ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Saturday, January 12, 2013

በ ጅማ ዩንቨርስቲ የ ኦርቶዶክስ ተማሪዎች ላይ ከ ሰሞኑ የተፈፀመ ግፍ (GUDAYACHN EXCLUSIVE )

ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ምእመናን ላይ እየደረሰ ያለው በደል ጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ ነው። ምዕመናን ስለ ቤተክርስትያናቸው ጉዳይ ለመነጋገር ካድሬ እና ጆሮ ጠቢ ኮቴ ማዳመጥ አለባቸው። ፍርሃቱ እና መሸማቀቁ መጠን አልፏል። ለምሳሌ በትናንትናው ጥር 3/2005 ዓም ታላቁ ዋልድባ ገዳም ተጨማሪ አባቶች እስር መዳረጋቸው እና ገዳማውያኑ መሬታችሁ ተነስታችሁ ሂዱ ካሳ ይሰጣችሁ የሚል ድፍረት በመንግስት በኩል መጀመሩን እና ይህንንም ገዳማውያኑ ባለመቀበላቸው አካባቢው ነዋሪዎች ለመዳኘት ወደ ገዳሙ ቢሄዱም መነኮሳቱ ጋር መታሰራቸውን አሜሪካ ድምጽ ራድዮ አማርኛው አገልግሎት ዘገባው አስታውቋል። ይህ ብቻ አይደለም ታላቁ ዋልድባ ገዳም ከሰሞኑ ጣልያን ኩባንያ ሸንኮራ አገዳውን ልማት እንዲሰራ የተሰጠ መሆኑን ከመዘገቡም በላይ ''ገዳሙ ባለበት ሸንኮራ አገዳው ልማት በጎን እንዲለማ ነው የፈለግነው '' የሚለው የመንግስት ቃል ተቀይሮ እንደ ገዳሙ ነዋሪ ቪኦኤ አማርኛው አገልግሎት እንደገለፁት'' መናንያኑ ቦታቸው እየተነሱ በምትኩ ካሳ እንዲሰጣቸው'' የሚል አዲስ የማግባብያ ዳር ዳርታ መጀመሩን ነው።

እግረ መንገዴን ዋልድባን ጉዳያ አነሳሁ እንጂ እዚህ አነስተኛ ፅሁፍ መነሻ የሆነኝ ወደ ጅማ ጉዳያችን ጡመራ የደረሳት ዜና ነው። ዜናውን ሌላ ነፃ ምንጭ ማረጋገጥ ባልችልም ታመነ ምንጭ ለመሆኑ ግን መናገር ይችላል።ጉዳዩ '' እምነታቸው ጉዳይ ለምን ይህ ይደረጋል ጉዳዩ ቢያንስ የሃይማኖት መከባበርን የሚንድ ተግባር ነው እና ሕግ አስከባሪው አካል ማሳሰብያ ይስጥበት።'' የሚል ጥያቄ ባቀረቡ ጅማ ዩንቨርስቲ እርሻ እና እንስሳት ሕክምና ኮሌጅ ተማሪዎች ቁም ስቅላቸውን እያዩ የመሆናቸው ዜና ነው።

ጉዳዩ እንዲህ ነው።በጅማ ዩኒቨርሲቲ እርሻ እና እንስሳት ህክምና ኮሌጅ እየተማሩ የሚገኙ ክርስቲያን ተማሪዎች የጌታችን እየሱስ ክርስን እና የእመቤታችን ድንግል ማርያም ስዕለ አድህኖ ሺንት ቤት ተጥሎ በማገኘታቸዉ ለዩኒቨርስቲዉ አካላት ይህንን አሳዉቀዉ መፍትሄ ለማፈላለግ ጥረት ያደርጋሉ።ይህ ጉዳይ ሆን ተብሎ በተደጋጋሚ በመፈፀሙ ተማሪዎቹ ሆነ አካል የሃይማኖት መከባበርን ለመናድ የተፈፀመ እና ተማሪውን ሰላም ለመንሳት ሊሆን ይችላል በሚል የሚመለከተው አካል ችግሩ ከመፈጠሩ በፊት አድራጊዎቹ ላይ ክትትል እንዲያደርግ የሚል ሃሳብ ይዘው ወደ ዩንቨርስቲው ቢሮ ያመራሉ። ዳሩ ምን ያደርጋል መጠየቅም ሆነ ሃሳብ መስጠት ወንጀል በሆነበት ሀገር ከዩንቨርስቲው ያገኙት ምላሽ ፖሊስ ተጠርቶ እየተደበደቡ መባረር እና የተቀሩት ደግሞ ወደ ጅማ ማረምያ ቤት መወርወር ሆነ። ይህ ብቻ አይደለም ግማሾቹን ማረምያ ቤት የተቀሩትን ደግሞ ጅማ ዞን ፖሊስ ጣብያ ተወስደው ካለ ምንም ምግብ እና መኝታ ስፍራ እንዲሰቃዩ እየተደረጉ መሆኑን ዜናው አክሎ ይገልፃል።ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ድረስ እስር ቤት የሚገኙት ተማሪዎች መኝታም ሆነ ምግብ አገልግሎት ክፍተንኛ ችግር መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።
ጅማ ዩንቨርስቲ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ተማሪዎች ላይ ግፍ ሲውል እና ስያስውል ይህ አዲስ አይደለም።የ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ተማሪዎች ብዙ በደል ይፈፀምባቸዋል። ዛሬ አራት አመት በፊት የተከወነ እውነተኛ ታሪክ ብነግራችሁ እውን ይህ ኢትዮጵያ ነውን? ትላላችሁ። ኢትዮጵያ ከፍተኛ የትምህርት ተቁዋማት ውስጥ ሙስሊም እህቶቻች ፀጉራቸውን መሸፋፈናቸው እና ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እህቶችም ነጠላ ለብሰው ግቢው አይታዩ ይህንን ግቢው ውጭ ነው ማድረግ ያለባቸው የሚል መመርያ በውይይት ላይ ነበር። ጉዳዩ ብዙዎች የሚወያዩበት እዚያን ሰሞን አርስት ነበር።ታድያ ጅማ ዩንቨርስቲ ተማሪዎቹ በሆኑት ሁለት ተማሪ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መነኮሳት ላይ ጥያቄ አስነሳ። ጥያቄው ነጠላ ብቻ ሳይሆን መነኮሳቱም ቀሚሳቸውን አድርገው ግቢ እንዳይገቡ አላቸው። መነኮሳቱ ይንቨርስቲው ዲን ድረስ ቀርበው ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የነበረ ስርዓት መሆኑን ለማስረዳት ቢጥሩም ኢትዮጵያ ተወልዶ ያደገው የዩንቨርስቲው ዲን አልቀበልም ይህን የሚገልፅ ማስረጃ አምጡ አላቸው።

