ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Saturday, June 8, 2013

የሰኔ 1፣1997 ዓም ሰማዕታት የተመለከተ ልዩ ጥናታዊ (ዶክመንተሪ) ፊልም በጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና

 ዛሬ ሰኔ 1 ነው።በዛሬዋ ዕለት 1997 ዓም በትንሹ ከአንድ መቶ ዘጠና ዘጠኝ ቤቶች በላይ ውስጥ አስከሬን የወጣበት ቀን በሺህ የሚቆጠሩ ዘመዶች፣ወዳጆች  ኢትዮጵያውያን   በሃዘን ሲያስቡ ይውላሉ።

ሕዝብ ጥያቄውን በሰላማዊ ሰልፍ ሲያቀርብ የጥይት አረር ለመለሱ መንግሥታትም ሆነ ትዛዙን ላስተላለፉ መሪዎች አለማችን ቦታ የላትም።
የግብፁ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ሁስኔ ሙባረክ አሁን ከተከሰሱበት ክስ መካከል አንዱ እና ዋናው በታህሪር አደባባይ ለተሰለፉት ሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ የኃይል እርምጃ በመውሰዳቸው ነው።በተመሳሳይ መንገድ ጎረቤት ሀገር ኬንያ ፕሬዝዳንቷ ጭምር በአለምአቀፍ ፍርድቤት ደረጃ ክስ የተመሰረተባቸው እ.አ.አቆጣጠር በ2007 ዓም የተካሄደውን  ምርጫ ተከትሎ በተነሳው ግጭት የኃይል እርምጃ እንዲወሰድ በመደረጉ ነው።

የሲሳይ አጌና የሰኔ 1፣1997 ዓም እልቂት የሚያስታውስ ልዩ ጥናታዊ (ዶክመንተሪ) ፊልም በኢትዮጵያ የዲሞክራሲ ጥያቄ ያነሱ ግን የጥይት አረር ሰለባ የሆኑ  ኢትዮጵያውያንን ታሪክ በትትክል ይዘግባል።ጉዳዩን መንግስት እራሱ በመሰረተው አጣሪ ኮሚሽን ያልተመጣጠነ እርምጃ መወሰዱን 8 ለ 2 ድምፅ ወስኖ ለምክርቤት ቢቀርብም የጉዳዩ ተዋናዮች ዛሬም ለፍርድ አልቀረቡም። 

ከአሁን በኃላ በሰላማዊ ሰልፍ ለሚጠየቁ ጥያቄዎች ተመሳሳይ ስህተት ለመስራት ሞራል ያለው ፖሊስም ሆነ ''የግደሉ'' ትዕዛዝ ለማስተላለፍ የሚደፋፈር  ባለስልጣን ባይኖረን እንመርጣለን።ለቀደመውም ተዋናይ የነበሩት ለፍርድ እንዲቀርቡ በሕይወት ያለነው መጠየቅ ባንችልም የሞቱት ግን ለፈጠራቸው አምላክ መጮሃቸው አይቆምም።ለሰማዕታቱ እረፍተ ነፍስን  ለቤተሰብ፣ለወዳጅ ዘመድ መፅናናትን ይስጥልን።





ጉዳያችን GUDAYACHNgetachewb221@gmail.com

No comments:

ሐያ ገዳማት የሚገኙበት በግሪክ የሚገኘው የአቶስ ተራራ ገዳማውያን አኗኗር (ቪድዮ)

ገዳሙ ከሰርብያ፣ሮማንያ፣ቡልጋርያና ሩስያ የመጡ ዓለምን የናቁ መነኮሳት ገድመውበታል።