ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Tuesday, September 1, 2015

ከ77 አመታት በፊት የታቀደው እና በተግባር የታየው የፋሽሽት ጣልያን ''የአማራን ዘር'' የማጥፋት ዘመቻ በዘመነ ኢህአዴግ/ህወሃትም ተጠናክሮ ቀጥሏል (ተጨባጭ የፅሁፍ ማስረጃዎች ይመልከቱ)

ከእዚህ በታች ያለው ፅሁፍ በሙሉ  ከZe Addis (ዘ-አዲስ)  ማኅበራዊ ድረ-ገፅ የተወሰደ ነው።

አማራን ማፈናቀልና ማጽዳት 

" አማራ ላይ ዘር ለይቶ ህገወጥ ሥራ ( ጥቃት) እየደረሰ ነው" የኢህአዴግ ምክትል ሊቀመንበር እና ም/ ጠቅላይ ምኒስትር ደመቀ
" ይህ ወንጀል ብአዴንን ብቻ ሳይሆን ሌሎቹንም ሊያሳስብ ይገባል" ደመቀ መኮንን
" ባለፈው ዓመት ቤኒሻንጉል ላይ የአማራ ዘርን ለይቶ የተፈጸመው ጥቃት ህገ ወጥ ነው" አቶ ደመቀ 

እንደ መግቢያ


ሰሞኑን የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ "ኢትዮጵያ ውስጥ ዘረኝነት ከባድና አሳሳቢ እየሆነ እንደመጣ " ገልጸው ነበር:: ትናትና ደግሞ የሀገሪቱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በሰጡት ረዘም ያለ ቃለመጠይቅ ላይ ኢትዮጵያ ውስጥ የአማራ ብሔር ላይ ዘር ተለይቶ ማጽዳትና ጥቃት እንደደረሰበት አምነዋል::

ይህ "ዘርን ለይቶ የሚደረግ ጥቃት" ሀገወጥ ሥራ መሆኑን ገልጸው የዛሬ ዓመት አካባቢ ቤኒሻንጉል ላይ ብዙ ሺህ አማሮች መፈናቀላቸውን እንደገናም ጋምቤላ ውስጥ በቅርቡ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ አማሮች ዘር ተለይቶ ማፈናቀልና ጥቃት እንደደረሰባቸው ይህም ኢ- ህገ መንግስታዊ መሆኑን አበክረው አሳስበዋል::

የአማራ ብሔርን ማፈናቀል አሳሳቢ እየሆነ በመምጣቱ ችግሩ የብ. አ .ዴ.ን ብቻ ሳይሆን የሁሉም ክልሎች ትኩረት እንዲሰጡት አስረግጠው በድፍረት ተናግረዋል::

አማራን የማፈናቀል ታሪካዊ አመጣጥ 

የ ዘጠኝ መቶ ሺህ( 900,000) አማሮች መፈናቀል 

ኢትዮጵያዊው የታሪክ ምሁር ዶክተር ላጲሶ ጌ ዴሌቦ በጻፉት " የኢትዮጵያ ገባር ሥርዓትና ጅምር ካፒታሊዝም" በተባለ መጽሃፋቸው ገጽ 69 እሰከ 70 ( መጽሃፉን ይህን ሊንክ ቢጫኑ ያገኙታል  http://cdn.good-amharic-books.com/capitol-1-cr.pdf ) ፋሺስት ጣልያን የዛሬ 78 ዓመት ለአገዛዜ እንቅፋት የሚሆኑብኝ አማሮች ስለሆኑ አማሮችን ማፈናቀል: መበተንና ማጥፋት በሚል አላማ 900 ሺህ አማሮችን ከደቡብ ክልል ለቅሞ እንዳፈናቀለ እንዲህ ሲሉ ገልጸውታል::


