ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Friday, November 8, 2013

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በአዲስ አበባ የሳውዲ ምክትል አምባሳደር በኢትዮጵያውያን ላይ እየደረሰ ስላለው ጉዳይ በፅሁፍ እና በቃል ማብራርያ እንዲሰጡ አደረገ።የሳውዲ አረብያ ዋናው አምባሳደር ሀገር ውስጥ አይደሉም ተብሏል።



''የኢትዮጵያዊው በሳውዲ አረብያ የፀጥታ ኃይሎች መገደል በምንም መልኩ ተቀባይነት የለውም በአዲስ አበባ የሳውዲ ምክትል አምባሳደር ስለጉዳዩ በፅሁፍም ሆነ በቃል ማብራርያ እንዲሰጡ  ጠይቀናል ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተልን ነው'' አምባሳደር ዲና ሙፍቲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዛሬ ምሽት የሰጡት መግለጫ።

በሌላ በኩል ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አገኘሁት ያለውን ኢዜአ ማምሻውን ባሰራጨው ዜና ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው የሚመለሱበትን ሁኔታ እየተሰራ መሆኑን እና ጉዳዩን የምያቀላጥፍ ተጨማሪ የሰው ኃይል ሳውድ አረብያ ወደሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ መላኩን ገልጧል።

በጉዳዩ ላይ ሚዛናዊ እና በጎ አስተሳሰብ መያዝ ትተው በእየማኅበራዊ ድህረ ገፁ ከኢህአዲግ በላይ ኢህአዲግ ሆነው በጭፍን ድጋፍ ''መንግስት ምንም ማረግ አይችልም መንግስት ዝምታውም ልክ ነው'' እያሉ እራሳቸውን የመንግስት ጠበቃ የሚያደርጉ ከእዚህ ምን ትምህርት ያገኙ ይሆን? ሀገራችንን ስንወድ ወተቱን ለማጥቆር ወይንም ጥቁሩን ለማንጣት መሆን የለበትም።እንደሰው የማሰብ ፍትሃዊ አስተሳሰባችንን ለምን በጭፍን የመንግስት ድጋፍ እንደምንጋርደው አይገባኝም።

በሌላ በኩል የውጭ ጉዳይም ሆነ ሌሎች አካላት  ሃገርን እስከወከሉ ድረስ በ 21ኛው ክፍለ ዘመን መሆናቸውን መርሳት አይገባቸውም። በእየደቂቃው በሚቀያየር የዓለም ስርዓት ውስጥ ሆነን የማኅበራዊ ድህረ ገፆች ይህንን ያህል ስለ ጉዳዩ እስኪያጮሁ ድረስ  የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መጠበቅ አልነበረበትም።

በጉዳዩ ላይ የሳውድ አረብያ መንግስት የሰጠው ምላሽም ሆነ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው የሚመለሱበት ሁኔታ ምን ያህል በኢትዮጵያ ኢምባሲ በኩል ምን ያህል እየተቀላጠፈ መሆኑ ገና አልታወቀም። የተለወጠ ነገር ካለ  በሳውድ አረብያ ያላችሁ ወገኖቻችን ሁኔታውን ባገኛችሁት መንገድ አሳውቁ።

ጉዳያችን ጡመራ ጥንቅር

//////////////////////////////////---------////////////////////////////////-------------------------///////////////////////////////////////////

No comments:

ህወሓት ሰሜን ወሎ ራያን ወርሮ የገጠር ወረዳዎችን እየዘረፈ ነው። ህዝብ ሲዘረፍ እና በአስር ሺዎች ሲፈናቀሉ የመንግስት የፖለቲካም ሆነ የወታደራዊው አመራሮች ዝምታቸው ከተጠያቂነት አያድናቸውም።

በሰሞኑ የህወሓት ወረራ ቆቦ ተፈናቅለው የገቡ የሰሜን ወሎ ተፈናቃዮች  በከፊል ፎቶ፡ ቢቢሲ ሚያዝያ 20፣2024 እኤአ ''ቅጥ አምባሩ የጠፋው'' የፕሪቶርያው ውል   ''ስኩዌር ዋን&#...