ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Wednesday, August 10, 2016

ዝም ያለ ከተስማማ እኩል ይቆጠራል።በሀገር ውስጥ እና በውጭ የሚኖረውን የትግራይን ሕዝብ ይመለከታል (የጉዳያችን ማስታወሻ)ህወሓት ከመነሻው ጀምሮ ግድያ የጀመረው በትግራይ ሕዝብ ላይ ነበር።የትግራይ ሽማግሌዎች ''የፊውዳል እና የነፍጠኛ አምላኪ'' እየተባሉ በህውሃት ግልፅ እና ስውር የግድያ መንገድ ተፈጅተዋል።የህወሓትን እንቅስቃሴ በቀዳሚነት የተቃወመ የትግራይ ሕዝብ ነበር።የአክሱም እና ተንቤን ሕዝብ ህወሓትን ደግፎ ቆሞ አያውቅም ነበር።ህወሓት በማኔፌስቶው ላይ '' የትግራይ ሕዝብ ትግል ፀረ-አማራ፣ ፀረ-እምፔራሊዝም እና ፀረ ንዑስ ከበርቴ'' መሆኑን ከገለፀ በኃላ አላማውም ''የትግራይ ሪፑብሊክ መመስረት ነው'' ይላል። ይህንን አባባል በመጀመርያ ላይ የተቃወሙት እና ለሰማዕትነት የደረሱት የትግራይ ወጣቶች እና አረጋውያን ነበሩ።ይህ ሁኔታ እስከ 1983 ዓም ሲቀጥል የአክሱም እና ተንቤን ሕዝብ በተለይ በኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ጉዳይ ህወሓትን በእየቦታው ሲሞግቱ የነበሩ አሁንም የትግራይ አዛውንት ነበሩ።በ1990 ዓም የተቀሰቀሰው የኢትዮ-ኤርትራ ግጭት ላይ የኢትዮጵያ ሕዝብ ለሰንደቅ አላማው እና ለኢትዮጵያዊነቱ ያሳየው ፅናት (ህወሓት ኢትዮጵያውያንን በአደባባይ ሲዋሹ ቢታዩም) ለትግራይ ሕዝብ ሰንደቅ አላማ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ዳግም ያረጋገጠ ታሪካዊ አጋጣሚ ነው።  

በ1968 የወጣው የህወሓት ማኔፈስቶ -

ኢትዮጵያውያን የህወሓት የጎጥ ፖለቲካ አይን ያወጣ ቢሆንም ሁሉን ችለው ኢትዮጵያዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ብቻ ሲያተኩር ቆይቷል።አቶ መለስ ሕይወት ሲያልፍ የአዲስ አበባ ሕዝብ ትግራይ ተወለዱ ኤርትራ ሳይል ከአየር መንገድ አስከሬን አጅቦ የወጣው ሕዝብ በኢትዮጵያ ላይ የተፈፀመውን ድርጅታዊ ወንጀልን ማንም እረስቶት አይደለም።በመላው ኢትዮጵያ ለቀናት የዘለቀ ሃዘን ሲታወጅ የኢትዮጵያ ሕዝብ በጨዋነት ቀናቱን በዝምታ አሳልፏል።
ይህ ሁሉ የሚያሳየን የኢትዮጵያ ሕዝብ ከሚገባው በላይ ጨዋ ሕዝብ መሆኑን ነው።ህወሓት ከጎንደር እና ዓለም ከተማ የመብራት ትራንስፎርመር በምሽት ሊሰርቅ እጅ ከፍንጅ የያዘው ሕዝብ የዘር አድልዎ እንደተደረገበት እያየ በአርምሞ አሳልፏል።በያዝነው ዓመትም በአርማጮ እና ወልቃይት ሕዝብ ላይ ህወሓት ከአድዋ እና ሽሬ እናቶችን በመኪና አመላልሶ ጠብመንዣ እያስያዘ በአማራው ሕዝብ ላይ ሁለት ጊዜ በሰልፍ ሲዝቱ የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን በዜና እወጃው ሲያሳይ የትግራይ ሕዝብ ይቃወማል ተብሎ ይጠበቅ ነበር።

ባለፈው ሳምንት መጨረሻም ጎንደር እና ጎጃም ላይ በህወሓት ሰራዊት ግልፅ የሆነ ወረራ ተፈፅሟል።እስከ አሁን ድረስ እንደ ሁማን ራይት ዘገባ ከአንድ መቶ በላይ ሕዝብ ተገድሏል።በሆስፒታል የሚገኙ በከባድ ሁኔታ የቆሰሉ ደግሞ ከ500 በላይ እንደሆኑ እና ከእነኝህ ከቆሰሉት ውስጥ አሁንም የሞቱት አስከሬን እየወጣ መሆኑ ይታወቃል።አሁንም ከትግራይ ሕዝብ በህወሓት ላይ የተሰማ ተቃውሞ የለም።


ይህ ብቻ አይደለም ዛሬ ሮብ ነሐሴ 4/2008 ዓም ከባህር ዳር እና ጎንደር የሚወጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ከመቀሌ በአንቶኖቭ አይሮፕላን የመጡ የአጋዚ ወታደሮች ወደ ጎንደር እና ባህርዳር ገብተዋል።ይህም ግልፅ የሆነ የጅምላ ፍጅት ህወሓት ልትፈፅም መሆኑን አመላካች ነው።ይህንንም የሚቃወም የትግራይ ሕዝብ ሰልፍ አልታየም።

ስለሆነም የትግራይ ተወላጅ እስካሁን እየሆነ ላለው ሁሉ ግልፅ ተቃውሞ በህወሓት ላይ ሲያሳይ አይታይም።ይልቁንም በማህበራዊ ድረ-ገፆች ላይ  የትግራይ ተወላጅ መሆናቸውን የሚናገሩት ''ትግራይ ኦንላይን'' እና ''አይጋፎረም'' በገፃቸው ላይ የሚፅፉት አማራውን እና ኦሮሞውን የሚያጣጥሉ እና ንቀት የሚያሳዩ ፅሁፎችን ነው።እነኝህ ድረ-ገፆች አላስፈላጊ ፅሁፎችን ሲለጠፉ አሁንም ከትግራይ በኩል ተቃውሞ የሚያሳይ አንድም የጎላ ድምፅ አልተሰማም።

ባጠቃላይ የትግራይ ሕዝብ ህወሓት ለሚሰራው ግፍ እና አገራዊ ወንጀል ሁሉ ዝም ማለት የለበትም።በእራሱ በትግራይ ህወሓትን የሚቃወም ሕዝብ ለማየት የኢትዮጵያ ሕዝብ እየናፈቀ ነው። አሁን ባለንበት ሰዓት የኢትዮጵያ ሰራዊት ውስጥም ግልፅ የሆነ መለያየት እየታየ ነው።ሰራዊቱ ውስጥ የትግርኛ ተናጋሪ እና ሌላ አካባቢ የመጡ በጥይት እርስ በርስ እንደተጋደሉ ተሰምቷል።ሰራዊቱ ከቀናት ምናልባትም ከሰዓታት በኃላ ሰራዊቱ አፈሙዙን በአቶ አባይ ወልዱ ቅልብ ሰራዊት ላይ እንደሚያዞር ምንም  ጥርጥር የለውም።የትግራይ ሕዝብ ግን የወገኖቹ መጨፍጨፍ እንዳልሰማ ዝም ሊል አይገባም። ይህ ሁኔታ ሁላችንም  አላስፈላጊ ወደ ሆነ መሰረታዊ የአስተሳሰብ ለውጥ ውስጥ እንዳያስገባን እና በግለሰቦች የተፈፀመብን የዘር አድልዎ ወደ ከፋ ድምዳሜ እንዳያደርሰን ያሰጋናል። ነገን አርቆ ማሰብ ለእራስ ነው።የትግራይ ሕዝብ ከእዚህ ሁሉ ውጥንቅጥ ውስጥ ሊወጣ የሚችልበት ቀላሉ መንገድ ህወሓትን መቃወም እና ፋሽሽታዊ አስተሳሰብ ከተፀናወታቸው አባይ ወልዱን እና ግብረ አበሮቻቸውን በቁጥጥር ስር በማዋል እና መሰረታዊ አገራዊ ፖለቲካዊ፣ምጣኔ ሃብታዊ ለውጦች ላይ እና እኩል ተጠቃሚነት ላይ ሲስማማ ብቻ ነው።ከእዚህ ውጭ ግን ''ዝም ያለ ከተስማማ እኩል ይቆጠራል'' እንዲሉ በድርጊቱ ከመስማማት እንዳያስቆጥር ከፍተኛ ስጋት አለ።እጅ አጣጥፎ ሁኔታውን እንደ ሲኒማ ከመመልከት ህወሓትን አደብ አስገዝቶ ለዘላለም ከምንኖርበት ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር አንድ መሆን ብቸኛው አማራጭ ነው።


ጉዳያችን GUDAYACHN
 www.gudayachn.com 

No comments:

ወቅታዊ የዓለም ሁኔታ እንድንነታረክ ዕድል የሚሰጥ አይደለም።ብንነቃ መልካም ነው።

========== ጉዳያችን ወቅታዊ ========== የዓለም ታሪክ እንደሚያስተምረን ዓለም በወሳኝ የእጥፋት(turning point) ታሪኮች ውስጥ አልፋለች። እነኝህ የእጥፋት ጊዜዎች የዋዛና የፈዛዛ ጊዜ አይደሉም።መላው ዓለ...