Friday, January 11, 2013

የ አገልግሎት ጥራት ¨ሎጎ¨(አርማ) በመቀያየር ይመጣልን? ቴሌ ¨ሎጎውን¨ለ ሶስተኛ ጊዜ ሊቀይር ነው

 







 የ ሚቀጥለው ¨ሎጎ¨ ምን ይሆን  ( ? )


የ ኢትዮዽያ ቴሌ ኮምዩኒኬሽን ኮርፖሬሽን ስራውን ¨የንፋስ ስልክ¨በሚል ከ መቶ አመታት በፊት በ ዳግማዊ ሚኒሊክ ዘመን ይጀምር እንጂ በ ዘመናዊ መልክ በ 1952እአአቆጣጠር በ አዋጅ ቁጥር 131/52 ¨በ ፖስታ፣ስልክና ቴሌግራፍ ሚኒስቴር¨ ስር ሆኖ ተመስረተ።

በ ዘመነ ደርግ ''የ ኢትዮዽያ ቴሌኮሙዩኒከሽን ባለስልጣን'' በማለት እ አ አቆጣጠር በ 1981ዓም አዋጅ ታወጀለት።

ኢህአዲግ በትረ ስልጣኑን ሲይዝ ስሙን ¨የ ኢትዮጵያ ቴሌኮሙዩኒከሽን ኮርፖረሽን¨ብሎ አሁንም እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር በ 1996 ዓም ሰየመው። በ ዘመነ ኢህአዲግ -ቴሌ መንግስት ያመነውም ሆነ ያላመነውም በ ቢልዮን የሚቆጠር ገንዘብ የተዘረፈበት፣በ ሺህ የ ሚቆጠሩ ሰራተኞች በ ግፍ የተባረሩበት፣አንድ ጊዜ ከቻይና ሌላ ጊዜ ለፈረንሳይ ተብሎ ወጥ አሰራር ያጣ ድርጅት መሆኑን ብዙዎች ይስማማሉ።

በቅርቡ የ ፈረንሳዩ ¨ፍራንስ ቴሌኮም¨ለ አስተዳደር ማሻሻያ ሥራ የ ሰላሳ ሚልዮን ኢሮ ክፍያ ከተፈፀመ በኃላ የ ኮንትራት ጊዜውን በያዝነው ወር ሲፈጽምና ሲሰናበት እንደ አቶ ደብረጽዮን(የድርጅቱ የ ቦርድ ሰብሳቢ አሁን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር) አገላለጽ ¨የተፈለገው የ ጥራት ደረጃ አልተገኘም¨ ተብሎ እንኳ ለተከፈለው ገንዘብ ተጠያቂ ያልተገኘበት መስርያቤት ነው።

ከሁሉም የሚገርመው ለ ሞባይል ኔት ዎርክ የተገጠመለት የመገናኛ አንቴናዎች ሲበላሹ በ ሌላ ካምፓኒ ስሪት የሆኑ መሳርያዎች ግዥ እንዳይፈጽም በ አለም ላይ ካለ ከ ማንኛውም ሌላ መሳርያ ጋር የማይገጥም መሳርያ ከ ¨ዘድ ቲ ኢ¨ የ ቻይናው ኩባንያ ጋር የ 1.5 ቢልዮን ዶላር ውል ፈጽሞ ማስተከሉ ነው። ይህንንም አሰራር ብዙ የድርጅቱ ባለሙያዎች ቢቃወሙም ሰሚ አላገኙም።

ዛሬ ለ ፅሁፌ መነሻ የሆነኝ ግን የ ''ሎጎ'' መቀያየር ሂደቱ ስላስገረመኝ ነው። የ ቴሌ ባለስልጣናት(የ ኢህአዲግ ከፍተኛ ባለስልጣናት) ከ ንጉሱ ጀምሮ የነበረው አንበሳው ከበሮ ሲመታ የሚያሳየውንና በቀላሉ ከሰው አዕምሮ የማይጠፋውን ¨ሎጎ¨(አርማ)በ ሌላ ከቀየሩት ገና አመታት ሳይቆጠር አሁን ለ ሶስተኛ ጊዜ ደግሞ በ ሌላ ሊቀየር መሆኑን ከ ወደ አዲስ አበባ የተሰማው ዜና ያወሳል ። ለ መሆኑ ያደጉት ሃገሮች የ ንግድ ድርጅቶቻቸውን ¨ሎጎ¨(አርማ) መንግስታት ሲቀያየሩ የማይለውጡት ኩባንያዎች ትውልድ ተሻጋሪ ለማድረግ መሆኑን የ ቴሌ ባልስልጣናት ¨የንግድ ህግ¨ሲማሩ አስተማሪው አልነገራቸው ይሆን? ሌላው ደግሞ በ እያንዳንዱ የ ''ሎጎ'' ቅየራ የሚወጣው ወጪ ሆድ ይፍጀው። ከ ድርጅቱ ደብዳቤ መፃፍያ ወረቀት ጀምሮ እስከ በ ብዙ መቶ የሚቆጠሩ መኪናዎቹ ላይ የሚለጠፍ በመሆኑ በገንዘብ የሚጠይቀው ወጪ ቀላል አይሆንም።በነገራችን ላይ የ አሁኑ ''ሎጎ'' የሚቀየረው ተመሳሳይ ምልክት በ አውሮፓ ተገኘ ተብሎ ነው። ቀድሞ ተመሳሳይ አለመኖሩን ማጣራት የአባት ነው። የነበረ ከ ድርጅቱ በጡረታ ከተሸኙት ጀምሮ የድርጅቱን አገልግሎት በ አለም አቀፍ ደርጃ በ አጋር  ካምፓኒዎች ዘንድ የሚታወቅበት የቀደመ ''ሎጎ'' ቢመለስለት ብልህነት ነበር። የ አገልግሎት ጥራት ¨ሎጎ¨(አርማ) በመቀያየር እና ልምድ ያላቸውን ሰራተኞች በማባረር አይመጣምእና።

አበቃሁ
ጌታቸው
ኦስሎ

No comments:

የመስቀል ደመራ በዓል በንግስት ዕሌኒ ሀገር በግሪክ ቅዳሜ መስከረም 16፣2019 ዓም በከፍተኛ ድምቀት ተከብሮ ዋለ።በግሪክ የምትገንኘው የአቴንስ ኪዳነምሕረት ቤተክርስቲያን ምእመናን ለቅዱስ ሲኖዶስ አቤቱታቸውን ደግመው አቀረቡ።

======== ልዩ ሪፖርታዥ ======== በእዚህ ርዕስ ስር የሚከተሉትን ንዑስ ርዕሶች ያገኛሉ።እነርሱም ፡  የመስቀል ደመራ ለምን ይከበራል? ግማደ መስቀሉ  ወደ  ኢትዮጵያ እንዴት መጣ? የዘንድሮው የመስቀል ደመራ በዓል...