ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Thursday, November 7, 2013

የበዕውቀቱ ግጥም በአውስትራልያው ዩንቨርስቲ ሲረጋገጥ!

በቅድምያ የበዕውቀቱን ግጥም ላስቀድም በመቀጠል የአውስትራልያው ''ኩይንስ ላንድ'' ዩንቨርስቲ ኢትዮጵያን በዓለም ላይ የድብርት ስሜት (clinical depression) ካልተጠናወታቸው ጥቂት ሃገራት ተርታ መሆኗን በጥናቴ አገኘሁት ያለውን ''የዋሽግተን ፖስት'' ጥቅምት 28/2006 ዓም ያወጣውን አስከትላለሁ።

ከድብርት ስሜት የራቀ ሕዝብ መሆናችን በምጣኔ ሀብት በልፅገን ወይም የመሰረታዊ ፍላጎቶቻችን ተሟልተው አይደለም።ይህ  ፀጋ ነው።ሀገር ቤት የሚኖሩ ወገኖቼ የውጭውን ዓለም የድብርት ደረጃ እና ሰው በባቡር ውስጥ  ሲሄድም  ምን ያህል ሳይነጋገር እንደሚሄድ ካልተመለከቱት ይህንን ላይረዱት ይችላሉ።ይውጭውን ዓለም ድብርት የተመለከተ የሃገር ቤትን የድብርት መድኃንትነት ይረዳዋል።

አንድ ጊዜ አንድ የውጭ ዜጋ በኢትዮጵያውያን ደስተኛነት ምንጭ ግራ መጋባቱን ሲገልፅ እንዲህ አለ።

''አዲስ አበባ መንገድ ላይ አንድ ልጅ መጣ እና ሳንቲም ለመነኝ።እንደሌለኝ እራሴን በመወዝወዝ ገለፅኩለት።እርሱ ግን መልሶ እኔን እያየ ሳቀብኝ እየሳቀ ሄደ።እኔ ገንዘብ ያለኝ የእርሱን ያህል ደስተኛ አይደለሁም።ይህንን ልጅ መልሼ ጠራሁት እና የት እንደሚኖር ጠየቅሁት ከመንገድ ዳር እንደሚኖር ነገረኝ።ይህንን ሲነግረኝም ፈገግ ብሎ ነበር።ኢትዮጵያውያን ውስጣዊ ደስታቸው  የሚመነጨው ከእግዚአብሔር መሆን አለበት አልኩኝ።በችግር ላይ ሆነውም አይደበሩም።''ብሏል።

ሃይማኖታዊ በዓላት ሲከበሩ ሕዝብ ሁሉ በደስታ ወጥቶ የሚያከብረው የቁሳዊው ነገርስለተሟላለት አይደለም።እየከፋን ደስ እንዲለን የተሰጠን ፀጋ አለ።ሃዘናችንን የምንረሳበት የተሰጠን ልዩ ስጦታ አለ።

ወደ ገጣሚ  በእውቀቱ ስዩም ግጥም እናምራ አርስቱ ''ኢትዮጵያዊ ነኝ'' ትላለች።

''ኢትዮጵያዊ ነኝ 

      ኑሮ ቢገፋኝ የማልወድቅለት፣

                      እንደ አክሱም ድንጋይ እንደ ሮሃ አለት፣

የጊዜ ሞገድ ያላደቀቀኝ፣

 የመከራ ዶፍ ያልነቀነቀኝ፣

     ለሙሾ ሲያጩኝ  ቅኔ የምቀኝ፣

በግራ ሲሉኝ የምገኝ በቀኝ፣

ኢትዮጵያዊ! ነኝ።''



A stunning map of depression rates around the world

BY CAITLIN DEWEY
November 7/2013  at 7:00 am


Redder countries have higher depression rates. Bluer countries have lower depression rates. (Max Fisher/The Washington Post)
በካርታው ላይ እነደሚታየው የሰማያዊ ቀለም ያለባቸው ሃገራት (በጥናቱ መሰረት) የድብርት መጠናቸው ከ 4% በታች የሆኑ ናቸው።የቀይ ቀለም የሚታይባቸው ደግሞ የድብርት ደረጃቸው ከፍተኛ የሆኑ ናቸው።ለምሳሌ ኢትዮጵያ፣አውስትራልያ ከ 4%በታች ሲሆኑ ሱማልያ፣ኤርትራ ሳውዳረብያ እስከ 6% የሚሆን የድብርት መጠን ላይ መሆናቸውን ያመላክታል።የድብርት መጠኑን ጥናቱ በ 7 እና 4% መካከል ሁሉንም ሃገራት አስቀምጧል።
ምንጭ- ዋሽግተን ፖስት ጋዜጣ  http://www.washingtonpost.com/blogs/worldviews/wp/2013/11/07/a-stunning-map-of-depression-rates-around-the-world/?tid=sm_fb  

No comments:

ሐያ ገዳማት የሚገኙበት በግሪክ የሚገኘው የአቶስ ተራራ ገዳማውያን አኗኗር (ቪድዮ)

ገዳሙ ከሰርብያ፣ሮማንያ፣ቡልጋርያና ሩስያ የመጡ ዓለምን የናቁ መነኮሳት ገድመውበታል።