When UN and the west talk about Crimea, it should not also forget its negligence mistake on Eritrea referendom of 1993 against UN resolution (September 15/1952 resolution no.390-A(V) which separate from main land Ethiopia.
ክሬምያ ከዩክሬን ተነጥላ የሩስያ አካል ለመሆን ዛሬ መወሰኗን የዜና ዘገባዎች እያወጡ ነው።እንደ ዘገባዎቹ ከሆነ ዘጠና ሶስት ከመቶ የሚሆነው ሕዝብ ደግፏል።በብዛኛው የሩስያ ትውልድ ያላቸው እንደሆኑ የተነገረላቸው የግዛቲቱ ነዋሪዎች ለውሳኔው እርግጠኛ ነበሩ።
የምዕራቡ አለም በአንፃሩ ሩስያ ከወረራ ያልተናነሰ ድርጊት ፈፅማለች።ዩክሬን ነፃ ሀገር ነች።ሉዓላዊነቷ ሊደፈር አይገባም በማለት ደጋግሞ ገልጧል።ፕሬዝዳንት ኦባማም ይህንኑ በደደጋጋሚ አስተጋብተዋል።
ጉዳዩ የአለም አቀፍ ሕግን ከተለያዩ ማዕዘኖች እንዲታዩ የሚያደርግ መሆኑ አይቀርም።የአለም አቀፍ ሕግ በአለማችን ላይ የሚከወኑ ታሪካዊ ክንውኖችን (historical cases) እየአቀፈ መሄዱ የሚጠበቅ ነው።
ከእነኝህ ዓለም አቀፍ ጉዳዮች አንዱ የኤርትራ ጉዳይ ነው።ከክሬምያ በበለጠ የኤርትራን ጉዳይ ውሳኔ ያሳለፈበት እና መልሶ በጠበንጃ ኃይል ለመጣው ኢ ፒ ኤል ኤፍ የተባበሩት መንግሥታት ባልታዘበበት ያንኑ ውሳኔውን በሌላ ውሳኔ ባልቀየረበት ሁኔታ ''ነፃነት ወንስ ባርነት'' ተብሎ የተጠየቀው ሕዝብ በፍርሃት ተሸብቦ ድምፅ እንዲሰጥ ሲደረግ የተባበሩት መንግሥታትም ሆነ ምዕራባውያን ወደፊት የሚመጣው የዓለም አቀፍ ሕግ ተቃርኖ ብዙም ያስታወሱት አይመስልም።ከእዚህ በፊት በክሬምያ ጉዳይ የተባበሩት መንግሥታት አልተወያየበትም፣የፀጥታው ምክርቤትም አልመከረበትም የኤርትራን ጉዳይ ግን መክሮበት ውሳኔ አሳልፎበታል።እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር መስከረም 15/1952 ዓም በውሳኔ ቁጥር 390-A(V) ኤርትራ ከኢትዮጵያ እንዳትለይ ይልቁን በፈድሬሽን እንድትዋሃድ ወስኗል።
እዚህ ላይ ብዙዎች የሚያነሱት የኢህአዲግ/ወያኔ መንግስት በራሱ ተስማምቶ ነበር የተባበሩት መንግሥታት ምን ማድረግ ይችላል? የሚል ሃሳብ ነው።የተባበሩት መንግሥታትም ሆነ የምዕራቡ አለም ጉዳዩን ማጤን የሚገባው ከአንድ በስልጣን ላይ ካለ መንግስት ፍላጎት አንፃር ሳይሆን ከአለም አቀፍ ዘለቄታዊ ሰላም አንፃር እና የአለም አቀፍ ውሳኔዎች ከመከበር አንፃር ብቻ መሆን ይገባው ነበር።ግን አልሆነም።ዛሬ ክሬምያ ስትነሳ ኤርትራ ላይ የታየው ቸልተኝነት እና በሺህ የሚቆጠሩ ተወላጆች በስደት እና በመከራ እንዲማቅቁ መደረጉ አሁንም የአለም አቀፉ ሕብረተሰብ የሚጋራው ኃላፊነት እንዳለ እያስታወሰ መሆን ይገባዋል።
ኮለኔል ጎሹ ወልዴ የቀድሞው መንግስት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለአሜሪካ ምክርቤት የውጭ ጉዳዮች ኮሚቴ ቀርበው ሰለጉዳዩ የሰጡትን ምስክርነት እና ማሳሰብይ ቪድዮው ላይ ይመልከቱ።
ጉዳያችን GUDAYACHN BLOG

No comments:
Post a Comment