"በፋሺስቶች አመለካከትና ግንዛቤ ...ለኢጣልያ ኮሎኒያዊ ጥቅምና ጸጥታ አደገኛ ጠላት የአማራ ማኅበረሰብ ነው:: የፋሺስት ባለስልጣኖች ከዚህ አቋማቸው በመነሳት በመጀመርያ ዓመታት ከሞሶሎኒ በተሰጣቸው የፖሊሲ መመርያ በአማራ ማኅበረሰብና በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ላይ መንግስታዊ የጥቃት እጅ አነሱ:: በዚህም ረገድ-- ከ ከ600000( ስድስት መቶ ሺህ) እስከ ስምንት መቶ ሺህ የሚገመቱ አማርኛ የሚናገሩ ነዋሪዎች ከሓረርና ከኦሮሞ ሲዳማ የአስተዳደር ክልሎች ወደ ሸዋና የአማራ አስተዳደር ክልሎች እንዲባረሩ--የአማራ ማኅበረሰብ አባላት በሌላ አስተዳደር ክልሎች የፖለቲካ ስልጣን እንዳይዙ: ተቀጥረውም እንዳይሰሩ--በሌላ የአስተዳደር ክልሎች በአማርኛ ቋንቋ መንግስታዊ ሥራ እንዳይሰራበት በማድረግ ፋሺስቶች ብዙ የፖሊሲ እርምጃዎችን ወሰዱ::" ገጽ 69 -70


(የኢትዮጵያ ገባር ሥርዓትና ጅምር ካፒታሊዝም በተባለ መጽሃፋቸው ገጽ 69 እሰከ 70  http://cdn.good-amharic-books.com/capitol-1-cr.pdf)

ዶ/ር ላጵሶ ገዴልቦ መፅሐፍ ገፅ 69 እስከ 70 (ከላይ)

የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስትያንም : " በመከራ ውስጥ ያበበች ቤተ ክርስትያን " በሚል ርዕስ ያሳተመችው የቃለ ሕይወት ቤተ ክርስትያን ታሪክ ውስጥ ገጽ 147 (http://cdn.good-amharic-books.com/wendiye-4-cr.pdf )ላይ ፋሺስቱ ጣልያን ለስልጣኔ ያሰጋኛል ያለውን የአማራ ብሔርን; የኦርቶዶክ ተዋህዶ ቤተክርስትያንን ከደቡብ ኢትዮጵያ የማፈናቀል ሥራ እንደጀመረ ያስረዳል:: በዚህም ወቅት ከደቡብ ኢትዮጵያ ከ 600,000 ሺህ እስከ 800 ,000 አማሮችን ማፈናቀሉን ይሄው መጽሓፍ ይጠቅሳል::  http://cdn.good-amharic-books.com/wendiye-4-cr.pdf

''የቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን ታሪክ'' ገፅ 147ነገር ግን የተፈናቀሉ አማሮች የበላይ ዘለቀን ጦር በመቀላቀል እስከመቸረው ጣልያንን በመፋለም ጣልያን የፈራው እንደደረሰበት ራሱ ጀነራል ደቦኖ እንዲህ ሲል ጽፎታል::
"ደጋግሜ ተናግሬ ነበር:: አማራና ኦርቶዶክ ቤተ ክርስትያን ካልጠፉ ሰላም እንደማናገኝ:: "

ከ70 ዓምታት በኋላ የህወሀቱ ባለስልጣን ስብሓት ነጋ " አማራንና ኦርቶክስን አከርካሪውን ሰብረነዋል" ሲሉ ተመሳሳይ መግለጫ መስጠታቸው ይታወሳል::

ሕ.ወ. ሀ. ት እና አማራ 


ሕዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ( ህ .ወ.ሀ.ት) በ1967 ባዘጋጀው ማኒፌስቶው ላይ የትግራይ ሕዝብ ዋናው ጠላቱ አማራ መሆኑና አማራን ህብረተባዊ እረፍት እንዳያገኝ እንደሚያደርግ በግልጽ አስቀምጦታል :: ለምሳሌ ይሄው ማኒፌስቶ ገጽ 15-16 ላይ እንዲህ ይላል ( መጽሃፉን እዚህ ሊንክ ላይ ያገኙታል


"የትግራይ ሕዝብ ለረጅም ዘመን ሰብ አዊና ፖለቲካዊ መብቱ ተነፍጎ ሲጠላና ሲናቅ እንዲሁም እንዲሁም አድልዎ ሲፈጸምበት ቆይቷል:: ይህም በደል ጨቋኝ የአማራ ብሔር ሆን ብላ እንደ መንግስት መመርያ አድርጋ ስትሰራበት የቆየች ሲሆን ..ደርግም ቀጥሎበታል::
...
" ሰፊው የትግራይ ህዝብ ሥራ አጥቶ በሽርሙጥናና በሰደት ወዘተ ብቻ ሳይሆን በረሃብና በድንቁርና እየተሰቃየ ይገኛል:: እነዚህም ችግሮች ወንጀል እንዲፈጽም ይገፋፉታል::ለችግሩ መሰረታዊ ምክንያት ኢምፔሪያሊዝምና ባላባታዊ ስራአት ይሁኑ እንጂ ጨቋኟ የአማራ ብሔር የምታደርገው የ ኤኮኖሚ ብዘበዛና ጭቆና ታክሎበት ነው::... ጨቋኟ የአማራ ብሔርም ጭቆናዋን እስካላቆመች ድረስ ብሔራዊ እረፍትን አታገኝም::"
 የዛሬ 40 ዓመት የህወሀት መኔፌስቶ ገፅ 15 እና 16_


ህወሀት አዲስ አበባን ከተቆጣጠረ በኋላ አማራ ብሔር ላይ የወረደው ጭፍጨፋ : እልቂትና ጥፋት ወደር ያለው አይመስልም:: ራሱ የኢትዮጵያ መንግስት እንዳመነው
https://www.youtube.com/watch?v=ikVl6auH83w ( fast forward it minute 7:10)

በሕዝብና ቤት ቆጠራ ውጤጥ እንደሚያሳየው 2.5 ሚሊዮን አማሮች የገቡበት አልታወቀም:: ምናልባትም ከ ጽዮናዊቷ እስራኤል ቀጥሎ ይሄን ያህል ቁጥር ያለው ሕዝብ የገባበት ሲጠፋ አማራ ሁለተኛው ሳይሆን አይቀርም።

በተለያዩ የሀገር ውስጥና የውጭ ሚድያዮች እንደተዘገበውም ከወልቃይት እስከ ከፋ ድረስ ባለፉት 24 ዓመታት የአማራ ደም ያልፈሰሰበት : የአማራ ንረት ያልወደመበት: አማራ በብሔሩ እየታደነ " ወደ ሀገርህ: ተብሎ ያልተባረበበት ቦታና ዓመት የለም ማለት ይቻላል::

በቅርቡ የተፈጸመውን እንኳን ብናይ 2013 ላይ ጉራ ፈርዳ ላይ ከ 80 ሺህ በላይ አማሮችን - ባለስልጣናት አፈናቅለዋል:: ለዚህ መፈናቀል ምክንያት የሆነው ሽፈራሁ ሽጉጤም ታዥዤ ነው ማለቱን ኢሳት ዘግቧል:: 2014 ላይ ቤኒሻንጉል ላይ በሺዎች የሚቆጠሩ አማሮች በግፍ ተፈናቅለዋል:: ተገድለዋል:: ደመቀ መኮንን በመግለጫቸው እንደገለጹትም ይሄ የተከናወነው በባለስልጣናት መሆኑን : ድርጊቱም ህገ ወጥና ወንጀል መሆኑን አስረግጠው ተናግረዋል:: 2015 ላይም የአማሮች ሰቆቃ አላለቀም:: ወንበራ ላይ እግጅ ዘግናኝ እልቂት መፈጸሙን አሁንማ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባንደበታቸው ገልጸዋል:: ራቅ ባሉትም አመታት በደኖ : ኢንቁፍቱ : ወተር : ላንጌ: እና መሰል ቦታዎች አማሮች ላይ የደረሰው ግፍ በባለስልጣኖች ሴራ እና ተንኮል እንጂ ባካባቢው ገበሬ አለመሆኑን ፕሮፌሰር አስራት በማያሻማ መልኩ አስቀምጠውት እንደነበር ይታወሳል::

በነዚህ ሁሉ እልቂቶች የአካባቢው ገበሬ እጅ የለበትም:: ያካባቢው ገበሬማ እስካሁን እኮ ከአማሮቹ ጋር ለብዙ ዘመናት ኖሯል::ጉራ ፈርዳ ላይ ያካባቢው ገበሬዎች " አማሮቹን ለምን ታፈናቅላላችሁ " በማለት ባለስልጣናትን ሲወቅሱ እንደነበር ቪ ኦ ኤ ዘግቧል:: በተለያዩ የኦሮሚያ ቦታዎች ላይም ያካባቢው አርሶ አደር ለተፈናቀሉት አርሶአደሮች እህልና ገንዘብ ለተፈናቃዮች እንዳዋጣ አሁንም ሚድያዎች ዘግበዋል::

