ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Wednesday, January 16, 2013

ቤተክርስቲያንን ለሚሰቅሏት እና ለሚያሰቅሏት ወዮላቸው!

አዲስ አበባ ስብሰባ የተቀመጠው ቅዱስ ሲኖዶስ ጥር 6 እስከ ጥር 8/2005 ዓም ያደረገው ስብሰባ ዝርዝር ጉዳዩ ባይገለፅም ኢትዮጵያ ቴሌቭዥን አቡነ አብርሃም የተነበበው የውሳኔ መግለጫ ሕዝበ ክርስቲያንን ያሳዘነ ቤተክርስቲያንን ሌላ የመከራ እና የመከፋፈል ዘመን ፊቷ የደቀነ ሆኗል  ዛሬው ጥር 8/2005 ዓም 'ኢሳት ' አጭር ሞገድ ራድዮ ስርጭቱ ላይ 'ዘግይቶ የደረሰን ዜና' ብሎ ባቀረበው ዜና '' አቡነ አብርሃም የተነበበውም ሆነ ለጋዜጠኞች የተበተነው ወረቀት የደብዳቤ ቁጥር እና ማህተም የሌለው መሆኑ ታወቀ '' ካለ በኋላ ቀጠለና ''አቡነ ሕዝቅኤል አብዛኛው አባቶች ባላመኑበት ሁኔታ ማህተም አላሳርፍም ማለታቸው እና ስብሰባውን እረግጠው መውጣታቸውም ተስምቷል '' በማለት ዘግቧል

ቤተክርስቲያን ሕይወቷ መስቀል ላይ ነው። ለሚሰቅሏት እና ለሚያሰቅሏት ወዮላቸው።

ቤተክርስቲያንን ለሚሰቅሏት

ኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን እጅግ የሚያሳዝን ወቅት ላይ ነች። አስተዳደራዊ ጉዳይዋን ሳትፈታው፣የ ፓትርያርክ ጉዳይ፣ይህን ፓትሪያርክ ጉዳይ ሳትፈታው የዋልድባው እያለ ይሄው ዛሬ ደግሞ ሁለት አስርተ አመታት የተለያዩባት አባቶቿ በአለፈው ወር ዳላስ አሜሪካ እንደተመለከትነው አባቶች አንድ ላይ ኪዳን ሲያደርሱ ደስ ያለንን ያህል ዛሬ ዳግም አዘንን።መንግስት እርቀ ሰላሙ ሂደት ጀመሮ እስከ ዛሬዋ እለት ድረስ በግልፅ ያሳያቸው ጣልቃ ገብነት ስራዎች ነበሩ። እነዚህም ውስጥ ፕሬዝዳንት ግርማ 'ብፁዕ አቡነ መርቆርዮስን ወደመንበራቸው እንዲመለሱ ቢደረግ'' በሚል የፃፉትን ደብዳቤ 'መንግስት በቤተክርስቲያን ጉዳይ አይገባም' በሚል እንዲነሳ ማድረጉ፣ አስታራቂ ኮሚቴ አባላት በፀጥታ ኃይላት እንዲዋከቡ እና ተገፍተው ሀገር እንዲወጡ መደረጉ፣እርቀ ሰላሙ እየተካሂያደ ' ፓትርያርክ አስመራጭ ኮሚቴ' እንዲዋቀር በመግፋት፣በመጨረሻም ጥር 6 እስከ 8 በተደረገው ቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ አባቶችን በማስፈራራት አዲስ ፓትርያርክ ምርጫው እንዲከወን በመጣደፍ ላይ መሆኑ ሁሉ ጉልህ ማስረጃዎች ነበሩ እናም ቤተክርስቲያንን እየሰቀላት ያለው መንግስት ቤተክርስቲያንን ቁስል ከማድረቅ ይልቅ ሌላ መለያየት እነሆ አዲስ ምዕራፍ ከፈተባት።

ቤተክርስቲያንን ለሚያሰቅሏት

''እናንተንጳጳሳት አድርጎ ለሾመበት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ እኔ በኋላ ለመንጋይቱ የማይራሩ ነጣቂዎች ተኩላዎች እንደሚመጡ እኔ አውቃለሁ '' ሐዋርያት ሥራ 2028-30

