ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Monday, June 17, 2013

የዘመናችን ስልቭያ ፓንክረስት- ፖርቱጋላዊቷ አና ጎሚዝ

አና ማርያ ሮሳ ማርቲንስ ጎሜዝ  ባጭሩ ሚስስ አና ጎሜዝ ይባላሉ።የካቲት 9፣1954 የፖርቱጋሏ ዋና ከተማ ሊዝበን  ውስጥ ተወለዱ። በ 2004 ዓም የአውሮፓ ህብረት ምክርቤት አባልነት የሀገራቸውን የሶሻሊስት ፓርቲ እንዲወክሉ ተመረጡ። ከእዛ በፊት ግን ሀገራቸውን በተባበሩት መንግሥታት በሚወክሉት ቆንስላዎች ውስጥ በኒውዮርክ እና በጀኔቭ እንዲሁም በቶክዮ እና በለንደን የፖርቱጋል ኢምባሲ ሀገራቸውን ወክለው አገልግለዋል።ይህ ብቻ አይደለም የፖርቱጋልንና የኢንዶነዥያንን የሻከረ ግንኙነት ሕይወት በመዝራት ይሞገሳሉ።

የሊዝበን ዩንቨርሲቲ የሕግ ምሩቅ የሆኑት አና ጎሜዝ ከአዚህ ሁሉ በኃላ አለምአቀፍ ልምድ እና ተሞክሮ በኃላ ነበር በ1997 ዓም በኢትዮጵያ የተደረገውን ምርጫ ለመታዘብ የአውሮፓ ህብረትን  ልዑክ በመምራት ወደ ኢትዮጵያ መጡ። አናጎሚዝ በወቅቱ በመንግስት የተወሰደውን የምርጫ ሸፍጥ ሲያነሱ አሁን ድረስ ያንገበግባቸዋል።ሲናገሩ ''ለምን ይዋሻል?'' የሚለው ስሜት ከውስጣቸው ሲፈነቅላቸው ይታያል። 

አንዳንዶች የምርጫውን ማጭበርበር ከጊዜ ብዛት እየለመድነው መጥተን  በውሸት መናደድ ወደማቆም የደረስን እንኖር ይሆናል።ለአና ጎሚዝ ግን ይህ ጉዳይ የህሊና እረፍት ነስቷቸዋል።እራሳቸውን እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ አድርገው ነው የሚናገሩት። ኢትዮጵያ አውሮፓውያን ለመብቷ የሚቆሙላት እናቶች አጥታ አታውቅም። እንግሊዛዊቷ ሲልቭያ ፓንክረስ (የርቻርድ ፓንክረስት እናት) በጣልያን ወረራ ዘመን በመላው አለም የኢትዮጵያ ድምፅ እንዲሰማ ሙሉ ግዝያቸውን የሰጡ ብቻ ሳይሆን ሞታቸው እና ቀብራቸውም ኢትዮጵያ (አራት ኪሎ ቅድስት ስላሴ ቤተ ክርስቲያን) ሆኗል። አና ጎሚዝ ፖርቱጋላዊ የዘመናችን ስልቭያ ፓንክረስት ሆነው ብቅ ብለዋል። በነገራችን ላይ አና ጎሚዝ ዛሬም ለኢትዮጵያ መጮሃቸውን አላቆሙም።በመጪው እረቡዕ  ሰኔ 12፣2005 ዓም በብራሰልስ፣ቤልጅየም ኢትዮጵያውያን በሚያደርጉት ሰልፍ ላይ ይገኛሉ።ኢትዮጵያን የወዱቱን ያብዛልን።

አና ጎሚዝ ስለ ፍትህ፣እውነት እና ዲሞክራሲ ይናገራሉ (ቪድዮ ይመልከቱ)
part 1

part 2 

2 comments:

Anonymous said...

she is great women. we Ethiopians never forget her.

Anonymous said...

talak sew nech. andi ken Addis Ababa metesh mesqel adebabay nigigir sitaregi lemachebcheb yabkagn. ye ewnet sew nech we Ethiopians love europe.we love portugal because of Ana Gomez.

Beynouna Village - Ethiopia (Video) ባለፈው ሳምንት የተመረቀው መተሃራ እምብርት ላይ የተገነባው አስደናቄው የበይኑና ሪዞርት መንደር (ቪድዮ)

Beynouna Village - Ethiopia (Video) ባለፈው ሳምንት የተመረቀው መተሐራ እምብርት ላይ የተገነባው አስደናቄው የበይኑና ሪዞርት መንደር (ቪድዮ)