ችግሩ ካርሶአደሮቹ ሳይሆን " አማራ ጠላቴ ነው" በሚል ሰይጣናዊ እሳቤ ህሊውን ካሳመነው አካል ነው https://www.youtube.com/watch?v=c1Ez4fnM1dI :: የዚህም ወደር የለሽ ጥላቻ መነሻው የጣልያን መርዝ ነው እንጂ : አማራ ለትግሬ ጠላቱ አልነበረም:: ትግሬም ላማራ ጠላቱ አይደለም:: ትግሬ ሲወረር አማሮቹ ደማቸውን ከትግሬው ጋር አፍሠዋል:: ጎንደርን ደርቡሽ ሲያጠቃት ትግሬው ለወገኑ ደሙን አፍሧል:: በኔ እነገስ እኔ እነግስ ሽኩቻ መኖሩ የማይካድ ታሪክ ቢሆንም ይሄን ያህል የመረረ ጥላቻንና በቀልን የሚያስቋጥር አይደለም:: አልነበረምም::

አማሮች ብቻ በመሆናቸው ንብረታቸው የተዘረፈው : ደማቸው የፈሰሰው አርሶአደሮች ደም እንደአቤል ደም ይጮሃል:: አንድ ቀንም የደማቸው ድምጽ የሰማይ አምላክ ዘንድ መድረሱ አይቀርም:; ደም አፍሳሹ ቃኤልም : ያለሀጥያቱ ደሙ የፈሰሰው አቤልም ፍርዳቸውን ያገኛሉ:: የአምላክም የተፈጥሮም ህግ ነውና ይህ መሆኑ አይቀርም:: የግፉ ጽዋም እየሞላ ይመስላል:: እስከዛው ግን "ጽድቅና ኩነኔ ቢኖርማ ባይኖርም : ከክፋት ደግነት ሳይሻል አይቀርም" እንዳለ ገጣሚ ;----- አረ ድሃን ማፈናቀል ማቅበዝበዝና መግደል ይብቃ:: ለነብስም : ለስጋም : ለልጅ ልጅም አይበጅም!!

ለትውስታ እነዚህን ሊንኮች ይመልከቱ
===========================
https://www.youtube.com/watch?v=AIUhkBpWS0g
http://ethiopianreview.com/videos/watch.php?vid=5da79b5fe ( ጀርመን ድምጽ)
http://www.africareview.com/News/Amhara-expelled-from-southern-Ethiopia/-/979180/1381230/-/g87yms/-/index.html ( አፍሪካን ሪቪው)
http://www.worldaffairsjournal.org/content/ethiopia-evicts-amhara-settlers-land
http://amharic.voanews.com/content/gura-ferda-eviction/1560849.html ( ቪ ኦ ኤ)
https://www.youtube.com/watch?v=3k20QKe9o1Y
https://www.youtube.com/watch?v=AZTz3S5LxB8 (ጊምቢ ) 8 ሺህ
https://www.youtube.com/watch?v=ndSzSPskwAw 2.5 ሚሊዮን ቁጥር መጥፋት
https://www.youtube.com/watch?v=WpUxU5suuLs
https://www.youtube.com/watch?v=l0IzfWqv85k
ምንጭ - ከZe Addis (ዘ-አዲስ)

ጉዳያችን GUDAYACHN BLOG

No comments:

ለፕሮፌሰር መራር፣ልደቱ፣ጀዋርና ኢንጅነር ይልቃል ዘፈን ይህችን ዜማ እንምረጥላቸው።

በቅድምያ ስለ አራቱም የመግቢያ ማስታወሻና ወቅታዊ ሁኔታቸው። አራቱም ከመስከረም በኋላ መንግስት የለም ብለው ኢትዮጵያን ለእርስ በርስ ጦርነት ሊነክሯት ሞክረዋል።ዝርዝሩን፣ከእነማን ጋር መክረው እንደነበር፣ለኢትዮጵያ ደግሰው...