ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Tuesday, October 26, 2021

ጆሮ ያለው ይስማ! ሽብርተኛው፣ ከህወሓት ቡድንነት ወደ የትግራይ ወራሪነት መቀየሩን የኢትዮጵያ ሕዝብ አሁን አምኗል።በመሃል ሀገርም ሆነ በውጪ የሚኖረው የትግራይ ማኅበረስብ ይህንን ወራሪ ከመቃወም መዘግየቱ ዋጋ የሚያስከፍለው ሰዓት የደረሰ ይመስላል።


የትግራይ ወራሪ ከአማራ ክልል ዘርፎ ሲሄድ (ፎቶ ኤኤፍፒ)

ጉዳያችን በየጊዜው የኢትዮጵያ የፖለቲካ፣ማኅበራዊ እና ምጣኔ ሃብታዊ ሁኔታዎች በተመለከተ የግለቱ ልኬት፣የሚሄድበት አቅጣጫ እና መድረሻ በተረዳችው ልክ ስታሳስብ አስር ዓመታት ሆኗታል።ወደ ኃላ ሄዶ ያለችው እና የሆነውን መመዘን የአንባቢ ፋንታ ነው።የተረዱትን ሳይናገሩ ከመቅረት ተናግሮ ቸል ያለው በቸልታው ይቀጥል።የተረዳው ደግሞ ነቅቶ እራሱንም አጥፊዎችንም ተጣልቶ መዳን ይችላል።

ኢትዮጵያ ላለፈው ግማሽ ክ/ዘመን በላይ እድገቷን ከገታባት፣የቁልቁለት ጉዞ ካስኬዷት የጠላት ጥፋቶች ውስጥ ከትግራይ የተነሳው ጎጠኛ እና በታኝ ወረራ አንዱ ነው።ይህ ከትግራይ የበቀለው የጥፋት፣የዘረኝነት እና የመሰሪ አስተሳሰቦች ሁሉ ወላጅ ሆኖ የወጣው ቡድን እራሱን ህወሓት/ወያነ በሚል አደራጅቶ ኢትዮጵያውያንን እና ኢትዮጵያን እያደማ ለ27 ዓመታት ሲገዛት ለመጪ ዓመታት የሚሆን መርዙን ተፍቶ ወደ ትግራይ ማፈግፈጉ ይታወቃል።

ኢትዮጵያውያን እና ኢትዮጵያ ይህንን መርዘኛ ቡድን '' የእናት ሆድ ዥንጉርጉር'' በሚል እንደ የቤት ልጅ አጥፊ እየታየ ብዙ ትዕግስት አሳይተዋል።በተለይ ቡድኑ በትግራይ ሕዝብ ውስጥ እንደመደበቁ የሕዝቡ ሃሳብ ሳይሆን የጥቂት ሰዎች እኩይ ሃሳብ ነው እየተባለ ከሚገባው በላይ በአንቀልባ እንደታዘለ ሕፃን ተይዞ ኖሯል።ይህ መርዛማ ቡድን በኤርትራ እና አማራ ሕዝብ ተደግፎ በ1983 ዓም አዲስ አበባ ገብቶ ስልጣን ከተረከበ በኃላ በርካታ ዕድሎች አበላሽቷል። ቀዳሚው በ1983 ዓም የተመሰረተው የሽግግር መንግስት ላይ ሲሆን ሁለተኛው በ1997 ዓም በተደረገው ምርጫ በመቀጠል በ2010 ዓም በተደረገው ሕዝባዊ ንቅናቄ ሁሉ የተሰጠውን ዕድል እንደ ጊዜ መግዣ እየወሰደ ዛሬ ደርሷል።

ባለፉት አራት ዓመታት ውስጥ ከመጣው ለውጥ የነበረውን ሂደት ብንመለከት ይህንን ጎጠኛ ቡድን ባላገለለ መንገድ በመጀመርያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ ወደ መቀሌ ሄደው ለክልሉ ምክርቤት ''ወርቅ ሕዝብ'' የሚል ሙገሳ የታከለከብት ንግግር አድርገው ሁኔታዎች በእርቅ እና በይቅርታ እንዲፈቱ ጥረት አደረጉ፣በመቀጠል ጳጳሳት እና ሸሆች እንዲሁም ታዋቂ ሰዎች ያካተተ ልዑክ መቀሌ ድረስ ሄዶ እናቶች እያለቀሱ የትግራይ ክልል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ደብረ ፅዮን ባሉበት ለመኗቸው።ሆኖም ለሽማግሌዎቹ ክብር ሳይሰጡ ገፍተው መለሷቸው። የብልፅግና ፓርቲ ውስጥ እንዲካተት ተለመኑ አሻፈረኝ አሉ።በዝርዝር የተደረጉ የሰላም ጥረቶችን ለመከለስ ይህንን ሊንክ ከፍተው ያድምጡ።

