ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Wednesday, October 27, 2021

የኢትዮጵያ ሕዝብ ጦርነት የጀመረው አሁን ነው። በህወሓት የሚመራው የትግራይ ወራሪ ቡድን ጀሌውም ሆነ የመሃል ሀገር ደጋፊው ከሞያሌ እስከ መቀሌ ይነቀላል።

  • ከፅሁፉ ስር የህወሓት እና የሸኔ ምስጢራዊ  የስልክ ንግግር የያዘ ዶክመንተሪ ፊልም ያገኛሉ።

የትግራይ ወራሪ ቡድን መሪ ደብረፅዮን ደሴ እና ኮምቦልቻ የተቆጣጠረ ይመስል።በአማራ ላይ የበቀል ጅራፋችንን ጨርሰናል የሚል መሰል ንግግር ተናግረዋል።ጦርነቱን ጨርሰናል የምትለውን ቃል ደብረፅዮንም ሆነ ጌታቸው ረዳ ለምን እንደሚጠቀሙ ከእዚህ በፊት በጉዳያችን ላይ ''...የመጨረሻ ውግያ የሚሉ ቃላት ሰሞኑን መጠቀም የፈለገባቸው ሦስት ምክንያቶች ታውቀዋል።'' በሚል ርዕስ ስር ለማብራራት ተሞክሯል።ላማንበብ ከላይ ርዕሱን ከፍተው ያንብቡ።

የትግራይ ወራሪ ቡድን የትግራይን ሕዝብ በብዛት በማምጣት ከአሮጊት እስከ ታዳጊ ወጣት እያስፈጀ አስከሬን በአስከሬን እየሆነ ነው ወሎ የደረሰው።የኢትዮጵያ ኃይሎች አሁን ከመቼውም ጊዜ በላይ በብዛት የሰለጠነ የጦር ኃይል በአጭር ጊዜ ተዘጋጅተዋል።ከጎጃም እስከ ጎንደር ልዩ ኃይል፣ከወሎ እና ሸዋ ፋኖ፣ከኦሮምያ እና ሱማሌ ልዩ ኃይል እስከ የደቡብ ዘማች የትግራይን ወራሪን ለመቅበር ተነስቷል።የጎንደር ፋኖ ለወሎ ሕዝብ ደርሷል።የጎጃም ፋኖ ወደ ወሎ ከቷል። የትግራይ ወራሪ ሰሜን ጎንደር ደባርቅ ላይ እንዳይድን ተደርጎ ተመቷል።አፋር ላይ አፈር ለብሷል።መከላከያ ሰራዊቱ በሁሉም ግንባሮች ከሁሉ በላቀ ደረጃ በአየር ኃይል ጭምር ተሰልፏል።

ከሊጥ እስከ የብረት ድስት ወጥ የሚልሰው የትግራይ ወራሪን በሃሳብ እና በገንዘብ የሚደግፉት የመሃል ሀገር የድብቅ ጀሌዎች ኢትዮጵያን ከድቶ እና አፈርሳለሁ ብሎ ዝቶ፣ሕፃናትን ገድሎ እና ሴቶችን ደፍሮ  ለባዕዳን ለመስጠት የሚደራደረው የትግራይ ወራሪን የሚደግፉ ሁሉ የጠሏት ኢትዮጵያ እንደማታውቃቸው ቁርጣቸውን የመንገርያው ጊዜ አሁን ነው።አሁን እየተሽሞነሞኑ የሚሄዱበት ጊዜ አይደለም።የትግራይ ወራሪ ቡድን ደጋፊ መሃል ሀገር ሆኖ የኦነግ ሸኔን እየደገፉ ኢትዮጵያን እያደሙ ነው።ይህ ከአሁን በኃላ አይቀጥልም።የትግራይ ወራሪ በኢትዮጵያ ላይ መቼም ሊያንሰራራ አይችልም።የኢትዮጵያ ሕዝብ ጦርነት የጀመረው አሁን ነው። በህወሓት የሚመራው የትግራይ ወራሪ ቡድን ጀሌውም ሆነ የመሃል ሀገር ደጋፊው ከሞያሌ እስከ መቀሌ ይነቀላል።ኢትዮጵያን የወጉትን የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዴት እንደሚቀጣ ያውቅበታል።

የህወሓት እና የሸኔ ምስጢራዊ  የስልክ ንግግር የያዘ 
ጥቅምት 17/2014 ዓም (ኦክቶበር 27/2021 ዓም) የወጣ አዲስ ዶክመንተሪ ፊልም  

No comments: