ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Friday, March 6, 2020

የእናት ፓርቲ ምስረታ በመጪው ዕሁድ አዲስ አበባ ላይ ይከናወናል።የ21ኛው ክ/ዘመንን ኢትዮጵያ ከሚያሻግሩ ፓርቲዎች ውስጥ እንደሚሆን ታምኖበታል።ፓርቲው ሁሉንም ብሔር፣ዕምነት እና ክልል ያሳተፈ እንደሆነ ተነግሯል።

ጉዳያችን ልዩ ዜና 

  • ለፖለቲካ በቁጥር  ብዙኃን፣በተሳትፎ ተመልካች  እና ወጣት የሆነው  የኢትዮጵያ ሕዝብ ክፍል ወደ መካከለኛው የፖለቲካ ዓውድ መጥቷል።
  • The Silence Majority of Ethiopians are organizing under the new forming party, ENAT PARTY


የአንዲት አገር የነገ ዕጣ በምን ላይ እንደተመሰረተ ለማወቅ፣በዛሬው ወጣት ርዕይ እና ፍላጎት ላይ የተመሰረተ  ሥራ እየተሰራ መሆኑን እና አለመሆኑን  መመልከቱ በቂ ነው።የብዙ አገሮች የዕድገት ምስጢር የተመሰረተበት አንዱ ምሰሶም ይሄው ነው።የትውልዱን ርዕይ እና ፍላጎት በተቃረነ መንገድ የሚሄዱ የፖለቲካ፣ማኅበራዊ እና ምጣኔ ሃብታዊ ሂደቶች እና ፖሊሲዎች  ሁሉ ውጤታማ የመሆናቸው ዕድል እጅግ የመነመነ ነው።

በኢትዮጵያ ፖለቲካም ላለፉት አርባ አምስት አመታት የቀጠለው የፖለቲካ ሂደት፣አዲሱን ትውልድ ፖለቲካውን እንዲሸሽ፣እንዳያምን እና በተሳትፎ የራሱን ገንቢ ሚና እንዳይጫወት እንቅፋት ሆኖበት ኖሯል።ይህ ሁኔታ ግን አሁን የኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባናል፣እንደዜጋ የድርሻችንን መወጣት አለብን፣ከየትኛውም ብሔር፣ዕምነት እና ክልል ያላደላ ከምርም ኢትዮጵያን  ያለ እና ሁሉንም የሚያከብር ብሎም 21ኛውን ክ/ዘመን ኢትዮጵያን አሻግሮ በክብር ለትውልድ የማስረከብ ኃላፊነቱን ለመወጣት ያለመ አዲስ የፖለቲካ ፓርቲ በመጪው ዕሁድ የካቲት 29/2012 ዓም በአዲስ አበባ፣ስድስት ኪሎ በሚገኘው የስብሰባ ማዕከል  የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ታዛቢዎች በተገኙበት መስራች ስብሰባውን እንደሚያካሂድ ለጉዳያችን የደረሰው መረጃ ያመለክታል።በመስራች ስብሰባው ላይ ሁሉንም የኢትዮጵያ ክልሎች፣ብሔሮች እና ዕምነቶች የሚወክሉ ኢትዮጵያውያን ይታደማሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ወጣቶቹ የእናት ፓርቲ አስተባባሪዎች ለጉባኤ ዝግጅት በንቃት እየሰሩ ነው።

''እዚህ ላይ ኢትዮጵያ ከመቶ በላይ የሚሆኑ የፖለቲካ ፓርቲዎች እያሉ ተጨማሪ ለምን አስፈለገ? ብሎ የሚጠይቅ ይኖራል'' ያለው አንድ የእናት ፓርቲ አደራጅ ኮሚቴ አባል ሲያብራራ '' ይህ አስተሳሰብ የፓርቲዎች ቁጥር መብዛት በራሱ የኢትዮጵያን ሕዝብ የመወከል አቅማቸው ያደገ አድርጎ መውሰድ የሚነሳ የተሳሳተ አስተሳሰብ ነው።'' በማለት ያብራራል።

ከእዚህ በተጨማሪ በጉዳያችን መረጃ መሰረትም የእናት ፓርቲ ሁሉን አቃፊነት፣የኢትዮጵያን መሰረታዊ ችግሮች ከመረዳት፣ ለችግሮች በቂ መፍትሄ ከመስጠት አቅም፣ፍላጎት እና ቁርጠኝነት አንፃር  የእናት ፓርቲ የራሱን አገራዊ ድርሻ እንደሚወጣ ከብዙ ጉዳዮች አንፃር አመላካች ጉዳዮች አሉ።የእናት ፓርቲ ከእዚህ በፊት ጊዜያዊ የዕውቅና ሰርተፍኬት ከኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ያገኘ ሲሆን በመጪው ዕሁድ የሚያደርገው አስር ሺህ በላይ ፊርማ አስፈርሞ ዋና እውቅና ሰርተፍኬት የሚያገኝበትን ሂደት ነው።የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ አስር ሺህ የድጋፍ ፊርማ ማሰባሰብ ያልቻሉ ፓርቲዎች ከመጪው ነሐሴ የምርጫ ሂደት ውጪ እንደሚሆኑ እና ቀነ-ገደቡም በቀናት ውስጥ እንደሚጠናቀቅ ማሳወቁ ይታወሳል። ጉዳያችን ለእናት ፓርቲ መልካም የምስረታ ጉባኤ ትመኛለች።

የእናት ፓርቲ ጊዚያዊ ዕውቅና ከኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ አግኝቷል።

ጉዳያችን GUDAYACHN 
 www.gudayachn.com

No comments:

Beynouna Village - Ethiopia (Video) ባለፈው ሳምንት የተመረቀው መተሃራ እምብርት ላይ የተገነባው አስደናቄው የበይኑና ሪዞርት መንደር (ቪድዮ)

Beynouna Village - Ethiopia (Video) ባለፈው ሳምንት የተመረቀው መተሐራ እምብርት ላይ የተገነባው አስደናቄው የበይኑና ሪዞርት መንደር (ቪድዮ)