የዛሬ ዓመት ጥቅምት 24/2013 ዓም ህወሓት በኢትዮጵያ መከላከያ ላይ ጥቃት ከፈፀመ በኃላ መከላከያ በቀናት ህወሓት እና ጀለውን ጠርጎ መቀሌ ከገባ በኃላም ሙሉ በሙሉ መደምሰስ የሚለው ቀርቶ ለገበሬው የእርሻ ጊዜ ለመስጠት፣የተናጥል ተኩስ አቁም ብሎ መንግስት ትግራይን ለቆለት ወጣ። ይህም ሆኖ ግን በመጨረሻው ዙር ላይ እንደ ህወሓት ሳይሆን እንደ የትግራይ ሕዝብ ሆኖ በአማራ እና አፋር ክልሎች ላይ ወረራ ፈፅሟል።በወረራው የተሳተፈው ጥቂት ቡድን ሳይሆን የትግራይ ሕዝብ እንደ ሕዝብ እጁን እየነከረ ለመሆኑ በቂ ማስረጃዎች ተገኝተዋል። በወረራ ብቻ ሳይሆን በዘረፋ ላይ የትግራይ ነጋዴ ሁሉ ተሳትፏል።ከዝርፍያ በላይ የሴቶች መደፈር ሕፃናትን ሳይቀር ሆን ብሎ በጅምላ መፍጀት በአፋር እና በአማራ የትግራይ ወራሪ ከሰራቸው ግፎች ውስጥ ናቸው።

የትግራይ ወራሪ የወረራው ግብ ሕዝብ መበተን፣ሀገር ማፍረስ እና ኢትዮጵያን ለባዕዳን አሳልፎ መስጠት ነው።ቡድኑ የህወሓት ቡድን ሲባል የኖረው አባባል አሁን በግልጥ የትግራይ ወራሪ ማለት የሚቻልበት ጊዜ ላይ ተደርሷል።ምክንያቱም አሁን ወደ አማራ እና አፋር ዘምቶ ከትምህርት ቤት እስከ ክሊኒክ፣ከገበሬ ጎተራ እስከ የተቦካ ሊጥ እየዘረፈ የሚሄደው የህወሓት ወታርደር ብቻ ሳይሆን ተራው የትግራይ ሕዝብ ሁሉ የተሳተፈበት ነው።

ይህ ምን ማለት ነው? መልሱ ቀላል ነው። የተዘረፈው ሕዝብ ጥላቻው ወደ የትግራይ ሕዝብ እንደዞረ ግልጥ ሆኗል።ከትግራይ ካህናት እና ሸሆች ተዉ የሚሉ አልተሰሙም።የተሰረቀ አልበላም ያለ የትግራይ ገበሬ ተቃውሞ አልተነሳም።ይህ ነገ ከባድ መዘዝ አለው የሚል የትግራይ ምሑር ውስጥ ከሁለት እና ሶስት በላይ አልተሰሙም።ጆሮ ያለው ይስማ! ሽብርተኛው፣ ከህወሓት ቡድንነት ወደ የትግራይ ወራሪነት መቀየሩን የኢትዮጵያ ሕዝብ አሁን አምኗል።በመሃል ሀገርም ሆነ በውጪ የሚኖረው የትግራይ ማኅበረስብ ይህንን ወራሪ ከመቃወም መዘግየቱ ዋጋ የሚያስከፍለው ሰዓት የደረሰ ይመስላል።የኢትዮጵያ ሕዝብ የጃሮስላው ካዚንኪ ''ሰላም ከፈለክ ለጦርነት ተዘጋጅ'' የሚለውን አባባል ደጋግሞ ከንፈሩ ላይ እየመላለሰው ነው።
"If we want to avoid the worst, that is war, we have to act according to the old rule: 'If you want peace, prepare for war,'" Jaroslaw Kaczynski said

አሁን ሕዝብ መሮታል።የትግራይ ወራሪ እንደ አንድ የእናት ኢትዮጵያ ልጅ ሳይሆን እንደ ምናምንቴ ቆጥሮ በቃኝ! ብሎ በአንቀልባ የታሰረ ልጅ ከእናቱ ጀርባ ተገፍትሮ እንደሚያፈርጠው የምያፈርጥበት ጊዜ እራሱ ግፉ እየገፋው ነው።የትግራይ ወራሪን የእናት ልጅ እንደሚቀጣው ያለ ቅጣት ሳይሆን እንደምናምንቴ ቆርጦ ለመጣል የትግስቱ ልክ መጠን አልፏል።ብዙ ኢትዮጵያውያን በትግራይ ወረራ ላይ የተሳተፉ፣የረዱ እና በተዘዋዋሪ የተሳተፉ ሁሉ ኢትዮጵያዊነት ዜግነታቸው ተገፎ ከሀገር እንዲባረሩ እየጠየቁ ነው።ይህ ብቻ አይደለም።የትግራይ ወራሪን ለሕሊናቸው ሲሉ መቃወም ቀርቶ በእናቶች መደፈር፣በህፃናት ግድያ እና በምስኪን ገበሬዎች መዘረፍ የሚሳለቁ ሁሉ ''ወይ ኢትዮጵያ!'' የሚያሰኝ ቅጣት እንደሚያስፈልጋቸው ሕዝብ እንዳመነበት በደንብ እየታየ ነው።ሕዝብ ከወሰነ ማንም አያቆመውም።
=======///=======

No comments:

ለፕሮፌሰር መራር፣ልደቱ፣ጀዋርና ኢንጅነር ይልቃል ዘፈን ይህችን ዜማ እንምረጥላቸው።

በቅድምያ ስለ አራቱም የመግቢያ ማስታወሻና ወቅታዊ ሁኔታቸው። አራቱም ከመስከረም በኋላ መንግስት የለም ብለው ኢትዮጵያን ለእርስ በርስ ጦርነት ሊነክሯት ሞክረዋል።ዝርዝሩን፣ከእነማን ጋር መክረው እንደነበር፣ለኢትዮጵያ ደግሰው...