ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Saturday, October 16, 2021

ሰበር ዜና - ህወሓት በሰሜን ወሎ የመጨረሻ ውግያ ብሎ የላከው ጀሌ ክፉኛ ተመቷል።የመጨረሻ ውግያ የሚሉ ቃላት ሰሞኑን መጠቀም የፈለገባቸው ሦስት ምክንያቶች ታውቀዋል።

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ስር ቃል ኪዳን ሲገቡ 

================
ጉዳያችን/Gudayachn
===============

ህወሃት በውሸት ዜና ተጥለቅልቋል።ሰኔ 21/2013 ዓም የኢትዮጵያ መከላከያ ለትግራይ ሕዝብ የፅሞና ጊዜ ለመስጠት እና የእርሻ ጊዜው እንዳይታጎል በሚል የተናጥል ተኩስ አቁም አድርጎ ቢወጣም፣ከተደበቀበት ዋሻ እየወጣ በፍርሃት መቀሌ የገባው የተረፈው የህወሓት ቡድን የትግራይን ሕዝብ በራሱ በህወሓት ጥፋት ማለትም በኢትዮጵያ መከላከያ ላይ ባደረሰው ጥቃት ሳብያ የደረሰውን ጥፋት ለማስተካከል ከመጣር ይልቅ ወደ አማራና አፋር ሕዝብ ላይ ለመዝመት ሞክሮ አራት ወር ሙሉ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች አስፈጅቶ የጅብ እራት ካደረገ በኃላ ከሕዝቡ ጋር ውስጥ ውስጡን የምንተከተክ ቁርሾ ውስጥ ገብቷል።የህወሓት ይሄው የጥፋት መንገድ በትግራይ ሕዝብ እናቶች ላይ ከባድ ሰቀቀን ጥሎ ከመሄድ  አልፎ  የትግራይ ቤቶች ውስጥ በአሁኑ ሰዓት ብዙ ሕዝብ መርዶ እየጠበቀ ይገኛል።

ያለፈው ሳምንት ዓርብ ሽብርተኛው ህወሓት ድንገት ተነስቶ መንግስት በአየር እና በምድር ወረረኝ ብሎ መጮህ ጀመረ።ሰኞ ማለዳ በእንግሊዝኛ ይሄው ለቅሶ ወጣ።ይህንን አስመልክቶ ከመንግስት በኩል ምንም የወጣ ነገር አልነበረም።ከአራት ቀናት በኃላ መከላከያ በማህበራዊ ሚድያ ላይ ባወጣው ፅሁፍ ላይ ህወሓት በአማራ ክልል ደግማ ለመተኮስ ያደረገችውን ሙከራ ክፉኛ እንደተመታ ገለጠ።የህወሓት ለቅሶ ግን እስከ ዛሬ ቅዳሜ ድረስ ቆይቶ ''እራሱ ምን ብሎ እራሱ አለቀሰ'' እንዲል እራሱ ተጠቃሁ ያለው የሽብር ቡድን ዛሬ ቅዳሜ ድንገት ተነስቶ ደግሞ የመንግስት ወታደር አሸነፍኩ የሚል መግለጫ ሰጠ።የገታቸው ረዳ መግለጫ ከደብረፅዮን፣የፃድቃን ከታደሰ ወረደ እርስ በርስ የተምታታ መግለጫ መስጠታቸው የመከፋፈሉ ማሳያ ብቻ ሳይሆን የውጭ ኃይልም ዳቦ እያላሰ እንደ የቤት ድመት እያተራመሳቸው መሆኑ ይታያል። ቢቢሲ ጌታቸው ረዳን ሲያናግር፣ አንዱ የፈረንጅ አክትቪስታቸው ተነስቶ ፃድቃንን ያሞግሳል፣ የህወሓት ማኅበራዊ ሚድያ ታደሰ ወረደን ያሞግሳል።ያፈሰሰሱት ደም አክለብልቧቸዋል።

ከላይ ህወሓት ተወረርኩ ከሚለው ለቅሶ ቀጥሎ የተነገረው ጉዳይ ፃድቃን ለኒውዮርክ ታይምስ ሲናገሩም ሆነ ጌታቸው ረዳ ለትግራይ ሚድያ ሲናገሩ ከሰሞኑ ያመጧት አዲስ ፋሽን አለች። ''የመጨረሻው ውግያ ነው።በቅርቡ ጦርነቱን እንጨርሰዋለን።'' የሚሉ ቃላት ናቸው።ለምንድነው እነኝህን ቃላት መጠቀም የፈለጉት?
በቀውስ ውስጥ ያለው የህወሓት የሰሞኑ ስብሰባ መቀሌ 

ህወሓት የመጨረሻ ውግያ የሚሉ ቃላት ሰሞኑን መጠቀም የፈለገባቸው ሦስት ምክንያቶች

ህወሓት ከሰሞኑ የመጨረሻው ውግያ የሚልባቸው ምክንያቶች ሶስት መሆናቸው ታውቀዋል።
 
1)  የትግራይ ሕዝብም ሆነ የክልሉ ኢኮኖሚ ከእዚህ በላይ ጦርነት ለመቀጠል ህዝቡ በሙሉ ከቦታው መፈናቀል ይኖርበታል።ስለሆነም ህወሓት የመጨረሻው አቅሙ ላይ ስለደረሰ።

የህወሓት ዕቅድ ሰኔ ላይ ወደ አማራ እና አፋር ሲዘምት ጦርነቱን ቢያንስ ሰሜን ሸዋ አድርሶ እና የጅቡቲን መንገድ ዘግቶ ከቻለ አዲስ አበባ መምጣት ወይንም መንግስትን አስገድዶ ወደ  ድርድር ማምጣት የሚል ነበር።ይህንን ደግሞ ክረምቱ እንደ አመቺ ጊዜ ተወስዷል።ምክንያቱም መንግስት የበላይ በሆነበት የአየር ኃይል ውግያ በክረምቱ ምክንያት የጉም መሸፈን እንደሚረዳ ታስቦ ነበር።ሌላው ክረምቱ የተፈለገበት ምክንያት መንግስት መካናይዝድ ጦር በክረምት ጭቃ በተለይ ወደ ደጋው አካባቢ ማንቀሳቀስ አይችልም የሚል ታሳቢ ተደርጎ ነበር።

ይህ ሁሉ ግን አልሰራም ክረምቱም አለፎ ጥቅምት ከባተ ሳምንት ተቆጠረ።ስለሆንም ከትግራይ ሕዝብ የተነሳበት ጥያቄ በጦርነት ካልተሳካ በፍጥነት ከአማራ ክልል ለቃችሁ ወጥታችሁ ተደራደሩ የሚል ጥያቄ ወጥሮ ይዞታል።በቅርቡ መቀሌ ላይ ሽማግሌዎች ተሰብስበው ይህንኑ ጥያቄ ለደብረፅዮን አቅርበው ህወሓት አዋርዶ መመለሱ ከአክሱም እስከ አድዋ ያሉ ከተሞች ተሰምቶ ቁጣ ፈጥሯል።ስለሆነም ይህንን ሕዝብ ለመደለል ጦርነቱ የመጨረሻ ደረጃ ደረሰ፣በቅርቡ እንጨርሰዋለን የሚሉ ቃላት በመናገር ሕዝቡን ለመደለል ሞክረዋል።በነገራችን ላይ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የመንግስት ሰራተኞች ደሞዝ ያልተከፈላቸው ከመኖራቸው ጋር በስራቸው የሚያስተዳድሯቸው ቤተሰቦች ጨምሮ እና የመብራት እና ስልክ አገልግሎት ከመቆሙ ጋር እንዲሁም አዲሱ የትምህርት ዘመን ከመጀመር ጋር የትግራይ ሕዝብ ህወሓትን ወጥሮ ይዟል።

2) በውጭ የሚኖረው የህወሓት ደጋፊ መከፋፈሉ መቀጠሉ።

በውጭ የሚኖረው የህወሓት ደጋፊ ቀድሞ በስሜት ሲፎክርበት የነበረው ''ግፋ በለው'' ፉከራ አሁን በትግራይ ሕዝብ ላይ ያደረሰው ጥፋት ብቻ ሳይሆን የሚያውቃቸው ቤተሰቦች ወደ አማራ እና አፋር እየተላኩ የማለቃቸው ዜና ሲሰማ እነጌታቸው ረዳን አንድ ዓይነት መፍትሄ በፍጥነት ካልደረሱ ትግራይን ሙሉ በሙሉ እንደሚያወድሙ የሚጠይቁ በዝተዋል።ሌላው አብረው ቆይተው የምንደግፈው ህወሓትን ሳይሆን ትግራይን ነው የሚሉ ሌላ አንጃዎች ተፈጥረው ሁሉም በአንድነት ጥያቄያቸው ወደ ገደል እየሄድን ነው።በቶሎ አንድ ነገር አድርጉ ይህ ካልሆነ ሌላ አደረጃጀት ተፈጥሮ ህወሓትን የሚቃወም ኃይል ተፈጥሮ ትግራይን ማዳን ላይ መስራት አለበት የሚለው ስሜት አይሏል።ስለሆነም ይህ የመጨረሻው ጦርነት ነው፣በቅርቡ እንጨርሰዋለን የሚለው መልዕክት ወጥሮ ለያዛቸው ለውጭው ደጋፊ መደለያ የቀረበች ነች።

3) የምዕራቡ ዓለም እረጅም ጊዜ ከህወሓት ጋር እንደማይቆይ እና ጊዜ እንደሌለው ይታወቃል።

የምዕራቡ ዓለም ጊዜ የለውም። የምስራቅ አፍሪካ ጉዳይ ጊዜ በተሰጠው ቁጥር ከእጁ ከመውጣቱ በላይ ለቻይና እና ሩስያ ስር የመስደድ ዕድል  እየበዛ ከመምጣቱ በላይ የምዕራቡ ዓለም ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር የባሰ ፀብ ከመግባት የህወሓት ጉዳይ ቶሎ ታውቆ የስልት ለውጥ ማድረግ እንደሚገደዱ ግልጥ ሆኗል።ስለሆነም የህወሓት መሸነፍ ዜና ከሱዳን ቀውስ ጋር ተዳምሮ የምዕራቡን ዓለም ተስፋ ስለሚያስቆርጠው ከኢትዮጵያ ጋር አዲስ አቀራረብ በተለየ ድብቅ ስልት ቀርቦ በሰጥቶ መቀበል መርህ ሊቀርብ ይችላል።በሌላ በኩል የምዕራቡ ዓለም ለህወሓት የሰጠው ''የማርያም መንገድ'' ረጅም ጊዜ መቆየት እንደማይችል በገደምዳሜ ለህወሓት አይነግሩትም ማለት አይቻልም።የምዕራቡ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ለማፍሰስ ጊዜ የላቸውም ህወሓት የዘላለም ወዳጅ እንደማይሆን ግልጥ ነው።ስለሆነም ህወሓት ለምዕራቡ ዓለም ጦርነቱን ልንጨረሰው ነው፣በቅርቡ ያልቃል እያለ ለኒውዮርክ ታይምስ በፃድቃን አማካይነት መናገር ነበረበት።

ባጠቃላይ ህወሓት ሁለቱን ዋና ዋና ሞቶች ሞቷል።ሶስተኛው እና የመጨርሻው ሞቱ ሸህ ሁሴን ጀብሪል እንዳሉት ወሎ ላይ ነው ቀብሩ ያሉት ትንቢት የደረሰ ይመስላል።ሁለቱ ሞቶች በጥቅምት 24 በመከላከያ ላይ ጥቃት ከፈፀመ በኃላ ዋሻ እስከምገባበት ያለው ሲሆን ሁለተኛው በአፋር እና ወሎ ላይ የደረሰበት በአስር ሺዎች የሞቱበት እልቂት ሲሆን አሁን በአራት አቅጣጫ ወሎ ላይ ተከቦ የፍፃሜ ሞቱን እየጠበቀ ነው።የምዕራቡ ዓለም ምንም አይነት እቀባ ቢያደርግ ነፃነት በእቀባ አይቀየርም።ይህንን ደግሞ ከአሁኑ ግልጥ ሆኖላቸዋል።በባለስልጣናቱ ላይ ለይተው እቀባ ለማድረግ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ ጀምሮ ይህ ነው የሚባል ሀብት በአሜሪካ የገንዘብ ድርጅቶች ውስጥ አለማግኘታቸው አበሳጭቷቸዋል።መግንስት ደግሞ በህወሓት ላይ አጠቃላይ ጥቃት የሚከፍትባትን ቀን እና ሰዓት ''ከአባት በቀር የሚያውቃት የለም'' እንዲል ከጥቂት ከፍተኛ መኮንኖች እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ ውጭ የሚያውቀው የለም።መንግስት ከእዚህ በፊት እንዳየነው በህወሓት ላይ አጠቃላይ ጥቃት ሲጀምር እጅ እንዲሰጡ የ72 እና 48 ሰዓታት ማስጠንቀቅያ ስለሚሰጥ ይህንኑ ህወሓት በተስፋ ብትጠብቅ የተሻለ ሳይሆን አይቀርም።

========///==========
No comments:

ለፕሮፌሰር መራር፣ልደቱ፣ጀዋርና ኢንጅነር ይልቃል ዘፈን ይህችን ዜማ እንምረጥላቸው።

በቅድምያ ስለ አራቱም የመግቢያ ማስታወሻና ወቅታዊ ሁኔታቸው። አራቱም ከመስከረም በኋላ መንግስት የለም ብለው ኢትዮጵያን ለእርስ በርስ ጦርነት ሊነክሯት ሞክረዋል።ዝርዝሩን፣ከእነማን ጋር መክረው እንደነበር፣ለኢትዮጵያ ደግሰው...