===========
ጉዳያችን ምጥን
===========
የሽብርተኛው የህወሓት ቡድን ሁለት ወሳኝ ዕድሎቹን አበላሽቷል።የመጀመርያው ወደመቀሌ ከከተተ በኃላ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ሂደት ውስጥ መሳተፍ ሲሆን ሁለተኛው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰኔ 21/2013 ዓም የትግራይ ሕዝብ የፅሞና ጊዜ እንዲያገኝ፣ገበሬው የእርሻ ሥራውን እንዲያከናውን መቀሌን ለቆ ከወጣ በኃላ ያለው ጊዜ ነው።የመጀመርያውን በኢትዮጵያ መከላከያ ላይ ጥቅምት 24/2013 ዓም ጥቃት በመፈፀም ሲያበላሸው፣ሁለተኛው ደግሞ ትግራይን ይዞ ሕዝቡ እድንያገግም ከመስራት ይልቅ ወደ አማራ እና አፋር በመውረር ያጠፋው ዕድሉ ነው።
የኢትዮጵያ መንግስት የህወሓትን ወረራ በሙሉ አውዳሚ መንገድ እየተዋጋው አይደለም።ለምሳሌ ለስልጠና የሚሰበስባቸው ወጣቶች ገና በማሰልጠኛ እያሉ በአየር ኃይል አልመታም።መንገድ ላይ የሚንቀሳቀሰው ማንኛውም የታጠቀ የህወሓት ጀሌን አልደበደበም።ይህም ወጣቶቹ በግድ መታፈሳቸውን እና ቤተሰቦቻቸው አሁንም በፍላጎት አልላኩም ከሚል እሳቤ ሊሆን ይችላል።
ይህ ሁሉ ትዕግስት ግን ለህወሓት የልብ ልብ ሰጥቶት እጅግ አረመኔያዊ በሆነ መንገድ ገበሬውን እየረሸነ፣ልጆቹን እየደፈረ እና ሰብሉን እያቃጠለ የጥፋት ስራውን ቀጥሏል።ከእዚህ ሁሉ ጥፋት ጋር በሺህ የሚቆጠር ሕዝብ እየተሰደደ ነው።ይህ ፅሁፍ እየተፃፈ ብዙ ሺዎች የደሴ እና ኮምቦልቻ ከተሞችን በስደት አጣበዋል።ይህ ሁኔታ አሁን ባለበት መንገድ አይቀጥልም።
ሽብርተኛው ህወሓት በሰዓታት ውስጥ በአማራ ክልል የወረራቸውን ቦታዎች ለቆ መውጣት ካልቻለ መንግስት ኢትዮጵያን የማዳን እና ያለማዳን ወሳኝ እና ወደየማይፈለገው ነገር ግን አማራጭ ወደ የሌለው እርምጃ የግድ መግባት ሊኖርበት ይችላል። ይህ እርምጃ ምንድነው? ብሎ መጠየቅ ይችላል።ነገር ግን ሀገር የማዳን ሥራ በትሕትና የሚሰራ አይደለም።ይህ ጦርነት በምንም ዓይነት መንገድ በፍጥነት መጠናቀቅ አለበት።ለእዚህ ደግሞ ወሳኝ እርምጃ የሚጠይቅበት ጊዜ ሆኗል።ይህ እርምጃ ግን የትግራይን መሰረተ ልማት እስከ ሰማንያ ከመቶ አያፈርስም ማለት አይቻልም። ወታደራዊ ውሳኔዎች ዋና ግባቸው ሀገር ማዳን ነው።የትግራይ ሕዝብ ህወሓትን ማውረድ እና ትግራይንም ሆነ ሕዝቡን ማዳን ብቸኛው አማራጭ ሲሆን ሌላው አማራጭ የሽብርተኛው ህወሓት በአማራ ሕዝብ ላይ የሚያደርሰውን ግፍ እያዩ ህወሓትን እያሽሞነሞኑ ትግራይን ማውደም ነው። መንግስት የሰብዓዊ ቀውሱን ለማስቆም እና ሀገርን ለማዳን ወሳኝ ወደ ሆነው ወደየማይፈለገው ነገር ግን አማራጭ ወደ የሌለው እርምጃ የግድ መግባት ሊኖርበት እንደሚችል አለመጠበቅ ግን አይቻልም።እስካሁን ህወሓትን ለማስታመም የተሄዱባቸው ሂደቶች በሙሉ ለመጪው ትውልድም በታሪክነት ተመዝግበው ትውልድ የራሱን ፍርድ ይሰጣል።የአንዳንድ ጦርነቶች አጨራረስ የራሱ የሆነ ባህሪ ይኖረዋል።ከሀገር እና ከጠቅላላ ሕዝብ በላይ የሚሆን ቡድንም ሆነ አስተሳሰብ የለም።
============///==========
No comments:
Post a Comment