ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Saturday, June 13, 2020

ማንም ሊሰራ የማይችልባት ሌሊት ሳትመጣ አሁኑኑ የኢ/ኦ/ተ/ ቤ/ክርስቲያን የ24 ሰዓት የቴሌቪዥን የቀጥታ ሥርጭትና የስቱዲዮ ግንባታ ግዴታዎን ይወጡ።

ከጊዜው ካልተማርን ከማን እንማራለን? 

ይህ ጊዜ ከወንጌል በላይ በራሱ ሰባኪ ነው።ዓለም ምንም ዓይነት ኃይል ከእንቅስቃሴዋ የማይገታት መስላ ትታይ ነበር።የአሜሪካ፣የአውሮፓ እና የሩቅ ምስራቅ የሽርክና ገበያዎች (''ስቶክ ኤክስቼንጅ'') ለአንድ ቀን የሚገታቸው ያለ አይመስላቸውም ነበር።የምድራችን ግዙፍ የመዝናኛ ቦታዎች ከአስረሽ ምችው ለአፍታም የሚያቆማቸው ነገር ይመጣል ብለው አላሰቡም።በሺዎች የሚቆጠሩ አይሮፕላኖች በሰማይ ላይ ከመብረር የሚገታ እና ዝናብ እንደመታት ዶሮ መሬት ይዘው የሚቆዩ አልመሰላቸውም ነበር።ሁሉም ግን በአንድ ምሽት ቆመ።ደግሞ ሁሉም የቆሙት በግዙፍ በሚያስፈራ እና አካላዊ ቁመናው በሚያስደነገጥ አካል አይደለም።በዓይን በማይታይ እጅግ ረቂቅ በሆነ ፈጣሪው ብቻ እንዴት እንደተፈጠረው በሚያውቀው ረቂቅ ኮሮና በተባለ ቫይረስ ቆመ።ኃያላን የተባሉት ከምስኪኖቹ ጋር እኩል አቆማቸው።በገንዘብ ኃይላቸው የተኩራሩት ገንዘባቸው ከረቂቁ ቫይረስ የማያስጥል ሆነ።ካለፈ ታሪክ ይልቅ አሁን እየሆነ ያለው በራሱ ከወንጌሉ በላይ አስተማሪ ነው።

''ማንም ሊሰራ የማይችልባት ሌሊት ትመጣለች'' ዮሐንስ ወንጌል 9፣4

ጊዜው አስተማሪነቱ የመስርያ ጊዜ ነገ ሳይሆን አሁን መሆኑን ነው።ጌታችን መድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ዮሐንስ ወንጌል 9፣4 ላይ ''ማንም ሊሰራ የማይችልባት ሌሊት ትመጣለች'' በማለት ሐዋርያትን አስጠንቅቆ ነበር።ከእርሱ ጋር እያሉ ቀላል የመሰላቸው ጉዳይ ሁሉ እርሱ በአይሁድ እጅ ከተያዘባት ሐሙስ ምሽት እስከ ትንሣኤው ድረስ ያሉ ምሽቶች ክርስቶስን አውቀዋለሁ፣ከእርሱ ጋር ነበርኩ ማለት በአይሁድ ዘንድ ሞት የምያስከትል ነበር። ጊዜው ከወንጌሉ በላይ አስተማሪነቱ የሚጎላው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተናገረውን በእዚህ ዓመት እንዴት ያቺ የማይቻልባት ምሽት እንደመጣች ስንመለከት ነው።ቅዳሴ በፈለጉ ሰዓት ሄዶ ማስቀደስ፣ማኅሌት መቆሙ፣መቁረቡ እና ተሰብስቦ በአንድነት ወንጌል መማሩ ሁሉ  የማይቻልባት ሌሊት ላይ ነን።

አሁንም ይህንን ዕድል እንዳናጣው እንፍጠን!

