ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Thursday, September 17, 2015

ሰበር ዜና - የምዕራብ አፍሪካዊቱ ሀገር የቡኪና ፋሶ መንግስት ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት ተደረገበት።


በአዲሱ መፈንቅል አድረጊ ወታደሮች የታገቱት ጊዚያዊ ፕሬዝዳንት  ካፋንዶ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ሌ/ኮ/ ኢሳቅ ዚዳ   Photo - BBC

የቡኪና ፋሶ ፕሬዝዳንታዊ ዘብ ከሰአታት በፊት መንግስቱን መቆጣጠሩን እና በድንገቱም አስር ሰዎች መሞታቸውን ለማወቅ ተችሏል።ቢቢሲ ወታደሮቹ የመንግስቱን የቴሌቭዥን ጣቢያ መቆጣጠራቸውን እና የእድገት እና የዲሞክራሲ ምክርቤት ፓርቲ መሪ ፕሬዝዳንት ብሌር ካምፓዌሪ ( B. Compaore) የቅርብ ሰው ጀነራል ግልበርት ዴንደረ ( Gen Gilbert Diendere) የሀገሪቱ መሪ እንደሚሆኑ ወታደሮቹ ማስታወቃቸው ተዘግቧል።

ጊዜያዊ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት እና ጠቅላይ ሚኒስትር ፕሬዝዳንት ሚቸል ካፋንዶ ( Michel Kafando) እና ጠቅላይ ሚኒስትር ኢሳቅ ዝዳ  (Isaac Zida) ቀደም ብለው በካቢኔ ስብሰባ ላይ ሳሉ ድንገት ዘው ብለው በገቡ ወታደሮች መታገታቸው እና  የአስር ወራትን ያስቆጠረ ጊዜያዊ መንግስታቸው መፈፀሙ እንደተነገራቸው ተሰምቷል።የቀድሞ የቡኪና ፋሶ ቅኝ ገዢ  ፈረንሳይ ድርጊቱን ተቃውማለች። 

የአፍሪካ መሪዎች ዲሞክራሲያዊ አስተዳደርን በአግባቡ መዘርጋት ሲያቅታቸው የጦር ሰራዊቱ ሃገራቱ ''ወደ ባሰ ትርምስ ከመግባታቸው በፊት''በሚል ሰበብ የስልጣን ኮርቻውን ሲቆጣጠሩት ይታያል።በቅርቡ በምስራቅ አፍሪቃዊቷ ሀገር ቡሩንዲ ተመሳሳይ ያልተሳካ መፈንቅለ መንግስት ሙከራ መደረጉ እና ከእዚያን ጊዜ ወዲህም የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ካለፈው ለመማር አለመቻላቸው ሌላው አስገራሚ ጉዳይ ነው።


ጊዜያዊ መንግስቱን ከስልጣን ያወረዱት ጀነራል ዲያንደር (Gen Diendere )  
                        Photo - BBC 

ቅጥ ያጡ ጎጠኞች እና ሙሰኞች መሪዎችን ለማስወገድ ብዙ ሺዎች ከሚያልቁ እውነተኛ ወታደሮች ሃገርን ወደ ባሰ ትርምስ ከሚመሩ ጉልበተኞች ማዳናቸው ክፉ ሥራ አይደለም የሚሉ አሉ።የቡኪናው ጉዳይ ግን ከእዚህ የተለየ ይመስላል።ምክንያቱም ጊዜያዊ ጠቅላይ ሚኒስትር እና ፕሬዝዳንት በመጪው ጥቅምት ወር ላይ በሚደረገው ምርጫ ስልጣን ያስረክባሉ ተብሎ ይጠበቅ ነበር።እውነት ሊያስረክቡ ነበር? ወይንስ እንደ ህወሃት ምርጫ አጭበርብረው ስልጣን ላይ ሊቀመጡ አስበው ነበር? የሚለው ጥያቄ እንዳለ ሆኖ።


ጉዳያችን GUDAYACHN BLOG
መስከረም 6/2008 ዓም (ሴፕቴምበር 17/2015)

የዜናው ምንጭ - ቢቢሲ ነው ( BBC)

No comments:

በኢትዮጵያ የእገታ ወንጀል ተሳታፊ አራት አካላት ናቸው። ለችግሩ የመፍትሄ አካላት ሁለት ናቸው።ሁለቱ አካላት ምን ይስሩ?

======= ጉዳያችን ======= በኢትዮጵያ ዜጎችን እያገቱ ገንዘብ የሚቀበሉ ወንጀለኞች ከተራ ወንጀለኝነት አልፎ በታጣቂ ቡድኖች የገንዘብ ማግኛነት መዋል ብቻ ሳይሆን ዜጎችን የማሸበርያ ፋሺሽታዊ ተግባር ሆኗል። እገታ የ...