ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Monday, January 7, 2013

ሃምሳ አመቱን ሊደፍን ወራት የቀሩት የ ኢትዮጵያ ቴሌቭዥን አሳዛኙ የ አቀራረብ ጥራት ደረጃው

ኢትዮጵያ ቴሌቭዥን 1957 ዓም ( እንደ አውሮፓያን አቆጣጠር 1964 ዓም) አፍሪካ አንድነት ድርጅትን መመስረት አስታኮ ስራውን እንደጀመረ የድርጅቱ ድርሳን ያወሳል። እስከ 1977 ዓም ድረስ ጥቁር እና ነጭ ብቻ ሲታይ ቆይቶ ኢሰፓ ( ኢትዮጵያ ሰራተኞች ፓርቲ) ምስረታን ምክንያት አድርጎ በ 1977 ዓም   ባለቀለም ዝግጅቶቹን ማቅረብ ጀመረ።ከ ደርግ መውደቅ እና ኢህአዲግ ወደ ስልጣን መምጣት ጋር በተያያዘ ኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ሀገሪቱ ወጥ የሆነ አሰራር ካጡት እና ተገቢውን የጥራት ደረጃ ለመጠበቅ ፖለቲካው ዱላ ደጋግሞ ካረፈባቸው የመንግስት ድርጅቶች አንዱ ሆኖ ቆይቷል። 1987 ዓም እንደገና በአዋጅ ተመሰረተ ከተባለም በኋላ ድርጅቱ ሕዝብ የጋራ መድረክ የመሆን እድሉን እያጣ ገዢው ፓርቲ ብቸኛ ልሳን መሆኑን ቀጥሏል።
 
እዚህ አጭር ፅሁፍ መነሻ እና መድረሻ ቴሌቭዥን ጣቢያውን መንግስት ፕሮፓጋንዳ መሳርያነት ለቀባሪው ለማርዳት አይደለም። ዛሬ ጉዳይ ግን እዛ መለስ ቢያንስ የጥራት ደረጃው ባለፉት አስር አመታት ውስጥ እንኳን ለምን እየወረደ እንዲሄድ እንደተፈለገ አልገባህ ያለኝ ሚስጥር ስለሆነ ነው።ጎረቤቶቻችን እንደ ኬንያ የመሰሉ ሃገራት ቴሌቭዥን አገልግሎትን ግል ዘርፉ ሰጥተው አንፃራዊ መልኩ የተሻለ ደረጃ ላይ ሲሆኑ ኢትዮጵያ ''አንድ እናቱ '' በሆነው ኢቲቪ እስከ መቼ እውቀትም ሆነ ክህሎት ሽግግር ሰማንያ ሚልዮን ለሚበልጥ ሕዝብ እንደምታሸጋግር እንቆቅልሽ ነው።
አካባቢ ሃገራትን ሚድያ ደረጃ በተለይ የግል ዘርፉን ተሳትፎ ያየን እንደሆነ ለምሳሌ ኬንያ እና ኡጋንዳ አምስት በላይ የግል ቴሌቭዥን ጣብያዎች እና ሃምሳ የማያንሱ ግል ኤፌም ራድዮኖች ህዝባቸው አገልግሎት የሚሰጡባቸው እና ካለ ሳተላይት ዲሽ በርካታ ውጭ ሀገር ቴሌቭዥን ጣብያዎችን የማግኘት ዕድል ለህዝባቸው ያመቻቹ ሃገራት ሆነው እናገኛችዋለን። እዚህም የሀገራቸውን ሕዝብ ዘመኑ ሉላዊነት (globalaization) ውድድር ዓለም ብቁ ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት ላይ ናቸው። እዚህ ፅሁፍ መነሻ ቴሌቭዥን ጣብያን ጉዳይ እናንሳ እንጂ ጋዜጣ ስርጭት ብቻ ስንመለከት ኬንያው ''ደይሊ ኔሽን'' ጋዜጣ ቀን ሩብ ሚልዮን ቅጂ በላይ ለሀገሩ አንባቢ አሰራጭቶ የሚያድር የሆነበት ዋናው ሚስጥር የሚፅፋቸው ፅሁፎች ደረቅ ፕሮፓጋንዳን ሳይሆን ሙያዊ ክህሎትን የተላበሰ በመሆኑ ነው። እኛው ኢቲቪ ግን የነበሩት የመዝናኛ ፕሮግራሞቹ እንኳን ሕዝብ አይን እየራቃቸው ትውልዱን የማያንፁ እና ብስለትን ባልተላበሱ ጋዜጠኞቹ የግድ ተመልከቱኝ ማለቱ በግድ ሳሎን የገባ እንግዳ አስመስሎታል።
 
