ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Monday, August 21, 2017

ማኅበረ ቅዱሳን በሚቀጥለው ሳምንት መጨረሻ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ላይ ያተኮረ በዓይነቱ ልዩ እና የመጀመርያ ዓለም አቀፍ የጥናት ጉባኤ ስዊድን ውስጥ ያካሂዳል።



ጉዳያችን / Gudayachn ዜና 

በጉባኤው ላይ የሚሳተፉ ኢትዮጵያውያን እና የውጭ ሀገር ተወላጅ ምሁራን ከአዲስ አበባ ዩንቨሲቲ ፣ ካምብሪጅ ዩንቨርሲቲ እንግዝ፣ሉንድ ዩንቨርሲቲ ስዊድን፣ስታቫንገር ዩንቨርሲቲ ኖርዌይ፣ሴንት ፒተርስበርግ ዩንቨርሲቲ ሩስያን ጨምሮ የሚመጡ ሲሆን በተለያዩ ርዕሶች የሚያቀርቡት የጥናት ወረቀቶች ከፍተኛ ዋጋ የሚሰጣቸው መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ስር የበጎ ፍቃድ አገልጋይ ምዕመናን የተመሰረተው እና ከሁለት አስር አመታት በላይ ለቤተ ክርስቲያን ሁለንተናዊ እድገት እየተጋ የሚገኘው ማኅበረ  ቅዱሳን ነሐሴ 27 እና 28/2009 ዓም (ሴፕቴምበር 2 እና 3/2017 ዓም ከሉንድ ዩንቨርሲቲ ጋር በተባበር በስዊድን፣ሉንድ ከተማ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን አስተዋፅኦ ለዓለም ላይ ያተኮረ ዓለም አቀፍ ጉባኤ ያካሂዳል።ማኅበረ ቅዱሳን  በዋናው ማዕከሉ ስር የጥናት እና ምርምር ማዕከል የተሰኘ ክፍል ያለው ሲሆን ይህ ክፍል በእየጊዜው ከኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ጋር ተያያዥነት ያላቸው በርካታ የጥናት እና ምርምር ስራዎች የተሰሩበት ሲሆን የምርምር ውጤቶቹ በማዕከሉ አዳራሽ በሚዘጋጁ ጉባኤዎች እያቀረበ በምሁራን ሃሳብ እንዲዳብሩ ማድረጉ ይታወቃል።የማኅበረ ቅዱሳን ጥናት እና ርምር  ማዕከል በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ እና በተለያዩ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ውስጥ በምርምር ሥራ የሚያገለግሉ ምሁራንን ያካተተ የእራሱ የሆነ የአማካሪ ቦርድ እና  ኢድቶርያል ቦርድ ኮሚቴ ያለው ሲሆን ክፍሉ በእየወሩ የተለያዩ የምርምር ውጤቶች የሚቀርቡበት የህዝብ ጉባኤ አለው።

በዋናው ማዕከል ስር የሚገኘው የማኅበረ ቅዱሳን የአውሮፓ ማዕከል የጥናት እና ምርምር ክፍል የተዘጋጀው በመጪው ሳምንት መጨረሻ በአማርኛ እና እንግሊዝኛ ቋንቋዎች የሚደረገው የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ለዓለም ያበረከተቻቸው ቅርሶች ላይ የሚያተኩረው ጉባኤ  የሚሳተፉ ኢትዮጵያውያን እና የውጭ ሀገር ተወላጅ  ምሁራን ከአዲስ አበባ ዩንቨሲቲ ፣ ካምብሪጅ ዩንቨርሲቲ እንግዝ፣ሉንድ ዩንቨርሲቲ ስዊድን፣ስታቫንገር ዩንቨርሲቲ ኖርዌይ፣ሴንት  ፒተርስበርግ ዩንቨርሲቲ ሩስያን ጨምሮ የሚመጡ ሲሆን በተለያዩ ርዕሶች የሚያቀርቡት የጥናት ወረቀቶች ከፍተኛ ዋጋ የሚሰጣቸው መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል።

