ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Tuesday, June 30, 2020

ሰበር ዜና -የሎሬንት ፀጋዬ ገብረመድህን ቤተሰብ ድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴን አስከሬን ከቤተሰቦቻቸው ለመንጠቅ የሞከረው ጀዋር እና የድርጊቱ ፈፃሚዎች 35 ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል።


ድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ 

(ጉዳያችን ዜና)

በጀዋር እና ግብረአበሮቹ ተግባር በርካታ የአምቦ፣የኦሮምያ እና ሌላውን ኢትዮጵያዊ አበሳጭቷል። 

ከእናቱ ወ/ሮ ጉደቱ ሆራ እና ከአባቱ አቶ ሁንዴሳ ቦንሳ ከአዲስ አበባ በስተ ምዕራብ 135 ኪሎሜትር ርቀት በምትገኘው በአምቦ ከተማ የተወለደው ድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴ ትናንት ሰኔ 23/2012 ዓም በአዲስ አበባ ገላን ኮንደሚንየም አካባቢ ባልታወቁ ሰዎች መኪናው ውስጥ እያለ በተተኮሰ ጥይት በሚያሳዝን መልኩ ህይወቱ አልፏል።የድምፃዊው ሕይወት በእንዲህ ዓይነት መልኩ መቀጠፉ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጪ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን ክፉኛ አሳዝኗል።ጉዳያችንም በድምፃዊ ሃጫሉ ሞት ላዘኑ ቤተሰቦቹ መፅናናትን ለሀጫሉም ዕረፍተ ነፍስን ትመኛለች።ድምፃዊ ሃጫሉ በኢትዮጵያ የስነ ፅሁፍ ታሪክ ትልቅ አሻራ ያስቀመጡትየአምቦው ተወላጅ  እና የሀገር ወዳዱ ሎሬንት ፀጋዬ ገብረመድህን ቤተሰቦች ጋር በአያቱ በኩል እንደሚገናኝ ከቤተሰቡ መረዳቱን አርቲስቱ በአንድ ወቅት በሰጠው መግለጫ ላይ ገልጦ እንደነበር ጉዳያችን ታስታውሳለች።

ይህ በእንዲህ እያለ ዛሬ ሰኔ 23/2012 ዓም የሃጫሉ ሁንዴሳን አስከሬን ቤተሰቦቹ ይዘው ወደ አምቦ በበርካታ ሕዝብ ታጅበው እየሄዱ ሳለ የቀድሞው የኦሮምያ ኔትወርክ ሚድያ ሥራ አስኪያጅ እና የአሁኑ የኦሮሞ ፈድራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) አባል ከጥቂት ግብረ አበሮቻቸው ጋር በመሆን አስከሬኑን ከቤተሰቦቹ ለመንጠቅ ሙከራ ማድረጋቸው እና በምላሹም ከፌድራል ፖሊስ ጋር ግጭት መፈጠሩን ለማወቅ ተችሏል። በኢትዮጵያ ባሕል መሰረት አንድ ሰው ከእዚህ ዓለም በሞት ሲለይ አይደለም በሀገር ውስጥ ሆኖ በውጪ ሀገርም ቢኖር  አቅሙ እንደፈቀደ በትውልድ ቦታው መቀበር የነበረ ልማድ እና ባሕል ነው።የድምፃዊ ሃጫሉ  ቤተሰቦችም ይህንኑ ለማድረግ ወደ አምቦ መንገድ እንደጀመሩ ነው ጀዋር እና ግብረአበሮቹ አስከሬኑን ነጥቀው በመኪና በመጫን ህዝቡ የአስከሬን ዝርፍያ ያለውን ተግባር የፈፀሙት።

በእዚሁ የአስከሬን ነጠቃ ሙከራ ሳብያ በተከተሉ ሶስት ፍንዳታዎች መሰማታቸውን እና ቁጥራቸው እስካሁን ያልተገለጠ ኢትዮጵያውያን መጎዳታቸው ተሰምቷል።ከሞቱት ውስጥ ያፈነዱትን ጨምሮ ጉዳት ማድረሱ ነው የተገለጠው።ይህንኑ ተከትሎ የድምፃዊ ሃጫሉ አስከሬን ወደ አዲስ አበባ ለመመለስ መገደዱን እና በኃላ በኤሊኮፍተር ወደ ትውልድ ከተማው አምቦ መወሰዱን ለማወቅ ተችሏል።ይህ በእንዲህ እያለ መንግስት ድምፃዊው ከተገደለበት ሰዓት ጀምሮ ማን እንደፈፀመው ሳይገለጥ የእርስ በርስ ግጭት እና ጠብ የሚፈጥር ቅስቀሳ ሲያደርግ የነበረው የኦሮምያ ሚድያ ኔትወርክ በፌድራል ፖሊስ ቁጥጥር ስር መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።በሌላ በኩል ከጀዋር ጋር አቶ በቀለ ገርባም በቁጥጥር ስር መዋላቸው የተሰማ ሲሆን በተለይ አቶ ጀዋርን በቁጥጥር ስር ለማዋል በተደረገው ተግባር ላይ የአቶ ጀዋር ጠባቂዎች በሙሉ ትጥቅ እንዲፈቱ የተደረገ ሲሆን በሂደቱ ላይ አንድ ፖሊስ ህይወቱን ማጣቱ ነው የተሰማው።

በነገራችን ላይ ድምፃዊ ሃጫሉ በተለያዩ ጊዜ በሰጣቸው መግለጫዎች የብዙዎችን ትኩረት የሳበ አርቲስት ነው።ከእነኝህ መግለጫዎቹ ውስጥ - ''ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው፣አይደለም የቴዲ አፍሮን የማሊንም ሙዚቃ እሰማለሁ፣''በማለት ከሚድያ ለተነሱለት ጥያቄዎች የመለሳቸውን ምላሾች አሁን ድረስ የምያስታውሱለት ብዙዎች ናቸው።በአንድ ወቅት ድምፃዊው፣ የጀዋርን እና በቀለ ገርባን አና አንዳንድ የኦሮሞ ዘውግ ፖለቲከኞች ከህወሓት ጋር የሚያደርጉትን መሞዳሞድ በግልጥ የወቀሰበት ጊዜም ነበር።ሌላ ጊዜ ደግሞ በጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አህመድ ላይ በአንድ ወቅት ''ኦሮሞ አይደለም'' የሚል የሐሰት ዘመቻ ለከፈቱትም የሰጠው ምላሽ ''ዓቢይን አውቀዋለሁ ከሁላችንም ያልተለየ ኦሮሞ ነው።ዓቢይ ሀገር እየመራ ነው።ዛሬ በእርሱ ላይ የሚደረግ የስም ማጥፋት ዘመቻ ነገ ሌላ የኦሮሞ ሰው ስልጣን ላይ ቢመጣም የሚቀር አይደለም።ስለሆነም ማናቸውም በጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ ላይ የሚደረገውን የስም ማጥፋት ዘመቻ አንቀበልም።'' ማለቱ ይታወሳል።

የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ተማሪ እያለ ለአምስት ዓመታት በቀድሞው የህወሓት/ኢህአዴግ ስርዓት ታስሮ የነበረው ድምፃዊው ሃጫሉ የሚሰማውን ፊት ለፊት በመግለጥ ይታወቃል።በ36 ዓመቱ ሕይወቱን ያጣው ድምፃዊ ሃጫሉ ባለትዳር እና የሶስት ልጆች አባት እንደነበር ለማወቅ ተችሏል።ለሀጫሉ ቤተሰብ መፅናናትን፣ለእርሱም እረፍተ ነፍስ ይስጥልን።




 


No comments:

ህወሓት ሰሜን ወሎ ራያን ወርሮ የገጠር ወረዳዎችን እየዘረፈ ነው። ህዝብ ሲዘረፍ እና በአስር ሺዎች ሲፈናቀሉ የመንግስት የፖለቲካም ሆነ የወታደራዊው አመራሮች ዝምታቸው ከተጠያቂነት አያድናቸውም።

በሰሞኑ የህወሓት ወረራ ቆቦ ተፈናቅለው የገቡ የሰሜን ወሎ ተፈናቃዮች  በከፊል ፎቶ፡ ቢቢሲ ሚያዝያ 20፣2024 እኤአ ''ቅጥ አምባሩ የጠፋው'' የፕሪቶርያው ውል   ''ስኩዌር ዋን&#...