ትናንት ዛሬ አይደለም
 ድህረ-ገፅ እና በ ሳተላይት ዲሽ ሌላውን አለም ቴሌቭዥን ፕሮግራሞች በቀላሉ መከታተል በተቻለበት ዘመን ኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ፕሮግራም አቅራቢዎቹንም ሆነ ፕሮግራሞቹን ይዘት ደካማነት ለመተቸት ብዙም ሚድያ ጠበብት መሆንን አይጠይቅም። እዚህ ላይ ከላይ ለመግለፅ እንደሞከርኩት ቴሌቭዥን ጣብያው ፖለቲካ ፕሮፓጋንዳነቱ መለስ ስላሉት አቀራረብ ጥራት እና መዝናኛ ፕሮግራሞቹ ደረጃ ላይ ለማተኮር እንጂ ሚድያ ነፃነቱን ጉዳይ ፀሐይ የሞቀው እና ማንም አሌ የማይለው ጉዳይ ስለሆነ እዚህ አርእስት ላይ አላተኮርኩበትም ።የ መዝናኛ እና ትምርታዊ ፕሮግራሞች ላይ ግን በጣም ከመውረዱ የተነሳ እራሳቸው ጋዜጠኞቹ የሰሩትን ፕሮግራም መልሰው በማየት እንደማይደሰቱበት መገመት ጀምርያለሁ።

ትክክለኛ ሰው ትክክለኛ ቦታ
እኔአስተያየትአንድ የኢትዮጵያ ቴሌቭዥንሥራ አስክያጅሆኖ ለአንድ ቀን አይደለምለ አንዲትሰከንድ የተመደበ ኃላፊ የመጀመርያ ስራው ቢሆን የምመኘው በ'ስክሪን'ላይ የሚታዩትን አቅራቢዎችም ሆኑ ዜና አንባቢዎችደረጃቸውን በጠበቁ ለቴሌቭዥን ዕይታ የሚገጥሙ(screen fit personnel) መቀየርእንደሆነአልጠራጠርም።የማንኛውምሥራ የተሳካየሚሆነው በሳይንሳዊ የአስተዳደር መርህ(scintific manegment principle) መሰረት''ትክክለኛ ሰውበትክክለኛ ቦታማስቀመጥ'' የሚለውንመርህ መከተልነው። ተቀጣሪውኢህአዲግ ላይሆንይችላል ለሀገሩግን በጎመስራት የሚሻኢትዮጵያዊነቱ ግንብቸኛ መለክያውሊሆን በተገባውነበር።የ ኢትዮጵያቴሌቭዥን የኢህአዲግ '' እኔሰዎች'' የሚላቸውፖሊሲውን ወደውምይሁን ሳይወዱለ ኑሮብለው የተቀበሉመሰባሰብያ መሆኑንሃምሳ አመቱንሊደፍን ወራትበሚቆጥረው ቴሌቭዥንጣብያ ላይከ ትምህርትቤት ከተመረቁገና የወራት ዕድሜንያስቆጠሩ ወጣቶች''መፈንጫ''(ይህን ቃል በመጠቀሜ ይቅርታ እየጠየኩ) መሆኑንሲመለከቱ ብቻይገባዎታል። እርግጥነው ወጣትጋዜጠኞች ሆነውታምር የሚሰሩመኖራቸውን አልዘነጋምእነኛን ግን''ትክክለኛ ሰውበትክክለኛ ቦታማስቀመጥ'' በሚለውሳይንሳዊ የአስተዳደር መርህመሰረት ቆፍሮማግኘትን ይሻል።ለ ቴሌቭዥን ዕይታ የተፈጠረ ተክለሰውነት አለ።ለ ራድዮ ንባብ የተፈጠረ ድምፅ አለ።ተናግሮ ለማሳመን የተፈጠረ ሰው አለ።አውቆ ለማሳወቅ የተፈጠረ ሰው አለ። ኢትዮጵያ ቴሌቭዥን የምናየው ጋዜጠኝነት ግን ሁሉን አላሟላ ብሎኝ ተቸግርያለሁ።ማንም ሰው የሀገሩ ቴሌቭዥን ቢያንስ ደረጃውን ቢጠብቅለት፣ፕሮፓጋንዳው ባይሳካ አስተማሪ ፕሮግራሞቹ አዲሱን ትውልድ የማይጎረብጥ ብሎም የሚያቃና ዝግጅት እንዲቀርብ ይመኛል።እኔም ቢያንስ ነፃ ሚድያነቱ ባይሳካለት ለሀገር ውስጥም ሆነ ውጭ ተመልካች ደረጃውን የጠበቀ አቀራረብ እና ተደናቂ ጋዜጠኞችን ማየት ይናፍቀኛል። ሀገር ናት እና።ሙሉ በሙሉ 'እስክሪን' ዕይታ ደረጃ መውረድ እስከ አሿፊ የፕሮግራም መሪዎች እና ዝግጅቶች ማየት ግን ነገሩን አሰቃቂ ያደርገዋል።
 
