Friday, February 11, 2022

ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ ኖርዌይ ናቸው።ቅዳሜ የካቲት 12/2014 ዓም (ፌብርዋሪ 19/2022 ዓም) ከጉዳያችን እና የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ጋር በመተባበር በኦስሎ ልዩ የኪነጥበብ ዝግጅት አላቸው።


የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ መምህር፣ደራሲ፣የኪነጥበብ ሰው እና በአነቃቂ ንግግራቸው የሚታወቁት ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ ኖርዌይ ናቸው።ቅዳሜ የካቲት 12/2014 ዓም (ፌብርዋሪ 19/2022 ዓም) በኦስሎ የኪነጥበብ ዝግጅት ያቀርባሉ።በእዚሁ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ በኖርዌይ ከጉዳያችን ጋር በመተባበር የሚቀርበው የኪነጥበብ ዝግጅት ላይ ልዩ መጣጥፎቻቸውን፣ በዝግጅትም በማቅረብም የተሳተፉበት አጭር ፊልም እና ካሳተሟቸው መጻሕፍቶች ውስጥ ጥቂት ኮፒዎች በዕለቱ ለሚገኙ የኦስሎ ነዋሪዎች ያቀርባሉ።የዝግጅት ቦታው ጥቂት ሰው ስለሚይዝ በሰዓቱ አለመድረስ የቦታ ማጣት ችግር እንዳያመጣብዎት፣በሰዓቱ ይገኙ።

ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ በኢትዮጵያ የጋራ ጉዳይ ላይ ንቁ ሃሳብ አመንጪ ናቸው።በቅርቡ በኢትዮጵያ ሃገር አቀፍ እርቅ ኮሚሽን ዕጩ ተመራጭ ናቸው።

ዝርዝር ሰዓቱን እና የቦታውን አድራሻ ከእዚህ በታች ከሚገኘው ፖስተር ላይ ይመልከቱ።



"እውን አንተን ወለደ?" ገጣሚ ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ (ኦድዮ)





No comments:

ወቅታዊው እና መጪው የኢትዮጵያ የፖለቲካ፣ምጣኔሃብታዊ እና ማኅበራዊ ሁኔታ በሶስት ርዕሶች ማጠቃለል ይቻላል።

  ፎቶ ፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የ2017 ዓም የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ መትከል ብሔራዊ ዘመቻ ሲከፍቱ። ========= ጉዳያችን ምጥን ======== በእዚህ ጽሑፍ ስር ሶስት ምጥን ርዕሶች ያገኛሉ። እነርሱም  አ...