስጥ ጣፈጠም መረረም ጥቅም አላት።በሕዝብ ዘንድ የሚነሱ ተፅኖዎች በምንም መልኩ የሚናቁ አይደሉም።

2/ ድርጊት ሁለት 

 በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በማህበራዊ ድህረ-ገፆቻቸው ጉዳዩን የዓለም ሕዝብ እንዲመለከት በመግለፅ፣በየሃገራቱ የሚገኙ የሳውዲ  አረብያ ኢምባሲዎችን በስልክ፣በፋክስ፣እና በኢሜል ጥያቄውን ለሀገራቸው መንግስት እንዲያቀርቡ በማሳሰብ እና የአዲስ አበባው ሰልፍ ከተደረገ በኃላ እንደችግሩ መቀጠል በተቃውሞ ሰልፍ ጭምር ጉዳዩን ለየምንኖርበት ሃገራት መንግሥታት ማሳወቅ።

3/ድርጊት ሶስት 


 በሶስተኛ ደረጃ ሁኔታው የመረጋጋት መልክ ሲያሳይ ወደሀገራቸው የሚሄዱትን እና በድርጊቱ እጅግ የተጎዱቱን ቅድምያ ሰጥቶ በውጭ ያለው ወገን መርዳት የሚችልበትን ሁኔታ ማቀናበር የሚሉት ይሆናሉ።

አሁን ግን በቅድምያ አዲስ አበባ ያለው ሕዝብ በመቶ ሺዎች የሚቆጠር ሕዝብ ይህንን የውርደት ድርጊት ወደ ኢምባሲው በመሄድ መቃወም የሚገባው ይመስለኛል።ይህ በመንግስት ደረጃ ምንም ያልተባለለትን ዲፕሎማሲ በፍጥነት ወደ ሕዝብ ዲፕሎማሲ  ያሳድገዋል።በተጨማሪም የሳውዲ መንግስት ነገሩን በአንክሮ እንዲያይ ያስገድደዋል እና አፋጣኝ መልስ ከህዝባችን ይጠበቃል።



።።።።።።።።።።።።።//////////።።።።።።።።።።።።።።።።።////////።።።።።።።።።።።።።።።።።።

No comments:

የመጀመርያዋ የኢትዮጵያ ሴት ፕሬዝዳንት የነበሩት ክብርት አምባሳደር ሣህለወርቅ ዘውዴን በክብር አለመሸኘት የኢትዮጵያን ክብር ብቻ ሳይሆን ለሴት ልጅ ያለንን የክብር ልኬት የሚያሳይ ነው።

የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሣህለወቅ ዘውዴ ጉዳዩ የዲሞክራሲ ባሕላችን ያኋልዮሽ ጉዞ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። የኢትዮጵያ ታዳጊ ሴትና ወንድ ልጆች የምናስተምራቸው ምንድን ነው? የመጀመርያዋ ሴት ፕሬዝዳንት ሲሰናበቱ እንዴት...