ኢትዮጵያቴሌቭዥን ላይየምትመለከቱት ግንብዙ ያላነበቡ፣ሲናገሩ ነገርእጥር የሚልባቸው፣የተመልካቻቸውን ደረጃ፣ስነ ልቦናእና ባህልጨምሮ ያልተረዱወጣቶች እንደፈለጉሲሆን ሲታይበጣም አሳዛኝብቻ ሳይሆንአዲስ የሚወጣውትውልድ ላይየሚያደርሰውን አደጋ ሲመለከቱት የ ችግሩን ግዝፈት ያመላክታል
ኢትዮጵያቴሌቭዥን በዘመነ ኢህአዲግአንዳንዶች ቴሌቭዥንጣቢያውን በሀገር መውደድስሜት የመንግስትን ማለቅያየለሽ ''እኔንብቻ ደግፉ''ፈተና ዋጥአድርገው ስራቸውላይ ለማተኮርእና ትውልድለመቅረፅ ሞክረዋል።ነገር ግንኢህአዲግ እንደእርሱ ያልዘመረ፣እንደእርሱ ያላፏጨ ሁሉ ስራውንቀስ በቀስእንዲለቅ ማድረጉአይቀርም እናሁሉም እየተዎትዛሬ '' ጋኖች አለቁናምንቸቶች ጋንሆኑ'' የሚባልበትደረጃ ላይደረሰ። ሁሉንትተው ሀገራችንንእንጥቀም ብለውተሰርተው ከነበሩትፕሮግራሞች ውስጥእና ብዙተመልካች አፍርተውከነበሩት ውስጥ እነ'' ሃምሳ ሎሚ''እና ''አውደ-ሰብ'' የተሰኙትፕሮግራሞች ከተመልካች አይምሮአሁንም ድረስያልጠፉ የጋዜጠኞቹን ብቃትያስመሰከሩ ብርቅየዎችነበሩ። ዛሬየ እነኚህፕሮግራሞች ደብዛመጥፋት ብቻሳይሆን ጋዜጠኞቹድርጅቱን እንዴትትተው እንደሄዱየሚያውቅ ያውቀዋል።


ለማጠቃለል
ሀገር መቼም ወንዙ እና ሸንተረሩ ብቻ አይደለም። ሕዝብ እነ ተቋማቱ ሁሉ በአንድነት መገለጫዎቹ ናቸው- ለሀገር። ኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ሀገር ውስጥ ዜናን በትክክል ይንገረን ብለን በተለይ በውጭ የምንኖር ዜጎች ለመሞገት ከደከመን ቆየን።የያዘ እንደያዘው ስለምንረዳለት።ቢያንስ ግን በቀጥታም ሆነ ያለፉትን ፕሮግራሞቹን ድህረ-ገፅ እያስተላለፈ እስከሆነ ድረስ እናም ኢትዮጵያ ቴሌቭዥን እስከተባለ ድረስ ለምን ቢያንስ አቀራረብም ሆነ ጋዜጠኞቹ ጥራት ያሳፍረናል? ዜና አቅራቢዎቹም ሆኑ መቶ ሃያ ፕሮግራሙ ፖለቲካው ውጭ የሆኑ ሊዳስሳቸው የሚችሉት ብዙ ቁም ነገር የያዙ ፕሮግራሞችን በሰለ ጋዜጠኝነት ሙያ ያላቸውን ኮንትራትም ቢሆን እየቀጠረ ቢያሰራ ቢያንስ የታዳጊውን ወጣት ትውልድ በጎውን የማስተማር ድርሻውን ቢወጣ ምን አለበት? ቅርቡ እሁድ ላይ ባቀረበው ' መቶ ሃያ' ፕሮግራም አስተዋዋቂዎቹ ''ስፎግር ነው'' ወዘተ የሚሉ ቃላት እየተጠቀሙ እንደፈለጉ 'ሲፎልሉብን' ዛሬው ገና ልዩ ፕሮግራም ደግሞ ባህል አለባበሱ ሁሉ ተረሳ እና ጡቷ በታች ብቻ በለበሰች ወጣት እና ሀገራቸውን በሚገባ ባልተረዱ ፕሮግራም አቅራቢዎች ተመልካቹን ለዛ ባጣ ንግግር ሲያቆስሉት በማየቴ ይሄው የሰሚ ያለህ ለማለት ተገደድኩ። ''እንዳዘንን አያስቀረን'' አሉ አንድ ሽማግሌ የሰውን ሃዘን ካዳመጡ በኋላ አሁንም ''እንዳዘንን አያስቀረን''።

አበቃሁ

ጌታቸው

ኦስሎ

 

2 comments:

Anonymous said...

አቦ ተባረክ። የልቤን ሃሳብ ነው የገለጽክልኝ።ቆንጆ ገንቢ ሃሳብ ነው። ድርጅቱ ቢያንስ ትውልዱን አስተማሪ ፕሮግራም ቢኖረው ምናለ?

Anonymous said...

ETV ye wishet fabrika new.

Beynouna Village - Ethiopia (Video) ባለፈው ሳምንት የተመረቀው መተሃራ እምብርት ላይ የተገነባው አስደናቄው የበይኑና ሪዞርት መንደር (ቪድዮ)

Beynouna Village - Ethiopia (Video) ባለፈው ሳምንት የተመረቀው መተሐራ እምብርት ላይ የተገነባው አስደናቄው የበይኑና ሪዞርት መንደር (ቪድዮ)