መነኮሳቱ ወደ ጅማ ሃገረ ስብከት አቡነ እስጢፋኖስ ዘንድ ቀርበው ደብዳቤ አፅፈው እና ዲኑ ሰጥተው ነበር ምንኩስና ልብሳቸውን ለብሰው እንዲገቡ የተፈቀደላቸው። ደብዳቤው ልዩ የሚያደርገው '' የምንኩስና ልብስ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መነኮሳት ልብስ'' መሆኑን አብራርቶ ''ልብሱ ዘወትር መውለቅ የሌለበት'' መሆኑን ዩንቨርስቲው ዲን አድራሻ መፃፉ ነበር። ይህች ነች ዛሬዋ ኢትዮጵያ እንግዲህ። እዚህ ነው ላይ መንግስት እስከ አካባቢ ባለስልጣናቱ ቤተክርስቲያንቱን መብት እንዲህ ሲዳፈሩ እንዳላየ ዝም የሚላቸው። ሲሆን ደግሞ እንደ ጅማ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች መከራ ዶፍ የሚያወርድባቸው።

ለምሆኑ ጅማ ዩንቨርስቲ ተማሪዎችን ለምን ጉዳዩ ለምን ይህን ያክል ተጋንኖ ስቃይ ዳረጋቸው? 'ችግር ከመፈጠሩ በፊት መንግስት የጥንቃቄ እርምጃ ይውሰድ'ማለታቸው ለምን እንደ ኃጢያት ተወሰደባቸው? መልሱ አጭር ነው። ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን ጉዳይ መንግስት ዋና ባለስልጣናቱ ጀምሮ እስከ አካባቢ ባለስልጣናት ድረስ ቸልተኛነት ያለፈ ዱላ መለማመጃ አድርገዋታል።

ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን የማዳከም ሥራ መንግስት በኩል ብዙ መልኩ ይስተዋላል።ስበካ ጉባኤያት ህዝብን ማገልገል ትተው ወደ ''ትንንሽ አምባገነን መንግስትነት'' ሊቀየሩ ሲዳዱ ተቃውሞውን ለገለፀ ወይንም 'ምዕመንን እንጂ እራሳችሁን አታገልግሉ' ላለ እንደሌባ እየተቆጠረ ፖሊስ ሲጠራበት እና ፈተና እና እንግልት ሲዳረግ ተስተውሏል። ''ጌታዋን ያመነች በግ ላቷን ውጭ ታሳድራለች'' እንዲሉ። በቤተክርስቲያኒቱን ችግሮች ለመፍታት ምዕመናን ለሚያደርጉት ጥረት አይነተኛ የሆነ የመንግስት ጥረት አይስተዋልም። ይልቁንም ጉዳዩ ይመለከተናል ከሚሉት መንግስት ቢሮዎችም ሆነ አካባቢ አሰዳደሮች ስራቸው ሁሉ '' ቁስሉ ላይ እንጨት ስደድበት'' አይነት መስሏል።ለመሆኑ አርባ ሚልዮን በላይ የሆነ ሕዝብ ጉዳይ ግድ ያላለው መንግስት የት ሆኖ ሊያስተዳድር እያሰበ ይሆን?

2 comments:

Anonymous said...

Betam yemigermina yemiyasazin new mengest tikuret mestet mefteha mefeleg alebet

Anonymous said...

ya this is so true!

ህወሓት ሰሜን ወሎ ራያን ወርሮ የገጠር ወረዳዎችን እየዘረፈ ነው። ህዝብ ሲዘረፍ እና በአስር ሺዎች ሲፈናቀሉ የመንግስት የፖለቲካም ሆነ የወታደራዊው አመራሮች ዝምታቸው ከተጠያቂነት አያድናቸውም።

በሰሞኑ የህወሓት ወረራ ቆቦ ተፈናቅለው የገቡ የሰሜን ወሎ ተፈናቃዮች  በከፊል ፎቶ፡ ቢቢሲ ሚያዝያ 20፣2024 እኤአ ''ቅጥ አምባሩ የጠፋው'' የፕሪቶርያው ውል   ''ስኩዌር ዋን&#...