ፕሮፌሰር ሳሙኤልሮቢንሰን "የኢትዮጵያ ሃይማኖታዊ ቅርሶች ለዓለም ክርስትና ያደረጉት አስተዋፅኦ" በሚል ስር የጥናት ወረቀታቸውን የሚያቀርቡ ሲሆን ፣ፕሮፌሰር ደቪድ ፊልፕሰን በበኩላቸው " የኢትዮጵያ ቤተ ክህነታዊ ቅርሶች ታሪክ" በሚል ርእስ ስራቸውን ለጉባኤተኛው ያካፍላሉ።ከእዚህ በተጨማሪ እውቁ የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የማኅበራዊ ሳይንስ ተመራማሪው ዶ/ር የራስ ወርቅ አድማሴ ስራዎች የጉባኤው ሌሎቹ ድምቀት የሚሰጡት እንደሚሆኑ ከወድ\ዲሁ ለመረዳት ተችሏል።ጉባኤው የእራሱ ድረ ገፅ የከፈተ ሲሆን ገፁን ለመጎብኘት ይህንን  ይጫኑ።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ዘመናት ከመሻገሯ እና ለኢትዮጵያም ሆነ ለአፍሪካ እድገት ያላት ሚና ከፍተኛ ቢሆንም እስካሁን በእንደዚህ አይነት ደረጃ ዓለም አቀፍ ጉባኤ ስታዘጋጅ ይህ የመጀመርያ ነው።ከማኅበረ ቅዱሳን የአውሮፓ ማዕከል የጥናት እና ምርምር ክፍል  የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው ይህ ጉባኤ በሚቀጥለው ዓመት ሁለተኛ ዓለም አቀፍ ጉባኤ ተብሎ በሌላ ሀገር እንደሚቀጥል ለማወቅ ተችሏል። ጉባኤው ኢትዮጵያን እና ቤተ ክርስቲያንን በዓለም አቀፍ መድረክ የሚያስተዋውቅ ሲሆን ከምርምር ውጤቶቹ የሚገኙት ግብአቶች ለቤተ ክርስቲያን ሁለንተናዊ እድገት የራሳቸውን ጉልህ ድርሻ እንደሚኖራቸው ይታመናል።


በሌላ ቤተ ክርስቲያንን የተመለከተ ዜና ደግሞ ማህበረ ቅዱሳን ከመጪው መስከረም 1 ቀን ጀምሮ የቴሌቭዥን ስርጭቱን እንደሚጀምር ለማወቅ ተችሏል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ከ40 ሚልዮን ምእመናንን ይዛ የእራሷን ተከታዮች የምትደርስበት የራድዮም ሆነ ቴሌቭዥን ጣቢያዎች የሏትም።በመሆኑም የማኅበረ ቅዱሳን  የቴሌቭዥን ስርጭት የእራሱ በጎ ሚና እንደሚኖረው ይገመታል። በማኅበሩ ድረ ገፅ ላይ አዲሱን የቴሌቭዥን ስርጭት አስመክቶ የወጣው ዘገባ እንደሚያመለክተው ስርጭቱ በአማርኛ፣ኦሮምኛ እና ትግርኛ የሚቀርብ ሲሆን በቀን ለሁለት ሰዓታት ያህል የአየር ሰዓት ይኖረዋል።ማኅበሩ ካሁን በፊት በኢቢኤስ የቴሌቭዥን ጣቢያ በሳምንት ለአንድ ሰዓት በአማርኛ ቋንቋ ሲያስተላልፍ የነበረው መንፈሳዊ መርሐ ግብር በልዩ ልዩ ምክንያት ከተቋረጠ በኋላ በየሳምንቱ ለሁለት ሰዓታት በኢንተርኔት ቴሌቭዥን በሚያሠራጫቸው መንፈሳዊ ዝግጅቶቹ ለሕዝበ ክርስቲያኑ ትምህርተ ወንጌል ሲያቀርብ ቆይቷል።በአሌፍ የቴሌቭዥን ጣቢያ የሚሰራጨው ስርጭት በሚከተሉት የሳተላይት መስመር በኩል እንደሚገኝ ዜናው አክሎ ያብራራል።የሳተላይት መስመሩም 
Aleph Television Nilesat (E8WB)
Frequency: 11595
Polarization: Vertical
Symbol Rate: 27500
FEC: 3/4
መሆኑን ከማኅበሩ ድረ ገፅ ላይ ለመረዳት ተችሏል።

ከስር የሚገኘው የቪድዮ መዝሙር ርዕስ - ቤተ ክርስቲያንን አንተውም ከቶ 
በማኅበረ ቅዱሳን የመዝሙር ልዑክ 



No comments:

በኢትዮጵያ የእገታ ወንጀል ተሳታፊ አራት አካላት ናቸው። ለችግሩ የመፍትሄ አካላት ሁለት ናቸው።ሁለቱ አካላት ምን ይስሩ?

======= ጉዳያችን ======= በኢትዮጵያ ዜጎችን እያገቱ ገንዘብ የሚቀበሉ ወንጀለኞች ከተራ ወንጀለኝነት አልፎ በታጣቂ ቡድኖች የገንዘብ ማግኛነት መዋል ብቻ ሳይሆን ዜጎችን የማሸበርያ ፋሺሽታዊ ተግባር ሆኗል። እገታ የ...