ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Monday, October 11, 2021

እንደሚገረፍ ያወቀ ልጅ አባቱ ገና ቀበቶውን ሲነካካ እሪ! ይላል።


----------------
ጉዳያችን/ Gudayachn
---------------

ጉዳያችን ምጥን 

ልጁ ገና አልተገረፈም።እሪታው ግን ሲገረፍ የማያወጣውን ድምፅ ነው የሚያውጣው።ልጅ ሆነን እንዲህ ሆነን አናውቅም? ግርፍያው እንደማይቀር ከአባታችን ፊት እናውቀዋለን።ቀጥሎ እያንዳንዱ የአባትን እንቅስቃሴ እንከታተላለን።በመቀጠል እጁን ወደ ቀበቶው ሰደድ ሲያደርግ እሪ! ማለቱ ይቀጥላል።ምናልባት አባት ለመግረፍ ሳይሆን ቀበቶውን ሊያስተካክል ሁሉ ሊሆን ይችላል።ልጅ ግን ጥፋቱን ያውቃልና ቀድሞ እሪታውን ያቀልጠዋል።የህወሓት አፈቀላጤ የጌታቸው ረዳ የዛሬ መግለጫ እንዲህ ነው።እንደሚገረፍ ያውቃል።እርሱና  ቡድኑ የሰራትን ያውቃል።በአማራ እና በአፋር ሕዝብ ላይ ብቻ ሳይሆን በራሱ በትግራይ ሕዝብ ላይ የፈፀመው ግፍ ከአሁን በኃላ ከራሱ ልጆቹን ካስጨረሰበት ከትግራይ ሕዝብም ምን ሊሆን እንደሚችል ያውቃል።መከላከያ በሀገር ላይ ለተሰራው ክህደት እርምጃ እንደሚወስድ እርግጠኛ ነው።ስለእዚህ ገና ሳይገረፍ የህወሓት ቃል አቀባይ በእንግሊዝኛ መግለጫ እሪታውን ዛሬ አቅልጦታል።መከላከያ ገና ዋና የማጥቃት ዘመቻውን አልጀመረም።ምናልባት ቀበቶውን ነካክቶ ይሆናል።

ጌታቸው ረዳ አባቱ ቀበቶውን ሲነካካ እንደተመለከተ ልጅ እሪ! ማለቱ ከ''ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ'' እና ሸፍጠኛ ደጋፊዎች ፈጣን እርዳታ አገኛለሁ በሚል እሳቤ ነው። ለነገሩ ግርፍያ ሲጀመር ለእሪታ ጊዜ አይኖርም።ከእንግሊዝኛ መግለጫው  ቀደም ብሎ ''መቀሌን አትነካም'' መሰል ፉከራም አሰምቷል።ለነገሩ ''ምን ያለበት ምን አይችልም'' መሆኑ ነው።በገደምዳሜ መቀሌን ማስተዳደር ስላልቻለ መከላከያ መቀሌ ቢገባለት የፈለገ ይመስላል።መከላከያ በጌታቸው ብልጣብልጥ አካሄድ አይመራም።የመከላከያ ዕቅድ እና አካሄድን ለማወቅ አይቻልም።የትግራይ ሕዝብም ህወሃትን አሽቀንጥሮ በመጣል መከላከያን በክብር መጥራት የራሱ ፋንታ ነው።ይህ ካልሆነ የዛሬ ዓመትም ህወሓት ትግራይን ማውደሙን ይቀጥላል።እስከ ዛሬ ዓመትም የትግራይ ሕዝብ ህወሓትን እያዳነቀ መኖር ከቀጠለ ትግራይ ሽፍታ የሰለጠነባት ሕዝብ ተሰዶ የሚያልቅባት ምድር እንደምትሆን ለማወቅ ጠቢብ መሆን አያስፈልግም።

በነገራችን ላይ ዛሬ በመላዋ ኢትዮጵያ ትምህርት ቤት ተከፍቷል።የትግራይ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት አይሄዱም።
በእዚህ ወር መጨረሻ የሚሰጠው የማትሪክ ፈተናም መውሰድ አይችሉም።ለእዚህ ሁሉ ተጠያቂው ህወሓት እና ቅምጥሎቹ 
በውጭ ሀገር እና በሀገር ውስጥ ያሉ የህወሓት አድናቂዎች ሁሉ ናቸው።

መከላከያ ቶሎ መቀሌ ገብቶ ትምህርት ቢጀመር፣መብራት ቢለቀቅ ደስ የማይለው የትግራይ ክልል ነዋሪ የለም ማለት አይቻልም።
ይህ ምን ማለት እንደሆነ በውጭ ሀገር ተቀምጠው የራሳቸውን ልጆች ወደ ትምህርት ቤት እየላኩ የትግራይ ልጆች ግን የጅብ ራት 
ሲሆኑ ትንሽ ቅር የማይላቸውን አይጨምርም። አሁን ጥያቄው አንድ ነው። በትግራይ ሰላም ለማምጣት ህወሓት መጥፋት አለበት።ህወሓት በመኖሩ ብቻ ትግራይን ጨምሮ ለመላዋ ኢትዮጵያ ጥፋት ነው።ህወሓትን ማውረድ የራሱ የትግራይ ሕዝብ ኃላፊነት መሆኑን ማወቅ አለበት።ከአሁን በኃላ መከላከያ መቀሌ እንዲገባ እና ሰላም በትግራይ ወርዶ ተማሪዎች በሰላም ወደ ትምህርት ቤት እንዲሄዱ ሕይወት እንደገና እንዲቀጥል እራሱ ህዝቡ ህወሓትን አውርዶ መከላከያን መጥራት አለበት።ይህ ካልሆነ ዝም ብሎ ህወሃትን አይን አይኑን እያዩ ለውጥ አይመጣም።

መከላከያ ከሰሜን ወሎ ጠራርጎ ያስወጣል።የኢትዮጵያን ድንበር ይጠብቃል።ህወሃትን ማውረድ እና መከላከያን መጥራት የራሱ የትግራይ ሕዝብ ሥራ ነው። ዛሬ ጌታቸው ረዳ ቀበቶ ገና ሲነካካ እሪ! ማለቱ ለትግራይ ሕዝብ ጥሩ አጋጣሚ ነው።የትግራይ ህወሓትን ዘወር በል ማለት ያለበት አሁን ነው።አይ! ህወሓትን እያሽሞነሞንኩ የትግራይን ሕዝብ ሲፈጅ ዝም እላለሁ ማለት ሌላው አማራጭ ነው። ይህ መንገድ ግን መጨረሻው ሞት ነው።መከላከያ የሁሉ አባት፣የሁሉ እኩል ዳኛ ነው።መከላከያ መቀሌ ተለምኖ እንጂ ተገላምጦ እንደማይገባ ማወቅ  ብልህነት ነው።
========/////=======


No comments:

ኢትዮጵያ በዘመናዊ ታሪኳ ታላቅ ተልዕኮ የሚኖረው ሀገራዊ የምምክር ኮሚሽን በተመለከተ ምን ያህል እናውቃለን?

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ኮሚሽን አማካሪ ኮሚቴ አባላትን ከሁሉም የኢትዮጵያ ክፍል ባካተተ መልኩ አዋቅሯል። በእዚህ ጽሑፍ ስር የሚከተሉት ነጥቦች ምላሽ ያገኛሉ፡  ኮሚሽኑ እንዴት ተመሰረተ?  የኮሚሽኑ 11 ኮሚሽነሮች እንዴት ተመ...