ቤተክርስቲያን ጉዳይ አባቶች የመምራት፣የማስተማር እና እስከ መስዋዕትነት የሚጠይቅ ጉዳይ ቢኖር ግንባር ቀደምትነት እንዲቆሙ ለአባቶቻችን አደራ መሰጠቱን መፅሐፍ ቅዱስ የሚያረጋግጥልን እውነታ ነው።ዛሬ ግን ቤተክርስቲያንን መስቀል ባይችሉ በመከራ መስቀል ላይ ሊሰቅላት ከሚታትሩ ጋር ጮማ እየቆረጡ የሚያሰቅሏት አንዳንድ አባቶች አልጠፉም። ''በአንድ ገበታ ተቀምጠው ሐሰት ይናገራሉ'' የተባለለት ዘመንን ደረስንበት ማለት ይሆን? ኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ታላቁ ገዳም ዋልድባ እየታመሰ ምንድነው የሆነው? ብለው ችግሩን ማዳመጥም ሆነ መፍትሄው ላይ ታች ማለት ያለባቸው አባቶች አዲስ አበባ ላይ ሲንሸራሸሩ መታየታቸው  ሌላው ቀርቶ የገዳሙን ችግር እንወያይ ብለው ምእመናንን ለማናገር መንግስት ሹመኞችን ግልምጫ እና እስር የፈሩ መሆናቸው፣ ይህ ሁሉ ባይሆንላቸው ባለፈው ቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ አጀንዳ አስይዞ ለመወያየት ቅምጥል መንግስት ሹማምንትን ፊት የሚመለከቱ አንዳንድ አባቶች  ቤተክርስቲያንን ከሚያሳቅሏት ወገን ናቸው።

ዛሬ ከወደ አዲስ አበባ የተሰማው ወሬ ቤተክርስቲያንን የሰቀሏት እና የሚያሰቅሏት ተባብረው ላለፉት ሁለት አስርተ-አመታት የነበረባትን ሲኖዶስ ክፍፍል ሌላ አዲስ ምዕራፍ ሊያራዝሙባት ሽር ጉድ ማለታቸውን ነው።

ጥያቄው እኛ ከየት ወገን ነን? ከሚሰቅሉት ወይስ ከሚያሰቅሉት?

ቤተክርስቲያን ችግር ውስጣችን የደማ ሁሉ እና በሚሰራው ማባርያ የሌለው ጥፋት ያዘንን ሁሉ ዝምታችን ከከንፈር መምጠጥ ባላለፈ ተግባር ላይ መሆናችን ከሚሰቅሏት ወይንም ከሚያሰቅሏት ወገን ላለመሆናችን ከቶ ምን አይነት መረጃ ይኖረን ይሆን? ኑሮዬ፣ጨርቄን፣ ወዘተ እያልን በመስቀል አልያም በማሰቀል ላይ መሆናችንን ልብ ብለነው ይሆን?ጌታችን ቀራንዮ ሲሰቀል ሰፍነግ ያቀበሉም ሆኑ ከመስቀሉ ስር ገበጣ የሚጫወቱ- ሁለቱም በሰቃይነትም ሆነ አሰቃይነት ተፈርጀዋል።ቤተክርስቲያንን ለሚሰቅሏት እና ለሚያሰቅሏት ወዮላቸው! ዝምታ የሚሰበርበት ''የቤተክርስትያኔ ጉዳይ ያገባኛል'' የምንልበት እውነተኛው ጊዜ ነው እና 


ይቆየን

ጌታቸው
ኦስሎ 

2 comments:

Anonymous said...

yemiyasleqs zemen new.

Anonymous said...

dingl mariam erijin

ለፕሮፌሰር መራር፣ልደቱ፣ጀዋርና ኢንጅነር ይልቃል ዘፈን ይህችን ዜማ እንምረጥላቸው።

በቅድምያ ስለ አራቱም የመግቢያ ማስታወሻና ወቅታዊ ሁኔታቸው። አራቱም ከመስከረም በኋላ መንግስት የለም ብለው ኢትዮጵያን ለእርስ በርስ ጦርነት ሊነክሯት ሞክረዋል።ዝርዝሩን፣ከእነማን ጋር መክረው እንደነበር፣ለኢትዮጵያ ደግሰው...