Sunday, August 6, 2017

ሃዘን ጎሳ የለውም።ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው።አባታቸውን፣እናታቸውን ወይንም ልጆቻቸው ከተገደሉባቸው ጋር አብረን እንዘን።

ጉዳያችን/Gudayachn 

ኢትዮጵያ ላለፉት አርባ ዓመታት የፖለቲካ ስልጣን  ለማስጠበቅ ሲባል ብቻ የመብት ጥያቄ ያነሱ ሁሉ በአደባባይ ሲገደሉ ኖረዋል።በህወሓት የሚመራው መንግስት ስልጣን ላይ ከወጣ ጀምሮ የኢትዮጵያውያን እንባ አልቆመም።በተለይ ባለፉት 10 ወሮች ውስጥ በአስር ሺዎች ወደ እስር ቤት ሲጋዙ ብዙ መቶዎች (ቁጥሩ ከእዚህም እንደሚልቅ ይታመትናል) በአደባባይ በስርዓቱ ወታደሮች ተገድለዋል።በጎንደር፣ነቀምት፣አምቦ፣ባህርዳር፣አዲስ አበባ፣ኮንሶ፣ቴፒ እና ሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎች በመቶ ሺዎች የሚቆጠር ቤተሰብ ሃዘን ላይ ነው።

ነገ ነሐሴ 1፣2009 ዓም በባህርዳር ከተማ ልክ የዛሬ ዓመት ባዶ እጃቸውን የመብት ጥያቄ ባነሱ ነዋሪዎች ላይ ጨካኞቹ የስርዓቱ ወታደሮች እና በጎሳ ስሜት እራሳቸውን  የተበተቡ ታጣቂዎች ከኮንደምንየም ቤቶች መስኮቶች ላይ ሁሉ በማድፈጥ በ60 ደቂቃዎች ውስጥ ከ50 ያላነሱ የከተማው ነዋሪዎች እንደቅጠል የረገፉበት ቀን ይታሰባል።በባህር ዳር ከተማ ሥራ የማቆም ጥሪ የተጠራ ሲሆን ጉዳዩ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊንም የሚመለከት ጉዳይ መሆኑ እሙን ነው።
ሃዘን ጎሳ የለውም።ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው።አባታቸውን፣እናታቸውን ወይንም ልጆቻቸው ከተገደሉባቸው ጋር አብረን እንዘን።በኢትዮጵያ የትኛውም ክፍል በግፍ በአገዛዙ ሕይወታቸው የተቀጠፈውን ሰማዕታት እንዘክራቸው።

ቪድዮ:  በፕሮፌሰር አሽናፊ ከበደ “እረኛው” የተሰኘው በመሳርያ ብቻ የተቀናበረ ሙዚቃ። 
                

ጉዳያችን GUDAYACHN www.gudayachn.com

No comments:

የመስቀል ደመራ በዓል በንግስት ዕሌኒ ሀገር በግሪክ ቅዳሜ መስከረም 16፣2019 ዓም በከፍተኛ ድምቀት ተከብሮ ዋለ።በግሪክ የምትገንኘው የአቴንስ ኪዳነምሕረት ቤተክርስቲያን ምእመናን ለቅዱስ ሲኖዶስ አቤቱታቸውን ደግመው አቀረቡ።

======== ልዩ ሪፖርታዥ ======== በእዚህ ርዕስ ስር የሚከተሉትን ንዑስ ርዕሶች ያገኛሉ።እነርሱም ፡  የመስቀል ደመራ ለምን ይከበራል? ግማደ መስቀሉ  ወደ  ኢትዮጵያ እንዴት መጣ? የዘንድሮው የመስቀል ደመራ በዓል...