ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Friday, October 15, 2021

የምዕራቡ ዓለም በተለይ አሜሪካ ለዩጎዝላቭያ መፍረስ ምን አድርጋ እንደነበር የሚያሳይ ጥናታዊ ፊልም ከህወሓት ደጋፊ እስከ የፅንፍ የኦሮሞ ብሔርተኝነት አራማጆች፣ከአማራ አክራሪ ብሔርተኝነት እስከ ኢትዮጵያዊነት ይቅደም የምንል ሁሉ በትዕግስት እንመልከተው።


ፊልሙን ከተመለከትኩ በኃላ እነኝህ ነጥቦችን ያስታውሱ -
  • ኢትዮጵያ ውስጣዊ የፖለቲካ ግጭቶቿ ታሪካዊ ዳራ እና ስነልቦናው ከዩጎዝላቭያ ጋር አይመሳሰልም።ይህ ማለት ግን ለኢትዮጵያ ካልሰራን አደጋ የለብንም ማለት አይደለም::
  • ዩጎዝላቭያ የነበረው ሕዝብ የመከፋፈል አካሄድ፣ የአሜሪካ እና የምዕራቡ የጣልቃ ገብነት መጠን እና ደረጃዎች በትክክል አሁን እያደረጉት ካለው ጋር ይመሳሰላል።
  • በኢትዮጵያ በብ/ጄ አሳምነው ዙርያ የተነሳው የባህርዳሩ አስዛኝ የአመራሮች ሞት፣የአርቲስት ሃጫሉ መገደል፣በሰሜን ዕዝ ላይ በህወሓት የተወሰደው ማጥቃት ሦስቱ ኢትዮጵያውያንን እርስ በርስ አጋጭቶ ለማፍረስ የመጡ መቅሰፍቶች ነበሩ።እነርሱን አልፈናል።ለቀጣይ ተመሳሳይ አደጋዎች ቢፈጠሩ ወደ ብሔር ስሜት እንዳይሄድ እያንዳንዱ ምሁር፣ጋዜጠኛ፣የማኅበራዊ ሚድያ ተጠቃሚ ሳይቀር ኃላፊነቱ ምን ያህል ከባድ እንደሆነ ያሳያል።
  • የትም ሆንክ የትም፣ህወሓትን ደገፍክ፣ኦነግ፣ኢትዮጵያዊነትን አስቀደምክ አላስቀደምቅ በምትሰራው ሥራ ሕዝብ የሚከፋፍል እና ኢትዮጵያን ለባዕዳን ከሚያስማማ ድርጅት እንደ ህወሓት እና ኦነግ ሸኔ ጋር ከቆምክ ሕዝብህን፣እራስህን እና ልጆችን ወደባርነት እየመራህ መሆኑን እወቀው።
ብልህ ከሌላው ስህተት ይማራል።በትግስት ጥናታዊ ፊልሙን ይመልከቱ።


No comments: