ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Thursday, March 20, 2014

የኖርዌይ ህገ መንግስት ከፀደቀ በመጪው ግንቦት አጋማሽ ላይ 200ኛ ዓመቱ ይከበራል።በኖርዌይ የምንኖር ኢትዮጵያውያን በዓሉ ኖርዌይ ከኢትዮጵያ ጋር የነበራትን መልካም ግንኙነት የምናሳይበት ጥሩ አጋጣሚ ነው።

የኖርዌይ ህገ መንግስት አርቃቂ መስራች አባቶች ግንቦት 17/1814

በዘመናዊው ዓለም ከአሜሪካ ቀጥሎ ለሰው ልጆች በሚያጎናፅፈው መሰረታዊ  መብት  በምሳሌነቱ ይነሳል።እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ ግንቦት 17/1814ዓም  መፅደቁ የሚነገረው ህገ መንግስት እስካሁን በየዘመኑ ዘመን አመጣሽ የህዝብ ፍላጎት ጋር ለማስታረቅ ሲባል 400 ጊዜ ማሻሻያዎች ተደርገውበታል።የፖለቲካ ፓርቲዎች ''ይህ ሕግ የሚቀየረው በመቃብሬ ላይ ብቻ ነው'' እያሉ እንደሚያስፈራሩን የአፍሪካ ፓርቲዎች አይደለም።አስተሳሰቦች ይከለሳሉ፣ይቀየራሉ።ኢትዮጵያ ሃገራችን ህገ መንግስቷ ብቻ ሳይሆን ሰንደቅ ዓላማዋ እና ብሔራዊ መዙሯ በየዘመኑ በሚነሱ ገዢዎቿ ሲቀየሩ ማየት አሳዛኝ ነው።በመንግስትነት ከአውሮፓውያን ከሶስት ሺህ አመታት ለበለጡ ዘመናት ዘልቀናል።ሁሉን ያቀፈ መሰረታዊ ግን በየዘመኑ ሊሻሻል የሚችል ህገ መንግስት ግን 'የለንም'።
ቀዳማዊ አፄ ኃይለ ስላሴ በኖርዌይ ጉብኝት 1954 ዓም እ ኤ አቆጣጠር የኖርዌይ ጋዜጣ 

መልሼ ደግሞ የለንም ወይ? ብዬ እጠይቃለሁ።ከሺህ ዓመታት በላይ የፍትሐ ነገስት በሥራ ላይ መዋል።ይሄው ሕግ እንደ ፈረንሳይ ለመሳሰሉት ሀገራትም ሆነ ለዓለም አቀፍ ሕግ ያደረገው አስተዋፅዖ ሁሉ ሲታሰብ 'የለንም ነበር' ከማለት ''በነበረን ላይ አዳብረን መጠቀም አልቻልንም'' የሚለው የተሻለ አባባል ይመስለኛል።ለሁሉም ግን ኖርዌይ የ 200 ዓመት ህገ መንግስት በዓል ደመቅ ተደርጎ ይከበራል።
ቀዳማዊ አፄ ኃይለ ስላሴ በኖርዌይ ጉብኝት 1954 ዓም እ ኤ አቆጣጠር የኖርዌይ ጋዜጣ

በኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንም በዓሉ ላይ የኢትዮጵያውያን እና የኖርዌይ ግንኙነትን የቆየ ታሪክ የያዘ መርሐ ግብር ማዘጋጀት ይገባቸዋል።ቀዳማዊ አፄ ኃይለ ስላሴ የአሁኑ የኖርዌይ ንጉስ አባት ሃኮን ጋር በመጀመርያ የተገናኙት በጣልያን ወረራ ወቅት እንግሊዝ ሀገር ሲሆን በኃላ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ህዳር 1954 ዓም ንጉሡ  ኖርዌይ፣ኦስሎን ሲጎበኙ ወዳጅነቱ ጠንክሯል።ኖርዌይ የኢትዮጵያ ባህር ኃይል ሲመሰረት የሰው ኃይል ስልጠናን ጨምሮ ድጋፍ ካደረጉ ሃገራት ግንባር ቀደምም ነች።በመሆኑም እነኝህን የቆዩ ግንኙነቶች የሚያሳዩ የፎቶ ግራፍ አውደ ርዕይ ማዘጋጀት እና የኖርዌይ ወዳጆቻችንን እና የመገናኛ ብዙሃንን በመጋበዝ ብዙ ማለት ይቻላል።

መልካም በዓል ኖርዌይ

ጉዳያችን መጋቢት 11/2006 ዓም 

No comments:

Beynouna Village - Ethiopia (Video) ባለፈው ሳምንት የተመረቀው መተሃራ እምብርት ላይ የተገነባው አስደናቄው የበይኑና ሪዞርት መንደር (ቪድዮ)

Beynouna Village - Ethiopia (Video) ባለፈው ሳምንት የተመረቀው መተሐራ እምብርት ላይ የተገነባው አስደናቄው የበይኑና ሪዞርት መንደር (ቪድዮ)