ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Saturday, November 2, 2013

ባለፉት ሶስት ዓመታት ውስጥ ብቻ በትንሹ 2,500 ኤርትራውያን ወጣቶችን በሜደትራንያን ባህር ውስጥ መስመጣቸው ታወቀ። የአቶ ኢሳያስ መንግስትም በአስተርጓሚነት ሰላዮቹን ጣልያን አስገብቷል። AFP
የብዙ አፍሪካውያን ከሊብያ ከአልጄርያ እና ከሞሮኮ ወደ ደቡባዊ አውሮፓ የሚያደርጉት ፍልሰት የመላው ዓለም መነጋገርያ ከሆነ ሰነበተ።በቅርቡ ባብዛኛው ኤርትራውያንን የያዘ ጀልባ ተሳፋሪዎቹን እንደያዘ በደቡባዊቱ የጣልያን ግዛት መስጠም ጉዳዩን በአዲስ መልክ መቀስቀሱ ይታወቃል።ባለፈው ሰሞንም የአውሮፓ ህብረት በጠራው ድንገተኛ ስብሰባ የደቡብ አውሮፓ መግብያ በሮች 'በዘመናዊ ካሜራ እና ልዩ ጥበቃ እንዲጠናከሩ' በሚል ሃሳብ ዙርያ ሃሳቦችን ተለዋውጧል።

አስገራሚው ነገር ግን አውሮፓውያንም ሆኑ የአፍሪካ መንግሥታት ችግሩን እንፍታው የሚሉት ከችግሩ ምንጭ ማለትም ከአፍሪካ አምባገነን እና ማን አለብኝ መንግሥታት ጀምረው ሳይሆን ስለ ጀልባው፣ድንበር ማጠር ወዘተ እያነሱ በጉዳዩ ላይ ከመሳለቅ ባላለፈ ዙርያውን የመዞሩ አባዜ አሁንም ለችግሩ መፍትሄ በቅርቡ እንደማይገኝለት አመላካች ነው።ለምሳሌ የኢትዮጵያውያንን እና የኤርትራውያኑ ስደት ምክንያት በሀገራቸው ካለው የኢኮኖሚ ችግር በዘለለ የአምባገነንነት እና የዘር ፖለቲካ መንሰራፋት መሆኑ እየታወቀ አውሮፓውያን የነገሩን ስረ-ምክንያት ትተው ስለ ድንበር ማጠር ማውራት ቀጥለዋል።

 ቄስ  ሙሴ ዘራይ እና ''ሀበሻ ኤጀንሲ'' የተሰኘ ድርጅታቸው  በተለይ በ ሜዴትራንያን በኩል አልፈው ለመምጣት የሚሞክሩትን ኤርትራውያንም ሆኑ ኢትዮጵያውያንን በመርዳት  ይታወቃሉ።ድርጅታቸው በስደተኞቹ ዙርያ ያደረገውን ጥናት እና ያሉትን መረጃዎች ትናንት ጥቅምት 21/2006 ዓም (Oct.31/2013) ለፈረንሳይ የዜና አገልግሎት (ኤኤፍፒ) እና ለሌሎች ዓለም አቀፍ የዜና አውታሮች መግለጫ ሰጥቷል።በመግለጫው ላይ የተተኮሩት ሁለት ነጥቦች ሲሆኑ-
የመጀመርያው  ከባህር ጉዞ የተረፉትን ስደተኞች ችግር ለጣልያን መንግስት የሚያስተረጉሙት የሻብያ መንግስት ሰላዮች መሆናቸውን እንደደረሱበት እና ጉዳዩን ከኢኮኖሚ ጋር ብቻ እያስተሳሰሩ ፖለቲካዊ ምክንያት እንዳላሰደዳቸው በመናገራቸው ችግር ከመፍጠራቸውም በላይ የስደተኞቹን መረጃዎች ለሻብያ መንግስት በሚስጥር እየላኩ ብዙ ቤተሰቦች ችግር ላይ መውደቃቸውን ገልፀዋል።
በሌላ በኩል እርሳቸው እና ድርጅታቸው ለጉዳዩ ቅርብ የመሆናቸውን ያህል እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከ 2010 ወዲህ አሁን እስካለንበት 2013 ዓም በሶስት አመታት ውስጥ ብቻ ወደ አውሮፓ ለመሻገር ሲሞክሩ በሜደትራንያን ባህር ውስጥ ሰምጠው የቀሩት ኤርትራውያን ቁጥር በትንሹ  2,500 መሆኑን ተናግረዋል።ዜናውን የጀርመኑ DW ራድዮ እና የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ለመላው ዓለም አሰራጭተውታል።ባለፈው ወር ላይ ጉዳዩ በአቶ ኢሳያስ መንግስት ላይ ከፍተኛ ተቃውሞ በተለያዩ የውጭ ሃገራት በሚኖሩ ኤርትራውያን መሰማቱ ይታወቃል።

በመጨረሻም ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ዛሬ ጥቅምት 23 እና ነገ ጥቅምት  24/2006 ዓም በቫቲካን በህገወጥ የሰዎች ዝውውር ላይ የምክክር ስብሰባ ጠርታለች።ስብሰባው የድርጊት መርሃግብር ለመቅረፅም የታለመ መሆኑ የቫቲካን ድህረ ገፅ ያትታል።

Sources-Priest claims Eritrea spies hunting shipwreck survivors in Italyhttp://www.globalpost.com/dispatch/news/afp/131031/priest-claims-eritrea-spies-hunting-shipwreck-survivors-italy ANTI-HUMAN TRAFFICKING MEETING AT VATICAN NOV. 2-3

Text from page http://en.radiovaticana.va/news/2013/10/29/anti-human_trafficking_meeting_at_vatican_nov._2-3_/en3-741883 
of the Vatican Radio website 


No comments:

ህወሓት ሰሜን ወሎ ራያን ወርሮ የገጠር ወረዳዎችን እየዘረፈ ነው። ህዝብ ሲዘረፍ እና በአስር ሺዎች ሲፈናቀሉ የመንግስት የፖለቲካም ሆነ የወታደራዊው አመራሮች ዝምታቸው ከተጠያቂነት አያድናቸውም።

በሰሞኑ የህወሓት ወረራ ቆቦ ተፈናቅለው የገቡ የሰሜን ወሎ ተፈናቃዮች  በከፊል ፎቶ፡ ቢቢሲ ሚያዝያ 20፣2024 እኤአ ''ቅጥ አምባሩ የጠፋው'' የፕሪቶርያው ውል   ''ስኩዌር ዋን&#...