አሁንም ባለው መንገድ ለመጠቀም መዘግየት ሌላ ሊሰሩ የማይችሉባት ሌሊት እንዳትመጣ መንገድ ይከፍታል።ሕዝበ ክርስቲያኑ በአሁኑ ጊዜ በኮሮና ወረርሽኝ ሳቢያ ወደ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ሄዶ የመማር፣የማስቀደስ እና በአጠቃላይ ከቤተክርስቲያን በአካል ቀርቦ ማግኘት ያለበትን መንፈሳዊ አገልግሎት ሁሉ ለማግኘት የማይችልበት ጊዜ ላይ ነን።ለእዚህ ደግሞ በአማራጭነት የተወሰደው የዘመናዊ መገናኛ መጠቀም ነው።ከዘመናዊው መገናኛ ውስጥ ደግሞ ቴሌቭዥን ለብዙ ሕዝብ የመድረስ ዕድል አለው።አሁን ባለንበት ዘመን የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን  ከሐምሳ ሚልዮን በላይ ምዕመን ይዛ ከሱዳን እስከ አሜሪካ እና አውስትራሊያ ድረስ በመላው ዓለም ተሰራጭታ ከ24 ሰዓታት ያነሰ ጊዜ የሚያስተላልፍ ቴሌቭዥን ሊኖራት አይችልም።

ስለሆነም አንዳንዶች ዛሬ ነገ እያሉ፣የቀሩት መረጃው ስለሌላቸው ይህንን የማኅበረ ቅዱሳንን ቴሌቪዥን የቀጥታ ሥርጭትና የስቱዲዮ ግንባታ በሚገባ ደረጃ አልደገፉ ከሆነ ይፍጠኑ።መስበክ ባይችሉ የሚሰብኩት እንዲሰብኩ በማድረግም ፅድቅ አለ።እናቶቻችን ቤተ መቅደስ ገብተው ባይቀድሱ፣የአብነት ተማሪዎች የሚመገቡትን በማዘጋጀት፣ካህናቱን ፈትለው በማልበስ ፅድቅን አትርፈዋል።እርስዎ ለጥቂት ደቂቅዎች ጊዜ ሰጥተው አነሰ በዛ ሳይሉ አሁኑኑ ድጋፍዎን ያድርጉ።ይህ ቁልፍ ጉዳይ ነው።ነገ ሊሰሩባት የማይችሉባት ሌሊት ሳትመጣ አሁን ግዴታዎን ይወጡ።ላልሰሙ ይንገሩ። 

እንዴት? በየት በኩል  ይደግፉ?

ከእዚህ በታች ካሉት አራት  አማራጮች ለመደገፍ በሚመቸዎት በአንዱ ይደግፉ 

1) በጎፈንድሚ

ወይንም  

2) በቀጥታ ለእዚሁ አገልግሎት በሚውሉት በእነኝህ የባንክ ሂሳቦች በማስገባት  

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፡1000010822657
ወጋገን ባንክ ፡ 395950/CO1/27
አቢሲኒያ ባንክ ፡ 4753388
ዳሸን ባንክ ፡ 0088872166011
አዋሽ ባንክ : 01304800017700

ወይንም 

3) ሰኔ 21 በቤትዎ በተዘጋጀ ሐዊረ ሕይወት ጉባኤ ለመሳተፍ ጥቂት በመስጠት ለረጅሙ ስጦታ የሚዘጋጁበት ዕድልም ተመቻችቷል።
ይህንን ሊንክ ከፍተው ይጠቀሙ 

ወይንም 

4) በፔይ ፓል ለመክፈል ይህንን ሊንክ ይክፈቱ 

የፔይ ፓሉ ሊንክ ከማኅበረ ቅዱሳን የአውሮፓ ማዕከል ሊንክ (https://eu.eotcmk.org/site/) ላይ የቴሌቭዥን እና ራድዮ አገልግሎት ከሚለው ሊንክ ''ዶኔት'' የሚለውን ሲጫኑ ያገኙታል።

+++++++++++++++++++++++++++++
የድርሻችንን እንወጣ ቪድዮ ማስታወቂያ ሊንክ 
ምንጭ = ከማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቭዥን ዩቱብ የተወሰደ 




No comments: