የ አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የ ዛሬ 40 አመት ያነሳው የነበረው ጥያቄ የ መላው ኢትዮጵያን ጥያቄ ነበር። ዛሬ ግን ዩንቨርስቲው በ ኢህአዲግ ፖሊሲ መሰረት በ ብሔር ድርጅቶች እንዲደራጅ ሆኗል። ማንኛውም ተማሪ የ ብ አ ዲ ን ፣የ ህ ዋ ሀ ት ፣ የ ኦ ህ ዲ ድ ወዘተ አባል መሆን እና በ እነኚህ የ ብሔር ድርጅቶች ስብሰባ ላይ መገኘት ነገ ተመርቆ ሥራ ለመያዝ ቅድመ ሁኔታ ተደርጎ ለ ተማሪው የቀረበለት የመከፋፈል ድግስ ነው።
የ ቀድሞው የ አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ሲነሳ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያምን ማንሳት ተገቢ ነው።ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም በ 1960 ዎቹ የ ነበረው የ ለውጥ ትውልድ አካል ነበሩ።በ ኢትዮጵያ የ ሰብአዊ እና የ ፖለቲካ መድረክ በተለይ ባለፉት ሃያ አመታት ጉልህ ሚናቸው ታይቷል። የ ሕንዱ ፑንጃብ ዩንቨርሲቲ እና ከ አሜሪካው ክላርክ ዩንቨርስቲ የተመረቁት ፕሮፌሰር መስፍን በ አዲስ አበበ ዩንቨርስቲ የ ጆግራፊ ዲፓርትመንት መሪ፣የ ኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ መስራች እና ሊቀመንበር የ ቅንጅት መስራችም ነበሩ። በ 1939 ዓም የድቁና ማዕረግ መቀበላቸውን የሚናገሩም አሉ።
እስኪ ከ አራት አመት በፊት ቦስተን ላይ አድርገውት የነበረው ንግግር ዛሬ ላለነው ትውልድም ጠቃሚ ስለመሰለኝ ከ አቡጊዳ ዩቱብ ላይ ያገኘሁትን ላካፍላችሁ ወደድኩ። ንግግራቸው ያሉብንን የ ባህል ችግሮች፣እራሳችንን መጠየቅ ያለብንን ጥያቄ፣የ ኢትዮጵያን መሰረታዊ ችግሮች ይዳስሳል እና ጊዜ ወስደው እስከመጨረሻው ያዳምጡት።
No comments:
Post a Comment